Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
[ † እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ቶማስ" : "ያዕቆብ ወዮሐንስ" : "አቢማኮስ ወአዛርያኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
🕊 † ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ † 🕊
ቅዱስ ቶማስ በ፯ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው:: ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና: ለቅስና: ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል:: በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር::
ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት [የመሐመድ ተከታዮች] ናቸው:: ፯ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ::
በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐመዳዊ "እንከራከር" አለው:: ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐመድ ሐሰተኛነት: ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በሁዋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው::
በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው:: ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ:: "እንዴት እምነታችን እስልምናን ትሳደባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት::
መኮንኑም "እሺ! ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው:: የቀናችው እመነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች::
ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው:: ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው::" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ:: ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ::
🕊 † ቅዱሳን ያዕቆብ ወዮሐንስ † 🕊
አሁን ደግሞ ወደ ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን: ወደ ምድረ ፋርስ [ኢራን] ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር:: እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ [ኢራን]: በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው:: ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው::
ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን: ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ:: ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች::
ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ: ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው:: ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው: መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል::
በሁዋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም:: የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ: እየናዘዙ ጠበቁላት:: ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው::
በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው:: ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ: አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት::
ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው:: ቅዱሳኑም በመከራው [በነደደው እሳት] መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ:: "አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው:: እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ::
🕊 † ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ † 🕊
አሁን ደግሞ ወደ ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን: ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ:: በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት ፪ቱ አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው:: አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ፪ ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ ፪ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር::
በዘመኑ እንኩዋን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ: መዘመር: እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር:: ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር: ካደሩበትም አላውል አሉ::
ታላቅ ግፍ: ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ: አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው ክርስቶስን ያመልኩ ነበር:: ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ::
መኮንኑ ፪ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ:: "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት::
"ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት:: "የፈጠረ: ያከበረ: ሥጋውን ደሙን የሰጠ ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት:: በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው:: በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል::
አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት በነርሱ ያሳደረውን ትእግስትና ጽናት በእኛም ላይ ያሳድርልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
[ ኅዳር ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ
፪. ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ
፫. ቅዱሳን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ
፬. አባ አበጊዶ ዘትግራይ
፭. ታላቁ አባ ዘካርያስ
፮. ጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት
[ ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
፪. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት]
"ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፰]
🕊
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ለወፎች ክንፍ የተሰጣቸው በወጥመድ እንዳይያዙ ነው። ሰዎችም የማሰቡ ኃይልን የተሰጣቸው ኃጢአትን እንዲያስወግዱ ነው። እንግዲህ እንዲህ የማሰብ ኃይል ተሰጥቶን ሳለ ይባስ ብለን ከምድር አራዊት በታች የማናስተውል ከኾንን ሊደረግልን የሚችል ምህረት ወይም ይቅርታ እንደምን ያለ ምሕረት እንደምንስ ያለ ይቅርታ ነው?
በወጥመድ ተይዛ የነበረች ወፍ ድንገት ከወጥመዱ ብታመልጥ፤ ወደ ወጥመድ ገብቶ የነበረ አጋዘን ወጥመዱን በጣጥሶ ቢሄድ ከእንግዲህ ወዲህ በተመሳሳይ ወጥመድ እነዚህን መያዝ ከባድ ነው። የሕይወት ተሞክሮ ለሁለቱም ጥንቃቄን አስተምሯቸዋልና። እኛ ግን ምንም እንኳ በተመሳሳይ ወጥመድ ብንያዝም ተመልሰን ወደዚያ ወጥመድ እንወድቃለን፣ ምንም እንኳን በለባዊነት የከበርን ብንኾንም አእምሮ እንደሌላቸው እንሰሳት እንኳን ቀድመን አናስብም፤ አንጠነቀቅም!
ሴትን በማየት እልፍ ጉዳቶችን ተቀብለን ወደ ቤታችን የተመለስነው፤ በዝሙት ተመኝተንም ስናበቃ ለአያሌ ቀናት ያዘንነው ስንቴ ነው? ነገር ግን ከዚያ በኋላም ቢሆን በዚሁ ጉዳይ ላይ ጠንቃቆች አልኾንም፤ አንዱን ቁስል ሳናገግም ወደዚያ ክፉ ጠባይ እንወድቃለን፣ በተመሳሳይ መንገድ እንያዛለን፤ እጅግ ጥቂት ለኾነች የደስታ ሽርፍራፊ ብለንም ረጅምና ተደጋጋሚ ሥቃይን እንቀበላለን።
ዘውትር "በወጥመዶች መካከል እንደምትኼድ በገደልም መካከል እንደምትመላለስ ዕወቅ" የሚለውን ኃይለ ቃል ደጋግመን ለራሳችን ብንነግረው ግን ከእነዚህ ጉዳቶች ኹሉ እንጠበቃለን። (ሲራክ 9፥13)"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

"ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስንት ሰው ነው?" ቢሉ 'ይህን ያህል' አይባልም። ሊቁ አካሉ አንድ ይኹን እንጂ ብዙ ሰው ነው። መምህር፣ ባሕታዊ መልአክ፣ ካህን፣ መነኩሴ፣ ጳጳስ፣ ሊቀ ጳጳስ ሰማዕት ነው። በባቢሎን ወንዞች መካከል ኾኖ ጽዮንን የሚያስብ ጎርፍ የማያናውጠው ጽኑ ቤት፣ ውኃ የማያጠፋው የፍቅር እሳት፣ ጨለማ የማያደበዝዘው የወንጌል ኮከብ ነው። ዮሐንስ አፈወርቅ የመጽሐፍ ተርጓሚ ብቻ ሳይኾን ራሱ የመጻሕፍት ትርጓሜም ነው።"
በረከቱ ይደርብን
(ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ)
በረከቱ ይደርብን
(ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
[ † እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "አባ ዮሐኒ" እና "ቅዱስ ለንጊኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
[ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ትግራይ ውስጥ የሚገኘው አስደናቂው የጻድቁ ገዳም ነው ]
🕊 † ታላቁ አባ ዮሐኒ † 🕊
በምድረ ኢትዮዽያ ዝናቸው ከወጣና ቀደምት ከሚባሉ ጻድቃን አንዱ ቅዱስ አባ ዮሐኒ ["ኒ" ጠብቆ ይነበብ] ነው:: አበው ሊቃውንት የቅዱሱን ታሪክና ገድል ገና በልጅነት ስለ ነገሩን አንረሳውም:: እጅግ ጣፋጭ ዜና ሕይወት ያለው አባት ነውና:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ቅዱስ አፄ ካሌብ ነግሦ ሳለ: አንድ ቅዱስ ሰው ከግብጽ ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: እኒህ ሰው "አሞኒ ዘናሕሶ" ይባላሉ:: ቅዱሱ ዓለምን ላለማየት ቃል ገብተው በትግራይ በርሃ ይጋደሉ ነበር::
በዘመኑ አፄ ካሌብ የናግራን [የመን] ክርስቲያኖችን ለመታደግ ዘመቻ አድርጎ ነበር:: ታዲያ አንድ የንጉሡ ወታደር ወደ ዘመቻ ሲሔድ ሚስቱን ይጠብቅለት ዘንድ ትንሽ ወንድሙን አደራ ይለዋል:: ወንድሙ ግን አደራውን ትቶ የትልቅ ወንድሙን ሚስት አስገድዶ ይደርስባትና ትጸንሳለች::
ከዘመቻ የተመለሱት ከ፩ ዓመት በሁዋላ ነውና ሚስቱን ምጥ ላይ ያገኛት ወታደር ደነገጠ:: ተቆጣ:: የጸነሰችው ከእርሱ እንዳልሆነ ያውቃልና ምጥ ላይ ሆና ሊያዝንላት አልፈለገም::
ለገልጋይ አስቸግሮ ሚስቱን ይደበድባት ገባ:: በዚህ ምጥ: በዚህ ዱላ ነፍሷን ከሥጋዋ ሊለየው የደረሰችው ያቺ ሴት ግን "ወንድማማችን አላጋድልም" ብላ ቻለችው:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ያን ግብጻዊ ባሕታዊ [አባ አሞኒን] አምጥቶ ከሰዎቹ በር ላይ አቆመው::
"ከእሱ ነው በይ" አላት:: እርሷም "ከዚያ ባሕታዊ ነው" ብላ ተናገረች:: ወታደሩ ባሏም በቁጣ ወጥቶ ቅዱስ አሞኒን በዱላ ስብርብር እስኪል ድረስ ደበደበው:: ልጁ ልክ ሲወለድም ከእናቱ ነጥቆ ለባሕታዊው አሳቅፎ አባረረው::
ቅዱስ አሞኒም ሕጻኑን አቅፎ ወደ ተምቤን በርሃ አካባቢ ወሰደው:: ግን ምን ምግብ: ምን ልብስ: ምን መኝታ እንደሚሰጠው ጨንቆት ጻድቁ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜም ቅዱስ መልአክ የጸጋ ምንጣፍን አነጠፈለት::
ጆፌ አሞራ መጥቶ ክንፉን ሲያለብሰው አጋዘን መጥታ ጡት አጠባችው:: በዚህ የተደነቀው ቅዱስ አሞኒ ሕጻኑን "ዮሐኒ" ሲል ስም አወጣለት:: ትርጉሙም "ወልደ አራዊት - ወላጆችህ [አሳዳጊዎችህ] አራዊት ናቸው" እንደ ማለት ነው::
ሕጻኑ ዮሐኒ በዚህ መንገድ ከአሞኒና ከአራዊቱ ጋር አደገ:: ፭ ዓመት በሞላው ጊዜም ትምሕርተ ሃይማኖትን: የቅድስና ሕይወትን ተማረ:: ልክ እንደ መንፈሳዊ አባቱ በጾምና በጸሎት ተወሰነ:: ግን እርሱ ከእርሱ: ከአሞኒና ከአራዊቱ በቀር ሌላ ፍጥረት: ዓለም [ብዙ ሰዎች] መኖራቸውን አያውቅም::
፲፪ ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ክህነት ይገባዋል ብሎ መንፈስ ቅዱስ ስላሳሰባቸው ቅዱሱ አሞኒ ዮሐኒን ወደ ዻዻሱ ወሰዱት:: መንገድ ላይም ቅዱስ ዮሐኒ ወጣት ሴቶች ተሰብሰበው ሲጫወቱ ተመልክቶ "አባ! እነዚህ ጸጉራቸው የረዘመ: ደረታቸው ወደ ፊት የወጣ ፍጥረቶች ምንድን ናቸው?" ሲል ጠየቀ::
አባ አሞኒም "ልጄ! እነዚህ ሴቶች ናቸው:: ግን ለእንደ እኔና አንተ ያሉ የበርሃ ሰዎች አይሆኑምና አትቅረባቸው" አለው:: ቅዱስ ዮሐኒ መልሶ "አባቴ!ድንገት ቢመጡብኝ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀ:: አባ አሞኒም "ልጄ! ከዘለዓለም ርስት ከምትነቀል ሩጠህ ብታመልጥ ይሻላል" አለው::
ከ፮ ዓመታት በሁዋላ [ዮሐኒ ፲፰ ዓመት ሲሞላው ማለት ነው] ቅዱስ አሞኒ ኅዳር ፭ ቀን ዐረፈ:: ለ፲፬ ዓመታትም ቅዱስ ዮሐኒ ከአራዊትና አባ አበይዶን ከመሰሉ አባቶች ጋር ኖረ:: ከንጽሕናው የተነሳም ቅዱሳን መላእክት ያነጋግሩት ነበር::
ስም አጠራሩ በምድረ ትግራይ ሲወጣ ወላጅ እናቱ በሕይወት ነበረችና ሰማች:: የአካባቢዋን ሴቶች ሰብስባም ልትገናኘው ወዳለበት ተራራ ገሰገሰች:: ወደ ተራራው ደርሳ ስትጠራው ቅዱሱ ተመለከታት::
ወዲያው ትዝ ያለው አባቱ ቅዱስ አሞኒ "ሴት ስታይ ሩጥ" ያለው ነውና እግሩን አንስቶ ሮጠ:: እናቱ ስትከተለው: እርሱ ሲሮጥ ከገደሉ ጫፍ ደረሰ:: ወደ ሁዋላ ሲመለከት ሊደርሱበት ነው::
በስመ ሥላሴ ፊቱን አማትቦ ወደ ገደሉ ተወረወረ:: በዚህ ጊዜ ግን መንፈሳዊ ክንፍ ተሰጥቶት ተሰወረ:: ቅዱስ መልአክም ብሔረ ሕያዋን አስገብቶታል:: ይህንን ታሪክ ሲያደንቁ አበው እንዲህ ብለዋል::
"ሰላም ዕብል ለዘኮነ ሱቱፈ::
ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ::
እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንትኒ ኢያትረፈ::
ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ::
ወከመ ክንፎሙ አብቆለ አክናፈ::" [አርኬ]
🕊 † ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት † 🕊
ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: [ዮሐ.፱፥፳፪]
ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ አሞኛል ብሎ እስከ ፱ ሰዓት ድረስ ቆየ::
በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ወደ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::
ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::
ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት::
ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት: ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::
በመጨረሻ በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት:: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽቅድ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: አይሁድም አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::
" አስተርዮተ ርዕሱ "
ይሕች ዕለት አስተርዮተ ርዕሱ ትባላለች:: እርሱን ከገደሉ በሁዋላ አይሁድ ራሱን ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው ጥለዋት ነበር:: የእርሱን ሰማዕትነት ያየች አንዲት ክርስቲያንም ከለቅሶ ብዛት ዐይኗ ቢጠፋ ሕጻን ልጇን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች::
ወዲያው ግን ሕጻን ልጇ ሞተባትና ሐዘኗ ከልኩ አለፈ:: ለአንዲት እናት ዐይንንና ልጅን በአንዴ ማጣት እጅግ ጭንቅ ነው:: በሌሊት ግን ቅዱስ ለንጊኖስ በራዕይ ተገልጦ ደስታ ነገራት::
"ልጅሽ በገነት ሐሴትን ያደርጋል:: አንቺ ግን ራሴን ከተቀበረችበት አውጪ" አላት:: ወደ ጠቆማት ቦታ በመሪ ስትቆፍር ብርሃን ወጥቶ ዐይኗ በራላት:: በታላቅ ሐሴትም ቅድስት ራሱን ወደ ሃገሯ ወስዳታለች::

አምላከ ቅዱሳን የቀደምቶቻችንን የዋህነት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
🕊
[ † ኅዳር ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ታላቁ ቅዱስ ዮሐኒ [ዘትግራይ]
፪. አባ አሞኒ ዘናሕሶ
፫. ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
፭. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
፫. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ]
፬. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
" ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል:: ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ: እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:- "ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:- "የወጉትን ያዩታል" ይላል::" [ዮሐ.፲፱፥፴፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
[ † ኅዳር ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ታላቁ ቅዱስ ዮሐኒ [ዘትግራይ]
፪. አባ አሞኒ ዘናሕሶ
፫. ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
፭. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
፫. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ]
፬. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
" ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል:: ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ: እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:- "ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:- "የወጉትን ያዩታል" ይላል::" [ዮሐ.፲፱፥፴፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊 💖 ▬▬ † ▬▬ 💖 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ❝ ከአንቺ ግን .... ! ❞ ]
🕊
❝ እግዚአብሔር ዐሥሩን ቃላት በእጁ የጻፈባቸውን ሁለቱን ጽላት በደብረ ሲና ሰጠ ከአንቺም እግዚአብሔር ቅዱስ ጽላትን ፈጠረ ይኸውም ሥጋው ነው። [ዘፀአ.፴፬፥፳፰-፴]
ከደብረ ሲና እሳት ጨለማ መጣ ፤ ከአንቺ ግን ሰው የሆነ አምላክ ተገኘልን፡፡
በደብረ ሲና በአይሁድ ላይ ድንጋፄ ሀውክ ተደረገ ፤ በአንቺም በአይሁድ በሄሮድስ በዲያብሎስና በሠራዊቱ ላይ ጽኑ ድንጋፄ ተደረገ፡፡ [ዘፀአ.፳፥፲፰ ፡፡ ዕብ.፲፪፥፲፱] ❞
[ ቅዱስ ኤፍሬም ]

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡
🕊 † ኅዳር ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † 🕊
✞ 🌹በዓለ ደብረ ቁስቁዋም🌹 ✞
የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ [ማቴ.፪፥፩-፲፰] እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ፪ ዓመቱ የጥበብ ሰዎች [ሰብአ ሰገል] ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ: እጣን: ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::
ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ መቶ አርባ አራት ሺህ [144,000] ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፩ አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች::
ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ: በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::
- የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
- ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
- የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
- የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
- የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
- እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች::
ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::
አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::
"መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምን ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?"
፩. ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና [ኢሳ.፲፱፥፩, ዕን.፫፥፯]
፪. ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ [እሥራኤል] : ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::
፫. ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: [ኢሳ.፲፱፥፩]
፬. የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::
፭. ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: [ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::]
፮. ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና
፯. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::
እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ፫ ዓመታት ከ፮ ወራት [ወይም ለ፵፪ ወራት] በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ድንግል ማርያም ከርጉም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር [ደብረ ሊባኖስ] ነው::
በዚያ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች:: በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች::
"እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ" እንዲል:: [እሴብሕ ጸጋኪ]
ቀጥላም በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ [አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው] ዐረፈች:: ከደብረ ቢዘን በደብረ ዳሙ: አክሱም: ደብር ዓባይ: ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ጣና ደርሳለች:: በጣና ገዳማትም: በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ፻ ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሽዋ ሒዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::
ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች:: በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች:: ከልጇም በአሥራትነት ተቀብላለች:: ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::
እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች [ከሰብአ ኦፌር] የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ፭ ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቁዋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል:: ሐሴትንም አድርገዋል::
ዳግመኛም ከክርስቶስ ስደት ፬፻ ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቁዋም ታንጻ ተቀድሳለች:: የቅዱሳን ማደሪያም ሁናለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ፫፻፺ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: አስከትሎ ወረደ::
የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው: ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሁኗል::
ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው :-
"እመ ኀሎኩ በጐይዮቱ ውእተ መዋዕለ:
እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ:
ወበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ጸበለ:
ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኀበ ተተክለ:
ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናየ ቆስለ::" እንዳሉ:: [ሰቆቃወ ድንግል]
እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል::
ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ:: የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና::
"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ:
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ" ልንልም ይገባል::
+" 🌷አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ 🌷 "+
ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::
የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ::
ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው /ሲያጠምቁዋቸው 'ጽጌ ድንግል' አሏቸው:: ሲመነኩሱም 'ጽጌ ብርሃን' ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::

የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን ፻፶ ዓርኬ አድርግው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው [ወለቃ አካባቢ የሚገኝ] ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: ጻድቁ ያረፉት ጥቅምት ፳፯ ሲሆን ዛሬ የቃል ኪዳን በዓላቸው ነው::
ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::
🕊
[ † ኅዳር ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም [ሚጠታ ለማርያም]
፪. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፫. ቅድስት ሰሎሜ ቡርክት
፬. ቅዱስ ዮሳ [ ወልደ ዮሴፍ ]
፭. ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ
፮. አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
፯. አባ ፊልክስ ዘሮሜ
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፯. ቅድስት ሰሎሜ
፰. አባ አርከ ሥሉስ
፱. አባ ጽጌ ድንግል
፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል
" ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኗን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች::" [ራዕይ.፲፪፥፬-፯]