Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን። †
[ ✞ መስከረም ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞ ]
🕊 † ቅዱስጐርጐርዮስ ዘአርማንያ † 🕊
✞ ይህ ቅዱስ አባት ከሰማዕታት: ከጻድቃን: ከሊቃውንትና ከዻዻሳት ዝርዝር ውስጥ ይገኛል:: በቤተ ክርስቲያንም ዓበይት ተጽፎ ከሚባሉ አበው አንዱ ነው:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሮማዊ ሲሆን ከክርስቲያን ወላጆቹ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት [በ፫ ኛው መቶ ክ/ዘመን] ነው::
አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ የታላቁዋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት :-
፩. ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት
፪. ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት
፫. የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::
ቅዱሱ ፫ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው በጣም ገፍቶ እስከበመልኩዋ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::
ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስበጸሎት ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::
በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና ለጥቂት ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::
በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግንእኔ አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::
ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::
አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
ወዲያው ደግሞ የቅዱስ ጐርጐርዮስ ማንነቱ በመታወቁ ይዘው እስኪያልቅ ገረፉት:: በእሳትም አቃጠሉት:: በብዙሽማግሌ ስቃይም አሰቃዩት::
በመጨረሻ ግን ከነ ሕይወቱ እንዲቀበር ተወሰነበት:: ወደ መጸዳጃ ቤት ወስደውም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት:: ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ መተንፈሻ ቀዳዳን ሠራለት:: አንዲት ክርስቲያንም በዚያች ቀዳዳ ቂጣ እየጣለችለት ለ፲፭ ዓመታት ተቀብሮ ኖረ::
አካሉና አፈሩ ተጣበቀ:: እርሱ ግን ፈጣሪውን እያመሰገነ ቆየ:: ከነገርየንጉሡ ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት [እሪያነት] ቀየራቸው::
የንጉሡ እንስሳ /አውሬ መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን-ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም በዚያች ሽማግሌ መሪነት ቆፍረው አወጡት::
አካሉንም እግዚአብሔር መለሰለት:: ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ፲፭ ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው:: ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::
ወደ ሰውነትም መልሶ መላ አርማንያን ወደ ክርስትና መለሰ:: የንጉሡን እግር ግን የአውሬ አድርጐት ቀርቷል:: በመጨረሻም ቅዱስ ጐርጐርዮስ የአርማንያ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሹሞ ብዙ መጻሕፍትን ደረሰ:: ከ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንትም አንዱ ሆኖ ተቆጠረ:: ዕረፍቱ ታሕሳስ ፲፭ ቀን ሲሆን ዛሬ ከተቀበረበት የወጣበት ነው::
🕊 † ቅዱስ ቂርቆስ ገዳማዊ † 🕊
ቅዱሱ የ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቅ ሲሆን በዓለም ከመናፍቃን: በገዳም ደግሞ ከአጋንንት ብዙ መከራን ተቀብሏል:: በወቅቱ መለካውያን [የአሁኖቹ ካቶሊኮችና ምስራቅ ኦርቶዶክሶች) አባቶችን ያሳድዱ ነበር:: ልክ ፱ኙ ቅዱሳን በዚህ ምክንያት ወደ ኢትዮዽያ እንደመጡት ቅዱስ ቂርቆስም ወደ ግብጽ በርሃ ከእርሷ ተሰደደ::
በበርሃው ውሃም ሆነ ዛፍ ባለመኖሩ በረሃብና በጥም በመሰቃየቱ ወደ ፈጣሪ ለመነ:: ጌታም አንዲት አጋዘን ልኮለት ወተትን አልቦ ጠጣ:: እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም ምግቡ ይሔው የአጋዘን ወተት ነበር:: በዚህ ምክንያት ይሔው ዛሬም ድረስ " ቅዱስ ቂርቆስ ገዳማዊ ዘሲሳዩ ሐሊበ ቶራ" እየተባለ ይጠራል::
በበርሃው ውስጥ በኖረባቸው ዘመናትም አንድም ሰው አይቶ ካለማወቁ ስትሆን ባለፈ አጋንንት በገሃድ እየመጡ ያሰቃዩት ነበር:: ቅዱሱ ግን በትእግስት ኑሮ በዚህች ቀን ሲያርፍ ብዙ ተአምራት በበዓቱ ውስጥ ተገልጠዋል:: ይህንን ያዩት ደግሞ ከዻዻሱ ዘንድ ተልከው የቀበሩት አበው ናቸው::
🕊 † ቅድስት ሮማነ ወርቅ † 🕊
ይህቺ ቅድስት እናት ደግሞ ኢትዮዽያዊት ናት:: የነገሥታቱ ልጅ አባቷ አፄ ናዖድ: እናቷ ደግሞ እሌኒ /ወለተ ማርያም ይባላሉ:: ወንድሟ ደግሞ አፄ ልብነ ድንግል ይባላሉ::
በቤተ መንግስት ውስጥ ብታድግም መንፈሳዊነቷ የገዳም ያህል ነበር:: ከተባረከ ትዳሯም ቅዱስ ላዕከ ማርያምን አፍርታለች:: አብያተ ክርስቲያናትን ከማነጽ ባለፈ የነዳያን እናትም ነበረች:: በክርስትናዋ ፈጣሪዋን ደስ አሰኝታ በዚህ ቀን ዐርፋለች::
✞ አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን: ክብሩን አይንሳን:: ከወዳጆቹ በረከትም እንደ ቸርነቱ ያድለን::
🕊
[ ✞ መስከረም ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማርያ
፪. ቅዱስ ቂርቆስ ገዳማዊ
፫. ቅድስት ሮማነ ወርቅ
፬. ቅዱስ ዕጸ መስቀል
" ጻድቃን ጮሁ: እግዚአብሔርም ሰማቸው:: ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው:: እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው:: መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል:: የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው:: እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል:: እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል:: " [መዝ.፴፫፥፲፯]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#VisitAmhara
ግሸን ደብረ ከርቤ !
ግሸን ደብረ ከርቤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአንጋፋነታቸው ከሚታወቁት ቅዱሳን ሥፍራዎች አንዷ ናት፡፡
የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ሌሎች የገዳሟን ታሪክ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው ወደ ግሸን ይጓዛሉ፡፡
በተለይ ከመስቀል በዓል እስከ መስከረም 21፣ ጥር 21 እንዲሁም መጋቢት 10 ወደ ግሸን የሚጓዘው ሕዝብ በመቶ ሽዎች ይቆጠራል፡፡
በረከት ለማግኘት፣ ታሪክ ለማወቅ እና ለመፈወስ ግሸን ለእምነቱ ተከታዮች ቀዳሚ መዳረሻ ናት፡፡
በኢትዮጵያ የሀይማኖት ቱሪዝም ታሪክ ብዙ እንግዶችን በማስተናገድ ግሸን ከቀዳሚዎች መካከል ትገኛለች፡፡
ነገ መስከረም 21 ታላቁ የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ክብረ በዓል ይከበራል፡፡
እንኳን አደረሳችሁ !
(Vist Amhara)
#TourismAndPeace #GishenDebreKerbe #SouthWollo #ReligiousFestival #Ethiopia #LandOfOrigins
@tikvahethiopia

[ † እንኳን ለአባ አትናቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
† 🕊 አባ አትናቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት 🕊 †
† 'ዻዻስ' ማለት 'አባት - መሪ - እረኛ' ማለት ነው:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ ፫ [3] ናቸው:: እነሱም ዲቁና: ቅስና: ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ ፱ [9] ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ዽዽስና ነው::
ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር 'ሸክም: ዕዳ' ሲሆን በሰማይ ግን 'ክብር' ነው:: ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን አይመኝም::
ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ - ማንም ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" [፩ጢሞ.፫፥፩] (3:1) ማለቱን ይዞ 'ሹሙኝ' ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ ነው::
አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኳ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ - መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" [ዮሐ.፲] (10) ስለዚህም ክህነት ዽዽስና ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::
አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች ፬ [4] ቱ የበላይ ናቸው::
እነዚህም የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::
እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ ፬፻፵፫ [443] ፬፻፶፩ [451] ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው [የግብጹ] እና የአንጾኪያው [የሶርያው] ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::
የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች:: በተለይ በግብጽ የነበሩ አበው ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ የከፈሉ ናቸውና በልዩ ታከብራቸዋለች::
ዛሬ ያሉትን አቡነ ታውድሮስን ጨምሮ በመንበሩ ላይ የተቀመጡ ፻፲፰ [118] ሊቃነ ዻዻሳት መካከል አብዛኞቹ ደጐች ነበሩ:: ቢያንስ ገዳማዊ ሕይወትን የቀመሱ: ለመንጋው የሚራሩና በየጊዜው እሥራትና ስደትን የተቀበሉ ናቸው::
ከእነዚህም አንዱ አባ አትናቴዎስ ካልዕ ይባላል:: ይህም አባት በመንበረ ማርቆስ ፳፰ [28] ኛው ፓትርያርክ ነው:: የነበረበት ፷ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ቤተ ክርስቲያን ለ፪ [2] የተከፈለችበት: ለተዋሕዶ አባቶች ስደት የታወጀበት ስለ ነበር ወቅቱ ፈታኝ ነበር::
አባ አትናቴዎስ በዚያው በምድረ ግብጽ ተወልዶ: አድጐ: መጻሕፍትን ተምሮ: ምናኔን መርጦ ሲኖር: መጋቤ ቤተ ክርስቲያን አድርገው መርጠውት አንገቱን ደፍቶ ፈጣሪውን ያገለግል ነበር:: በጊዜው ግብጽ ፓትርያርክ ዐርፎባት እውነተኛውን እረኛ ትፈልግ ነበርና የህዝቡም: የሊቃውንቱም ዐይን ወደ አባ አትናቴዎስ ተመለከተ::
ሁሉም በአንድነት ተመካክረውም "አንተ ለዚህ ሹመት ትገባለህ" አሉት:: እርሱ ግን መለሰ "የለም እኔ እንዲህ ላለ ኃላፊነት አልመጥንምና ሌላ ፈልጉ::" ይህ ነው የክርስትና ሥርዓቱ:: የክርስቶስን መንጋ 'እኔ ችየ እጠብቀዋለሁ' ማለት ታላቅ ድፍረት ነውና::
ነገር ግን "ወአኀዝዎ በኩርህ" ይላል - በግድ ሾሙት:: እርሱም የግል ትሩፋቱን ሳያቋርጥ መንጋውን ተረከበ:: በወቅቱ እንደ አሸን ከፈሉ መናፍቃን ሕዝቡን ይጠብቅ ዘንድ ስለ ሕዝቡ ባፍም: በመጣፍም ደከመ:: በፈጣሪ እርዳታም ለ፯ [7] ዓመታት ሕዝቡን ከተኩላ ጠብቆ አካሉ ደከመ:: በዚህች ቀንም ይህችን የመከራ ዓለም ተሰናብቶ ዐረፈ::
† አምላከ አበው አባቶቻችንን ለመንጋው የሚራሩ ያድርግልን:: ከወዳጆቹ ጸጋ በረከትም ይክፈለን::
🕊
[ † መስከረም ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አባ አትናቴዎስ ካልዕ
፪. ቅድስት መሊዳማ ድንግል
፫. ቅድስት አቴና ድንግል
፬. ቅዱስ ስምዖን ዘኢየሩሳሌም
፭. ቅዱስ አብርሃም መነኮስ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፪. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፫. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፬. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
፮. ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት
† " ኤዺስ ቆዾስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና:: የማይኮራ: የማይቆጣ: የማይሰክር: የማይጨቃጨቅ: ነውረኛ ረብ የማይወድ: ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ: በጐ የሆነውን ነገር የሚወድ: ጠንቃቃ: ጻድቅ: ቅዱስ: ራሱን የሚገዛ ይሁን:: " † [ቲቶ. ፩፥፯]

†
🌼 [ እንኳን አደረሳችሁ ! ] 🌼
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
❝ አንብር መስቀልዬ በዲበ መስቀል ❞
[ ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ]
🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ ከደሴ ከተማ ፹፪ ኪ/ሜ ርቃ ከፍ ብሎ በሚታይ መስቀለኛ ተራራ ላይ ትገኛለች። በተለይ አቡነ ሚካኤል ጳጳስ ዘጎንደር መንፈሳዊ መናኝ በመባል የሚታወቁት ደገኛ አባት ባሠሩት ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሆነው የተራራውን ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ሲመለከቱ አንድ ጥሩ አናጢ ከጥሩ እንጨት ባማረ ጌጥ ጠርቦ የሠራውን ግሩም የእጅ መስቀል ይመስላል።
በአቅራቢያዋም ከሚገኙ በርካታ ታሪካውያንና ጥንታውያን መካናት መካከልም ፦ ጥንታዊው የደብረ ሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም ፣ የድጓ ምስክር የነበረው ደብረ እግዚአብሔር ፣ የቅኔ ትምህርት ምንጭ የሆነው ዋድላ/ደላንታ ፣ የ፲፱ ኛው ክፍለ ዘመን የሃይማኖት ውሳኔ የተደረገበት የቦሩ ሜዳ ሥላሴ ፣ የውጫሌ ውል የተፈረመበት የውጫሌ ከተማ ፣ የመቅደላ አምባ ፣ የበሽሎ ወንዝ ሸለቆና ሌሎችም ናቸው።
ግሸን ደብረ ከርቤ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት በልዩ ልዩ ታሪካዊና ምሥጢራዊ ምክንያቶች ደበረ ነገሥት ፣ ደብረ ነጎድጓድ ፣ ደብረ እግዚአብሔር በሚባሉ ስሞች ትጠራ ነበር፡፡ ግሸን ደብረ ከርቤ መጀመሪያ የተመሰረተችው በዘመነ አክሱም በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡
ዐፄ ካሌብ በየመን በሩ ክርስቲያኖች እየደረሰባቸው ከነበረው መከራ ለመታደግ ወደ ናግራን ዘምተው ድል አድርገው መንግሥት አጽንተው ሲመለሱ በዚያ ይኖሩ የነበሩ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የሚባሉት መነኰስ አብረው ተመልሰዋል።
አባ ፈቃደ ክርስቶስም ከናግራን ሲመለሱ ሁለት ጽላቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የበሽሎ ወንዝን ተሻግረው ወደ ግሸን ተራራ ጫፍ ለመውጣት የአምባውን ዙሪያ ሲመለከቱ በገደሉ ላይ ንብ ሰፎ ማሩ ሲንጠባጠብ አይተው የአምላክን ስጦታ ለማድነቅ በጥንታውያን ግእዝና ዓረብኛ ቋንቋዎች ቦታውን "አምባ " "አሰል " [ አምባሰል ] ብለው ጠሩት። ትርጉሙም "የማር አምባ " ማለት ነው እስከ አሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል።
አባ ፈቃደ ክርስቶስም ይዘዋቸው የመጡትን ሁለት ጽላቶች ወደ አምባው በማስገባት ሁለት ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ደብሩን መሥርተዋል። ይኽንኑ ታሪክ በመከተልም ይመስላል በጉዲት ጦርነት የስደት ዘመን የአክሱሙ ንጉሥ ድል ነዓድ በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ከአምባሰል ባሻገር ከሐይቅ ባሕር አጠገብ ባለው ተራራ ላይ ደብረ እግዚአብሔርን መሥርቶ ኖሯል።
ከዚህም በኋላ መንግሥት ከደብረ እግዚአብሔር በመራ ተክለሃይማኖት አማካኝነት ወደ ላስታ ሲሻገር የደብረ ከርቤ ክብር በላስታ ዘመንም አልተቋረጠም፡፡ በቅዱስ ላልይበላል ዘመን እንደተፈለፈሉ የሚነገርላቸው ጅምር ዋሻዎች አሁንም በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም ይገኛሉ። በዚህ ዘመንም ደብረ ከርቤ የነገሥታት መናኸሪያ የሊቃውንት መገኛ የቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት መፈጸሚያ ቅድስት ቦታ ነበረች።
በመጨረሻም በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መቀመጫ ሆናለች። ፲፬፻፵፮ ዓ/ም መስከረም ፳፩ ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳትን አምጥተው በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አስቀመጡ፡፡
የግማደ መስቀል በረከት የእመቤታችን ምልጃና ጸሎት ከሁላችን ጋር ይሁን !
አምላካችን በኃይለ መስቀሉ ሀገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅልን።
† † †
🌼 🍒 🌼

🕊 [ እመቤቴ ] 🕊
💖
❝ የልዑል እግዚአብሔር እናቱ ድንግል ማርያም ሆይ ከኪሩቤል ትበልጫለሽ፡፡ ከሱራፌልም ትበልጫለሽ፡፡ ለሚያበራው የምስጋና ዙፋን አንቺ ነሽና፡፡ በዘመን የከበረ እግዚአብሔር በላዩ የተቀመጠበት ፣ የሚያንጸባርቅ የእሳት ሰረገላም አንቺ ነሽ፡፡ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ዳንኤል ያየሽም አንቺ ነሽ፡፡
ድንግል ሆይ አንቺ ደመና ነሽ፡፡ ልጅሽም የይቅርታ ዝናም ነው፡፡ አንቺ መዝገብ ነሽ ልጅሽም የሀብት መገኛ ምንጭ ነው፡፡ አንቺ የወይን ሐረግ ነሽ ፣ ልጅሽም ፍሬ ነው፡፡ የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሙሽራ ሆይ በልመና እጠራሻለሁ ፤ በፊትሽም እማጸናለሁ፡፡ ከሚያስለቅስ የኀዘን መቅበዝበዝም አረጋጊኝ፡፡ የማይጎድል ሙሉ ደስታንም ስጪኝ፡፡ በዘመኔ ሁሉም ጤነኛ አድርጊኝ፡፡ ለዘላለሙ አሜን። ❞
[ እንዚራ ስብሐት ]