Telegram Web Link
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  †

🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊

[ †  እንኩዋን ለሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ዓመታዊ
የቅዳሴ ቤት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊 † ቅዱስ ሚናስ ምዕመን ሰማዕት † 🕊

ቅዱስ ሚናስ [ ማር_ሚና ] በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::

ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::

ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ እርሱ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው ሲባልም ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት: በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ የምንጠቀምበትን ስንክሳር ፹ [80] ከመቶ እጁን ያዘጋጁት እነርሱ ናቸው::

አባቶቻችንና እናቶቻችን ኢትዮዽያውያን ቅዱሳን ግን አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ [ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው] :-

- በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ
- በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ
- በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ
- ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ
- በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው::

እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::

የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን አደረገ:: አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::

በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም::

ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች::

ቅዱስ ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " መርዩጥ " ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል::

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን::

🕊

[ †  ሰኔ ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሚናስ [ማር ሚና] ሰማዕት [ቅዳሴ ቤቱ]

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
፪. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ [አፈ በረከት]
፫. ቅድስት እንባ መሪና
፬. ቅድስት ክርስጢና

" ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይሕን እጽፍልሃለሁ:: ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ:: ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔርንም የመምሠል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው:: " [፩ጢሞ.፫፥፲፬] (3:14)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

              #ሰኔ_፲፭ (15) ቀን።

እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለሰማይ_ጭፍራ ለተባለ #ለቅዱስ_ሚናስ_ቤተ_ ክርስቲያን_መርዩጥ በተባለ አገር #ለከበረችበት_ለቅዳሴ_ቤቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                        ✝️ ✝️ ✝️
#የቅዱስ_ሚናስ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅዳሴ_ቤት፦ ከዚህ አስቀድሞ የቅዱስ ሚናስ ሥጋ ተሠውሮ ይኖር ነበር ጌታችንም ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ምክንያት አደረገ ይኸውም እንዲህ ነው ቅዱስ ሚናስ ሥጋው ተደፍኖ በሚኖርበት ኮረብታ አቅራቢያ በጎችን የሚያረባ አንድ ሰው በጎቹን እየጠበሸ ይኖር ነበር። ከዚያ እረኛ በጎች ውስጥ ደዌ ያለበት አንዱ በግ በዚያ በኮረብታው አጠገብ ባለ የጒድጓድ ውኃ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከደዌው ዳነ እረኛውም አይቶ አደነቀ ሌሎችንም ደዌ ያለባቸውን አመጣ በዚያ ውኃም በታጠቡ ጊዜ ሁሉም ዳኑ።

ከዚህም በኋላ ይህ በቦታው ሁሉ ታወቀ ደዌ ያለባቸውም ሁሉ እየመጡ አፈሩን ከውኃው ጋራ አንድ አድርገው ለውሰው በመቀባት ወዲያውኑ ይድኑ ነበሩ ምክንያቱን ግን አላወቁም። በዚያ ውኃና በአፈሩ በሽተኞችን እንደሚያድን የዚያ በግ ጠባቂ ወሬው በሮሙ ንጉሥ ዘንድ ተሰማ ለንሡም የቊስል ደዌ የታመመች ልጅ ነበረችው ወደ በግ ጠባቂውም ላካት እርሱም በጎቹን እንደ አዳናቸው አዳናት። እርሷም በተፈወሰች ጊዜ ከዚያ ቦታ ፈውስ የሚደረግበትን ምክንያት ታውቅ ዘንድ ወደደች።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚናስ በሕልም ተገለጸላትና ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተደፍኖ ስለሚኖር እነሆ አስቆፍረሽ ታወጪው ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል" አላት። ከእንቅልፍም በነቃች ጊዜ ቅዱስ ሚናስ እንዳዘዛት አደረገች የከበረ ሥጋውንም አወጣች በዚያም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠራችለት ንጉሡም በዚያ ቦታ ከተማ እንዲሠሩ መኳንንቱንና ሹሞቹን አዘዛቸው ታላቅ ከተማም ተሠራች ስሟም መርዩጥ ተባለች።

እግዚአብሔር ከቅዱስ ሚናስ ሥጋ ቊጥር የሌላቸው ድንቆችንና ተአምራትን ገለጠ። ሊቀ ጳጳሳቱም ከኤጲስቆጶሳቱ መጥቶ ቤተ ክርስቲያኒቱን በዛሬዋ ሰኔ 15 ዕለት አከበራት በዚያቺም ቦታ የሚሠሩ የድንቆችና የተአምሮች ወሬ በቦታው ሁሉ ተሰማ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ15 ስንክሳር።

                           ✝️ ✝️ ✝️
"#ሰላም_ለቅዳሴ_ቤትከ እንተ ተሐንፀት በመርዩጥ። በትእዛዝ ንጉሥ ሥሉጥ። #ሚናስ ዘአንቃሕከ በድነ ሐራውያ እምጸጥ። አስተዋጺኦሙ ዕደው ዘበበ፪ቱ ቂራጥ። መባአ ለከ ዘነሥኡ በሤጥ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_15

                           ✝️ ✝️ ✝️
#የዕለቱ_ምስባክ፦ "ውእተ አሚረ ተናገርኮሙ በራእይ ለደቂቅከ። ወትቤ እሬሲ ረድኤተ በላዕለ ኃይል። ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝብየ"። መዝ 88፥19። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 7፥10-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 4፥16-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 25፥1-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥44-51። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ የቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚናስ የቅዳሴ ቤት በዓልና የበዓለ ዕርገቱ ሰሞን  ለሁላችንም ይሁንልን።

@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
ሰላም እንዴት ናችሁ... ይህ አካውንት 1000442598391 (የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ክርሰቶስ ሠምራ አንድነት ገዳም የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ሲሆን አባቶችና እናቶች በጣም ስለተቸገሩ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልና የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ውለታ ያለበቻሁ እግዚአብሔር በፈቀደና በወደደ የተቻላችሁን እንድታደርጉ ወይም እንድትደግፋ የሁላችን እናት በሆነች በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እንጠይቃለን)
ሰላም እንዴት ናችሁ... ይህ አካውንት 1000442598391 (የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ክርሰቶስ ሠምራ አንድነት ገዳም የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ሲሆን አባቶችና እናቶች በጣም ስለተቸገሩ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልና የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ውለታ ያለበቻሁ እግዚአብሔር በፈቀደና በወደደ የተቻላችሁን እንድታደርጉ ወይም እንድትደግፋ የሁላችን እናት በሆነች በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እንጠይቃለን) አቢሲኒያ 👉 141029444
Forwarded from Bketa @¥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Bketa @¥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለበአለ ጰራቂሊጦስ በአል ከመላ
ቤተሰብ ጋር አደረሳችሁ። የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ከሐገራችን ከቤተክርስቲያናችን ከቤተሰባችን ጋር ይሁን
ዛሬ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የተወለደችበት የልደት በአል ነው።
በማርቆስ አናት ቤት አስራሁለቱ ሐዋርያት
ሰባሁለቱ አርድእት ሰላሣ ስድስት ቅዱስን
አንስት እናታችን ደንግል ማርያም በተገኘችበት
መንፈስ ቅዱስ የወረደብት ቀን ነው።
መንፈስ ቅዱስ ለምን ወረደ?
-ኃይል ለመስጠት (ሉቃ 24:49,ሐዋ1:8)
-ሐሰተኛውን ዓለም ለመውቀስ(ዮሐ 16:8-12)
-ወደ እውነት ሰዎችን ለማድረስ ለመምራት
(ዮሐ16:13,መዝ142:10,መዝ14:18,ማቴ
10:20-23,ዮሐ14:6,1ኛ ቆሮ12:3)
-ለማጽናናትወረደ(ዮሐ14:16,ዮሐ15:26,
ዮሐ16:5-16)
-ሰለወልድ ለመሰክር(ዮሐ15:271ኛቆሮ12:3)
አልቃሻውን ዓለም ሊያጽናና ለመጣው
ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ክብር ውዳሴ
ምስጋና ቅዳሴ አኮቴት ይሁን።
መልካም በአል። መልካም ቀን።
Forwarded from Bketa @¥
#እንኳን_አደረሰን_አደረሳችሁ

           #በዓለ__ጰራቅሊጦስ

⛪️ ጰራቅሊጦስ ቃሉ ከሦስቱ አካላት አንዱ ለሆነው ለእግዚአብሔር መንፈሰ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ነው።
ትርጓሜውም በግሪክ ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዘዝ)፣ መጽናዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው።

⛪️ በተጨማሪም በዓለ ጴንጤቆስጤ በመባልም ይታወቃል። በኪዳነ ወልድ ክፍሌ የመዘገበ ቃላት መጽሐፍ ላይ እንደተቀመጠው በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲክ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የመከር /የእሸት በዓል) የሚል ትርጓሜም አለው።

⛪️ በሉቃስ ወንጌል ፳፬፥፵፱ /24፥49/ ላይ እንደተቀመጠው "እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ" ባለው መሰረት በአንድነት ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበር።

⛪️ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በ፲ኛው ቀን እመቤታችን፤ ፲፪ ደቀመዛሙርት፣ ፸፪ቱ /72/ አርድእት፣ ፴፮ቱ /36/ ቅዱሳን አንስት እና ፭፻ /500/ ባልንጀሮች ባሉበት መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል።

⛪️ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ እውቀትንና ጸጋን አድሏቸዋል።

⛪️ ይህ ዕለት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠበት፤ ብዙ ሺህ ምዕመናን የተገኙበት ዕለት በመሆኑ ሊቃውንት የቤተክርስቲያን የልደት ቀን በማለት ይጠሩታል።

⛪️ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ከተቀበሉ በኋላ፤ ሕገ ወንጌልን ለሕዝቡ ከማስተማራቸው በፊት ሐዋርያት ጾመዋል።

ይህንኑ የሐዋርያትን መጾም ተከትለን እኛም ከነሱ በረከታቸውን ለመካፈል ሐዋርያዊት የሆነችው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንደአባቶቻችን እስከ ሐምሌ 5 ድረስ በጾም በጸሎት እናሳልፋለን ።
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

              #ሰኔ ፲፮ (16) ቀን።

እንኳን #የእግዚአብሔር_መልአክ_ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦለት #ሕፃኑንና_እናቱንም_ይዞ_ወደ #እስራኤል_አገር_እንዲመለስ_ላአዘዘበት_ዕለትና #መልካም_ሽምግልና_ላለለው ስም አጠራሩ ለከበረ በገዳም ለሚኖርና በገድል ለተጠመደ #ለስልሳ_ዓመት ብቻው ሰው ሳያይ ለኖረ አባት ለላይኛው ግብጽ ሰው #ለአባ_አቡናፍር_ለዕረፍቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #የአባ_አቡናፍርን_ገድል ከተናገረ #ከአባ_በፍኑትዮስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                            ✝️ ✝️ ✝️
#አባ_አቡናፍር፦ የዚህም አባት ገድል የተናገረ አባ በፍኑትዮስ ነበር እርሱ ቊጥሩ ከገዳማውያን ነውና። አባ በፍኑትዮስም ወደ በረሃ ውስጥ በገባ ጊዜ አንዲት የውኃ ምንጭና አንዲት የሰሌን ዛፍ አግኝቶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ።

በአንዲት ዕለትም አባ በፍኑትዮስ ወደርሱ ሲመጣ አባ አቡናፍርን አየው ፈርቶም ደነገጠ የሰይጣን ምትሐት የሚያይ መስሎታልና ይህም አባት አቡናፍር ልብስ አልነበረውም ጸጒሩና ጽሕሙ ሥጋውን ሁሉ ይሸፍናሉ አባ በፍኑትዮስም በላዩ በመስቀል ምልክት አማትቦ አጽናናው በፊቱም አቡነ ዘበሰማያት ጸለየ ከዚህም በኋላ "አባ በፍኑትዮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው" አለው ይህንንም በማለት ከእርሱ ፍርሃቱን አራቀለት።

ከዚህ በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ ተቀመጡ። ከዚህም በኋላ ወደዚህ በረሀ ከዓለም አወጣጡ እንዴት እንደሆነ በዚያ በረሀ አኗኗሩ እንዴት እንደሆነ ይነግረው ዘንድ አባ በፍኑትዮስ አባ አቡናፍርን ለመነው። አባ አቡናፍርም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ ደጋጎች ዕውነተኞች መነኰሳት በሚኖሩበት በአንድ ገዳም እኖር ነበር የገዳማውያንን ልዕልናቸውን ሲናገሩ ሲያመሰግኑአቸውም ሰማሁ "እኔም ከእናንተ የሚሻሉ አሉን?" አልኳቸው እነርሱም "አወን እነርሱ በበረሀ የሚኖሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበሩ ናቸው እኛ ለዓለም የቀረብን ስለሆን ብንተክዝና ብናዝን የሚያረጋጋን እናገኛለን ብንታመም የሚጠይቀንና የፈለግነውን ሁሉ እናገኛለን በበረሀ የሚኖሩ ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ ናቸው" አሉኝ። ይህንንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልቤ እንደ እሳት ነደደ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ የፈቀደውን ይመራኝ ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ተነሥቼ ጸለይኩ። ትንሽ እንጀራም ይዤ ተጓዝኩ አንድ ጻድቅ ሰውም አግኝቼ የገዳምውያንን ገድላቸውንና ኑሮአቸውን እያስተማረኝ በእርሱ ዘንድ ኖርኩ።

ከዚህም በኋላ ወደዚህ ደረስኩ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝን ይቺን ሰሌን አገኘኋት በየዓመቱም ዐሥራ ሁለት ዘለላ ታፈራለች ለየወሩም የምመገበው አንዱ ዘለላ ይበቃኛል ውኃም ከዚች ምንጭ እጠጣለሁ በዚች በረሀ እስከ ዛሬ ስልሳ ዓመት ኖርኩ ከቶ ያላንተ የሰው ፊት አላየሁም" አለኝ። ይህንንም ሲነጋገሩ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ ወረደ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ሰጣቸው። ከዚያም በኋላ ከሰሌን ፍሬ ጥቂት ምግብ ተመገብን። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ አቡናፍር መልኩ ተለወጠ እንደ እሳትም ሆነ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክኮ ሰገደ ለአባ በፍኑትዮስም ሰላምታ ሰጠው ያን ጊዜም ነፍሱን በጌታ እጅ ሰጠ። ቅዱስ በፍኑትዮስም በጸጉር ልብስ ገንዞ በዚያች ቦታ ቀበረው።

ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ በዚያች ቦታ ይኖር ዘንድ አሰበ በዚያን ጊዜ ያቺ የሰሌን ዛፍ ወደቀች የውኃውም ምንጭ ደረቀ። ቅዱስ አባ በፍኑትዮስ ወደ ዓለም ተመልሶ የገዳማውያንን ዜና ይልቁንም የቅዱስ አባ አቡናፍርን ዜና ይሰብክ ዘንድ ይህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ የከበሩ ገዳማውያን በአባ አቡናፍርና በአባ በፍኑትዮስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 16 ስንክሳር።

                        ✝️ ✝️ ✝️
"#ሰላም_ለአቡናፍር_ጊዜ ተዳደቆ_መዊት። እንተ ተለወጠ ገጹ አምሳለ ውዑይ እሳት። ድኅረ ቀበሮ በፍኑትዮስ በውሳጤ በዓት። ኢትትዋስ ለካልአን ዘተውህበቶ ሲሲት። ነቅዐ ማይ የብስት ወወድቀት በቀልት"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_16

                         
@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKw
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ሰኔ ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

🕊  † ቅዱስ አቡናፍር ገዳማዊ  †  🕊

ጻድቁ ተወልዶ ያደገው በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ነው:: ወቅቱ ሥርዓተ መነኮሳት የሚጠበቅበት:አበው ባሕታውያን እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝተው የደመቁበት ነበር:: ታላቁ አቡናፍርም ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: በሥርዓት አድጎ: መጻሕፍትንም ተምሮ ገና በወጣትነቱ መንኗል::

ሥርዓተ መነኮሳትን ከአባ ኤስድሮስ ታላቁ አጥንቶ ገዳሙንና መምሕሩን እየረዳ ለብዙ ዓመታት በጾምና በጸሎት ኑሯል:: መነኮሳቱ ስለ ትሕትናውና ስለ ታዛዥነቱ ፈጽመው ያከብሩት ነበር::

ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋውያን መነኮሳት ጭው ባለ በርሃ ስለሚኖሩ ባሕታውያን ሲጨዋወቱ: ሲያደንቁዋቸውም ሰማ:: እርሱ በዛ ወቅት ባሕታውያን በበርሃ መኖራቸውን አያውቅም ነበርና ሒዶ መምሕሩን አባ ኤስድሮስን ጠየቃቸው:: እርሳቸውም "አዎ ልጄ! ከዚሕ በጣም ርቅው: ንጽሕናቸውን ጠብቀው: ከሰውና ከኃጢአት ተይለው የሚኖሩ ገዳማውያን አሉ" አሉት::

ቅዱስ አቡናፍር "በዚሕ ካሉት መነኮሳትና በበርሃ ካሉት ማን ይበልጣል?" ቢላቸው "እነርሱ በጣም ይበልጣሉ:: ዓለም እንኩዋ ከነ ክብሯ የእግራቸውን ሰኮና አታህልም" አሉት:: ይሕንን የሰማው ቅዱስ አባ አቡናፍር ጊዜ አላጠፋም::

ከመምሕሩ ቡራኬ ተቀብሎ ወደ በርሃ ሔደ:: ለብዙ ቀናት ከተጉዋዘ በኋላ አንድ ባሕታዊ አግኝቶ አብሯቸው ተቀመጠ:: ከእርሳቸው ዘንድም ሥርዓተ ባሕታውያንን ተምሮ እንደገና ወደ ዋናው በርሃ ጉዞውን ቀጠለ::

ከብዙ ቀናት መንገድ በኋላም አንድ ሠፊ ሜዳ ላይ ደረሰ:: አካባቢው የውሃ ጠብታ የማይገኝበት: ይቅርና መጠለያ ዛፍ የሣር ዘር እንኩዋ የሌለበት ወይም በልሳነ አበው "ዋዕየ ፀሐይ የጸናበት: ልምላሜ ሣዕር የሌለበት: ነቅዐ ማይ የማይገኝበት" ቦታ ነበር:: በዚህ ቦታ ይቅርና የሰው ልጅ አራዊትም አይኖሩበትም::

ለአባ አቡናፍር ግን ተመራጭ ቦታ ነበር:: ቅዱሳኑን ይሕ አያሳስባቸውም:: ምክንያቱም ለእነርሱ ምግባቸውም: ልብሳቸውም ፍቅረ ክርስቶስ ነውና:: አባ አቡናፍር ወደ ፈጣሪ ጸለዩ:: በእግዚአብሔር ቸርነት ከጎናቸው አንዲት ዘንባባ [በቀልት] በቀለች:: ከእግራቸው ሥርም ጽሩይ ማይ [ንጹሕ ምንጭ] ፈለቀች::

ጻድቁ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: ዓመታት አለፉ:: ልብሳቸውን ፀሐይና ብርድ ጨርሶት ቅጠል ለበሱ:: በዚያ ቦታም የሰው ዘርን ሳያዩ ለ፷ [60] ዓመታት በተጋድሎ ኖሩ:: የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስ እግዚአብሔር አባ በፍኑትዮስን [የባሕታውያንን ዜና የጻፈ አባት ነው] ላከላቸው::

ቃለ እግዚአብሔርን እየተጨዋወቱ ሳለ የአባ አቡናፍር አካሉ ተለወጠ:: እንደ እሳትም ነደደ:: አባ በፍኑትዮስም ደነገጠ:: ታላቁ ገዳማዊ ግን እጆቻቸውን ዘርግተው ጸለዩ: ሰገዱና አማተቡ:: ነፍሳቸውም ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ቅዱሳን መላዕክትም በዝማሬና በማኅሌት አሳረጉዋት:: የሚገርመው ደግሞ አባ በፍኑትዮስ ይሕን ሲያይ ቆይቶ ዘወር ቢል ዛፏ ወድቃለች: ቅርንጯም ደርቃለች::

ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱሳን አበው ባሕታውያን መታሠቢያ ናት::

ከሰው [ ከዓለም ] ርቀው: ንጽሕ ጠብቀው: ዕጸበ ገዳሙን: ግርማ አራዊቱን: ጸብዐ አጋንንትን ታግሠው የኖሩ: ስማቸውን የምናውቀውንም ሆነ የማናውቃቸውን እንድናከብራቸው ቤተ-ክርስቲያን ሥርዓትና በዓል ሠርታለች::

አምላካችን ከአበው ባሕታውያን ጸጋ በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † ሰኔ ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ አቡናፍር ገዳማዊ [ስም አጠራሩ የከበረ:
ሽምግልናው ያማረ አባት]
፪. አበው ቅዱሳን ባሕታውያን [ ዛሬ የሁሉም ቅዱሳን ባሕታውያን [በተለይም የስውራኑ] ዓመታዊ በዓል ነው::

- ከሰው: ከዓለምና ከኃጢአት ርቀው
- ንጽሕ ጠብቀው
- ዕጸበ ገዳሙን
- ድምጸ አራዊቱን
- ግርማ ሌሊቱን
- የሌሊቱን ቁር
- የመዓልቱን ሐሩር
- ረሐቡን: ጽሙን: መራቆቱን . . . ሁሉ
ስለ ፍቅረ-ክርስቶስ ሲሉ ታግሠውታልና::

"ዛሬም በየበርሃው የወደቁ: ስለ ዓለም ምሕረትን
የሚማጸኑ አሉ::"

አምላካቸው በረከታቸውን ያድለን።

፫. የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ከግብጽ እንዲመለስ የነገረበት [ተዝካረ ሚጠታ ለእግዝእትነ ማርያም]
፬. አፄ ይኩኖ አምላክ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩፡ ኪዳነ ምሕረት ማርያም
፪፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ
፫፡ አባ ዳንኤል ገዳማዊ
፬፡ ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሠ ሮሜ
፭፡ አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፮፡ ቅዱስ ሐርቤ ንጉሠ ኢትዮጵያ

" . . . ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ: ከዚሕም በላይ በእሥራትና በወኅኒ ተፈተኑ . . . ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: ዕብ.፲፩፥፴፮] (11:36) "

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
                       †                       

[ ይህም ጰራቅሊጦስ የተባለ መንፈስ ቅዱስ ነው።  ]

†   🕊   †    🕊   †

💖

❝ ይህም ለሐዋርያት የተሰጠ በሁለተኛው ልደት ፣ ከእነርሱ በተወለዱት ክርስቲያኖች ሁሉ የወረደው መንፈስ ቅዱስ ነው። እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስም ጰራቅሊጦስ የተባለ መንፈስ ቅዱስ ከቤተክርስቲያን ማኅበር [ አንድነት ] አይለይም።

ይህም ጰራቅሊጦስ የተባለ መንፈስ ቅዱስ ነው። በክርስትናው ዕለት ጥምቀት በሚጠመቁት ሁሉ ላይ የሚያድርም እርሱ ነው። ክርስቲያን የሚሆኑትም በአንዲት የሐዋርያት ጉባኤ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ብሎ ካህኑ እፍ ባለባቸው ጊዜ ነው። ያን ጊዜም መንፈስ ቅዱስ በተጠመቁት ሁሉ ላይ በርግብ አምሳል ያድራል።

ይህም በተጠመቀበት ዕለት በጌታችን ላይ በርግብ አምሳል የወረደው ፣ በራሱ ላይም የተቀመጠው ፣ በነቢያት አንደበትም የተናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው። ❞

[ ርቱዓ ሃይማኖት  ]

🕊

❝ በእርግጥም መንፈስ ቅዱስ በጥምቀት በእኛ ውስጥ ሳያድር በፊት እግዚአብሔር አብን አባት ብለን መጥራት አንችልም ነበር። ስለዚህም በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅነትን ሥልጣን ያልተቀበሉ እርሱን አባት ብለው መጥራት እንዳይችሉና " አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ... " ብለውም መጸለይ እንዳልተፈቀደላቸው እንገነዘባለን። ለዚህ እንዳይበቁ የሚያደርጋቸው ዋነኛው ምክንያት በውስጣቸው መንፈስ ቅዱስ ባለማደሩ ነው። ❞

[ ፊልክስዩስ ]

†   🕊   ክብርት ሰንበት   🕊   †

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
2024/06/30 21:51:18
Back to Top
HTML Embed Code: