Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
[ † እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ † ]
[ † 🕊 ደብረ ታቦር 🕊 † ]
+ ደብረ ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው:: ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
+ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ: ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር:: በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው: አንድም ገና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም::
+ ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም: በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር:: በርግጥ ያንን ነደ እሳት: ሰማያት የማይቸሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም::
+ ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል:: እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል:: ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ :-
፩. ትንቢቱ ሊፈጸም [መዝ.፹፰፥፲፪]
፪. ምሳሌው ሊፈጸም [ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና]
፫. ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ፩ ሺህ ፭ መቶ [1,500] ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም
፬. አንድነቱን: ሦስትነቱን ለመግለጽ
፭. ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
፮. ተራራውን ለመቀደስ
፯. የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው::
+ ነሐሴ ፯ [ 7 ] ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልዾስ ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቁዋቸው ነበር:: እነርሱም የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ: አንዳንዶቹም ሙሴ: ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት::
+ ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ደንግጠው ዝም አሉ:: የሃይማኖት አባት: ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ዼጥሮስ ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው - የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለው:: በዚያን ጊዜ ቃለ-ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው:: [ማቴ.፲፮፥፲፫]
+ መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከ6ኛው ቀን በሁዋላ ጌታችን ፲፪ [12] ቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው:: ዘጠኙን በእግረ ደብር [ከተራራው ሥር] ትቶ ፫ቱን [ዼጥሮስን: ዮሐንስንና ያዕቆብን] ይዟቸው ወጣ:: እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ::
+ በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ ፯ [7] እጅ አበራ: ከመብረቅም ፯ [7] እጅ አበረቀ:: "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል:: ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ::
+ በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ:: አንዳንዶቹ ጌታን 'ነቢይ' [ሎቱ ስብሐት] ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ :- "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል: እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት: አመሰገኑት::
+ ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም:: መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ: ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል::
+ በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ: ንግበር ሠለስተ ማሕደረ: አሐደ ለከ: ወአሐደ ለሙሴ: ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው:: በዚህም 3 ዳስ እንሥራ:: አንዱን ላንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል::
+ ቅዱስ ዼጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ" በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል:: ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው::
+ እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው:: አብ ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት" ሲል ተናገረ::
+ ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ ነበር:: [ማቴ. ማር. ሉቃ.]
በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ ፫ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት ፲፪ቱ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል::
ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል:: ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል:: [ኢሳ.]
ሊቁም የደብረ ታቦርን ምሥጢር ሲያደንቅ እንዲህ ብሏል:-
"ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ:
ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ:
አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ:
መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ:
ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::"
ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዐይነ ልቡናችንን ያብራልን:: ከበዓሉ በረከትም ያሳትፈን::
🕊
[ † ነሐሴ ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ደብረ ታቦር / ደብረ ምሥጢር / ደብረ በረከት
፪. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት (ልደቱ)
፫. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፬. ቅዱሳን አበው ሐዋርያት
፭. አባ ጋልዮን መስተጋድል
፮. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ [ልደታቸው]
፯. ቅድስት ኦፍራ ሰማዕት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
፫. ፺፱ "99ኙ" ነገደ መላዕክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. ፲፫ "13ቱ" ግኁሳን አባቶች
፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
" ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል:: ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው:: እጅህ በረታች: ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች::" [መዝ.፹፰፥፲፪]
" ከስድስት ቀንም በሁዋላ ጌታ ኢየሱስ ዼጥሮስን: ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው:: በፊታቸውም ተለወጠ:: ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ:: ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ:: እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው:: ዼጥሮስም መልሶ ጌታ ኢየሱስን:- "ጌታ ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው:: ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ: አንዱን ለአንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ" አለ:: እርሱም ገና ሲናገር እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው:: እነሆም ከደመናው:- "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው: እርሱን ስሙት" የሚል ድምጽ መጣ:: ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ::" [ማቴ.፲፯፥፩] (17:1)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላችን_ለመድኃኒታች #ለኢየሱስ_ለክርስቶስ_ከዘጠኙ_ዐበይት በዐል ለአንዱ ለሆነው #በደብረ_ታቦር_ተራራ ላይ ለቅዱስሙሴ ለቅዱስ ኤልያስ ለሐዋርያት ለቅዱስ ጴጥሮስ ለቅዱስ ያዕቆብና ለለቅድስጨዮሐንስ ብርሃነ መለኮቱ ለገለጠበት በዐልና እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና ቀጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሊቀ_ነቢያት_ከቅዱስ_ሙሴ ከልደቱ፣ #ከብንያምም ከመታሰቢያው፣ ከተጋዳይ #ከአባ_ጋልዮን ከዕረፍቱና በሰማዕትነት ከዐረፈች #ከቅድስት_ኦፍራ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን ክብር ይግባውና #የጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ታላቅና_ክቡር_በዓል ነው። በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን #ቅዱሳን_ጴጥሮስ_ያዕቆብንና_ዮሐንስን_ይዞ_ወደ_ታቦር_ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
❤ ስለ እነርሱም ጌታችን "የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ" አለ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
❤ ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው "አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ለአንተ አንድ ለሙሴ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ"። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት።
❤ ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና እራሱን የሚሰውርበት ቤት ይሠራለት ዘንድ የተጋገረው ነገር ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። እራሱንና ባልጀሮቹን ሐዋርያት እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና። ስለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያ ጊዜ ፍፁማን አልሆኑምና።
❤ እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ አነሆ ደመና ጋረዳቸው። የጌታችንን ጌትነነቱ የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት"።
❤ ሙሴና ኤልያስም ከእነርሱ ጋር ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
❤ ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያ ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሳው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያወጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ስልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ያስነሳቸው ማንም አይችልም።
❤ ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይ እና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና።
❤ የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደሙታን ሆኑ ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስ ወደ ቦታው ተመለሱ።
❤ ሐዋርያትን በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የደዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።
❤ እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ድንግል ማርያም በአበሠራት ጊዜ "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው" እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ "ለመግሥቱ ፍጻሜ የለውም" እንዴት አላት። ሰው ካልሆ በበረት እንዴት አስተኙት አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው "ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው" እያሉ እንዴት አመሰገኑ።
❤ ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውሃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆ አልዓዛር ከመቃብር እንዴት ሊያስነሳው ቻለ።
❤ ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለመለየት አንድ አካል አንድ ባሕሪ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሁልጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬ ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ተጋዳይ_አባ_ጋልዮስ፦ ይህም በቀንና በሌሊት ጸሎት የማይታክት ተጋዳይ ሆነ ጎልማሳ ሆኖ ሳለ ከመነኰሰም ጀምሮ እስከ ሸመገለ ድረስ ከበአቱ ቅጽር ውጪ አልወጣም ከማህበር ጸሎት ጊዜ በቀር ከመነኰሳቱ ማንም አያየውም።
❤ ሰይጣናትም ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ መነኰሳትን ተመስለው ወደ እርሱ በመንፈቀ ሌሊት ገብተው እንዲህ አሉት "እኛ ተሰውረን የምንኖር ገዳማውያን ነን ከእኛ አንዱ በሞት ስለተለየ ከእኛ ጋር ልንወስድህ ወደን ወደ አንተ መጣን" ለእርሱም ቃላቸው እውነት መስሎት ልብስና ሲሳይ ወደ ማይገኝበት ጠፍ ወደ ሆነ ተራራ ላይ እስከ አደረሱት ድረስ አብሯቸው ሔደ።
❤ ሲጠቃቀሱበትም በአየ ጊዜ ሰይጣናት መሆናቸውን አውቆ በላያቸው በመስቀል ምልክት በአማተበ ጊዜ ተበተኑ። በሚመለስም ጊዜ በወዲያም በወዲህም መንገድ አጣ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታችን ጸለየ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም የሚዘዋወሩ ከአባ ሲኖዳ ገዳም የሆኑ መነኰሳት ተገለጡለት እነርሱም የዳዊት መዝሙር ያገቡ ነበር ስለ ሥራው ጠየቁቱ በእርሱ ላይ የደረሰውን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ከእነርሳቸው ጋር ወስደውት በፀሐይ የበሰለ ዓሣ እየተመገበ ከእርሳቸው ጋር አንዲት ዓመት ሙሉ ኖረ።
❤ ያመነኰሰው መምህሩ አባ ይስሐቅም ወሬውን በአጣ ጊዜ ፊቱን ያሳየው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አባ ጋልዮንም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ርሱ መጣ አባ ይስሐቅም በአየው ጊዜ በእርሱ ደስ አለው "ወዴት ነበርክ" አለው እርሱም ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ነገረው።
❤ ከዚህም በኋላ የሚያርፍበት ጊዜ ደርሶ ነሐሴ 13 ቀን በሰላም ዐረፈ። መነኰሳቱም በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጋልዮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ የነሐሴ 13 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ጸርሐ_አብ_ኪያከ_በውዳሴ። ወበርእስከ ጸለለ መንፈስ ቅዳሴ። አመ ገበርከ በታቦር እግዚኦ ምስለ ሐዋርያት ክናሴ። ኤልያስ መንገለ ቆመ ወኀበ ሀለወ ሙሴ። ዘመለኮትከ ወልደ ከሠትከ ሥላሴ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_13።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል። ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉአን። ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ። መዝ 67፥15-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥1-14።

Telegram
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)
❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል።
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ። ወይሴብሑ ለስምከ። መዝራዕትከ ምስለ ኃይል"። መዝ 88፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥23-30፣ 2 ጴጥ 1፥15-ፍ.ም እና የሐ ሥራ 7፥44-54። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 9፥28-38። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

[ † እንኳን ለጌታችን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
[ † 🕊 ቅዱስ ዕፀ መስቀል 🕊 † ]
† የዕፀዋት ሁሉ ንጉሣቸው የሚሆን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ለእኛም ኃይላችን: ቤዛችን: መዳኛችን: የድል ምልክታችን ነው:: መስቀል በደመ ክርስቶስ ተቀድሷልና አንክሮ: ስግደት ክብርና ምስጋና በጸጋ ይገባዋል::
ቅዱስ መስቀለ ክርስቶስ ላለፉት ሁለት ሺ ዓመታት ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: ከእነዚህ መካከልም አንዱን በዚህ ዕለት እናዘክራለን::
ታሪኩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በ፬ መቶ [400] ዓ/ም አካባቢ በግብፅ አባ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ሳለ: ቅዱስ ቄርሎስም በሊቀ ዲቁና ሲያገለግል ሳለ በእስክንድርያ ከተማ ሁለት ደሃ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር:: የቀን ሠራተኞች በመሆናቸው ከዕለት ምግብ አይተርፋቸውም ነበር::
ከሁለቱ አንዱ ፍጹም አማኝ ሲሆን ሌላኛው ግን ተጠራጣሪ ነበር:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- በከተማዋ ብዙ ሃብታም አይሁድ ነበሩና እነሱን እየተመለከተ ነው:: ለእርሱ ክርስትና ማለት ገንዘብ መስሎታልና ዘወትር "ለምን ክርስቶስን እያመለክን ድሃ እንሆናለን?" እያለ ያማርር ነበር::
"ያዛቆነ ሰይጣን . . . " እንደሚባለው አንድ ቀን ባልጀራውን "ለምን ክርስቶስን አንክደውም? [ሎቱ ስብሐት!] እርሱን ከማምለክ የተረፈን ድህነት ብቻ ነው" አለው:: ባልንጀራው ሊመክረው ሞከረ:: "እግዚአብሔር አምላከ-ነዳያን ነው:: ቅዱሳን ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታትም በሥጋዊ ሃብት ነዳያን ነበሩ::" ብሎ ቢለውም ሰይጣን ሠልጥኖበታልና አልሰማውም::
ያ ስሑት ደሃ ወዲያው ወጥቶ ወደ ማኅበረ አይሁድ ሔደ:: እነርሱ በቁጥር ብዙ ሁነው በአንድነት ይኖሩ ነበር:: "ሥራ ቅጠሩኝ" አላቸው:: "በእምነት አትመስለንምና አይሆንም" አሉት:: ያን ጊዜ ለአለቃቸው [ፈለስኪኖስ] "አንተ ሥራ ቅጠረኝ እንጂ እኔ ክርስቶስን እክዳለሁ::" [ሎቱ ስብሐት!] አለው::
ወዲያው የከተማው ሕዝብ ተጠርቶ: በጉባኤ መካከል ሊያስክዱት ተዘጋጁ:: በፍጥነትም መስቀል: ጦር: ሐሞት አዘጋጁ:: ሥዕለ ስቅለቱንም አመጡ:: ያን ደሃ ከሃዲም "በል-ክርስቶስ ሆይ! ካድኩህ ብለህ ምራቅህን ትፋበት: ሐሞቱን አፍስበት: በጦርም ውጋው::" [ሎቱ ስብሐት!] አሉት::
ያ ልቡ የደነቆረ መስቀለ ክርስቶስ ላይ ተፋ:: ሐሞትም አፈሰሰበት:: በመጨረሻ በጦር ሲወጋው ግን ድንቅ ተአምር ተገለጠ:: በጦር ከተወጋው ከመስቀሉ ጐን ብዙ ደም ፈሰሰ:: ለረዥም ሰዓትም አላቋረጠም:: በዚህች ሰዓት በአካባቢው የነበሩ ሁሉም አይሁድ በግንባራቸው ተደፍተው ለክርስቶስና ቅዱስ መስቀሉ ሰገዱ::
ሁሉም በአንድነት "ክርስቶስ የአብርሃም አምላክ ነው:: መድኃኒትም ነው::" ሲሉ እየጮሁ ተናገሩ:: ባለማወቅ ስላደረጉት እነርሱ ምሕረትን ሲያገኙ ያ አዕምሮ የጐደለውን ደሃ ግን ዘወር ብለው ሲያዩት ወደ ድንጋይነት ተቀይሮ ነበር:: ነፍሱንም: ሥጋውንም በፈቃዱ አጠፋ::
የአይሁድ አለቃም ዓይነ ሥውር ዘመድ ነበረውና ወዲያው አምጥቶ ከደሙ ቢቀባው ዐይኑ በራ:: ታላቅ ደስታም በዚያ ሥፍራ ተደረገ:: ነገሩን የሰሙት ቅዱሳን ቴዎፍሎስ እና ቄርሎስ ሲመጡ ደሙ ከመፍሰስ አላቆመም ነበር::
በተአምሩ ደስ ተሰኝተው: ከደመ ክርስቶስ ለበረከት ተቀቡ:: የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ከነአፈሩ አንስተው: መስቀሉን በትከሻ ተሸክመው: በፍፁም እልልታና ዝማሬ ወስደው በቤተ መቅደስ አኑረውታል:: የከተማዋ ሁሉም አይሁድም በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል::
† 🕊 ቅዱሳን ስምዖንና ዮሐንስ 🕊 †
† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ አስደናቂ ታሪክ ካላቸው ጻድቃን እነዚህ ሁለቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ::
እርሱስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ቅዱሳኑ በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ተወልደው ያደጉ ክርስቲያኖች ናቸው::
ዘመዳሞች ከመሆናቸው ባሻገር አብረው ስላደጉ እጅጉን ይፋቀሩ ነበር:: የዋሃንም ነበሩ:: ወጣት በሆኑ ጊዜ ትልቁ ዮሐንስ ሚስት አገባ:: ታዲያ አንድ ቀን ከጌታችን መቃብር ኢየሩሳሌም ደርሰው ሲመለሱ ገዳመ ዮርዳኖስ አካባቢ ደረሱ:: እርስ በእርሳቸውም "ይህ ገዳምኮ የመላእክት ማደሪያ ነው::" ተባባሉ::
በዚያውም መንነው ለመቅረት አሰቡ:: ፈረስና ንብረታቸውን ለዘመዶቻቸው ልከው ጸሎት አደረሱ:: ፈቃደ እግዚአብሔርን ሊረዱም ዕጣ ተጣጣሉ:: ዕጣውም "ወደ ገዳም ሒዱ" የሚል ስለሆነ ተቃቅፈው ደስ አላቸው::
ወደ ገዳሙ ሲደርሱም አበ ምኔቱ አባ ኒቅዮስ ፈጣሪ አዞት የገዳሙን በር ከፍቶ ጠበቃቸው:: ተቀብሎ ሲያስገባቸውም አንድ ደግ መነኮስ ሲያልፍ: ቆቡ ቦግ ቦግ እያለ እንደ ፋና ሲያበራ እና መላእክት ከበውት አዩ:: ወዲያውም አበ ምኔቱን "እባክህ አመንኩሰን" አሉት::
እርሱም የአምላክ ፈቃድ ነውና በማግስቱ አመነኮሳቸው:: ፍቅረ ክርስቶስ ገዝቷቸዋልና በጥቂት ዓመታት ተጋድሎ ከብቃት [ከጸጋ] ደረሱ:: ሁለቱም ቆመው በፍቅር ሲጸልዩ የብርሃን አክሊል በራሳቸው ላይ ይወርድ ነበር:: አካላቸውም በሌሊት ያበራ ነበር::
እንዲህ ባለ ቅድስና ለዓመታት ቆይተው ከገዳሙ ወደ ጽኑ በርሃ ሊሔዱ ስለ ፈለጉ የገዳሙ በር በራሱ ተከፈተ:: አበ ምኔቱ አባ ኒቆን [ኒቅዮስ] እያነባ በጸሎት ሸኛቸው:: በበርሃም በጠባቡ መንገድ: በቅድስና ተጠምደው ለሃያ ዘጠኝ ዓመታት ተጋደሉ:: በዚህ ሰዓት ግን ሁለቱን የሚለያይ ምክንያት ተፈጠረ::
እግዚአብሔር ቅዱስ ስምዖን ወደ ከተማ እንዲገባ: ቅዱስ ዮሐንስ ግን በዚያው እንዲቆይ አዘዘ:: ሁለቱ ለረዥም ሰዓት ተቃቅፈው ተላቅሰው ተለያዩ:: ከሃምሳ ዓመታት በላይ ተለያይተው አያውቁም ነበርና::
ቅዱስ ስምዖን ወደ ከተማ ሲገባ ክብሩን ይደብቅ ዘንድ እንደ እብድ ሆነ:: በዚህ ምክንያትም የወቅቱ ከተሜዎች ይንቁት: በጥፊም ይመቱት ነበር:: [እባካችሁ ብዙ በየመንገዱ የወደቁ አባቶች አሉና እንጠንቀቅ!] ቅዱሱ ግን ስለ እነርሱ ይጸልይ ነበር::
በከተማዋ የነበሩ እብዶችን ሁሉንም በተአምራት ፈወሳቸው:: አንድ ቀን ግን ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች ደብድበውት ደከመ:: የእግዚእብሔር መልአክ ወርዶ "ና ልውሰድህ" ብሎ ዮሐንስን ከበርሃ: ስምዖንን ከከተማ በዚህች ቀን ወሰዳቸው:: እነሆ ብርሃናቸው ዛሬም ድረስ ለሚያምንበት ሁሉ ያበራል::
† 🕊 ቅዱስ ባስሊቆስ ሰማዕት 🕊 †
† በመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ከነበሩ ስመ ጥር ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ ባስሊቆስ ነው:: ብዙ ጊዜ "ኃያሉ ሰማዕት" በመባልም ይጠራል:: ስለ ፍቅረ ክርስቶስ በመከራ በቆየባቸው ዘመናት ሁሉ ከማመስገን በቀር ምግብ አይቀምስም ነበር::
"ለምን አትበላም?" ሲሉት "እኔ የአምላኬ ስሙና ፍቅሩ አጥግቦኛል::" ይላቸውም ነበር:: አሥረው በግድ ለጣዖት ሊያሰግዱት ወደ ቤተ ጣዖት ቢያስገቡት በጸሎቱ እሳት ከሰማይ ወርዳ አማልክቶቻቸውን በልታለች:: ተበሳጭተው ለቀናት የደረቀ ባላ ላይ አንጠልጥለው ቢገርፉት ደሙ ፈሰሰ::
የታሠረባት ደረቅ እንጨት ግን ለምልማ: አብባ: አፍርታ በርካቶች ተደንቀዋል:: ከበረከቱም ተሳትፈዋል:: ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ባስሊቆስ በዚህች ቀን ተከልሎ ጌታችንና መላእክቱ ወርደው ሲያሳርጉት ብዙ ሰው አይቶ አምኗል::
† አምላከ ቅዱሳን ከፍቅረ መስቀሉ አድሎ: በኃይለ መስቀሉ ይጠብቀን:: የወዳጆቹን ጸጋ ክብርም ያድለን::

[ † ነሐሴ ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ መስቀለ ክርስቶስ
፪. ጻድቃን ቅዱሳን [አባ ስምዖንና አባ ዮሐንስ]
፫. ቅዱስ ባስሊቆስ [ኃያል ሰማዕት]
፬. ቅዱስ ድምጥያና ደቀ መዛሙርቱ [ሰማዕታት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. አቡነ አረጋዊ [ዘሚካኤል]
፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫. ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ሙሴ [የእግዚአብሔር ሰው]
፭. አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፮. እናታችን ቅድስት ነሣሒት
† "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን:: " [፩ቆሮ.፩፥፲፰-፳፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
፩. ቅዱስ መስቀለ ክርስቶስ
፪. ጻድቃን ቅዱሳን [አባ ስምዖንና አባ ዮሐንስ]
፫. ቅዱስ ባስሊቆስ [ኃያል ሰማዕት]
፬. ቅዱስ ድምጥያና ደቀ መዛሙርቱ [ሰማዕታት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. አቡነ አረጋዊ [ዘሚካኤል]
፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫. ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ሙሴ [የእግዚአብሔር ሰው]
፭. አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፮. እናታችን ቅድስት ነሣሒት
† "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን:: " [፩ቆሮ.፩፥፲፰-፳፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
† እንኳን ለንጹሐት እናቶቻችን ቅድስት እንባ መሪና እና ቅድስት ክርስጢና ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
[ † 🕊 ቅድስት እንባ መሪና 🕊 † ]
ቤተ ክርስቲያን "እንቁዎቼ" ከምትላቸው ሴት ጻድቃን አንዷ ቅድስት እንባ መሪና ናት:: ጣዕመ ዜናዋ: ሙሉ ሕይወቷ: አስገራሚም: አስተማሪም ነው:: ቅድስቷ በ፬ ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ተወልዳ ያደገች ክርስቲያን ናት:: ወላጆቿ ከእርሷ በቀር ሌላ ልጅ የሌላቸው ሲሆን በአኗኗራቸውም ደግና ቅን ነበሩ::
ቅድስት እንባ መሪና ትክክለኛ ስሟ "መሪና" ነው:: ምክንያቱም "እንባ መሪና" የወንድ ስም ነውና:: ነገር ግን በወንድ ስም የተጠራችበት የራሱ ታሪክ አለውና እርሱን እንመለከታለን::
ቅድስት መሪና ገና ልጅ ሳለች እናቷ ማርያም ሞተችባት:: ደግ አባት አንድ ልጁን በሥጋዊም: በመንፈሳዊም ሳያጐድልባት አሳደጋት:: ዕድሜዋ አሥራ አምስት ዓመት በሆነ ጊዜ ወደ ፊቱ አቅርቦ "ልጄ! እኔ ወደ ገዳም ስለምሔድ አንቺን መልካም ባል ላጋባሽ::" አላት::
ቅድስት መሪናም "ነፍሰ ዚአከ ታድኅን: ነፍሰ ዚአየኑ ታጠፍእ-የአንተን ነፍስ አድነህ እንዴት የእኔን ትተዋታለህ? እኔም እመንናለሁ::" አለችው:: አባቷ የተናገረችው ከልቧ እንደሆነ ሲያውቅ "ልጄ! ገዳም ሁሉ በአካባቢው የወንድ ብቻ ነውና ስሚኝ::" አላት::
እርሷ ግን "አባቴ! ግዴለህም: ስሜን እንደ ወንድ ቀይረህ: አለባበሴንም ለውጥ::" አለችው:: [እንደ ወንድ ለበሰች ማለት ግን እንደ ዘመኑ ዓይነት እንዳይመስላችሁ አደራ!]
ከዚያ አባትና ልጅ ሃብት ንብረታቸውን ሸጠው ለነዳያን አካፈሉ:: በፍጹም ልባቸውም መነኑ:: በደረሱበት ገዳም ቅድስት መሪና በወንድ ስም "እንባ መሪና" በሚል ገባች:: ቀጣዩ ሥራዋ እንደ ወንዶች እኩል መስገድ: መጾምና መጸለይ ነበር::
ይህችን ቅድስት ልናደንቃት ግድ ይለናል:: ማንም በእርሷ አይፈተንም:: አያውቋትምና:: እርሷ ግን ወጣት ሆና: አንድም ሴት በሌለበት ገዳም ጸንቶ መቆየት በራሱ ልዩ ነው:: መልአካዊ ኃይልንም ይጠይቃል::
ተጋድሎዋ በጣም ስለ በዛ ወንድሞች መነኮሳት ይደነቁባት ነበር:: ጺም ስለሌላትና ድምጿ ቀጭን ስለሆነ አልተጠራጠሩም:: ምክንያቱም ጃንደረባ ናት ብለው አስበዋልና:: ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን አባቷ ታሞ ከማረፉ በፊት አበ ምኔቱን ጠርቶ "ወደ ከተማ ልጄን እንዳትልክብኝ: አደራ!" ብሎት ነበር::
ያም ሆኖ አንዳንድ መነኮሳት ቅሬታ በማንሳታቸው ወደ ከተማ ተላከች:: ችግሩ ለተልእኮ ባደሩበት ቤት አንድ ጐረምሳ ገብቶ የአሳዳሪውን ልጅ ከክብር አሳንሷት ሔደ:: ሲወጣም "ድንግልናሽን ያጠፋ ማን ነው? ካሉሽ ያ ወጣት መነኩሴ አባ እንባ መሪና ነው በይ::" አላት::
ከሦስት ወራት በኋላ የዚያች ዘማ ሴት ጽንስ በታወቀ ጊዜ ለአባቷ "አባ እንባ መሪና እንዲህ አደረገኝ::" አለችው::
አባት መጥቶ እየጮኸ መነኮሳትን ተሳደበ:: አበ ምኔቱ ግራ ተጋብቶ ቢጠይቀው "የአንተ ደቀ መዝሙር እንባ መሪና ልጄን ከክብር አሳነሳት::" አለው:: አበ ምኔቱ እውነት መስሎታልና ቅድስቲቱን ጠርቶ ቁጣና እርግማንን አወረደባት:: በዚያች ሰዓት ተንበርክካ አንድ ነገር ወሰነች::
"ሴት ነኝ" ብሎ መናገሩስ ቀላል ነው:: ግን ደግ ናትና የእነዛን አመጸኛ ሰዎች ኃጢአት ልትሸከም ወሰነች:: ቀና ብላ "ማሩኝ ወጣትነት ቢያስተኝ ነው?" አለቻቸው:: ተቆጥተው ዕለቱን እየገፉ ከገዳም አስወጧት:: ከባድ ቀኖናም ጫኑባት:: ከስድስት ወራት በኋላም የእርሷ ልጅ ነው የተባለ ሕፃን አምጥተው ሰጧት::
ይህኛው ግን ከባድ ፈተና ሆነባት:: እንዳታጠባው አካሏ በገድል ደርቁአል:: በዚያ ላይ ድንግል የሆነች ሴት ወተት የላትም:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት: የበጋውን ሐሩር: የክረምቱን ቁር ራሷ ታግሣ ለሕፃኑ ከእረኞች ወተት እየለመነች: እየመገበች ሦስት ዓመታት አለፉ::
በዚህ ጊዜ ወደ ገዳሙ ከከባድ ቀኖና ጋር ተመለሰች:: ሕፃኑን ስታሳድግ: ለገዳሙ ስትላላክ: ምግብ ስታዘጋጅ: ውኃ ስትቀዳ: የእያንዳንዱን ቤት ስታጸዳ ሰላሳ ሰባት ዓመታት አለፉ:: ሕፃኑም አድጐ ደግ መናኝ ወጣው:: [የቅድስቷ እጆች ያሳደጉት የታደለ ነው::]
በመጨረሻ ቅድስት መሪና [እንባ መሪና] ታማ ዐረፈች:: እንገንዛለን ብለው ቢቀርቡ ሴት ናት:: እጅግ ደንግጠው አበ ምኔቱን ጠሩት:: በዙሪያዋ ከበው እንባቸውን አፈሰሱ:: ጸጸት እንደ እሳት በላቻቸው:: ሥጋዋን በክብር ገንዘው: በአጐበር ጋርደው: በራሳቸው ተሸክመው ምሕላ ገቡ::
ሙሉውን ቀን "ስለ ቅድስት መሪና ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን?" ሲሉ ዋሉ:: ድንገት ግን ከተባረከ ሥጋዋ "ይቅር ይበለን::" የሚል ድምጽን ሰምተው ደስ ብሏቸው ቀበሯት:: እነዚያ ዝሙተኞችም ከእርሷ ይቅርታን እስካገኙበት ቀን አብደው ኑረዋል::
[ † 🕊 ቅድስት ክርስጢና [ክርስቲና] 🕊 † ]
በ፪ኛው መቶ ክ/ዘመን የተነሳችው ሰማዕቷ ቅድስት ክርስጢና ከዋና ሰማዕታት አንዷ ስትሆን በዓለማቀፍ ደረጃም ተወዳጅ ናት:: ከመነሻው የሃገረ ገዢ ልጅ ብትሆንም ቤተሰቦቿ ጣዖት አምላኪዎች ነበሩ:: አጥር አጥረው: በር ዘግተው: ከማንም ጋር ሳትገናኝ: ጣዖት እንድታጥን አደረጓት::
ወጣት በሆነች ጊዜ ግን ጣዖቱን ተመለከተችው: መረመረችው:: አምላክ እንዳልሆነም ተረዳች:: ወደ ምሥራቅ ዙራ "እውነተኛው አምላክ ራስህን ግለጽልኝ?" ስትል ጸለየች:: መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ክርስትናን በልቡናዋ አሳደረባት:: ቅዱስ መልአክም መጥቶ ሰማያዊ ሕብስትን መገባት::
ፈጥና ተነስታ አብርሃማዊት ቅድስት ጣዖታቱን ሰባበረች:: በዚህ አባቷ ተቆጥቶ [ርባኖስ ይባል] በዛንጅር [ሥጋን የሚልጥ: የሚቆርጥ ጀራፍ ነው::] አስገረፋት:: ንጽሕት ናትና ከአካሏ ደም ሳይሆን ጣፋጭ ማር ፈሰሰ::
በድጋሚ በእሳት ቢያቃጥላትም አልነካትም:: ድንገት ግን አባቷ ርባኖስ ተቀሰፈ:: ሌላ ንጉሥ መጥቶ በእሳትም: በስለትም አሰቃያት:: እሱንም መልዐክ ቀሠፈው:: ሦስተኛው ንጉሥ ግን ብዙ አሰቃይቶ: ጡቶቿንና ምላሷን አስቆረጣት:: በመጨረሻውም በዚህች ቀን ለእፉኝት [እባብ] አስነድፎ ገድሏታል::
የቅዱሳት እናቶቻችን አምላክ ለእነርሱ የሰጣቸውን ጽናት አይንሳን:: ከበረከታቸውም አብዝቶና አትረፍርፎ ያድለን::
🕊
[ † ነሐሴ ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት እንባ መሪና ገዳማዊት
፪. ቅድስት ክርስጢና ሰማዕት
፫. ቅዱስ ለውረንዮስ ሰማዕት
፬. ሰላሳ ሺ ሰማዕታት [የቅድስት ክርስቲና ማኅበር]
፭. አበው ቅዱሳን ሐዋርያት [ወላዲተ አምላክን ለመገነዝ በዚህ ዕለት ተሠብስበዋል::]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
፪. ቅዱስ ሚናስ [ማር ሚና] ሰማዕት
፫. ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ [አፈ በረከት]
"ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ::" [፩ጴጥ. ፫፥፫]