Telegram Web Link
Forwarded from Bketa @¥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን



📌 ስንክሳር ዘሚያዚያ ፲፪


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ ነቢዩ ኤርሚያስ የተላከበት ዕለት ነው፡፡
❖ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ነቢዩ ኤርሚያስ ላከው፡፡

❖ ነቢዩ ኤርሚያስን ጠባብና ረግረግ ከሆነ እሥር ቤት ንጉሥ ሴዴቅያስ ባሠረው ጊዜ የንጉሡ ባለሟልና የጭፍራ አለቃ የሆነው ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አውጥቶታል፤ ያንጊዜም የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ መራራ ምርኮንም እንዳይቀምስ ነቢዩ ኤርሚያስ መረቀው፡፡

❖ እንደመረቀውም ሆነለትና ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ 66 ዓመት ተኝቶ ኖረ፤ ከእርሱም ጋራ ወይንና በለስ ነበረ፣ ነገር ግን አልተለወጠም ነበር፡፡

❖ የእስራኤልም ልጆች ከምርኮ እስኪመለሱ ድረስ የኢየሩሳሌምንም ጥፋት እንዳያይ እግዚአብሔር በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት ጠብቆታል መግቦታልም፡፡

❖ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ600 አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው::

❖ አባቱ ኬልቅዩ ይባላል፤ ከካኅናተ እስራኤል አንዱ ነበር፤ እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕጻንነቱ ነበር::


✍️"ከእናትህ ማሕጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል::

📖ኤር 1፥5

❖ ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም፤ ከ70 ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና፤ ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል::

❖ ዘመኑ ዘመነ ኃጢአት (ዘመነ ዐጸባ) ነበር፤ እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም፤ ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት::

❖ እግዚአብሔር ግን በኢትዮዽያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው፤ የተሰበከላቸውን የንስሃ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ አሦር (ነነዌ) አወረዳቸው::

❖ በሁዋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ::

❖ ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ::

❖ ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው፤ ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ እኩሉንም ማርኮ ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ ባቢሎን አወረዳቸው::

❖ ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን (ከመከራው የተረፉት) ይዘውት ወደ ግብፅ ወረዱ እንጂ አልተማረከም::

❖ በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል፤ ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት ነቢይ መምሕርም ነውና ወደ ሕዝቡ (ወደ ባቢሎን) ወረደ::

❖ በዚያም ትንቢትን እየተናገረ ሕዝቡን ከ70 ዓመታት በሁዋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል፤ ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል::
❖ ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው::

❖ በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት ምሥጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ (ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ) አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ፤ አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል፤ ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው::

❖ ስለ እነርሱ ሲል 70 ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት፤ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ 52 ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል / ጽፏል::

❖ ዜና ሕይወቱ ከራሱ የትንቢት መጽሐፍ በተጨማሪ በተረፈ ኤርምያስ በመጽሐፈ ባሮክ በገድለ ኤርምያስ በዜና ብጹዐን በመጽሐፈ ስንክሳርም ተጽፏል::

❖ በዚህች ዕለት ንጉሡ ሴዴቅያስ ቅዱስ ኤርምያስን አስሮት እያለ ኢትዮዽያዊው ቅዱስ አቤሜሌክ ያስፈታበት (ከረግረግ ያወጣበት) ይታሰባል::

ቸር እግዚአብሔር በኤርምያስ ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት ሕዝቦቿን ከስደትና ከመቅሰፍት ይሰውርልን፤ በረከቱ ረድኤቱ ይደርብን
📌 ከሃዲው መክስምያኖስ ያሠቃየው የኢየሩሳሌሙ ቅዱስ አባ እለእስክንድሮስ ዐረፈ፡፡

📌 ጠመው የምትባለው አገር ኤጲስቆጶስ የሆነው የአባ እንጦንስና የአውሳንዮስ መታሰቢያቸው እንዲሁም መጥምቁ ዮሐንስ የተገለጠላቸው ጋይዮስና ኤስድሮስ ዕረፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡




📌 ሚያዝያ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. አቡነ ሳሙኤል ዘቆየጻ (ኢትዮዽያዊ)

2. ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ

3. ቅዱስ አቤሜሌክ ኢትዮዽያዊ

4. ቅዱስ ባሮክ

5. ቅዱስ እለእስክንድሮስ ዘኢየሩሳሌም



📌 ወርሐዊ በዓላት
1. ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት

2. ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ

3. ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ

4. ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)

5. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

6. አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

7. ቅዱስ ድሜጥሮስ
የሌሊቱ ተማሪ ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በዮሐ. 3÷1 ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ 1÷2) በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው ኒቆዲሞስ “መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርገ የሚችል የለምና።" በማለት ተናገረ።(ዮሐ3፥2) በዚህ ጊዜ ጌታችን የገነት በር ስለሆነው ስለ ምስጢረ ጥምቀት አስፍቶና አምልቶ በምሳሌ ጭምር አስረዳው። "እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” (ዮሐ 3፥3) በማለት መንፈሳዊ እውቀት የጎደለው መሆኑን አሳይቶ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ከእግዚአብሔር መንግሥት ውጪ እንደሚሆን አስርግጦ ነገረው።

በዚህም ታላቅ ምስጢርን ሊገልጥለት ወደደ። ይህ አነጋገር ከአይሁድ አለቆች አንዱ ለሆነው ፈሪሳዊ ሰው ከባድ ነበር። ምሥጢሩም ቢጸናበት ጊዜ ጌታን እንዲህ በማለት ጠየቀው “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንደምን ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማሕጸን ተመልሶ ሊገባ ይችላልን?“። (ዮሐ 3፥4) ጌታችንም ለኒቆዲሞስ መልሶ የአዳም ልጆች ሁሉ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ካልተወለዱ (በመንፈስ ቅዱስ መታደስን በሚያሰጥ ጥምቀት ካልተጠመቁ) መንግሥተ ሰማያትን መውረስ እንደማይችሉ ነገረው።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር!!!

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
"ድኃ በቤትኽ ደጃፍ ይጮኻልን? ተነስተህ በደስታ የቤትህን ደጅ ክፈትለት የድኃውን ልመና ቸል አትበል፡፡ በነፍሱ የመረረው ነውና ቢረግምህ እግዚአብሔር አቤቱታውን ይሰማዋል፡፡ ስለዚህ ይረግምህ ዘንድ ምክንያት አትሁነው አዝኖ ከሆነ በመልካም መስተንግዶ ደስ አሰኘው፡፡ በኀዘን የከበደው ልቡ በአንተ ይረፍ፤ በሕይወት ዘመንህ ማጣት የሚያመጣቸውን ስቃዮች ታውቃቸዋለህና ችግረኛውን ከቤትህ ደጅ አትመልሰው፡፡"

#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶሪያዊ
Forwarded from Dawit Gebeyehu
ጉባኤ ኒቆዲሞስ 222.jpg
756.5 KB
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን

📌 ስንክሳር ዘሚያዚያ ፲፭

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ፲፭ የመጥምቁ ዮሐንስ አንገት ከተቆረጠች በኋላ 15 ዓመት በአየር እየበረረች ስታስምር ኖራ በዚህ ዕለት ዐረፈች፡፡
❖ ዮሐንስ ማለት ‹‹ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ›› ማለት ነው፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው የሐዲስ ኪዳን ደግሞ የመጀመሪያው ነቢይ ነው፡፡



❖ መጥምቁ ዮሐንስ ጌታችንን በዕድሜ በ6 ወር ይበልጠዋል፤ ርጉም የሆነ ሄሮድስ መሢሕ ሕፃን ክርስቶስ መወለዱን ሲሰማ መንግሥቴን ይቀማኛል ብሎ በመፍራት በቤቴልሔም ያሉ ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች ያሉ 144,000 (መቶ ዐርባ አራት ሺህ) የቤቴልሔም ሕፃናትን በሰይፍ ሲያስገድል ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ፣ ቅድስት ኤልሳቤጥ ደግሞ ወደ ሲና በረሃ ሄዳ ልጇን ዮሐንስን ከዚያ ደብቃዋለች።


❖ ቅዱስ ዮሐንስና እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ወደ በረሃ ከገቡ አምስት ዓመት በሆናቸው ጊዜ እርሱ ዕድሜው ሰባት ዓመት ከመንፈቅ ከሆነው በኋላ እናቱ ኤልሳቤጥ ሞተችበትና ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ተወችው፡፡


❖ ዮሐንስም በሰፊዋ በረሃ ውስጥ በአራዊቶች መካክል ብቻውን ቀረ፤ ለዮሐንስ ግን በእርሱ ላይ ምንም መጥፎ ነገር ሳያደርጉ የቶራና የአንበሳ፣ የነብርም ልጆች እንደ ወንድምና እንደ እኅት ሆኑት፡፡

❖ አራዊቶችም ሁሉ ወዳጅ ሆኑት እንጂ፤ ምግቡም የበረሃ ቅጠል ነው፤ መጠጡም ከተቀመጠባት ድንጋይ ሥር የምትፈልቀው ውኃ ነበረች፡፡


❖ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችንን መንገድ ለመጥረግ ለእስራኤል መምህር ሆኖ እስከተገለጠ እስከ 30 ዘመኑ ድረስ የሰውን ፊት እንኳን ከቶ ሳያይ በበረሃ ብቻውን ከአራዊት ጋር ኖረ፡፡


❖ ጌታችንም 30 ዓመት በሆነው ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ለእስራኤል ተገልጦ በማስተማርና የንስሓን ጥምቀት በማጥመቅ የጌታን መንገድ ጠረገ፤ ክፉዎችን ከክፋታቸው እንዲመለሱ በግልጽ የሚገስጽ ሆነ፡፡


❖ የሄሮድያዳ ልጅ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገ፤ ‹እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት› እንዲህም እያለ ‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ› እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡


❖ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ልመና ከአፏ በሰማ ጊዜ ‹የፈለግሽውን እሰጥሻለሁ› ብሎ በሕዝቡ ፊት ስለማለ ለሰው ይምሰል አዘነ፣ ተከዘ፤ ኃዘኑም ስለ ዮሐንስ መሞት አይደለም፣ ዮሐንስን ሕዝቡ ይወደው ስለነበር እነርሱን ስለ መፍራቱና መሐላ ምሎ ከዳ እንዳይባል ነው እንጂ፤ ስለ ዮሐንስ አዝኖ ቢሆን ኖሮ ቀድሞውንም በግፍ እንዲታሰር ባላደረገው ነበር፡፡


❖ ከዚህ በኋላ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሄዱ፤ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ ጭፍሮች ሊገድሉት እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡

❖ የሄሮድስን ቃል እንዳያቃልሉ ጭፍሮቹም የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስን አንገት ስለ መሐላው ቆረጡት፤ በመሐላ ምክንያት ባይሆን ኖሮ ሄሮድስ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ባላስገደለው ነበር፡፡


❖ ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ_ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች፤ ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት።



❖ ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት፤ በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

📌 ቅዱስ ጊዮርጊስ በተአምራቱ ያሳመናት የከሃዲው ንጉሥ የዱድያኖስ ሚስት እለእስክንድሪያ በሰማዕትነት ዐረፈች፡፡

❖ ይህችውም ቅድስት እለእስክንድርያ የሰማዕታት አለቃ ታላቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ በትምህርቱና በተአምራቱ ያሳመናትና በጌታችን ስም ሰማዕትነትን የተቀበለች የንጉሡ የዱድያኖስ ሚስት ናት፡፡

❖ ከሃዲውና ጣዖት አልምላኪው ባሏ ንጉሥ ዱድያኖስ ከ70 ነገሥታት ጋር ሆኖ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሦስት ጊዜ ገድሎት ጌታችን ከሞት ካስነሣው በኋላ ንጉሡ መልሶ ያባብለው ጀመር፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም ንጉሡን ዱድያኖስን ከነጣዖታቱ በሰው ሁሉ ፊት ሊያዋርደው ፈልጎ እንዲህ አለው።

✍️‹‹ለጣዖትህ ከሰገድኩና ከሠዋሁለት በመንግሥትህ ሁሉ ሁለተኛ አድርገህ እንደምትሾመኝ የነገርከኝ ነገር ደስ አሰኝቶኛልና በሰው ሁሉ ፊት ለምታመልከው ለአጵሎን እሰግድ ዘንድ ሕዝቡም ሁሉ ለጣዖትህ ስሠዋ ይመለከቱ ዘንድ እንዲሰበሰቡ በአዋጅ ነገር›› አለው፡፡

❖ ንጉሡም ቅዱስ ጊዮርጊስ የነገረው እውነት መስሎት እጅግ ተደስቶ እስኪነጋ ድረስ ብሎ ቅዱስ ጊዮርጊስን ወደ ሚስቱ እልፍኝ አስገባው፤ የንጉሡም ሚስት እለእስክንርያ ብቻዋን ከቅዱስ ጊዮርጊስ በተገናኘች ጊዜ ሰማዕቱ የዳዊትን መዝሙር ሲጸልይ ሰማችው፤ ጸሎቱንም ሲጨርስ ይጸልይ ስለነበረው ነገር ጠየቀችው፡፡

✍️‹‹ክርስቶስ ብለህ የጠራኸ እርሱ ማነው›› አለችው፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም ይህን ጊዜ ስለ ጌታችን ለንግሥቲቱ አስተማራት፤ ከብሉይና ከሐዲስም መጻሕፍትን እየጠቀሰ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ እነርሱ እስካሉበት ዘመን ድረስ ያለውን የሃይማኖትን ነገር በሚገባ አስተማራት፡፡

❖ ንግሥቲቱም ‹‹በአምላክህ አምኛለሁና ስለ እኔ አምላክህን ለምንልኝ›› አለችው፤ ስለ ክፉው ባሏ ስለ ንጉሡ እንዳትፈራ አጽናናትና ሲሰግድ ሲጸልይ አደረ፤ በነጋም ጊዜ ነጉሡ አስቀድመው በተነጋገሩት መሠረት መጥቶ ለጣዖቱ እንዲሰግድና እንዲሠዋ ለቅዱስ ጊዮርጊስ መልዕክት ላከበት፡፡
"ጌታ ሆይ አንተን ምን ብሎ መጥራት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ጌታ ሆይ እናትህን ድንግል ብለን እንጥራትን? እንዲያ ብለን እንዳንጠራት የአንተ እናት መሆኑዋ ምስክር ይሆንብናል፤ ጌታ ሆይ እናት እንበላትን? እንዲህ እንዳንል ወንድ የማታውቅ ድንግል ናት፤ የእናትህ ነገር ለመረዳት የረቀቀ ከሆነ አንተን ሊረዳ የሚችል ሰው ማን ነው?"

ቅዱስ ኤፍሬም
Forwarded from Zemen Asnake
Forwarded from Bketa @¥
2024/06/30 21:58:02
Back to Top
HTML Embed Code: