Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ እና ለቅዱስ ሚልክያስ ነቢይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† መሐሪ እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ በዛ: ሰውነታችሁ ከፋ ሳይል በአባታዊ ርሕራሔው ጠብቆ ይሔው ወርኀ ነሐሴን በሰላም አስፈጸመን:: አይመስለንም እንጂ በእነዚህ ሰላሳ ቀናት ሚሊየኖች አንቀላፍተዋል: ሚሊየኖች በደዌ ዳኝነት ተይዘዋል: በርካቶቹም ከሃይማኖታቸው ወጥተዋል::
እኛ ይህ ሁሉ ያልደረሰብን በጐ ስለሆንን አይደለም:: ይልቁኑ ቸርነቱ በእኛ ላይ ስለበዛ ብቻ ነው እንጂ:: አሁንም በሰላም ከአዲሱ ዘመን እንዲያደርሰን ልንማጸነው ይገባል::
በዚህች ዕለት ደግሞ እነዚህን ቅዱሳን እናከብራለን::
[ 🕊 † ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ † 🕊 ]
† ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ አካባቢ ሲሆን የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ትንሽ ወንድም ነው:: አባቱም ዮና ይባላል:: ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ዓሣ ማጥመድን ከትልቅ ወንድሙ ተምሯል:: እድሜው ከፍ ባለ ጊዜ ኦሪትን ተምሮ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኗል::
ከእርሱም እያገለገለ ለስድስት ወራት ተምሯል:: በወቅቱ ከወንጌላዊው [ወልደ ዘብዴዎስ] ዮሐንስ ጋር ቅርብ ባልንጀራም ነበር:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ያን ድንቅ ምሥጢረ ሥላሴ ከተመለከቱትም አንዱ ነው::
ጌታ ከጾም [ከገዳመ ቆረንቶስ] በተመለሰ ጊዜ እንድርያስ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ተከትሎታል:: መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ "ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያዐትት ኃጢአተ ዓለም - የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ::" ማለቱን ሰምቶ ቅዱስ እንድርያስ ጌታን ተከተለ::
በዚህም የመጀመሪያው የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመባል በቃ:: [ዮሐ.፩፥፵፯] (1:47) ሊቁ ማር ገላውዴዎስም እመቤታችንን ሲያመሰግናት
"ለሐዋርያ እንድርያስ ቀዳማዊ ማርያም ሃይማኖቱ [ለመጀመሪያው ሐዋርያ ለእንድርያስ ሃይማኖቱ ማርያም አንቺ ነሽ::]" ብሏል::
[መልክዐ ስዕል]
ቅዱሱ ሐዋርያ ስሉጥ [ፈጣን] አገልጋይ እንደ ነበርም ወንጌል ይነግረናል:: [ዮሐ.፮፥፱ (6:9), ፲፪፥፳፪ (12:22) ለሦስት ዓመታት ከሦስት ወር ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሎ: ምን ሃገረ ስብከቱ ልዳ ብትሆን ብዙ አሕጉረ ዓለምን ሰብኳል::
ይህች ቀን ሐዋርያው ከጌታ ጋር በመርከብ ውስጥ የተነጋገረባትና ቅዱስ ማትያስን ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ያዳነባት ናት::
ቅዱስ እንድርያስ ሰላሳ ቀናት የሚፈጅ የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ ከአርድእቱ ጋር ወደ ወደብ ቢሔድም መርከበኞች ሁሉ አናሳፍርም በማለታቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወጣት መርከበኛ መስሎ ሐዋርያውንና አርድእቱን የሰላሳውን ቀን መንገድ በሰዓታት ልዩነት እንዲጨርሱ አድርጓል::
ቅዱስ እንድርያስም ፍጡር [እንዲሁ ሰው] መስሎት ለጌታችን ስለ ጌታችን ሰብኮለታል: መርቆታልም:: መርከበኛው ጌታችን መሆኑን ሲያውቅም ደንግጦ አልቅሷል::
"ሶበ አእመረ ኪያሁ ወጠየቀ አምሳሎ:
ዘተናገርኩ በድፍረት ምስሌከ ኩሎ:
ሥረይ ሊተ ጌጋይየ ወኅድግ ይቤሎ::" እንዲል "ማረኝ?" ብሎታል:: ጌታችንም "አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ::" ብሎታል:: ቅዱሱ ሐዋርያ ለወንጌል አገልግሎት ተግቶ ያረፈው ታኅሣሥ 4 ቀን ነው::
[ 🕊 † ቅዱስ ሚልክያስ ነቢይ † 🕊 ]
† ሚልክያስ ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ሲሆን "የመጨረሻው ነቢይ" እየተባለ ይጠራል:: ለዚህ ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው::
፩ኛ. ከእርሱ በኋላ የተጻፈ ጥሬ የትንቢት መጽሐፍ የለም::
፪ኛ.እርሱ ካረፈ በኋላ ያለው ዘመን "ዘመነ ካህናት" በመሆኑ ምንም ነቢያት በየጊዜው ባይጠፉ ጐልተው የተነገረላቸው ጥቂቶቹ ናቸው::
ቅዱሱ የተወለደው ቅ/ል/ክርስቶስ ስድስት መቶ ዓመት አካባቢ ሲሆን ከሚጠት [ከባቢሎን ምርኮ መልስ] ሕዝቡን ገስጿል:: ሕዝቡ ከሰባ ዓመት መከራ እንኳን ተመልሶ ኃጢአትን መሥራትን ቸል አላለም ነበር::
በተለይ የልጅነት ሚስታቸውን የሚያታልሉትን ገስጿል:: [ሚል.፪፥፲፬] (2:14) ስለ አሥራትና በኩራትም ተናግሯል:: [ሚል.፫፥፰] (3:8) እመቤታችን ድንግል ማርያምንም በንጽሕት አዳራሽ መስሎ ተናግሯል::
"ጽርሕ ንጽሕት ዘሚልክያስ" እንዳሉ አባ ሕርያቆስ:: [ቅዳሴ ማርያም]
ነቢዩ ቅዱስ ሚልክያስ ፈጣሪውን አገልግሎ: ሕዝቡን መክሮ ዐርፏል:: ሚልክያስ ማለት "መልአክ: አንድም የተላከ" ማለት ነው:: ነገዱ ከነገደ ይሳኮር ነው::
† አምላከ ቅዱሳን አሥራ ሁለቱን ወራት እንደ ባረከልን አሥራ ሦስተኛዋንም ለንስሐ ቀድሶ ይስጠን:: ከቅዱሳኑም በረከትን ያካፍለን::
🕊
[ † ነሐሴ ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ሚልክያስ ነቢይ
፫. አባ ሙሴ ዘሃገረ ፈርማ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ [ሐዋርያ]
፪. አባ ሣሉሲ ክቡር
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፭. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
† "ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ:: ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል:: 'መፋታትን እጠላለሁ' ይላል የእሥራኤል አምላክ: የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር::" † [ሚል. ፪፥፲፭]
† " ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃቹሃል:: እናንተም 'የሰረቅንህ በምንድን ነው?' ብላቹሃል:: በአሥራትና በበኩራት ነው:: እናንተ: ይህ ሕዝብ ሁሉ እኔን ሰርቃቹሃልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ::" † [ሚል. ፫፥፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

[ † እንኳን ለተባረከ ወር ጳጉሜን እና ለቅዱሳኑ ዮሐንስ መጥምቅ : ዑቲኮስ ሐዋርያና ቀሲስ አባ ብሶይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

[ 🕊 † ወርኀ ጳጉሜን † 🕊 ]
† እግዚአብሔር አዝማናትን የፈጠራቸው ለሰው ልጆች ጥቅም መሆኑ ይታወቃል:: እርሱ ባወቀ: በረቂቅ ሥልጣኑ ዓለምን ፈጥሮ: ጊዜያትን እንዲከፍሉ ብርሃናትን [ፀሐይ: ጨረቃ: ከዋክብትን] ፈጥሮልናል::
ጊዜያትንም በደቂቃ: በሰዓት: በቀን: በሳምንት: በወር: በዓመታት: በኢዮቤልዩ: በክፍላተ ዘመናት እንድንቆጥር ያስማረንም እርሱ ነው:: የሰከንድ ፭ መቶ ፵ ሺህ [540,000] ክፋይ ከሆነችው 'ሳድሲት' እስከ ትልቁ ቀመር ፭፻፴፪ [532 ዓመት] ድረስ እርሱ ለወደዳቸው እንዲያስተውሉት ገልጧል::
በየዘመኑም በቅዱስ ድሜጥሮስ: በቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ : በቅዱስ አቡሻኽር እና በሌሎቹም አድሮ መልካሙን አቆጣጠር አስተምሯል:: ሃገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ የአሥራ ሦስት ወራት የፀሐይ ጸጋ [thirteen months sun shine] ያላት: አራቱ ወቅቶች የተስማሙላት ናት::
† ሌላው ዓለም ወሮችን 31,30,29 [28] እያደረገ
ሲጠቀም እኛ ግን እንደ ኖኅ [ዘፍ.፰፥፩-፭] (8:1-15) አቆጣጠር ወሮችን በሠላሳ ቀናት ወስነን: ጳጉሜንን ለብቻዋ እናስቀምጣለን:: ጳጉሜን 'ኤጳጉሚኖስ' ከሚል የግሪክ [ጽርዕ] ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም 'ትርፍ: ጭማሪ' እንደ ማለት ነው::
የወርኀ ዻጉሜን አምስቱ [ስድስቱ] ቀናትም ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገሪያ እንደ መሆናቸው ብዙ ምሳሌያት [ምሥጢራት] አሏቸው:: ዋናው ግን በዚህ ጊዜ ዳግም ምጽዓት ይታሠባል:: ጊዜውንም በጾምና በጸሎት ሊያሳልፉት ይገባል:: ግን በፈቃድ ነው እንጂ የግዴታ አይደለም::
[ 🕊 † ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ † 🕊 ]
¤ የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
¤ በማኅጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
¤ በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
¤ እሥራኤልን ለንስሐ ያጠመቀ
¤ የጌታችንን መንገድ የጠረገ
¤ ጌታውን ያጠመቀና
¤ ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
† ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን :-
ነቢይ:
ሐዋርያ:
ሰማዕት:
ጻድቅ:
ገዳማዊ:
መጥምቀ መለኮት:
ጸያሔ ፍኖት:
ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::
† ቅዱሱ በዚህች ዕለት ወደ እሥር ቤት ገብቷል::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ንጉሡ ሔሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሔሮድያዳን በማግባቱና በመሰል ክፋቶቹ ቅዱስ ዮሐንስ ይገስጸው ነበር:: ቅዱስ ዮሐንስ "መምሕር ወመገስጽ: ዘኢያደሉ ለገጽ - ፊት አይቶ የማያዳላ" ነውና ገሰጸው::
ሔሮድስ ቅዱሱን ይፈራው: ያከብረውም ነበር:: በኋላ ግን ፈቃደ ሥጋው ስላየለበት: በተለይ ደግሞ ከሰባት ቀናት በኋላ ልደቱን ሲያከብር እንዳይረብሸው በመስጋት በዚህች ቀን በወታደሮቹ አስይዞ እሥር ቤት ውስጥ
ጥሎታል:: ለሰባት ቀናት በጨለማ ውስጥ አሥሮ መስከረም 2 ቀን አንገቱን እንዴት እንዳስቆረጠው ዕለቱን ጠብቀን እንመለከታለንና የዚያ ሰው ይበለን::
[ 🕊 † ቅዱስ ዑቲኮስ ሐዋርያ † 🕊 ]
† ቅዱሱ ሐዋርያ ጭራሽ ከነስማቸው እንኳ እየተዘነጉ ከሔዱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን ቁጥሩም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ነው:: በወጣትነት ዘመኑ የጌታችን ደቀ መዝሙር መሆንን መርጦ ለሦስት ዓመት ከሦስት ወር ምሥጢረ ወንጌልን ጠንቅቆ ተምሯል::
መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜም እንደ መጠኑ ተቀብሎ ለአገልግሎት ወጥቷል:: በመጀመሪያ የወንጌላዊው ዮሐንስ ተከታይ ሁኖ ብዙ ምሥጢራትን ተካፍሏል:: ቀጥሎም ቅዱስ ጳውሎስን ተከትሎ ብዙ አሕጉራትን በስብከተ ወንጌል አዳርሷል::
በመጨረሻም በእስያ አካባቢ ለብቻው ተጉዞ: ብዙ ነፍሳትን ማርኮ: ጣዖታትን አጥፍቷል:: ስለዚህ ፈንታም በእሳት: በስለትና በግርፋት ብዙ መከራዎችን አሳልፏል:: በዚህች ቀንም በበጐው እርግና [ሽምግልና] ዐርፏል::
[ 🕊 † ቅዱስ ብሶይ ቀሲስ † 🕊 ]
† ከ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ካህናት አንዱ የነበረው አባ ብሶይ ለአገልግሎት ወጥቶ ሲመለስ የቤተሰቦቹ ቤት ሰው አልነበረበትም:: "የት ሔዱ?" ብሎ ቢጠይቅ "ወንድምህ አባ ሖር እና እናትህ ቅድስት ይድራ ወደ እስክንድርያ ሔደዋል:: በዚያም ስለ ክርስቶስ ፍቅር ተሰውተዋል::" አሉት::
በማግስቱ የኔ ብጤዎችን ጠርቶ ሃብቱን: ንብረቱን: ቤቱን አካፈላቸው:: ለራሱ ግን አንዲት በትር እና ሦስት የዳቦ ቁራሾች ይዞ ጉዞ ተነሳ:: ወደ እስክንድርያ እንደ ደረሰ አፈላልጐ የቤተሰቦቹን መቃብር አገኘ:: ከፊታቸው ወድቆም የናፍቆት ለቅሶን አለቀሰ::
ወዲያውም እንዲህ አላቸው:- "ፈጥኜ ወደ እናንተ ስለምመጣ ጠብቁኝ:: ደግሞም ጸልዩልኝ::" ከዚያ ተነስቶ በመኮንኑ ፊት ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት መሰከረ:: በዚህ ምክንያት ብዙ ተሰቃይቶ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆኗል:: ከወገኖቹም ጋር ተቀብሯል::
† አምላከ ቅዱሳን ተረፈ ዘመኑን ባርኮ ለአዲሱ ዘመን በቸር ያድርሰን:: ከወዳጆቹም ጸጋ በረከትን ይክፈለን::
🕊
[ † ጳጉሜን ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ [የታሠረበት]
፪. ቅዱስ ዑቲኮስ ሐዋርያ [ከሰባ ሁለቱ አርድእት]
፫. ቅዱስ ብሶይ ቀሲስ [ሰማዕት]
፬. አባ ጳኩሚስ /ባኹም [የሦስት ሺ ቅዱሳን አባት]
፭. አባ ሰራብዮን /ሰራፕዮን [የአሥር ሺ ቅዱሳን አባት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
- የለም
[ † " ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ::" † [ማቴ. ፲፩፥፯-፲፭]

Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #የተባረከ_የጳጒሜን_ወር_ባተ።
❤ #ጳጒሜን ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን #ለወንጌላዊው_ለቅዱስ_ዮሐንስ ረድእ #ለሐዋርያውና_ለሰማዕቱ_ለከበረ_ቅዱስ_ዑቲኮስ ለዕረፍት በዓል፣ #ለአባ_ሖር_ወንድም ለሰማዕቱ #ለቀሲስ_ቅዱስ_አባ_ብሶይ_ለዕረፍት በዓል አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ #ከአባ_ጳኩሚስና_ከአባ_ሰራብዮን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #በዚች_ቀን_መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ ሄሮድስን የወንድምህን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ማግባት የለብህም ብሎ ይገስጸው ስለነበር በሳምንቱ በልደቱ ቀን መስከረም 2 እስኪገለው በዛሬው ዕለት ወደ እስር ቤት ያስገባበት ነው።
✝ ✝ ✝
❤ #የሐዋርያው_የቅዱስ_ዮሐንስ_ረድእ_ቅዱስ_ዑቲኮስ፦ ይህም ቅዱስ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስን ሲያገለግለውና ሲታዘዘው ኖረ። ከዚያም ከሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ጋራ ሔደ እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲሰብክ አዘዘው በአረማውያንና በዮናናውያንም መካከል ሰበከ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ወደማወቅ ብዙዎችን መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው።
❤ የጣዖታት ቤቶችን አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። ከሀድያንም ብዙ መከራ ደረሰበት መታሠርና ብዙ ቀኖች ግርፋቶችን በመቀበል የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ እሥር ቤት ከምግብ ጋር መጥቶ ይመግበዋል።
❤ ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጣሉት እሳቱም ከቶ አልነካውም ሁለተኛም ለአንበሶች ጣሉት እነርሱም እንደ በጎች ሆኑለት።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ሔደ ሲሔድም የእግዚአብሔር መልአክ ይመራውና ያጸናናው ነበር ተጋድሎውንም ፈጽሞ በበጎ ሽምግልና ጳጉሜን 1 ቀን ወደ እግዚአብሔር ሔደ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ዑቱኮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአባ_ሖር_ወንድም_ቀሲስ_ቅዱስ_ብሶይ፦ ይህም ቅዱስ ከአንጾኪያ አገር ክብር ካላቸው ወገኖች ውስጥ ነው ስለ ዕውቀቱና ስለ ሃይማኖቱ ጽናት ቅስና ተሾመ።
❤ ወንድሙ አባ ሖርና እናቱ ወደ ግብጽ አገር ሒደው በሰማዕትነት ከሞቱ በኋላ እርሱም ተነሥቶ ወደ እስክንድርያ ሥጋቸውን ያይ ዘንድ ሔደ። ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ሰጠ ከሦስት እንጀራና ከሚመረጐዛት ከአንዲት የሰኔል በትር በቀር ምንም አልያዘም ነበር።
✝ ወደ እስክንድርያ አገርም በደረሰ ጊዜ የዘመዶቹ በድን ወዳለበት ሰዎች መርተው አደረሱት የእናቱንና የወንድሙንም ሥጋ በአየ ጊዜ ከእርሳቸው ስለ መለየቱ መሪር ልቅሶን አለቀሰ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ መነኰንኑ ሒዶ በፊቱ ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ለመኰንኑም የአባ ሖር ወንድም እንደሆነ ነገሩት መኰንኑም ታላቅ የደንጊያ ምሰሶ በሆዱ ላይ እንዲአቆሙበት አዘዘ ይህንንም በአደረጉበት ጊዜ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጠ።
❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ ሥጋውን ከወንድሙና ከእናቱ ሥጋ ደግሞ ቊጥራቸው ሰማንያ ስምንት ከሆነ ከሌሎች ሰማዕታት ሥጋ ጋር በአንድነት ያቃጥሉ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ ወደ እሳት በጨመሩአቸውም ጊዜ ከቶ እሳቱ አልነካቸውም።
❤ ምዕመናን ሰዎችም መጥተው የከበሩ የአባ ሖርና የወንድሙ የአባ ብሶይን የእናታቸውንም ሥጋ ወሰዱ። አገርዋ ዲብቅያ የሚባል የቅድስት ዳሞንንም ሥጋ አገሩ በረሞን ከሚባል የቅዱስ ቢማኮስም ሥጋ ጡልያ ከሚባል አገር የመጣ የውርሱኑፋን ሥጋም አብስላሲ ወደሚባል አገር እስከሚያደርሷቸው በመርከብ ጫኗቸው። የስደቱ ወራት እስከሚፈጸም አክብረው ወስደው በመልካም ቦታ አኖሩዋቸው።
✝ ከዚህም በኋላ አብያተ ክርስቲያን ተሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጣቸው አኖሩ ከእርሳቸውም ተአምራት ተገለጡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆኑ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጳጕሜን 1 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለዑቲኮስ_ዘተሰምየ_ሱታፎ። ለወንጌላዊ ዮሐንስ ለንጹሐ መላእክት ዘተዐጽፎ። መኰንን ዕልው አመ ውስተ እሳት ገደፎ። ካዕበኒ እምህየ ለአናብስት አኅለፎ። በአናብስት ስእኑ ይግሥሥዎ ወእሳት ይልክፎ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጳጒሜን_1።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ ጽድቀ ወምጽዋተ ያበድር እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ይሁብ ክብረ ወሞገሰ። እግዚአብሔር ኢያስተፄንሶሙ እምበረከቱ ለእለ የሐውሩ በየዋሃት"። መዝ 83፥11። የሚነበቡት መልዕክታት ፊል 1፥12-25፣ 1ኛ ዮሐ 5፥1-6 እና የሐዋ ሥራ 18፥21-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 14፥1-7። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም፡ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።

❤ እንኳን #ለጾመ_ዮዲት_ለጾመ፤ የኢትዮጵያ ንጉሥ #ዐፄ_ናኦድ_ስምንተኛው_ሺህ እንዳያዩት ለጾሙት (የፈቃድ ጾም) እግዚአብሔር አምላከ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ "ሰብአ ነነዌ #ጸዊሞሙ_ተማኅሊሎሙ ድኅኑ እሞቶሙ" ትርጉም፦ የነነዌ ሰዎች #ጾመውና_ምሕላ ይዘው ከሞት ዳኑ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በጾመ_ድጓው_ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ እግዚአብሔር አምላክ ጾሙንና ጸሎቱን ተቀብሎ በአዲሱ ዓመት በዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በአገራችን ኢትዮጵያዊ ያለውን የእርስ በእርስ ጦርነት አስወግዶ ሰላም፣ ፍቅርን፣ አድነትንና መተሳሰብን ይላክል፤ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን በቅዱስ ሲኖዶስ በአባቶችን ዘንድ ያለው መከፍፈል አስወግዶ አንድ ያድርግልን። መልካም የጾምና የጸሎት ዕለታት ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ #ጳጒሜን ፪ (2) ቀን።
❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው ሐዋርያው #ቅዱስ_ጳውሎስ_መልእክት_ለጻፈለት ለከበረ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ቲቶ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ቲቶ፦ የዚህም ቅዱስ ትውልዱ ቀርጤስ ከሚባል አገር ነው። እርሱም ለዮናናውያን ወገን ለሆነ ለአገረ ገዥው እኅት ልጅዋ ነው። ከታናሽነቱም የዮናናውያንን ትምህርትና ፍልስፍና ተምሮ እጅግ አዋቂ ሆነ በጠባዩም ቅን ሥራው ያማረ ለድኆችና ለችግረኞች መራራት የሚወድ ነው። ከሌሊቶችም በአንዲቱ "ቲቶ ሆይ ስለ ነፍስህ ድህነት ተጋደል ይህ ዓለም አይጠቅምህምና" የሚለውን በሕልሙ አየ። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ደነገጠ ምን እንደሚሠራም አላወቀም።
❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በተሰማ ጊዜ ብዙዎች ሰዎችም ተአምራቱን እርስበርሳቸው ተነጋገሩ የአክራጥስ መኰንንም ሰምቶ አደነቀ ዕውነት እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ወይም የሥራይ እንደሆነ ሊያውቅ ሽቶ የሚልከው ብልህ ሰው ፈለገ የእኅቱንም ልጅ ቲቶንን መረጠው ከእርሱ የሚሻል የለምና። ሲልከውም ታላቅና ጥልቅ የሆነ ምርመራ እንዲመረምር አዘዘው።
❤ ቲቶም ከይሁዳ ምድር በደረሰ ጊዜ የመድኃኒታችንን ድንቆች የሆኑ ተአምራቶቹን አየ ሕይወትነት ያላቸው ትምህርቶቹንም ሰማ። ከዮናናውያንም በትምህርታቸውና በሥራቸው መካከል ታላቅ የሆነ መራራቅን አግኝቶ የዮናናውያን ሃይማኖታቸው የቀናች እንዳልሆነች ለይቶ ዐወቀ።
❤ ከዚህም በኋላ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ አመነ፤ ደቀ መዝሙሩም ሁኖ ተከተለው። ወደ እናቱ ወንድም ወደ አገረ ገዥውም መልእክትን ላከ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስተምረውና የሚሠራው ዕውነት እንደሆነ ነገረው።
❤ ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ውስጥ የተቆጠረ አደረገው ከዕርገቱም በኋላ ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀብሎ ከእሳቸው ጋር በሀገሮች ሁሉ ዙሮ አስተማረ። ጌታችንም ጳውሎስን ጠርቶ ሐዋርያው በአደረገው ጊዜ ያን ጊዜ ሐዋርያ ጳውሎስን ተከተለው በብዙ አገሮችም ወንጌልን ሰበከ።
የከበረ ቅዱስ ጳውሎስም በሮሜ ከተማ ምስክር ሆኖ ከሞተ በኋላ ቅዱስ ቲቶ ወደ ሀገረ አክራጥስ ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው በዙሪያቸው ላሉ አገሮችም እንዲሁ አደረገ።
❤ ከዚህም በኋላ ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ወደደው እግዚአብሔር ጳጒሜን 2 ቀን ሔደ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለከ_ቲቶ_መስተሳልም። ለእከ ጳውሎስ ዘኮንከ እንበለ ድካም። ከመ ገሠጸከ በቃል ወይቤለከ በሕልም። ተጋደል በእንተ ነፍስከ በገድለ ሃይማኖት ፍጹም። ኢይበቊዓከ ዝንቱ ኃላፊ ዓለም"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጳጒሜን_2።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ እግዚአብሔር። ምክር ሠናይት ለኵሉ ዘይገብራ። ወስብሐቲሁኒ ይነብር ለዓለም"። መዝ 110፥10። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥1-11፣ 2ኛ ጴጥ 3፥7-14 እና የሐዋ ሥራ 4፥31-36። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ቲቶ የዕረፍት በዓልና የጾም፣ የጸሎትና የምሕላ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

Telegram
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)
❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል።
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
[ † እንኳን ለቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
[ 🕊 † ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ † 🕊 ]
† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቲቶ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሲሆን በተወሰነ መንገድም ቢሆን የተዘነጋ ሐዋርያ አይደለም:: በተለይ ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፋቸው አሥራ አራት መልእክታት መካከል አንዷ የተላከችው ለዚህ ቅዱስ በመሆኗ ታሪኩ እንኳ ባይነገር ስሙ አይረሳም:: ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክታቱ በጐ ስሙን እየደጋገመ ያነሳዋል::
ለመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ማን ነው?
ቅዱስ ቲቶ የተወለደው በ፩ ኛው መቶ ክ/ዘመን እስያ ውስጥ: ቀርጤስ በምትባል ከተማ ነው:: የዘር ሐረጉ ከእሥራኤልም: ከጽርእም [ግሪክ ለማለት ነው::] ይወለዳል:: አካባቢው አምልኮተ እግዚአብሔር የጠፋበት ስለሆነ እሱም: ቤተሰቦቹም የሚያመልኩት ከዋክብትን ነበር::
መዳን በእውቀት ይመስላቸው ስለ ነበር የአካባቢው ሰዎች የግሪክን ፍልስፍና ጠንክረው ይማሩ ነበር:: ቅዱስ ቲቶም በወጣትነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልሥፍናና የዮናናውያንን ጥበበ ሥጋ ተማረ:: በጥቂት ጊዜም የሁሉ የበላይ ሆነ::
ቅዱሱ በወቅቱ ምንም እውነተኛውን ፈጣሪ አያምልክ እንጂ በጠባዩ እጅግ ቅንና ደግ ነበር:: ምክንያቱን ሳያውቀው ለእኔ ቢጤዎች ያበላ: ያጠጣ: ይንከባከባቸውም ነበር:: እግዚአብሔር ግን የዚህ ቅን ሰው በጐነቱ እንዲሁ እንዲቀር አልወደደምና አንድ ቀን በራዕይ ተገለጠለት::
በራዕይም አንድ ምንነቱን ያልተረዳው ነገር "ቲቶ ሆይ! ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል:: ይህ ዓለም ኃላፊ ነው::" ሲለው ሰማ:: ከእንቅልፉ ነቅቶ በእጅጉ ደነገጠ:: የሚያደርገውንም አጣ:: ያናገራቸው ሁሉ ምንም ሊገባቸው አልቻለም::
ለተወሰነ ጊዜም ለጉዳዩ ምላሽ ሳያገኝለት በልቡ እየተመላለሰ ኖረ:: ድንገት ግን በዚያ ሰሞን ከወደ ኢየሩሳሌም አዲስ ዜና ተሰማ:: "ክርስቶስ የሚሉት ኢየሱስ: እርሱም የባሕርይ አምላክ የሆነ ወደ ምድር ወርዶ: ስለ እግዚአብሔር መንግስትም እየሰበከ ነው::" ሲሉ ለቲቶ ነገሩት::
"ሌላስ ምን አያችሁ?" አላቸው:: "በእጆቹ ድውያን ይፈወሳሉ:: ሙታን ይነሳሉ:: እውራን ያያሉ:: ለምጻሞች ይነጻሉ:: ሌሎች ብዙ ተአምራትም እየተደረጉ ነው::" አሉት:: የወቅቱ የሃገረ አክራጥስ መኮንን ፈላስፋ ነበርና ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ሊመራመር ወደደ::
እርሱ መሔድ ስላልተቻለው "ብልህ ጥበበኛ ሰው ፈልጉልኝ::" ብሎ ተከታዮችን ቢልካቸው ከቲቶ የተሻለ በአካባቢው አልነበረምና እርሱኑ አመጡት:: መኮንኑ ቲቶን "ነገሩ ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በጥልቅ መርምረህ ምላሽ አምጣልኝ::" ብሎ ላከው::
ቅዱስ ቲቶም ፈጥኖ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ:: ወደ ከተማዋ እንደገባም ጌታችንን አፈላልጐ አገኘው::
፩.ጌታችን ክርስቶስ በሥልጣነ ቃሉ ደዌያትን ሲያርቅ: አጋንንትን ሲያሳድዳቸው ተመልክቶ ይህ ሥራ የፍጡር እንዳልሆነ ተረዳ::
፪.ጌታችን የሚያስተምረው ትምሕርት ከግሪክ ፍልሥፍና እጅግ ርቆና መጥቆ አገኘው:: የግሪክ ፍልሥፍና መነሻውም ሆነ መድረሻው ሥጋዊ ነው:: ጌታ ግን በጣዕመ ቃሉ የሚያስተምረው ሰማያዊ: በዚያ ላይ ዘላለማዊ የሆነ ትምሕርት ነው:: በራዕይ "ስለ ነፍስህ ተጋደል::" ያለው ምሥጢር አሁን ተተረጐመለት::
በዚህ ምክንያትም ጊዜ አላጠፋም:: ወዲያውኑ አምኖ ተከታዩ ሆነ:: ጌታም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ደመረው:: የአክራጥስ መኮንን "ምነው ዘገየህ?" ቢለው ያየውን ሁሉ ጽፎ: እንደማይመለስም አክሎ ደብዳቤ ላከለት::
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ቲቶ ከጌታችን እግር ለሦስት ዓመታት ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ: በመላው እስያ ለስምንት ዓመታት ወንጌልን ሰብኳል:: ቅዱስ ጳውሎስ ባመነ ጊዜ ደግሞ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለሃያ አምስት ዓመታት አስተምሯል::
ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ደግሞ ወደ አክራጥስ ተመልሶ: ሕዝቡን አሳምኖና አጥምቆ: ቤተ ክርስቲያንን አንጿል:: ዕድሜው በደረሰ ጊዜም መምሕራንን: ካህናትን ሹሞላቸው: ባርኳቸውም በዚህች ቀን ዐርፏል::
† አምላከ ቅዱስ ቲቶ መልካሙን የሕይወት ምሥጢር ይግለጽልን:: ከሐዋርያውም በረከቱን ያድለን::
🕊
[ † ጳጉሜን ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
1.ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ [ከሰባ ሁለቱ አርድእት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
- የለም
† " የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ. . . መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ: ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ: በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ለሚሆን ልጄ ቲቶ:: ከእግዚአብሔርም አብ: ከመድኃኒታችንም ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን::" † [ቲቶ. ፩፥፩]