Telegram Web Link
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡   †

†    እንኳን አደረሳችሁ   †
ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

[  † ግንቦት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  †  ]

🕊   †  አርዋ ቅድስት  †   🕊

እናታችን ቅድስት አርዋ በስነ ገድላቸው ከደመቁ የቀደመው ዘመን ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: በሕጻንነቷ የሚገባውን የክርስትና ትምሕርት ተምራለችና ምርጫዋ ሰማያዊው ሙሽርነት ሆነ::

ለሰዎች ሕይወት እንቅፋት እየሆኑ ከሚያስቸግሩ ነገሮች አንዱ መልክ ነው:: እግዚአብሔር የፈጠረውን ደም ግባት [ቁንጅና] በማይገባ ተጠቅመው የአጋንንት ራት የሆኑ: ሌሎችንም አብረው ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው:: አርዋ ግን ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ብትሆንም እርሷ ለዚሕ ቦታ አልነበራትም:: በለጋ እድሜዋ በክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር ተጠመደች እንጂ::

ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግስተ ሰማያት ሁሉን ንቃለች:: በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል ዘንድ ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ "መዋኢተ ፍትወት" [የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች] አስብሏታል::

የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን መሆን የቻለ የደግነት: ርሕራሔ: የፍቅርና የምጽዋት ሕይወትም ነበራት እንጂ::

አንድ ቀን በተንኮለኞች የሐሰት ምስክር ያለ ጥፋቷ ለፍርድ ቀረበች:: ፍርደ ገምድል ዳኛ ሞት ፈረደባት:: በአደባባይ በጭካኔ ቅድስት እናታችንን ገደሏት:: እግዚአብሔር ግን ድንቅ ነውና ከሞት አስነስቷት ገዳዮቿ እንዲጸጸቱ አድርጓል:: ከዚሕ በኋላም በንጹሕ አኗኗሯ ቀጠለች::

አንድ ቀን ግን ከባድ ፈተና መጣባት:: አንድ በደም ግባቷ ተማርኮ ሲፈልጋት የኖረ ጐልማሳ አሳቻ ሰዓትና ቦታ ላይ አገኛት:: የሥጋ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አስገደዳት::

እርሱን መታገሉ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት እርሱ ልብሱን እያወለቀ እርሷ ከወደቀችበት ሆና ወደ ፈጣሪዋ ለመነች :- "ጌታየ ሆይ! የእኔንም ድንግልና ጠብቅ: እርሱንም ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አትተወው:: ስለዚሕም ነፍሴን ተቀበላት" ብላ አለቀሰች::

እመቤታችን እንደ ዐይን ጥቅሻ ወርዳ ነፍሷን አሳረገች:: ጐልማሳው ወደ ጣላት ቅድስት ዘወር ቢል ሙታ አገኛት:: እርሱም ተጸጸተ:: ወገኖቿ በዝማሬ እናታችን ቅድስት አርዋን ቀብረዋታል::

🕊  †  ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ  †   🕊

ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ አርፏል::

ቅዱስ ቆሮስ ከ72ቱ [ ፸፪ቱ ] አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር የተማረ: ለስብከተ ወንጌል ብዙ ሃገራትን የዞረ ታላቅ ሐዋርያ ነው:: ባስተማረባቸው ቦታዎች ብዙ ሕማማትን ተቀብሏል::

ብዙ አሕዛብንም ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሷል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለዓመታት አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲታሠር መልዕክቶችንም ይወስድለት ነበር::

† ወርኀ ግንቦትን በሰላም ላስፈጸመን እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን:: አምላካችን ከወዳጆቹ በረከትን ይክፈለን::   †

🕊

[  † ግንቦት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅድስት አርዋ እናታችን
፪. ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት
፬. አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት

[   †  ወርኃዊ በዓላት    ]

፩፡ ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
፪፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፫፡ አባ ሣሉሲ ክቡር
፬፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት
፭፡ ቅድስት ሶፍያና ሰማዕታት ልጆቿ

" መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው:: እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥረዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት:: " [ምሳሌ.፴፩፥፳፱] (31:29)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
                           †                           

🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞

🕊

❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ።

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ]


❝ እኔ ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ።

መከራዬን አይተሃልና ፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና በምሕረትህ ደስ ይለኛል ሐሤትም አደርጋለሁ። በጠላቴ እጅ አልዘጋኸኝም ፥ በሰፊም ስፍራ እግሮቼን አቆምህ። ❞

[ መዝ . ፴፩ ፥ ፮ - ፰ ]

🕊

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Forwarded from M.A
፨፨፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚችም ዕለት የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም አመታዊ የበዓሏ መታሰቢያ ነው፨፨፨

ቅድስት ዜና ማርያም

፨  በ11መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት ግንቦት 30 ቀን በጎጃም ክፍለ ሀገር ተወለደች። የአባቷ ስም ገብረ ክርስቶስ የእናቷ ስም አመተ ማርያም ይባላሉ። እጅግ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፡ ቅዲስ ጋብቻቸውን በንጽሕና የሚጠብቁ፡ ለሰው የሚራሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ። እንዲህ ባለ መልካም ግብር ከኖሩ በኀላ በፈቃደ እግዚአብሔር 3 ወንዶች ልጆች እናት አንዲት ሴት ልጅ ወለዱ። ይህችም ሴት ልጅ ተወዳጇ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ናት።

፨ ቅድስት ዜና ማርያም እናት እና አባቷን እያገለገለች፡ ፈርሐ እግዚአብሔን፡ በጎ ምግባርን ከወለጆቿ እየተማረች አደገች። ለአቅመ ሔዋንም በደረሰች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ  ወጣት አጯት። ታላቅ ግብዣ ተደረጎ በተክሊል ተዳረች። በዚያው ወራት ግን የዜና ማርያም እናት አመተ ማርያም አምስተኛ ልጅ ወልዳ ተኝታ ሳለች በአካባቢው ሕማመ ብድብድ (ተላላፊ በሽታ) በመነሳቱ የዜና ማርያም እናት ታማ ነበር፡ በመጨረሻም ከዚህ ኃላፊ ዓለም አረፈች።

፨ ከዚህ በኋላ የታመመውን ወንድሟንና ሌሎቹንም በመያዝ ከተላላፊው በሽታ ለመትረፍ ሲሉ አካባቢውን ለቀው ወደ በረሃ ወጡ። በዚያም ሌሊት የዱር አራዊት መጥተው ከበቧቸው ሁሉንም ሊበሏቸው ሞከሩ እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ስመ እግዚአብሔርን ስትጠራ አራዊቱ ወደኋላ በመሸሽ ከአካባቢው ራቁ። እርሷም ከክፉ ሁሉ የጠበቃቸውን፡ ከአራዊት መበላት የሰወራቸውን እግዚአብሔርን አመሰገነች። በነጋም ጊዜ የታመመውን ወንድሟን እና ሌሎችን በመያዝ መንገድን ቀጠሉ አንዲት ባዶ ቤት አግኝተው ከእርሷ ተጠጉ። በፀሐዩ ንዳድና ታናሽ ወንድሟን በማዘል እጅግ ስለደከመች ከባድ እንቅልፍ ጣላት። ጠዋት ስትነሳ ግን የታመመው ወንድሟ ከአጠገቧ አላገኘችውም ሌሊት የዱር አራዊት በልተውታልና። አጅም አዘነች የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብላ አራሷን አፅናናች የወንድሟን ተረፈ ሥጋ አጠራቅሟ ቀበረች። በመቀጠልም በአካባቢው ካለ ገዳም ሔዳ ምንኩስናን ተቀበለች።

፨ ከዚህ በኋላ ባሏ አባቷን ሚስቴን አምጣ እያለ ስለጨቀጨቀው ከብዙ ልፋት እና ድካም ፈልጎ አገኛት ወደ ሀገሯም ወሰዳት። በዚያም ወደ ጉባኤ ቀርባ ለምን ወደ ገዳመ እንደሄደች እና ባሏን አንደከዳች ተጠየቀች። እርሷም እግዚአብሔር ከብዙ መከራ አድኖኛል እና እራሴን ለእግዚአብሔር ሰጥቻለሁ አለች። የጉባኤው ተሰብሳቢ በሏ ሀብቷን ወርሶ እንዲያሰናብታት ፈረዱ። እርሷም በዚህ ነገር በመስማማት የነበራትን ላም እና በሮች አስረከበች።
፨ ከዚህ በኋላ በአባቷ ቤት ለአንድ ዓመት ያህል በመቀመጥ የእናቷን ተዝካር አውጥታ ወደ ገዳሙ ተመለሰች በዛም ለጥቂት አመታት የተለያዩ ገድላትን ስትፈጽም ከቆየች በኋሏ ከነፍስ አባቷ ባሕታዊ አባ ገብረ መስቀል ጋር ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ልዩ ስሙ እንፍራንዝ (ጣራ ገዳም) አካባቢ ዋሻ እንድርያስ በተባለው ለ25 ዓመት በብሕትውና ኖረች። አሁንም ድረስ በዚያ ዋሻ እናታችን ዜና ማርያም በፀሎት ጊዜዋ እንቅልፍ እንዳይጥላት ስትጠቀምበት የነበረ ዘንግ ፣ የምተቆምበት ዙሪያውን በገመድ የታሰረ የተቦረቦረ ግንድ አሁንም ድረስ ተአምር እየሰሩ ይገኛሉ። ከዚህም በመቀጠል ዛሬ ዜና ማርያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ዋሻ ሔደች በዚያም በጾምና በጸሎት በልዩ ልዩ ተጋድሎ እስከ እለተ እረፍቷ ድረስ በዚያ ኖራለች።

+++ የገድል ዓይነቶች +++

፨ በየሰዓቱ ከ 100-300 ትሰግድ ነበር
፨ ሁለት ቀን እየፆመች በሶስተኛ ቀን ጥቂት ጥሬ ቀምሳ ሳምንቱን ታሳልፈው ነበር
፨ 150ን መዝሙረ ዳዊት እና ወንጌል በየቀኑ ትጸልይ ነበር
፨ በብሕትውና ወራት ማር፣ ቅቤን፣ ወተትን ፈጽሞ አትቀምስም ነበር
፨  የጌታችን መከራ መስቀል እና ስትየ ሐሞት በማሰብ በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ ኮሶ የሚባል ቅጠል እየበጠበጠች ከቅል ውስጥ ከሚገኘው መራራ ፍሬ ጋር በማዋሐድ ትጠጣ ነበር
፨ ከጸሎት እና ከስግደት በምታርፍበት ጊዜ አትክልት በመትከል እና በመኮትኮት ጊዜዋን ታሳልፍ ነበር
፨ የጌታችንን ግርፋቱን በማሰብ 100 ጊዜ ጀርባዋን ስለምትገረፍ እና ደም ስለሚፈሳት  ጀርባዋ ይቆስል እና ይተላ ነበር።

+++ተአምራት+++

፨ ዓይናቸውን በተለያየ በሽታ የታመሙ ሰውዎች ሁሉ ከህመማቸው ተፈውሰዋል
፨ የራስ በሽታ ( የራስ ፍልጠት፣ ጭንቀት፣ ማዞር) የታመሙ ጸበሉን በመቀባት ድነዋል፡፡

፨ ጸበሉን በመጠመቅ፤ የጻድቋን ተአምር በማዘል፤ ስዕለት በመሳል መካኖች ወላድ ሆነዋል።  ሌሎች በየቀኑ ብዙ ተአምራትን እናታችን ቅድስት ዜና ማርያም ታደርጋለች።

+++ቃል ኪዳን+++

ቅድስት ዜና ማርያም ከዚህ ዓለም የምታርፍበት ጊዜ እንደደረሰ በመንፈስ ቅዱስ በአወቀች ጊዜ ከታላቅ ዛፍ ወጥታ ስትፀልይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት ጋር፣ ከነቢያት፣ ከሐዋርያት፣ ከሰማዕታት፣ ከጻድቃን፣ ከደናግል መነኮሳት ጋር በመሆን ተገልጾ ከአረጋጋት በኋላ ቃል ኪዳንን ሰጧታል።
፨ በፀሎትሽ ያመነውን ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ
፨ በስምሽ የተራበውን ያበላ በመንግስተ ሰማያት ኅብስተ ሕይወት አበላዋለሁ፤ የተጠማውን ያጠጣ ጽዋዓ ሕይወትን አጠጣዋለሁ
፨ መጽሐፈ ገድልሽን የጻፈውን፡ ያጻፈውን፡ የሰማውን፡ ያሰማውን ስሙን በዓምደ ወርቅ እጽፈዋለሁ
፨ ከሕፃንነትሽ እስከ አሁን ድረስ ስለ እኔ ብለሽ ብዙ መከራ ተቀብለሻል፦ ደጅሽን የረገጠ የሦስት ጭነት ጤፍ ያህል ነፍሳትን እንደሚምርላት፡ እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት ጌታችን በማይታበል ቃሉ ቃልኪዳን ገብቶላታል። እንዲሁም ከሲዖል ነፍሳትን እንደሚያወጣላት፡፡

+++ ገዳሟ እና መገኛው+++

፨ የቅድስት ዜና ማርያም መካነ መቃብሯ ( ጸበሏ) በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ከም ከም ወረዳ ይገኛል ቦታውም አዲስ ዘመን ከተማ 20 ኪ.ሜ ርቆ የሚገኝ ሲሆን ከከተማው በስተሰሜን በኩል "ደሪጣ" ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ይገኛል።

"ደሪጣ"

ሸክላ ማርያም ተብላ ትጠራ የነበረችው ቦታ ስያሜው ተቀይሮ ደሪጣ ዜና ማርያም ዋሻ (ገዳም) ተብሎ እስከ አሁን ድረስ እየተጠራ ይገኛል፡፡ ይህን ስያሜ ያገኘውም በቅድስት ዜና ማርያም ገድል ውስጥ " ወትሰቲ ሲካር (ኮሶ) ደሪፃ" የሚል ቃል ይገኛል። ይህም ማለት ኮሶ የተባለውን እንጨት (ቅጠል) ቀጥቅጣ (አልማ) ከቅል ውስጥ ከሚገኘው ፍሬ ጋር በማደባለቅ ትጠጣለች ማለት ነው። ስለዚህ ቦታው "ደሪፃ" ተብሎ ተሰየመ በማለት በአካባቢው የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ። በመጨረሻም ተጋድሎዋን በመፈጸም በዚሁ በተቀደሰ ስፍራ ነሐሴ 30 ቀን ከዚህ አለም ድካም ዐርፋለች። የእናታችን የቅድስት ዜና ማርያም በረከቷ ቸርነቷ ይደርብን። አሜንን!!

+++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎታ፡፡ ወበረከታ ለቅድስት ዜና ማርያም የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን!!! +++
Forwarded from M.A
<<+>>   #የሰኔ_መዓልት <<+>>

=>ቀደምት #ኢትዮዽያውያን ሰው ወሬ ሲያበዛባቸው "#ምነው_የሰኔ_መዓልትን_ሆንክብኝ!" ሲሉ ይተርቡ ነበር:: "አሳጥርልኝ! ወሬህ ረዘመብኝ!" ለማለት ነው::

+ለዚህ መነሻ የሆነው ደግሞ ከ13ቱ ወራት መዓልቱ (ቀኑ) ቶሎ የማይመሽበት ወር ሰኔ መሆኑ ነው:: በእርግጥ ንግግራችን አጭርና ግልጽ ቢሆን ሁሌም መልካም ነው:: ሰው እስኪሰለቸን ድረስ ማውራቱ የሚገባ: የሚመችም አይደለምና::

+"ሺ ዓመት አላወራ! በናትህ (ሽ) ትንሽ ላውራ?" እያሉ መንዛዛቱም ቢሆን አይመከርም::

<< እኔም ወደ ጉዳዬ ልግባ >>

+ከዓመቱ 13 ወራት የሰኔ መዓልቱ ለምን ረዘመ ብንል:- መልሱ አጭር ነው:: "#ይህ_የእግዚአብሔር_ጥበብና_ሥራ_ነው::"
ሳይንሱ ሺህ መንስኤን ሊደረድር ይችላል:: ለእኛ ግን አበው እንዳስተማሩን ሰኔ #የሥራና_የጾም ወር ነው::

+ትጋትን የሚወድ አምላክ ይህንን ወቅት ለጾም ለሥራና: ለበጐ ተግባር አርዝሞልናል:: በእርግጥ ጥቂት ሠርተን ብዙ ለምንተኛ ለዚህ ዘመን ሰዎች ይህ ሊጸንብን ይችል ይሆናል:: ግን ምንም እንኩዋ ሁሉ ወራት ለሥራ ቢሠሩም ወርሃ ሰኔ #ለገበሬና #ለክርስቲያን ትልቁን ሥራ የሚጀምሩበት ወቅት ነው::

+በሰኔ ያልተጋ #ገበሬ ዓመቱን ሙሉ መከረኛ ነው:: ከነ ተረቱም "#ሰነፍ_ገበሬ_ይሞታል_በሰኔ" ይባላል::

+#ክርስቲያንም ከበዓለ ሃምሳ ማግስት #በዓለ ዸራቅሊጦስን ተደግፎ ሰኔን ሊተጋባት ግድ ይላል:: በመከራ ዘመን የሚመሰል #ክረምት ሳይመጣ በወርሃ ሰኔ ሊተጋ ግድ ይለዋል:: ሽሽቱ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆንም ይጸልያል:: (ማቴ.24:20)

+#እግዚአብሔር ሁሉን በሁሉ የሠራ: ያዘጋጀና የፈጸመ ጌታ ነው:: ምንም እንዳይጐድልብንም አድርጐናል:: በተለይ #የኢ/ኦ/ተ_ቤተ_ክርረስቲያን ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነው:: ለሁም ነገር ትርጉምና ሸጋ የሆኑ ሐተታዎች አሏት::

+ስለዚህም የዘመን ቀመሯን መሠረት አድርጋ #ወርሃ_ሰኔ መዓልቱ 15: ሌሊቱ 9 ነው ትላለች:: ብርሃኑ ሲበዛም እንዲህ ትለናለች::

¤ብርሃን #ጌታ_ነው:: (ዮሐ. 9:5)
¤ብርሃን #ድንግል_ማርያም_ናት:: (ራዕይ. 12:1)
¤ብርሃን #ቅዱሳን_ናቸው:: (ማቴ. 5:14)

+ቀጥሎም መጽሐፍ እንዲህ ይለናል:-
"#አምጣነ_ብክሙ_ብርሃን: #እመኑ_በብርሃን: #ከመ_ትኩኑ_ዉሉደ_ብርሃን: #ዘእንበለ_ይርከብክሙ_ጽልመት" (ጨለማ ሳያገኛችሁ: ብርሃንም ሳለላችሁ: የብርሃን ልጆች ትሆኑ ዘንድ: በብርሃን እመኑ) (ዮሐ. 12:36)

=>አምላከ ብርሃን: ወላዴ ሕይወት አምላካችን: ቸር ብርሃኑን ይላክልን:: ተረፈ ዘመኑንም የሰላምና የበረከት ያድርግልን::

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ

የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል።

እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ተንከራትታ ያጠራቀመችውን ገንዘብና ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣ ስታሳክም ነበር። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች።

እናም እናንት ደጋግ ኢትዮጵያውያን ይህንን ወጣት ህይወቱን ለማትረፍ አነሰ በዛ ሳትሉ የእርዳታ እጃችሁን ትዘረጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
ፍሩታ አሻግሬ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000629004045

ለበለጠ መረጃ
➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929
➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689
Forwarded from Bketa @¥
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም


እንኳን አደረሳችሁ

❖ ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ +"+

=>ቤተ_ክርስቲያን
በዚህ ስም ብዙ ቅዱሳን አሏት:: በተለይ ደግሞ እስራኤል
የተባለ የቅዱስ_ያዕቆብ
ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል::
ታላቁ ቅዱስ_መጽሐፍ
ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው::

+ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን
ለማግኘት ኦሪት_ዘፍጥረትን
ከምዕራፍ 39 እስከ 50 ድረስ ማንበብ ይኖርብናል::
ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ
ተብሏል::

+መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም
ይነግረናል:: ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ
ሴት
ሔኖክ
ኖኅ
ሴም
አብርሃም
ይስሐቅና
ያዕቆብ
ነግሮን ቅዱስ_ዮሴፍ
ላይ ይደርሳል::

+ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት
ሚስቱ ራሔል
ከወለዳቸው 2 የስስት ልጆቹ አንዱ ነው:: ቅዱሱ ምንም
እናቱ ብትሞተበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ
ነበረው::
ምክንያቱም ቅን: ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና::

+እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን
አያስብም ነበር:: ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ
ሊፈልጋቸው
በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ::
+መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን
አልበላባቸውም:: የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ
አድርጐ
መግቦታል:: 10ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ
ሊገድሉት ተማከሩ:: ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም
"ሊነግሥብን
ነው" ብለው ቀንተውበታልና::
+በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን
ሸጠውታል:: በዚህም ለምሥጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና
ሕማማት) ምሳሌ
ለመሆን በቅቷል:: ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ
ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት
በተሸጠበት በዺጥፋራ
ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው::
+ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ
ነበርና የዺጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ
አላንበረከከውም:: "ማንም
አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ
እግዚአብሔር" (ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት
ኃጢአትን
አሠራለሁ?) በማለት ከበደል አምልጧል:: ስለዚህ
ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል::
+ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና
አለቅነትን ተሾመ:: "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት"
እንዲል
መጽሐፍ:: ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች
ሕልም ተረጐመ:: ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ
አስደመመ::
ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው::
+ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ
ታደገ:: ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት
ወንድሞቹም መጋቢ
ሆናቸው:: አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም
ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል::
+በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ: ከአባቱ
ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ110 ዓመቱ
በዚህች ቀን በመልካም
ሽምግልና ዐርፏል:: ወገኖቹም በክብርና በእንባ
ቀብረውታል:: "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት
መሠረትም ልጆቹ
(እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ
ከነዓን አፍልሠዋል::

+" ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት "+

=>ቅዱሱ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ
ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት
ነገሥታቱን
ያገለግል ነበር:: ድንግል: ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ
ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው::

+እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር
ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ
ይጸልየው:
ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት
የታሸ ነውና ብዙ ጉዋደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት:
ከክፋት ወደ
ደግነት መልሷል::

+የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን
ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ
ጊዜም
አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት:
ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር::

+በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል::
ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና
በእምነት
እንጥራው:: ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት
ታስባለች:: ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚሁ ዕለት ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ወርኀ ሰኔን የፍሬ: የበረከት: የንስሃና
የጽድቅ አድርጐ ይስጠን:: ከሰማዕቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን
ይክፈለን::

=>ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (የያዕቆብ ልጅ)
2.እናታችን አስኔት (የቅ/ ዮሴፍ ሚስት)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት
4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
5.ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ልደታ ለማርያም
2፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3፡ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4፡ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
5፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

=>+"+ እንዲህም አላቸው:- "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ
ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ:: አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ
አትዘኑ:: አትቆርቆሩም:: እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን
ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና . . . እግዚአብሔርም በምድር
ላይ
ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ: በታላቅ መድኃኒትም
አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ::" +"+ (ዘፍ.
45:4-8)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Forwarded from M.A
Forwarded from M.A
2024/09/27 14:15:19
Back to Top
HTML Embed Code: