Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
✞ ጥቅምት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞
† 🕊 ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ንጉሥ 🕊 †
✞ የሰው ልጅ 'ንጉሥ' ተብሎ 'ቅዱስ' መባል ግን ምን ይደንቅ?! ይህ ታላቅ ኢትዮዽያዊ መሪ ንጉሥ ሲሆን: እንደ ደናግል ድንግል: እንደ ባሕታውያን ገዳማዊ: እንደ ቀስውስት ካህን: እንደ ሐዋርያት ሰባኪ ሆኖ መገኘቱ ይደንቃል::
+ የሚያሳዝነው ይህንን እንቁ ንጉሣችን ብዙ ኢትዮዽያውያን መዘንጋታችን ብቻ ነው:: የላስታ አካባቢ እጅግ የታደለችና የተቀደሰች ናት:: እንደ ሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ሁሉ እሷም መካነ ቅዱሳን ናትና::
+ ቅዱስ ይምርሐ የዘር ሐረጉ ከዛግዌ ነገሥታት ሥር ሲሆን አባቱ ግርማ ስዩም ይባላል:: ይኸውም በመጀመሪያው ሺህ ዓመት [Millenium] መጠናቀቂያ ላይ ነግሶ የነበረ ነው:: ዣን ስዩም [የላሊበላ አባት] : ጠጠውድም [ንጉሡ] እና ግርማ ስዩም ወንድማማቾች ናቸው::
+ ቅዱሱ ሲወለድ አባቱ በሕይወት አልነበረም:: እናቱና የወቅቱ አባቶች "ይምርሐነ ክርስቶስ-ክርስቶስ ይምራን" አሉት:: ገና ከሕጻንነቱ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ረቡዕና ዓርብ ቀን እስከ ፱ [9] ሰዓት ድረስ የእናቱን ጡት አይቀምስም ነበር:: እናቱ ግን ባለመረዳት ትጨነቅ ነበር::
+ የወቅቱ ንጉሥ ጠጠውድም "ከእኔ ቀጥሎ የሚነግሠውን ባወኩት" እያለ ሲመኝ በሕልሙ "ሕጻኑ ይምርሐ ነው" የሚል በማየቱ ሕጻኑን አስመጣው:: ከደም ግባቱ የተነሳም ቅንዓት አድሮበት አማካሪዎቹን "ምን ላድርገው?" አላቸው::
+ እነርሱም "ብትገድለው እግዚአብሔር በደሙ ይጠይቅሃል:: ግን እንዳይወርስብህ ከፈለክ እረኛ አድርገው" አሉት:: [የዋሃን! ቅዱስ ዳዊት ከእረኝነት መጠራቱን ዘንግተውታል] ከ፯ [7] ቀናት በኋላ ግን መጥተው "ንጉሥ ሆይ! ፈጣሪ ካለ የሚቀር ነገር የለምና በቃ ዝም ብለህ ግደለው" አሉት::
+ በዚያች ሰዓት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ እናቱን "ይምርሐን ስጭኝ" አላት:: እናት ናትና ጨነቃት:: መልአኩ ግን እንደሚጠብቀው ቃል ገብቶላት ከላስታ ነጥቆ ኢየሩሳሌም አደረሰው::
+ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም ለዓመታት ተምሮ ዲቁናን ተቀበለ:: በኢየሩሳሌም አካባቢም በጾምና በጸሎት ተወስኖ ፈጣሪውን እያገለገለና ወንጌልን እየሰበከ የወጣትነት እድሜውን ገፋ::
+ አንድ ቀን ግን መድኃኒታችን ተገልጦ "ወዳጄ ይምርሐ! ሚስት አግብተሀ: ቅስና ተቀብለህ አገልግለኝ" አለው:: ቅዱሱ ይህንን ሲሰማ አዝኖ "ጌታየ! የእኔስ ፈቃዴ በድንግልና አገለግልህ ዘንድ ነው" አለው:: ጌታችንም "ግዴለህም! ሁሉም አይቀርብህም" ብሎ አንዲት ሕዝባ የምትባል ደግ እሥራኤላዊት ጠቆመው::
+ ቅዱስ ይምርሐም ቅድስት ሕዝባን በተክሊል አግብቶ: ቅስናን ተቀበለ:: ግሩም የሚያሰኘው ግን ፪ [2]ቱ ቅዱሳን ከ፵ [40] ዓመታት በላይ በትዳርም: በድንግልናም መኖራቸው ነው:: "ለሚያምን ሁሉ ይቻላል" ይል የለ ቅዱስ መጽሐፍ!
+ ቅዱሳኑ ወዲያው ለአገልግሎት ወደ ግብጽ ወረዱ:: በዚያ ለጥቂት ዓመታት እንደቆዩ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ወደ ኢትይዽያ መመለስ ፈለገ:: አንድ ቀን ሕዝቡ ተሰብስበው ጸሎተ ኪዳንን ሲመራ "እግዚአብሔር አብ ወሐቤ ብርሃን-ብርሃንን የምትሰጥ እግዚአብሔር አብ" ከሚል ሲደርስ ወደ ሰማይ ጮኸ::
+ ከሰማይም "አቤት ልጄ ሆይ!" የሚል መልስ መጣለት:: ይምርሐም "ምነው ጌታየ በሰው ሃገር ረሳኸኝ?" ቢለው "አልረሳውህም:: ይልቁኑ ሊገድልህ የሚፈልግህ ንጉሥ ሙቷልና ሒደህ ንገሥ" ሲል አዘዘው::
+ ቅዱሱም ሚስቱን ሕዝባን ይዞ ላስታ ሲደርስ ሕዝቡ በዕልልታ ተቀብሎ ወዲያው አነገሠው:: በዚያም ለ፲፭ [15] ዓመታት ቅዱስ ሩፋኤል እየተራዳው: ሕብስትና ጽዋዕ ከሰማይ እየወረደለት ቀድሷል:: ሃገሪቱንም መርቷል::
+ አንድ ቀን ግን ክፉ መካሪዎች "ተጨማሪ ሚስት አግባ" ቢሉት ተቆጣቸው:: በኋላ ደግሞ 'ለምን ተቆጣሁ' ብሎ አዘነ:: ስለዚህም ሃሳቡ ሰማያዊው ስጦታ ቀረበት::
+ እያለቀሰ ጌታን ቢማጸን ጌታችን "ስላሰብከው ክፉ ሃሳብ [ለምን ተቆጣሁ ማለቱ ወደ ምክራቸው ማዘንበሉን ያሳይነበርና] ይቅር ብየሃለሁ:: ነገር ግን እኔ ወደ ማሳይህ ቦታ ካልሔድክ ፪ [2]ኛ አይወርድልህም" አለው::
+ ቅዱሱ ለጊዜው ትንሽ ቢከራከርም "እሺ" ብሎ በቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ዛሬ ወደ ምናውቀው አካባቢው ሔደ:: በዚያም አራዊትን በጸሎቱ አድክሞ: መሠሪዎችን አስተምሮ: ሕዝቡንም አሳምኖ አጠመቃቸው::
+ ጌታም "ከኢየሩሳሌም በደመና እየጫንክ በዚህ ባሕር ላይ ቤቴን ሥራልኝ" አለው:: ቅዱስ ይምርሐም መስከረም ፲፫ [13] ቀን [በበዓለ ባስልዮስ] ጀምሮ ሰኔ ፳ [20] [በበዓለ ሕንጸታ] ፈጸመና ታቦተ ገብርኤልን ሰኔ ፳፩ [21] ቀን ቀደሰው::
+ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ግን በዚያ ቦታ እየቀደሰ ለ፳፭ [25] ዓመታት ሃገሪቱን አስተዳደረ:: አንድ ጊዜ ቅዱስ ሩፋኤል ለንጉሡ ከሰማይ ሕብስትና ጽዋዕ ሲያወርድለት ፩ [1] ባሕታዊ አይቶ "ለምን?" ብሎ ተቆጣ:: መልአኩ ግን የንጉሡን ክብር ነግሮ "እየዞርክ ስበክ" ብሎታል::
+ በዚያ ባሕታዊ ስብከትም ከመላው ዓለም ብዙ ሺህ ሰወች መጥተው ቅዱስ ይምርሐን "ቀድሰህ አቁርበን?" ብለውለምነውታል:: ቅዱሱም ሲያቆርባቸው በመምሸቱ ጸሐይን አቁሟታል::
+ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ እንዲህ ባለ ጣዕመ ሕይወት ኑሮ: ለ፵ [40] ዓመታት ሃገራችንን አስተዳድሮ ጥቅምት ፲፱ [19] ቀን ዐርፎ በዚያው ሥፍራ ተቀብሯል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን: ደጅህን የረገጠውን እምርልሃለሁ" ብሎታል::
† 🕊 ቅዱስ ዮሐንስ ዘጸይለም 🕊 †
✞ በምድረ ግብጽ በዘመነ ጻድቃን የተነሳው ታላቁ አባ ዮሐንስ "ሐዋርያዊ ጻድቅ" ይባላል:: ወላጆቹ ደጋግ: የተወለደው በጾምና ጸሎት: ያደገውም በሥርዓት ነው:: በወጣትነቱ ከቤተሰቦቹ ጠፍቶ: በርሃ ገብቶ የአባ ስምዖን ደቀ መዝሙር ሆኗል::
+ በዚያም በፍጹም ትሕርምት ሲኖር ባልንጀሮቹ ይጠፉበታል:: እነሱን ሊፈልግ ሲሔድ ግን አረማውያን ይዘው አሠሩት: አሰቃዩት:: መንገድ ላይ ውሃ ጠምቷቸው ሲጨነቁ "ውሃ ባጠጣችሁሳ?" አላቸው:: "እንለቅህ ነበር" አሉት::
+ ጸልዮ: ውሃ አፍልቆ ቢያጠጣቸው "አንተማ ታስፈልጋለህና አንለቅህም" አሉት:: ወስደውም ጸይለም በምትባል ሃገር ለባርነት ሸጡት:: በዚያ ሲያሰቃዩት ተአምራትን አድርጐ በክርስቶስ አሳምኗቸዋል::
+ ወደ ጐረቤት ሃገር ሔዶም ዛፍ ሲያመልኩ አገኛቸው:: "ወደ ክርስቶስ ተመለሱ" አላቸው:: "እንቢ" ሲሉት ምሳር [መጥረቢያ] ይዞ: ወደ ዱሩ ውስጥ ገብቶ ጸለየና ምሳሩን አነሳ::

+ "በስመ ሥላሴ እገዝመክሙ" ብሎ ቢቃጣቸው አጋንንት የሠፈሩባቸው ፲ሺህ [10,000] ዛፎች ባንዴ ወደቁ:: በዚህ ምክንያትም ፬ መቶ ሺህ [400,000] ሰዎች አምነው ተጠምቀዋል:: ወደ ሌላ ሃገር ሒዶም ስቃይን ታግሦ: ተአምራትን ሠርቶ ብዙዎችን አሳምኗል:: በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል::
✞ አምላከ ይምርሐ ደጉን መሪ: አምላከ ዮሐንስ ቸሩን አስተማሪ ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
[ † ጥቅምት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ [ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ዘጸይለም
፫. አባ ስምኦን ገዳማዊ
፬. ቅዱሳን በርተሎሜዎስና ሚስቱ [ሰማዕታት]
፭. አበው ኤዺስ ቆዾሳት [ሳምሳጢን ያወገዙ]
፮. ጻድቃን እለ መጥራ
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
" አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል:: የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም:: በበጐ በረከት ደርሰህለታልና:: ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱላይ አኖርህ:: ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም:: ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ:: በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው::" [መዝ.፳፥፩-፭] (20:1-5)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
✞ አምላከ ይምርሐ ደጉን መሪ: አምላከ ዮሐንስ ቸሩን አስተማሪ ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
[ † ጥቅምት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ [ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ዘጸይለም
፫. አባ ስምኦን ገዳማዊ
፬. ቅዱሳን በርተሎሜዎስና ሚስቱ [ሰማዕታት]
፭. አበው ኤዺስ ቆዾሳት [ሳምሳጢን ያወገዙ]
፮. ጻድቃን እለ መጥራ
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
" አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል:: የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም:: በበጐ በረከት ደርሰህለታልና:: ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱላይ አኖርህ:: ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም:: ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ:: በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው::" [መዝ.፳፥፩-፭] (20:1-5)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
[ ✞ እንኩዋን ለታላቁ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር እና ለቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]
🕊 † ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር † 🕊
በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም:: እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስን [ዛሬ የምናከብረውን] ያህል አጭር አልነበረም:: በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም "ዮሐንስ ሐጺር - አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል::
ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ :-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::
ቅዱሱ የተወለደው በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል:: ወደ ምናኔ የገባው ገና በ፲፰ ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::
ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ "አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር::
ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::
አባ ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::
አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: [የአካባቢው ጅብ መናጢ ነበር] አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል::
ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ ወስዶ ተከለው::
ከዚያም ለ፪ ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ::
በ፫ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም::
ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ፲፪ ዓመት አስታሞታል::
መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::
መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር:: ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::
አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ [ተመስጦ] መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን ሊቃነ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል በግርማ በጌታ ፊት ቆመው ተመለከተ::
"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል::
ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ ባቢሎን [የአሁኗ ኢራቅ] ሒዶ ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ፬፻ ዓመታት በዚያው ቆይቷል::
በ፰፻፳፭ ዓ/ም ግን በአባ ዮሐንስ ፓትርያርክ ዘመን ክቡር ሥጋው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው ጥቅምት ፳ ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል::
ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም [መብረቆች] ተብለጨለጩ:: ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::
🕊 † ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ † 🕊
+ ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ
+ ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ
+ መናኔ ጥሪት የተባለ
+ በድንግልና ሕይወት የኖረ
+ የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት
+ እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ
+ አንዴ በሕይወቱ: አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው::
ቅዱስ ኤልሳዕ በጣም ረዥም: ራሱ ገባ ያለ [ራሰ በራ] : ቀጠን ያለ: ፊቱ ቅጭም ያለ [የማይስቅ] ሽማግሌ ነበር::
አምላከ ቅዱሳን የሐጺር ቅዱስ ዮሐንስን መታዘዙን: ትሕትናውን: ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን:: በበረከቱም ይባርከን::
🕊
[ † ጥቅምት ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር
፪. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ
፫. አባ ባይሞይ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፪. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፫. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፬. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
፮. ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት
[ " እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን: ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል' በሉ::" [ሉቃ.፲፯፥፲] ]

Forwarded from ✞ገድለ ቅዱሳን✞
እንኳን አደረሰን
ጥቅምት 21 የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።
ከተፈጥሮ ሕግ በላይ ለሰው አእምሮ በረቀቀ
ከእግዚአብሔር በተሰጣት ጸጋ ድንቅ ተአምራት የምታደርገው
ሊገለበጥ ያለን የተሳፈረችበት አውሮፕላን ቅዱስ ሩፋኤል
አንዱን ክንፍ ቅዱስ መርቆሬዎስ አንዱን የአውሮኘላን ክንፍ ጫፍ
ያዙ ብላ ቃል እያወጣች የብዙዎችን ሕይወት ከሞት የታደገች።
ታላቋ እናታችን የየካይሮ
ቅዱስ መርቆሬዎስ (አቡሰይፌን )
የሴቶች ገዳም
እመምኔት እማሆይ ኤሪኒ ናት።
እግዚአብሔር በዘመናችን የገለጣት ቅድስት ናት
ክርስትናችን ለጠወለገ ለወየበብን ዜና ገድሏ ወዝ ነው።
ከእጆቿ በረከት የተቀበልን በጸሎቷ የተጠቀምን ዛሬም በአጸደ ነፍስ ሆና ከእግዚአብሔር እያማለደለደች ድንቅ ተአምራት የምታደርግልን ልጆቿ እናስባታለን።
እናቴ ሆይ ኃጥእ ልጅሽን ዛሬም ጎብኚኚኝ እኔም ስላንቺ አንስቼ
አውግቼ አልጠግብም የምልጃሽ ጥላ የጸሎትሽ ኃይል ነው ያቆመኝ ኹሌም አጠገቤ እንደምትቆሚ ሳስብ ሐሴት አደርጋለሁ።
እውነተኛ እናት እድፍ ጉድፍ ኃጥያት የማትጸየፊ እንደ አምላክሽ "ከባቴ አበሳ።" ገበና ሸፋኝ ለክርስቲያኖች ደኃንነት የምትማልጂ
አንቺን የሰጠንን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ካንቺ ያስተዋወቁኝ
እናቴን ናዲያን ኹሌ በልጅ አንደበት እመርቃለሁ።
ወንድሜ
Michael Misrue
በጥሩ ቃላት በአጭሩ ዜና ገድሏን የጻፈውን እናንብብ።
በበለጠው በእህታችን አዜብ በርሔ የተተረጎመውን
ሙሉ የእናታችን ዜና ሕይወት "ዝክረ ቅዱሳን አንስት ዘተዋሕዶ።"
ብላችሁ አንብቡ ተጠቀሙ።
ይህች ቅድስት የተወለደችዉ በግብፅ አገር ልዩ ስሙ ጊርጋ በተባለ ስፍራ ነዉ፡፡ የልደተት ስሟ ፋውዚያ ይባላል፡፡ ይህች ቅድስት እንደ ሌላዉ ቅዱሳን በሰላም አልተወለደችም ማለትም እናቷ ከመጠን በላይ ነበር የታመመችዉ(እርሷን በምትልድበት ጊዜ) በዚያ በጭንቅ ሰዓት አባቷ እና አያቷ ይፀልዮ ነበር አባቷ አምላክን ለወለደቸች ለክብርት እመቤታችን አያቷ ደግሞ ለሰማዕታት አለቃ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲያማልዷቸዉ አጥቀብዉ ይጸልዮ ነበር ከዚያም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ መጠጥተታ ለእናትዋ ተገለጸችላት ቅዱስ ጊዮርጊስንም 'ጀርባዋን ዳስሰዉ' አለችዉ እርሱም እጅ ነስቶ ጀርባዋን ዳሰሰዉ በሰላምም ተገላገለች እመቤታችንም ህጻኗኗን ታቅፋ 'ይህች ልጅ የእኛ ናት' ብላ ህጻኗኗን ባርካ ወደ ሰማይ አረገች፡፡ከዚያም እያደገች በሄደች ቁጥር ለክርስቶስ ያላት ፍቅር እየጨመረ መጣ ሳታውቀውም ወደ ገዳም ለመሔድ ትናፍቅ ጀመረ እንደዚህ አይነት ፍላጎት የጀመረት ገና የ8 ዓመት ልጅ በነበረችበት ጊዜ ነዉ፡፡
የምትማረዉ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነበረ በዚያም ደናግላን(ሴት መነኮሳየያት) ነበሩ እንደ እድሜ ጓደኞቿ መጫትን ትታ እነርሱን ታይ ነበረ እንድ ቀን በትምህርት ቤታቸዉ በሚገኝ የደናግላኑ ጸሎት ቤት ሔደች ከዚያም አንዷ የካቶሊክ ደናግል ስትጸልይ አገኘቻት ጸለሎቷን እስክትጨርስ ቁጭ ብላ መጠበቀቅ ጀመረቸች ያቺ መነኩሲት ጸሎቷን ፈጽማ ወደ ተቀመጠቸዉ ቅድስት ሄዳ ልጄ ምን ሆንሽ አለቻት ቅድስቲቱም እኔ እንደ እናንተ መነኩሴ መሆን እችላሁ? ብላ ጠየቀቻት መነኩሲቷም አዎን ትችያለሽ አለቻት በመቀጠልም በመጀመሪያ እኔ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ስለሆንኩ በራሴ ቤተክርስትያን ልቁረብና ከዚያም ልቀላቀላችሁ አለቻት መነኩሲቷም መነኩሴ መሆን ከፈለግሽ ትችያለሽ ግን መቁረብ የምትችይዉ በእኛ ቤተክርስትያን ነዉ ምክንያቱም የእኛ እምነት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይያልና አለቻት ቅድስቲቱም ታዲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማትን አላውቃቸውም አለቻት መነኩሲቷም እኔ እገርሻለሁ ለምንኩስና የመሚያስፈልጉትን ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ አስተምርሻሁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖትሽን እንድትለቂ አልፈልግም አለቻት፡፡
መነኩሲቷም እንደነገረቻት በቤቷም ሆነ በቤክርስትያን ትጸልይ ነበረ በተለይም ጠዋት ጠዋት ደስ የሚል የቤተክርስትያን ዕጣን ይሸታት ነበረ ግን ይህ የሚሆነዉ ከቅዳሴ በፊት ነበረ፡፡ ይህ ነገር ያሳሰባት እናቷ ወደቤተክርስትያን ሄዳ ለካህኑ ነገረችዉ እርሱምም ልጅሽ የተባረች ናት ያ የዕጣን ሽታ ሥውራን ባህታውያን በሚጸልዩት ሰዓት የሚሸት ነዉ አላት፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እናቷ ታመመች ህመሙም የሚያቃንቅ አልነበረመም ይህንን የምታውቀዉ ቅድስቲቱ እናቷን አጽናንታ ወደ ቤተ-ክርስትያን ሄዳ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ስዕል ፊት ቆማ መጸለይ ጀመረች እመቤቴ ሆይ እባክሽ እናቴን ፈውሻት እኛ ልጆችሽ ነን አምንሻሁ ብላ ጸለየች በመቀጠልም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ለእናቷ ተገለጸቸላት እንዲህም አለቻት ለምን ታቅሻለሽ እናትየዋም ልጆቼ ህጻናት ናቸዉ እኔ ከሞትኩ እግዚአብሔር እንደሚፈልገዉ ላያድጉ ይችላሉ እባክሽን ከጌታ ፊት አማልጂኝ ታላቅ እህታቸዉ እስክታድግና ኀላፊነትን እስክትረከብ ድረስ አለቻት አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን መልሳ ከእኔ ጋር ነይ አለቻት ከዚያም እናትየዋ ወዴት እኔ ለባለቤቴ ሳልናር አልወጣም አለቻት አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን መልሳ አንቺ በባልሽ ቦታ ብትሆኚ ከጌታ እናት ጋር ለመሔድ ደስ ይልሽ ነበረ ብላ ወደ ሰማይ ይዛት ሄደች ከዚያም በመልካም መኝታ አስተኛቻት ከዚያም እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ጊዮርጊስ እስኪ እያት መርራት አለችዉ እርሱም እናቴ እመቤቴ ሆይ እንደምታውቂዉ የእርሷ ጉዳይ አብቅቷል ድናለች አላት ክብርት እመቤታችንም እኔ እንዳማልዳት ጠይቃኝ ነበረ እኔም ልመናዋን ተቀብዬ ለልጄ ለወዳጄ ነግሬዋለሁ አሁን ያለባትን ችግር ነቅለህ ጣልላት አለችዉ ቅዱስ ጊዮርጊስም እናቴ ያንቺ እጅ ይዳሳትና ከዚያ አወጣወዋለሁ አላት እመቤታችንም ዳሰሰቻት ቅዱስ ጊዮርጊስም አውጥተቶ ለእናትየዋ ይህንን ይዘሽ ወደ በቤትሽ ሒጂ አላት፡፡
ቅድስቲቱ ገዳም የመግባት ፍላጎቷ እየጨመረ መጣ ከዚያም ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆርዮስ ተገለጸላት ስለእርሱ ሰምታ አታውቅም ነበረ እርሱም ራሱን ካስተዋቃት በኋላ ወደ ገዳሙ ወሰዳት ከሰዳትም በኋላ ገዳሙን ሁሉ አስጎኛት በኋላ ወደ ቤቷ በደቂቃ መለሳት ገዳሙ ርቀት ነበረዉ የወሰዳትም በሕልም ሳይሆን በውን በፈረሱ ነዉ፡፡ እመቤታችን ለእናትየዋ ተገለልጻላት ያኔ ስትወልጂ የኛ ነች ብየሽ አልነበረ አሁንም ወደ ገዳም ውሰጃት አለቻት(ምክንያቱም አባቷ አትሄጂም ብሎ ስለከለከላት)፡፡ ገዳምም ገብታ የገዳም ኑሮ ጀመረች በዚያ ገዳም እማሆይ አፍሮዚና የምትባል ኢትዮጵያዊት ቅድስት መናኝ ነበረች እርሷም እንዳየቻት "ኢንቲ አልደብራ ረይሳ ደብራ አቡ ሰይፈን" አሏት ትርጓሜውም አንቺ የደብረ አቡሰይፈን ገዳም እመምኔት(አለቃ) ትሆኛለሽ አለቻት(በግብጽ ቅዱስ መርቆሬዎስ አቡሲፊን ተብሎ ይጠራል አቡሰይፈን ማለት የሁለት ሰይፎች አባት ማለት ነዉ፡፡)
የበጎ ነገር ጠላት የሆነዉ ሰይጣን ቅድስቲቱን ይፈትናት ነበር እርሷም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታባርዉ ነበር እመቤታችንም በየጊዜዉ ትጎበኛት ነበር፡፡የተተነበየላት ነገር ደረሰ እመምኔት እንድትሆን በቅዱስ ቄርሎስ ስድስተኛ ተመረጠች እርሱም ፕትርክና ከመሾሙ በፊት አንድ ጊዜ አግኝቷት እመምኔት እንደ ምትሆን ነግሯት ነበር፡፡ ከዚያም ቅድስት ታማቭ ኢሪኒ እኔ እመምኔት መሆን አልፈልግም አለች በግድ ጎትተዉ ወደ ጳጳሱ ወስደዋት ተባርካ አስኬማ ለብሳ

እመምኔት ሆነች እመምኔት ከሆነች በኋላ በግል ፀባዩዋ ላይ የታየ ለውጥ አልነበረም እንደድሮ ትህትናዋን ለብሳ እናቶችን ታገለግል ነበር።የቅዱስ ፓኩሚየስን ( ጳጉሚስ) የገዳማዊ ኑሮ ሥርዓት እንደገና በስራ ላይ እንዲውል ያደረገች ቅድስት ናት፡፡ካለችበት ቦታ ወደ ፈለገችው ቦታ ልክ እንደቀሙት ቅዱሳን ወዲያውኑ ሰከንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትደርስ ነበር ገነት እና የተሰወሩ የቅዱሳን ያሉበትን ቦታ በየጊዜው ትጎበኝ ነበር ።ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ድንግል እናቱ እና ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሌሎች ብዙ ቅዱሳን ጋር መጥተው ያረጓጓት ነበር።የሰዎችን ችግር ማንም ሳይነግራት አውቃ እስከነ መፍትሄው ነግራ ታጽናናቸው ነበር።በሽተኞችን ትፈውስ ነበር ያዘነውን ታረጋጋ ነበር ገዳሙን ከነረበት ችግር አላቃ ወደ ትልቅ ገነትነት ለውጣዋለች ።
እናም ብዙ ልጆችን(መነኮሳያት) አፍርታ እነርሱም እንደእርሷ የበቁ ለመሆን ችለዋል፡፡መሞት አይቀርምና ገዳሙን በደንብ ካስተደረች በኋላ በክብር አርፋች፡፡ጸሎትና በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቋ እናት ታማቭ ኢሪኒ ጸሎት ይማረን።
እናም ብዙ ልጆችን(መነኮሳያት) አፍርታ እነርሱም እንደእርሷ የበቁ ለመሆን ችለዋል፡፡መሞት አይቀርምና ገዳሙን በደንብ ካስተደረች በኋላ በክብር አርፋች፡፡ጸሎትና በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቋ እናት ታማቭ ኢሪኒ ጸሎት ይማረን።
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
✞ ጥቅምት ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞
† 🕊 እግዝእትነ ማርያም 🕊 †
እመቤታችን ድንግል ማርያም የወልደ እግዚአብሔር እናቱ ናትና ሁሉን ትችላለች:: እርሱን ከሃሊ [ሁሉን ቻይ] ካልን እርሷን "ከሃሊት" ልንላት ይገባል:: ልክ ልጇ ሁሉን ማድረግ ሲችል በትእግስት ዝም እንደሚለው እመ ብርሃንም ስንት ነገር እየተደረገ: በእርሷ ላይም አንዳንዶቹ ስንት ነገርን ሲናገሩ እንደማትሰማ ዝም ትላለች::
እኛ ኃጥአን ንስሃ እስክንገባ ድረስም "ልጄ! የዛሬን ታገሣቸው?" እያለች ትለምንልናለች:: ቸሩ ልጇም ሊምረን እንጂ ሊያጠፋን አይሻምና "እሺ እናቴ!" እያለ ይኼው በዚህ ሁሉ ክፋታችን እስከ ዛሬ ድረስ አላጠፋንም::
- ቸር ነው
- መሐሪ ነው
- ይቅር ባይ ነው
- ታጋሽ ነው
- ርሕሩሕ ነው
- ቂምም የለውም:: በንስሃ ካልተመለስን ግን አንድ ቀን መፍረዱ አይቀርምና ወገኖቼ ንስሃ እንግባ: ወደ እርሱም እንቅረብ::
ይህቺ ዕለት ለእመቤታችን እሥረኞችን የምትፈታባት ናት:: የሰው ልጅ በ፫ ወገን እሥረኛ ሊሆን ይችላል:: በሥጋዊው :- አጥፍቶም ሆነ ሳያጠፋ ሊታሠር ይችላል:: በመንፈሳዊው ግን ሰው በኃጢአት ማሠሪያ የሚታሠረው በጥፋቱ ብቻ ነው::
ሌላኛው ማሠሪያ ደግሞ ማዕሠረ ደዌ [በደዌ ዳኝነት] መታሠር ነው:: መታመም የኃጢአተኛነት መገለጫ አይደለም:: ምክንያቱም ከቅዱሳን ወገን ከ፹ % [ፐርሰንቱ] በላይ ድውያን ነበሩና::
ታዲያ በዚህች ዕለት እመ በርሃን 3ቱንም ማሠሪያዎች እንደምትፈታ እናምናለን:: በእሥር ቤትም: በኃጢአትም ሆነ በደዌ ማሠሪያ የታሠርን ሁላችን በዚሁ ዕለት እንድትፈታን የአምላክ እናትን እንለምናት::
በ፫ቱም ማሠሪያዎች የታሠሩ ወገኖቻችንንም እያሰብን "ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሐን-የእሥረኞች ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ" እያልን [መዝ.፸፰፥፲፩] ልንጸልይ ይገባል::
- እመ ብርሃንንም እንደ ሊቃውንቱ :-
"እማእሠረ ጌጋይ ፍትሕኒ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክ:
እምነ ሙቃሔ ጽኑዕ ወእማዕሠር ድሩክ:
ከመ ፈታሕኪዮ ዮም ለማትያስ ላዕክ::" እንበላት::
† 🕊 ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ 🕊 †
ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ፸፪ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::
በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ::
ቅዱስ መጽሐፍ እንደነገረን ጌታችን በነአልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::
ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: [ዮሐ.፲፩]
ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በኋላ ሊያስነሳው ይመጣል::
ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው::
'አዳም ወዴት ነህ' ያለ [ዘፍ.፫] የአዳም ፈጣሪ 'አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት' አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::
ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: [ዮሐ.፲፩፥፩ -ፍጻሜው]
ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በኋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ [ቁጥሩ ከ፸፪ቱ አርድእት ነውና] : ለ፵ ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ፸፬ ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::
† 🕊 ፍልሠት 🕊 †
ይህቺ ዕለት ለቅዱሱ ሐዋርያ በዓለ ፍልሠቱ ስትሆን ይህ የተደረገውም በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ቅዱሱ ያረፈው ቆዽሮስ ውስጥ ነው:: ግን ባልታወቀ ጊዜና ምክንያት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል::
አንድ ቀንም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲቆፍሩ አንድ አንድ ሳጥን አገኙ:: በላዩ ላይ ደግሞ "ይህ የጌታ ወዳጅ የአልዓዛር ሥጋ ነው" የሚል ጽሑፍ አግኝተው ደስ ተሰኝተዋል:: በታላቅ ዝማሬና ፍስሐም ከኢየሩሳሌም ወደ ቁስጥንጥንያ አፍልሠውታል::
የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::
† 🕊 አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም 🕊 †
እኒህ ጻድቅ ሰው ግብጻዊ ሲሆኑ በሰፊው የሚታወቁት በኢትዮዽያና በኢየሩሳሌም ነበር:: ገና በወጣትነት የጀመሩትን የተጋድሎ ሕይወት ገፍተው በበርሃ ሲኖሩ የወቅቱ የግብጽ ሲኖዶስ ከበርሃ ጠርቶ የኢየሩሳሌም ዻዻስ እንዳደረጋቸው ይነገራል::
በቅድስት ሃገርም በንጽሕናና በመንኖ ጥሪት ወንጌልን እየሰበኩ ኑረዋል:: አባ ዮሐንስ የነበሩበት ዘመን ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የወቅቱ የኢትዮዽያ ንጉሥ ደጉ አፄ ዳዊት ነበሩ::
ንጉሡ የግብጽ ክርስቲያኖችን ደም ለመበቀል [በወቅቱ ከሊፋዎች ያሰቃዩዋቸው ነበር) እስከ ላይኛው ግብጽ ወርደዋል:: በሃገር ውስጥ ያሉ ተንባላት አባሪዎቻቸውንም ቀጥተዋል:: በዚህ የተደናገጠው የግብጹ ሡልጣን 'አስታርቁኝ' ብሎ ስለ ለመነ ለእርቅ የተመረጡ አባ ዮሐንስና አባ ሳዊሮስ ዘምሥር ናቸው::
እነዚህ አባቶች በ፲፫፻፺ዎቹ አካባቢ ወደ ኢትዮዽያ ከመጡ በኋላ አልተመለሱም:: ምክንያቱም ደጉ አፄ ዳዊት እጅግ ስለ ወደዷቸው 'አትሔዱም' ብለው ስላስቀሯቸው ነው:: እንዲያውም ለግማደ መስቀሉ መምጣት ትልቁን አስተዋጽኦ ያደረጉት አባ ዮሐንስ ሳይሆኑ አይቀሩም:: ዛሬ የጻድቁ ዕረፍታቸው ነው::
አምላከ ቅዱሳን ስለ ድንግል እናቱ ብሎ ከኃጢአት ሁሉ ማሠሪያ ይፍታን:: የወዳጆቹን በረከትም አያርቅብን::
🕊
[ † ጥቅምት ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. እግዝእትነ ማርያም
፪. ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ
፫. አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
፬. ቅዱስ ኢዩኤል ነቢይ
፭. ቅዱስ ማትያስ ረድእ
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
፪. አበው ጎርጎርዮሳት
፫. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፬. አቡነ አምደ ሥላሴ
፭. አባ አሮን ሶርያዊ
፮. አባ መርትያኖስ ጻድቅ
" ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት... ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም 'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው::" [ዮሐ.፲፩፥፵-፵፬]

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ቅዱስሲኖዶስ
" በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለም !! ... ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን የሰላም ጥሪ እናቀርባለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ
የጥቅምት 2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቋል።
ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።
የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ተሰጥቷል።
ከመግለጫው የተወሰደ ፦
" በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡
ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡ "
(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት)
/ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል /
@tikvahethiopia

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✞
✞ ጥቅምት ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞
† 🕊 ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ 🕊 †
✞ ቅዱስ ሉቃስ :-
- ሐዋርያ ነው
- ወንጌላዊ ነው
- ሰማዕት ነው
- ዓቃቤ ሥራይ [ዶክተር] ነው
- የጥበብ ሰው [ሰዓሊ] ነው
- ዘጋቢ [የሐዋርያትን ዜና ሕይወት የጻፈ] ነው:: ይሕስ እንደምን ነው ቢሉ :-
በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን መነሻ አካባቢ: በተወደደች የጌታ ዓመት ከእሥራኤላውያን ወገኖቹ ቅዱስ ሉቃስ ተወልዷል:: ያደገውም መቄዶንያ አካባቢ ነው:: ጌታችን ተጠምቆ ማስተማር ሲጀምር ከተከተሉት የ፭ ገበያ ሕዝብ መካከል ፻፳ውን ለቤተሰብነት መምረጡ ይታወቃል::
ታዲያ እንዲጠቅም አውቆ ቅዱስ ሉቃስን ከ፸፪ቱ አርድእት ደምሮታል:: ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከተከተለ በኋላ ለ፫ ዓመት ከ፫ ወር: ከዋለበት እየዋለ: ካደረበትም እያደረ የቃሉን ትምሕርት: የእጆቹን ተአምራት በጥሞና ይከታተል ነበር::
ጌታችን ለዓለም ድኅነት ተሰቅሎ: ሙቶ: ከተነሳ በኋላ ስለዚህ ቅዱስ የሚናገር አንድ የወንጌል ክፍል እናገኛለን:: በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬ ላይ ከምናያቸው የኤማሁስ መንገደኞች አንዱ ይህ ቅዱስ እንደ ሆነ አባቶች አስተምረውናል::
በእርግጥ 'ቀለዮዻ' የሚለው ስም በዘመኑ የብዙዎች መጠሪያ ቢሆንም እርሱም ጌታን ከመከተሉ በፊት በዚህ ስም ይጠራ እንደ ነበር ይታመናል:: በወቅቱ ታዲያ ፪ቱ ደቀ መዛሙርት [ሉቃስና ኒቆዲሞስ] ወደ ኤማሁስ ሲሔዱ ጌታ መንገድ ላይ ተገልጦ እያጫወታቸው አብሮ ተጉዟል::
እነርሱም ማንነቱን አላወቁምና ስለ ራሱ ለራሱ እየሰበኩለት ተጉዘዋል:: ከሐዘናቸው ብዛት ማስተዋል ተስኗቸው: ቀቢጸ ተስፋም ወሯቸው ነበርና መድኃኒታችን ክርስቶስ የነቢያትን ትንቢት ተረጐመላቸው::
በዚህ ጊዜም ከነገሩ ማማር: ከምሥጢሩ መሥመር ጋር እየገረማቸው ልቦናቸው ይቃጠል [ይቀልጥባቸው] ነበር:: "አኮኑ ይነድደነ ልበነ" እንዲል:: ወደ ኤማሁስ ሲደርሱ ግን ደጐች ናቸውና "በቤት ካላደርክ: ራት ካልበላህ" ብለው ግድ አሉት::
በማዕድ ሰዓት ግን ቡራኬውን ሰጥቷቸው: ቸር አምላክነቱን ገልጦላቸው ተሰወራቸው:: እነርሱም በሐሴት ከኤማሁት ተመልሰው እየሮጡ ኢየሩሳሌም ደርሰው ትንሳኤውን ሰበኩ::
የመንገዱ ርዝመትም አልታወቃቸውም ነበር:: ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሉቃስ እንደ ሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ: መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::
† 🕊 ቅዱሱ ዶክተር 🕊 †
✞ በትውፊት ትምሕርት እንደ ተማርነው ቅዱስ ሉቃስ ጌታን ከመከተሉ በፊት ሥራው ሐኪምነት [ዶክተር] ነበር:: በዚህም አበው "አቃቤ ሥራይ / ባለ መድኃኒት" ይሉታል:: በተሰጠው ሙያም ብዙዎችን አገልግሏል::
የጌታ ደቀ መዝሙር ከሆነ በኋላ ደግሞ "አቃቤ ሥራይ ዘነፍስ-የነፍስ ሐኪም" ተብሏል:: እንዲያውም አባቶቻችን ሐዋርያትን ያክማቸው ነበር ይባላል:: ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት አብዛኞቹ በሽተኞች ነበርና ነው:: ከደግነታቸው የተነሳም እልፍ አእላፍ ድውያንን በተአምራት ሲፈውሱ እነርሱ ግን በስቃይ ይኖሩ ነበር::
ሕመማቸው ሲጠናባቸው ግን ቅዱሱ ዶክተር ሉቃስ ይራዳቸው ነበር:: ይሕንንም ቅዱስ ዻውሎስ በቆላስይስ መልእክቱ ላይ "የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ: ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል" ሲል ገልጾታል:: [ቆላ.፬፥፲፬]
† 🕊 ዘጋቢው ሐዋርያ 🕊 †
ቅዱስ ሉቃስ እንደ ዛሬው ነገሮች ምቹ ባልነበሩበት ዘመን እጅግ አድካሚ የሆነ ጉዞ አድርጐ የሐዋርያትን ዜና ሕይወት ዘግቦልናል:: ልክ ወንጌሉን ለታኦፊላ [ቴዎፍሎስ] ደቀ መዝሙሩ እንደ ጻፈለት ግብረ ሐዋርያትንም ለእርሱ በትረካ መልክ አቅርቦለታል::
ሲጽፍለትም "ሰማሁ" እያለ ሳይሆን: አብሮ እያለ ያየውንና የተሳተፈበትን ነው:: አተራረኩም በአንደኛና በ፫ኛ መደብ አድርጐ እያቀያየረ ነው:: ማለትም አንዳንዴ "እኛ" እያለ ሌላ ጊዜ ደግሞ "እነርሱ" እያለ ነበር የሚተርክለት::
መጽሐፉም ፳፰ ምዕራፎች ሲኖሩት በጌታ ዕርገት ጀምሮ በኢየሩሳሌምና በአሕዛብ የነበረውን ስብከተ ወንጌል ገልጦ: የቅዱስ ዻውሎስን ጉዞዎች በሰፊው ዳስሶ ይጠናቀቃል::
† 🕊 ወንጌላዊው ሐዋርያ 🕊 †
ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን እንዲጽፉ ከተመረጡ [ከተፈቀደላቸው] ሐዋርያት አንዱ ነው:: በቤተ ክርስቲያንም "ዘላሕም" እየተባለ ይጠራል:: ለዚህም ምክንያቱ :-
፩. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በበረት: በላምና በአህያ መካከል መወለዱን በመጻፉ
፪. ጌታችንን "መግዝአ ላሕም-የሚታረድ ሜልገች [ላም]" ብሎ በመግለጹ እና
፫. ከ፬ቱ እንስሳ [ኪሩቤል] አንዱ [ገጸ ላሕም] ይራዳው: ይጠብቀውም ስለ ነበር ነው::
ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈው ጌታ ባረገ በ፳፪ኛው ዓመት ሲሆን ይኼውም በ፶፮ ዓ/ም አካባቢ ማለት ነው:: ሲጽፍም ብቻውን አልነበረም:: ልክ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን የጻፈው ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር እንደ ሆነው ሁሉ: ቅዱስ ሉቃስም የጻፈው ከብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ጋር ነው:: ምክንያቱም ለረዥም ዓመታት አብረው ለስብከተ ወንጌል ተጉዘዋልና::
ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን ሲጽፍ በነ ዘካርያስ ቤተሰብ ጀምሮ: ብሥራተ ገብርኤልን: ክብረ ድንግል ማርያምን: የጌታን ልደት: እድገት: መጠመቅ: ማስተማር: መሰቀል: መሞት: መነሳትና ማረግ በቅደም ተከተል ይተርክልናል::
† 🕊 ጥበበኛው [ሰዓሊው] ሐዋርያ 🕊 †
ቅዱስ ሉቃስን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች ሌላኛው ደግሞ ጐበዝ ሰዓሊ የነበረ መሆኑ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም የመጀመሪያውን የእመቤታችንን ስዕል [ምስለ ፍቁር ወልዳን] የሳለው እሱ ነው::
አንድ ቀን የአምላክ እናት ባለችበት ከጌታ አስፈቅዶ የሳላት ስዕለ አድኅኖ ሥጋን የለበሰች: ከፊቷ ወዝ የሚወጣ: የምታለቅስ: ስትወጋ የምትደማና ድውያንን የምትፈውስ ሆና ተገኝታለች:: ይህች ስዕል ዛሬ ሃገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ አለች ይባላል::
† 🕊 ሰማዕቱ ሐዋርያ 🕊 †
ቅዱስ ሉቃስ እንዲህ ባለ ሕይወት ሲመላለስ በትጋት [ያለ ዕረፍት] ወንጌልን እየሰበከ ነበር:: በ፷፮ እና በ፷፯ ዓ/ም ብርሃናተ ዓለም ዼጥሮስ ወዻውሎስ በኔሮን ቄሣር እጅ ሲገደሉ የሮም ግዛት ክርስቲያኖች ኃላፊነት በእርሱ ላይ ነበረ::
ከወንጌሉና ግብረ ሐዋርያቱ ባለፈ በመልእክታት: አንድም እየዞረ ክርስቲያኖችን አጸና: አሕዛብንም አሳመነ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ዝናውን የሰማው ኔሮን ሊገድለው ፈለገ:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሉቃስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሲላስ የሚባለውን ሽማግሌ መርጦ መጽሐፎቹን ሁሉ አስረከበው::
በድፍረትም ወደ ኔሮን ቄሣር ቀርቦ ተናገረው:: ንጉሡም "ክርስቶስን አምልኩ የምትል ቀኝ እጅህ መቆረጥ አለባት" ብሎ እጁን ከትክሻው በሰይፍ ለይቶ መሬት ላይ ጣለው:: ሁሉ ሰው ሲደነግጥ ቅዱሱ ተጐንብሶ የወደቀች እጁን አነሳትና እንደ ነበረችው አደረጋት::
በዚያ የነበሩ አሕዛብም "ግሩም" አሉ:: መልሶ ግን "አሁን እጄ ሥራዋን ስለ ጨረሰች አልፈልጋትም" ብሎ እንደ ገና ለይቶ ጣላት::
"ከመ ያርኢ ኃይለ ቅድመ ኔሮን ወተዓይኑ:
አስተላጸቃ ወሌለያ ለምትርት የማኑ:
እስመ ላዕሌሁ ተሰውጠ ለክርስቶስ ስልጣኑ::" እንዲል::
በዚህ ጊዜም ይህንን ድንቅ ያዩ ፬፻፸፯ ያህል አሕዛብ በክርስቶስ አምነው አብረውት ተሰይፈዋል:: የስብከት ዘመኑም ከ፴፮ ዓመታት በላይ ነው::