Telegram Web Link
እንኩዋን ለጻድቁ አባታችን "ቅዱስ መርቄ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" ጻድቁ ቅዱስ መርቄ "*+

=>ቅዱስ መርቄ በሁለት ዓለም የተሳካለት ደግ ሰው ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

+ቅዱሱ በዓለም የሚኖር ታዋቂ ነጋዴ ነው:: ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እንደ አስቸጋሪ ከሚታዩ የሥራ ዘርፎች አንዱ የንግድ ሥራ ቢሆንም እርሱ ግን "ቅዱሱ ነጋዴ" ለመባል በቅቷል::

+ለዚህም ምክንያቱ 2 ነገሮች ናቸው:-
1.በንግድ ሕይወቱ ማንንም ሳያጭበረብር ከመኖሩ ባለፈ ፍጹም ጸሎትን ጾምንና ምጽዋትን ያዘወትር ነበር::
2.ለንግድ በተዘዋወረባቸው ሃገራት ሁሉ ስለ ክርስቶስ ያለማቁዋረጥ የሚሰብክ በመሆኑ በርካቶችን አሳምኖ ሐዋርያዊ ክብርን አግኝቷል::

+ቅዱስ መርቄ በሕይወቱ ይሕንን ከፈጸመ በሁዋላ አንድ አረማዊ ጉዋደኛ ነበረውና : ሐብት ንብረቱን ሰብስቦ "ጌታችን ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለ ለርሱ ስጥልኝ" ብሎ ላከው::

+አረማዊው ጉዋደኛውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ግርማ አግኝቶ ንብረቱን ከእጁ ተቀብሎታል::

+አረማዊውም በዚህ ምክንያት ከ75 ቤተሰቦቹ ጋር አምኖ ተጠምቁዋል:: ቅዱስ መርቄ በርሃ ውስጥ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዳዊት ከሰማይ ወርዶ ዘምሮለታል:: መላዕክት በምስጋና ገንዘውት አንበሶች ቀብረውታል::

=>አምላክ ከቅዱሱ በረከትን ያድለን::

=>ሚያዝያ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መርቄ ጻድቅ (ክርስቲያናዊ ነጋዴ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
3.አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ
4.እግዚአብሔር:- በእግር የሚራመዱ : በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ : በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታትን ፈጠረ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

=>+"+ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:14-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† ሚያዝያ ፬†

† ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት) †

=>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ አራት በዚች ቀን የከበሩ ፊቅጦርና ዳኬዎስ ኤርሞ ሌሎችም ብዙዎች ሰዎች ሴቶችና ወንዶች ደናግሎች በሰማዕትነት ሞቱ።

እሊህም ቅዱሳን በታላቁ ቈስጠንጢኖስና በልጁ ዘመነ መንግስት የጣዖታትን ቤቶች አፍርሰው ጣዖታትንም ሰብረው አቃጥለው በቦታቸውም አብያተ ክርስቲያናትን ሠርተው አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሌሎችም በብዙዎች ቅዱሳን ስም ታቦቱን ሰይመው ነበር።

ከሀዲ ዮልያኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖትን አምልኮ አቆመ የጣዖቱንም ካህናቶች አከበራቸው ብዙዎች ክርስቲያኖችንም አስገደለ።

የእሊህ ቅዱሳን ዜናቸው አስቀድሞ በጣዖታት ቤቶች ላይ ያደረጉት ጣዖታትን እንደሰበሩ ሁሉ ተሰማ።ይዘውም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩአቸው ብዙ ቀንም ሲሰቅሏቸውና ሲገርፉአቸው ቆዳቸውንም በሾተል ሲነጥቁ ኑረው በኃላም ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ቆረጡ።

በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ በረከታቸው ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

=>ሚያዝያ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት=
1.እግዚአብሔር የሰው ልጅን ፈጠረ
2.ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሐ (ጻድቃን ነገሥት)
3.ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊው)
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
5. ቅዱስ አቡነ አሮን መንክራዊ

=>+"+ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ:: በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው:: ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው . . . እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ:: እነሆም እጅግ መልካም ነበረ:: +"+ (ዘፍ. 1:26-31)

†ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
#በስድብ_ፈንታ_አመስግኑ

ብዙ ጊዜ ስንሳደብ እና መጥፎ ቋንቋ ስንጠቀም “እኔ ይህን አለማድረግ አልችልም ልማዴ ነው" እንላለን፡፡ እናም ሲጎዱን አንድ ነገር መናገር ካለብንም፣ በስድብ ፈንታ ምስጋና መናገርን እራሳችንን እናስተምር።

ነገር ግን፣ ሰው እያሰቃየኝ ዝም ማለት አልችልም ትላለህ፡፡ ከመናገርም አልከለክልህም፡፡ ሆኖም ከመሳደብ ይልቅ ምስጋናን ተናገር፡፡ ከመበሳጨት ይልቅ ምስጋናህን ግለጽ፡፡

ለጌታህ መናዘዝ ትችላለህ፡፡ በጸሎትህ ውስጥ ጩኽ፤ እንዲሁ መከራህን ያቀልልሃል፣ ፈታኙም ሰይጣን በምስጋናህ ውስጥ ይሸሻል፣ የእግዚአብሔርም እርዳታ ወዳንተ ይቀርባል። ከተሳደብክ፣ የእግዚአብሔርን ስጦታ ትከለክላለህ፤ እናም ፈታኙ በአንተ ላይ እንዲበረታ ታደርጋለህ፤ በዚያም እራስህን የበለጠ በህመም ውስጥ ታስገባለህ፡፡ ብታመስግን ግን የክፉ መንፈስን ጥቃት ትቃወማለህ፡፡

ነገር ግን ምላስ ብዙውን ጊዜ በልማድ ኃይል አንዳንድ መጥፎ ቃላትን ከመናገር ወደኋላ ማለት አይችልም:: ከዚያም በምትወድቅበት ጊዜ ኹሉ ቃሉ ከመናገርህ በፊት ጥርሶችህን ጠብቀው ይዘጉ፡፡ ምላስህ የደም ጠብታ ብታፈስስ ይሻላታል ፤ ከስድብም በኋላ የማያቋርጥ ቅጣት ከምትቀበል በጊዜው ሥቃይን ብትታገሥ ይሻልሃልና፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
                      አሜን

🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዚያ ፮

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ፮ አባታችን ቅዱስ አዳምና እናታችን ቅድስት ሄዋን ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡

❖ አባታችን አዳም የመጀመሪያው ፍጥረት (በኩረ ፍጥረት) ነው፤ አባታችን አዳም
❖ በኩረ ነቢያት
❖ በኩረ ካኅናት
❖ በኩረ ነገሥትም ነው::

❖ በርሱ ስሕተት ዓለም ወደ መከራ ቢገባም ወልድን ከዙፋኑ የሳበው የአዳም ንስሃና ፍቅር ነው::

❖ አባታችን ለ100 ዓመታት የንስሃ ለቅሶን አልቅሷል፤ ስለዚህ አባታችን አዳም ቅዱስ ነው፤ ከሌሎቹ ቅዱሳን ቢበልጥ እንጂ አያንስም::

❖ ለአባታችን አዳም የተናገርነው ሁሉ ለእናታችን ሔዋንም ገንዘቧ ነው፤ ዛሬ የሁለቱም የዕረፍታቸው መታሠቢያ ነው::

አምላካችን እግዚአብሔር ለሰማይ ለምድሩ በቅድስናቸው ከከበዱ ወዳጆቹ በረከትን ረድኤት ያድለን፤ በጸሎታቸው ይጠብቀን።

🛎 በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጉኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሳትህን አመንኩ አለ።

❖ ጌታችንም ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት፤ በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኀኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች ።

በረከቱ ረድኤቱ ይደርብን

🛎 በዚች ቀን በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያም አረፈች፤ ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ሁና ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው።

❖ እድሜዋ አስራ ሁለት አመት በሆናት ጊዜ የመልካም ስራና የሰው ሁሉ ጠላት ሸንግሎ አሳታት በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ እርሱ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና ።

❖ በዚህም በረከሰ ስራ ውስጥ ኖረች በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር፤ ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት።

❖ ከእሳቸውም ጋራ ትሄድ ዘንድ ልቧ ተነሳሳ ከብዙ ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች፤ ባለ መርከቦችም የመርከብ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው ኢየሩሳሌምም እስከ ደረሰች ይህን ስራ አልተወችም።

❖ የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት።

❖ እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም።

❖ ከዚህም በኃላ ስለ ረከሰ ስራዋ አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሔር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስእል አየች፤ በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጅአቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ እኔ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት።

❖ ቤተክርስቲያን ፈጥና ገባች በገባችም ጊዜ የበአሉን ስራ ፈፀመች፤ ከዚህም በኃላ አምላክን ወደ ወለደች ወደ እመቤታችን ወደ ከበረች ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ ወደ እርሷ መሪር ልቅሶ እያለቀሰች ረጅም ፀሎትን ፀለየች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ከዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ እረፍትንና ድኀነትን ታገኚ አለሽ የሚል ቃል ወጣ።

❖ ከእመቤታችን አምላክን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ይህን ቃል ተቀብላ ወድያውኑ ወጣች፤ በውጪም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ግርሽ ሰጣትና አምባሻ ገዛችሸት።

❖ ከዚያም በኃላ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት አመት ኖረች ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር፤ እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች ከዚያም ከገዛችው አምባሻ ብዙ ቀን ተመገበች፤ ሁለት ሁለት ቀን ሶስት ሶስት ቀን ፁማ ከዚያ አምባሻ ጥቂት ትቀምስ ነበር በአለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች።

❖ በዚያችም በዮርዳኖስ በረሀ እየተዘዋወረች አርባ አባት አመት ሲፈፀምላት እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ቅዱስ ዘሲማስ ወደዚያች በረሀ መጣ፤ በሱ ደብር ላሉ መነኲሳት ልማዳቸው ስለሆነ በየአመቱ ወደ በረሀ ወጥተው የከበረች የአርባ ቀን ፆም እስከ ምትፈፀም በፆምና በፀሎት ተፀምደው በገድል ይቆያሉ ።

❖ ስለዚህም ዘሲማስ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚፅናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው፤ በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሀት መሰለችው በፀለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት፤ ወደ ርሷም ሄደ እርሷ ግን ከእርሱ ሸሸች ወደርሷም ይደርስ ዘንድ ከኃላዋ በመሮጥ ተከተሉት።

❖ ከዚህም በኃላ ዘሲማስ ሆይ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ እከለልበት ዘንድ ብላ በስሙ ጠራችው።

❖ በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት እርስ በርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጥተው በላዩዋ ይፀልይላት ዘንድ ለመነችው እርሱ ካህን ነውና ካህን ሰለሆነ።

❖ ከዚህም በኃላ ገድሏን ታስረዳው ዘንድ ቅዱስ ዘሲማስ ለመናት ከእርሷ የሆነውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው።

❖ እርሷም በሚመጣው አመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እሺ አላት።

❖ አመትም በሆነ ጊዜ ስጋውንና ደሙን በፅዋ ውስጥ ያዘ ደግሞ በለስ ተምርንና በውኃ የራሰ ምስርን ይዞ ወደርሷ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ቅድስት ማርያምን በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ስትሄድ አያት ወደርሱም ደርሳ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ በአንድነትም ፀለዩ ከዚህም በኃላ ስጋውንና ደሙን አቀበላት።

❖ በለሱን ተምሩንና ምስሩንም አቀረበላትና ትመገብለት ዘንድ ለመናት ስለ በረከት ከምስሩ በእጇ ጥቂት ወሰደች፤ ደግሞም በሁለተኛው አመት ወደእርሷ ይመለስ ዘንድ ለመነችው ።

❖ ሁለተኛ አመትም በሆነ ጊዜ ወደዚያ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ያቺ ቅድስት ሴት ሙታ አገኛት በራስጌዋም ድኀዪቱን ግብፃዊት ማርያምን ከተፈጠረችበት አፈር ውስጥ ቅበራት የሚል ፅሁፍ አገኘ፤ ከፅሁፉ ቃልም የተነሳ አደነቀ።

❖ ያን ጊዜም ከግርጌዋ አንበሳን ሲጠብቃት አየ እርሱ መቃብርዋን በምን እቆፍራለሁ ብሎ ያስብ ነበር በዚያም ጊዜ ያ አንበሳ በጥፍሮቹ ምድሩን ቆፈረ የከበረ ዘሲማስም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት ።

❖ ወደ ገዳሙም ተመልሶ ለመነኮሳቱ የዚችን የከበረች ግብፃዊት ማርያምን ገድሏን እንዳስረዳችው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገራቸው እጅግም አደነቁ ምስጉን ልኡል እግዚአብሔርንም አመስገኑት፤ መላው እድሜዋም ሰማንያ አምስት ሆኗታል።
‹‹ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው››  ቅዱስ  ያሬድ
      
  ሚያዚያ ፬፤፳፻፲፮ ዓመተ ምሕረት
 
ከማንም አስቀድሞ አገልግሎት ለአምላካችን እግዚአብሔር ይገባል፤ በጥንተ ተፈጥሮ በመጀመሪያው ቀን የተፈጠሩት መላእክት ፈጣሪያቸውን ዘወትር ያለማቋረጥ ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያሉ እንደሚያመሰግኑት ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመጽሐፈ አክሲማሮስ ገልጾልናል፡፡ (አክሲማሮስ ዘእሑድ) በዕለተ ዓርብ ሰው ሲፈጠር እንደ መላእክቱ የፈጠረውን ጌታውን እንዲያመሰግን፣ እንዲያገለግል እንዲሁም ስሙን እንዲቀድስና ክቡርን እንዲወርስ በመሆኑም የቀደመ ሰው አዳምም አምላኩን እያመሰገነና በገነትም በጸሎት እየተጋ ኖሯል፡፡      
 
በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ተመዝግቦ እንደምናገኘው ጥንተ ጠላት ዲያብሎስ አምላኩን ለማመስገን ባለመፍቀዱ ተረግሞ ወደ ምድር ከተጣለ በኋላ የሰውን ዘር በተለያዩ መንገዶች በማሳት፣ ከቀናው መንገድና ከጽድቁ ጎዳና በማስወጣት ፈጣሪያቸውን እንዳያገለግሉ ያደርጋል፡፡ (ዘፍ.፩-፰፣ አክሲማሮስ ዘዓርብ)   

 
ይህ በእርግጥ አስከፊና አሳዛኝ ቢሆንም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት  ‹‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ›› በማለት እንደ ነገራቸው ምንም እንኳን ጠላታችን መከራ አጽንቶና ተስፋ አስቆርጦ ብኩንና ከንቱ ሊያደርገን ቢጥርም መከራውን አልፈን፣ ሥቃያችንን ተቋቁመንና ችግራችን ተወጥተን በመልካም አገልግሎት ወደ አምላካችን መንግሥት መግባት ይቻለናል፡፡ (ዮሐ.፲፮፥፴፫)
 
መልካም አገልግሎት ለእግዚአብሔር አምላክ በሰውነታችን በበጎነታችን፣ በቅንነታችን፣ በትሕትናችን፣ በዕውቀታችንና በጉልበታችን የምናቅርበው የጸሎት፣ የጾም፣ የምጽዋት፣ የትሩፋትና የፍቅር አገልግሎት ነው፡፡ አምላካችንን ከማመስገን በተጨማሪ ዘወትር እርሱን በመፍራት በዕለት ኑሮአችን ልናስበውና ልናገለግለው ይገባል፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስት ቢሆን ክፋትና ኃጢአት ከመሥራት ርቆ ይኖራልና፡፡ በቅንነትና በትሕትና የተሞላ የማኅበራዊ ሕይወትም ይኖረዋልና፡፡ ለሌሎች ሰዎችም መልካም ከማድረግ አይቦዝንም፡፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ ባካበተው የመንፈሳዊ እና ዓለማዊ ዕውቀት እንዲሁም ባለው ጉልበት አምላኩን ዘወትር ያገለግላል፤ ይህም ተግባሩ ለጌታው የታመነ ታማኝና ቸር አገልጋይ ያሰኘዋል፡፡  
 
በመጽሐፍ ቅዱስ የሐዲስ ኪዳን ክፍል ወንጌል ላይ ቅዱስ ማቴዎስ የጻፈውን አንድ ታሪክ እናንሣ፤ ‹‹አንድ ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ባለጸጋ ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤  ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት፣ ለአንዱ ሁለት፣ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድር ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።››
 
ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ “ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት” አለ። ጌታውም “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው።
 
ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ “ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት” አለ። ጌታውም “መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው።
 
አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ “ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ” አለ። ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ “አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁበት እንዳጭድ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፤ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት፤ ዐሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳን ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።›› (ማቴ.፳፭፥፲፬-፴)
 
ባለ ጸጋ የተባለው ጌታችን ነው፡፡ መክሊት የተባለው ደግሞ ከአምላካችን የተጠን የተለያዩ የአገልግሎት ጸጋዎች ናቸው፡፡ በታማኝነት ያገለገሉት ሰዎች ምሳሌ በምድራዊ ሕይወታቸው በተሰጣቸው ጸጋ በትጋት አምላካቸውን አገልግለው በመልካም ዕረፍት ገነት የገቡት ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፤ መክሊቱን የቀበረው ሰነፍ አገልጋይ ደግሞ በተሰጣቸው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል  ሲገባቸው ያላገለገሉ ሰዎች ምሳሌ ነው፡፡
 
ጌታቸው ሊቆጣጠራቸው የመምጣቱ ነገር ጌታችን በዕለተ ምጽአት ለፍርድ ሲመጣ ለሁሉም በሠራው ሥራ መጠን ዋጋ ለመስጠት እንደሚመጣ የሚያመለክት ነው፡፡ ያገለገሉትን ታማኝ አገልጋየችም ለእያንዳንዱ  ‹‹ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!››  ማለቱ ታማኝ አገልጋዮች መንግሥተ ሰማያትን እንደሚወርሱ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ሰነፉ አገልጋይ ወደ ጨለማና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ቦታ መወርወሩም ኀጥአን ወደ ገሃነመ እሳት መጣላቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
 
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው›› በማለት የተናገረው ይህን የወንጌል እውነት የሚገልጽ ነው፡፡ ታማኝነትና ቸርነት ለአገልግሎታችን እጅጉን አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ታማኝ መሆን ያለ ጥርጥርና በፍጹም እውነት ለአምላካችን መገዛት፣ መታዘዝና መኖር እንዲሁም በሕጉ መኖር ነው፡፡ ይህም ለእርሱ ታምነን ያለ ሐሰት፣ ያለ ስርቆት፣ ያለ አመንዝራነት እና ያለ ክህደት ወዘተ. እንድንኖር ይረዳናል፡፡ በተሰጠንም ክሂሎት፣ ተሰጥኦና ትሩፋት ማገልገል ያስችለናል፡፡ በአንደበታችን እንድናመሰግናው፣ በእጆቻችን አጨብጭበን፣ በጣቶቻችን በገና ደርድረንና መሰንቆ መትተን እንድንዘምርለት፣ በጉልበታችን እንድንሰግድለት በልባችን እንድናፈቅረው አስተምሮናል፡፡   
 
ቸር በመሆን ለሌሎች በለጋስነት ካለን ነገር በመስጠትና በማካፈል መኖርን አሳይቶናል፡፡ አንድ ዳቦ ያለው ግማሹን ለሌላው እንዲያካፈል፣ ሁለት ልብስ ወይም ጫማ ያለው ለሌለው እንዲሰጥ፣ ከማዕዳችን ለተራቡ እንድናበላ፣ ከማድጋችን ለተጠሙ እንድናጠጣ፣ ለተቸገሩትና ላዘኑት ቸርነት በማድረግ እንድናስተዛዝን፣ የታመሙትን እንድናስታምም የአምላካችን ቅዱስ ቃል ያዘናል፡፡ እኛም እንደ መልካም ልጆቹ ለእርሱ በመታዘዝ ታማኝና ቸር አገልጋይ እንሁን!
 
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነትና ረድኤት አይለየን፤ አሜን!    

👉 በማኅበረ ቅዱሳን
Forwarded from Bketa @¥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
                          አሜን

      🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዚያ ፯

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሚያዝያ ፯ በዚች ቀን የእመቤታችን አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም አባትዋ ጽድቅ ኢያቄም አረፈ።

❖ ቅዱስ ሰው ኢያቄም የሰማይና የምድር ንግስት እመቤታችን ድንግል ማርያም አባት ነው::

❖ ቅዱሱ ከቅስራ አባቱ የተወለደ የቅዱስ ዳዊት ዘመድ ሲሆን "ኢያቄም ሳዶቅ እና ዮናኪር" በሚባሉ 3 ሰሞቹ ይታወቃል።

❖ ቅዱስ ኢያቄም እንደ ኦሪቱ ሥርዓት አድጎ ከነገደ ሌዊ የተወለደች የማጣትና ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) ሔርሜላን ልጅ ሐናን አግብቷል፤ ሁለቱም በንጽሕናና በምጽዋት እንደ ሕጉ ቢኖሩም መውለድ የማይችሉ መካኖች ነበሩ።

❖ በዚሕ ምክንያት ከወገኖቻቸው ሽሙጥን ታግሰው በታላቅ ሐዘን ኑረዋል፤ ከጊዜ በሁዋላ ግን ስም አጠራሯ የከበረ ደም ግባቷ ያማረ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር መረጣቸውና ከተባረከ ሰውነታቸው ድንግል ማርያምን ወለዱ፤ እርሷ "ወላዲተ አምላክ" ተብላ እነርሱን "የእግዚአብሔር የሥጋ አያቶች" አሰኘቻቸው::

❖ ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችንን ቤተ መቅደስ ካስገቡ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ በመልካም ሽምግልና አርፎ ከቅድስት ሐና ጋር በጌቴሴማኒ ተቀብሯል::

❖ ቅዱሱ ሰው ያረፈበት ዓመት ግልጽ ባይሆንም ድንግል እመቤታችን 8 ዓመት ሲሞላት 2ቱም ቅዱሳን ወላጆቿ በሕይወተ ሥጋ እንዳልነበሩ አበው ነግረውናል፤ በማረፍ ደግሞ ቅድስት ሐና ትቀድማለች፤ መቃብሩ ዛሬ ድረስ አለ፤ ያደለው ከቦታው ደርሶ ይሳለመዋል::

አምላካችን ከቅዱስ ኢያቄም በረከት ረድኤት ያሳትፈን፤ በጸሎቱ ይማረን
📌 ሚያዝያ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱስ ኢያቄም (የድንግል ማርያም አባት)
2. ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት
3. ቅድስት ቴዎድራ ሰማዕት
4. ቅዱስ አባ መቅሩፋ ጻድቅ

📌 ወርኃዊ በዓላት
1. ሥሉስ ቅዱስ
2. አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
3. አባ ሲኖዳ
4. አባ ዳንኤል
5. አባ ባውላ
6. ቅዱስ አትናቴዎስ
7. ቅዱስ አግናጥዮስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
                       አሜን


🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዚያ ፰



አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ፰ ሦስቱ ቅዱሳት ደናግል አጋሊስ፣ ኤራኒና ሱስንያ በሰማዕትነት ዐረፉ።
❖ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት መቶ ሃምሳ ሰዎች በፋርስ ንጉሥ እጅ በአንዲት ቀን ሰማዕትነትን ተቀበሉ። 
❖ የከበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጢሞቴዎስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ነው። 

  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
     ቅዱሳት ደናግል
  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ቅዱሳት ደናግሉ አጋሊዝ (አጋሊስ)፣ ኢራኒና ሱስንያ ይባላሉ፤ በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ተሰሎንቄ የምትባል ሃገር ውስጥ ይኖሩ ነበር።

❖ ሦስቱም እጅግ ቆንጆዎችና ከብዙ ወንዶች ዓይን የሚገባ መልክ ቢኖራቸውም የእነርሱ ምርጫ ግን ሰማያዊ ሙሽርነት ነበርና በጾምና በጸሎት ተወሰኑ፤ ለብዙ ዓመታትም ደናግሉ በሚኖሩበት ደብር ውስጥ በቅድስና ኑረዋል።

❖ ከቆይታ በኋላ ያ የመከራ ዘመን (ዘመነ ሰማዕታት) ሲመጣ ለጊዜውም ቢሆን ወደ በርሃ ሸሽተው ተቀመጡ፤ ያሉበትን ቦታ የምታውቅ አንዲት ደግ ባልቴት እየሔደች ትጎበኛቸው በእጃቸው የሚሠሯቸውን የተለያዩ እቃዎችንም እየሸጠች እኩሉን በስማቸው መጽውታ በተረፈው ለራት የሚሆን ደረቅ ቂጣ ትገዛላቸው ነበር።
❖ አንድ ቀን ግን አንድ አረማዊ ሰው ተከትሏት መጥቶ በማየቱ ሦስቱንም ደናግል ወደ ከሐዲው ንጉሥ አቀረባቸው።

❖ ንጉሡ ሃይማኖታቸውን ቢክዱ የሃብትና የሥልጣን ተስፋ እንዳላቸው ነገራቸው፤ ደናግሉ ግን በፍቅረ ክርስቶስ በመጽናታቸው ከብዙ ስቃይ በኋላ በዚህች ቀን አስገድሏቸዋል፤ የጌታችን በጐ ምሕረቱ በሁላችን ትደርብን።

ከደናግሉ በረከትን ረድኤት ያሳትፈን፤ በጸሎቱ ይማረን
  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
  መቶ ሃምሳ የፋርስ ሰማዕታት

❖ የፋርስ ንጉሥ ለአገሩ ቅርብ የሆነ ክርስቲያንን አገር ከበበና ብዙ የሰው ምርኮ ማርኮ ወደ አገሩ ወሰዳቸው።

❖ በዚያም ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትንም ያመልኩ ዘንድ አስገደዳቸው፤ እነርሱ ግን ጣኦታትን አናመልክም ባሉት ጊዜ የሁሉንም ራስ ራሶቻቸው ሚያዝያ 8 አስቆረጧቸው።

❖ ሰማዕታቱም የመንግሥተ ሰማያትን የሕይወትን አክሊል ተቀበሉ።


       ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ቅዱሳት ደናግል አጋሊስ፣ ኤራኒና ሱስንያ
     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ እነዚህም ቅዱሳን ከሰሎንቄ አገር የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያመልኩ ናቸው፤ ወላጆቻቸው እግዚአብሔር የሚፈሩ ነበሩ።

❖ እነዚህም ቅዱሳት ደናግል በድንግልና በንጽሕና መኖርን ወደው በአንድ ምክር ተስማሙ ጽኑዕ በሆነ ገድልም ተጠመዱ ይልቁንም ያለማቋረጥ ተግተው ይጸልዩና ይጾሙ ነበር፤ በገዳምም ከመነኰሳት ጋራ ያገለግላሉ።
❖ ከሀዲው መክስምያኖስ በነገሠ ጊዜ የጣዖታትን አምልኮ በማስፋፋት የንጹሓንን ደም በከንቱ አፈሰሰ።

❖ እነዚህም ደናግል በዚህ ወቅት ወደ ተራራ ሸሽተው በመውጣት በዚያም በዋሻ ውስጥ ተቀምጠው በጾምና በጸሎት በዋሻው ውስጥ ኖሩ።

❖ አንዲት የክርስቲያን ወገን የሆነች ሴትም በየሰባት ቀን ትጐበኛቸውም ነበር፤ የሚያሻቸውንም ትሰጣቸዋለች፤ የእጅ ሥራቸውን ትሸጥላቸውና ከእነርሱ የሚተርፈውን ትመጸውታለች።

❖ አንድ ቀን የሆነ ሰው ከከተማ ወጥታ ወደ ተራራ ስትሔድ አያትና ሳታየውም ተሠውሮ በሩቅ ተከተላት ወደ ዋሻውም እስከምትገባ ተመለከተ።

❖ ከዚያ እስከምትወጣ ተሰውሮ ቆየ በዚያ ቦታ ብዙ ገንዘብ ያላት መስሎታልና፤ ያቺ ሴትም ከዋሻው በራቀች ጊዜ ያ ሰው ገባና ለክብር ባለቤት ሙሽሮቹ የሆኑ የከበሩ አዕናቊ ደናግልን ቁመው ሲጸልዩ አገኛቸው።

❖ ከዚያም ተሰሎንቄ ከተማ እስኪያደርሳቸውም አሥሮ ጐተታቸው፤ ከሃዲው መኰንንም ሃይማኖቻውን በጠየቃቸው ጊዜ ስለ እርሳቸው የተሰቀለ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያመልኩ ክርስቲያኖች እንደሆኑ በፊቱ አመኑ፤ መኰንኑም ተቆጥቶ ይገርፏቸው ዘንድ አዘዘ።

❖ የሚአሠቃይ ጽኑ ግርፈትም ገረፋአቸው፤ ዳግመኛም ባልታዘዙና ወደ ክህደቱ ባልገቡ ጊዜ ወደ እሳት እንዲጨምሯቸው አዘዘ።

❖ በእሳትም ውስጥ በጣሏቸው ጊዜ ነፍሳቸውን ሚያዝያ 8 ቀን ሰማዕትነታቸውን ፈጽመው በመንግሥተ ሰማያትም የሕይወትን አክሊል ተቀዳጁ።

የከበረች በረከታቸው ረድኤታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር፤ በጸሎታቸው ይማረን

📌 ሚያዝያ 8 ቀን የሚከበሩ
ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱሳት ደናግል አጋሊዝ፣ ኢራኒና ሱስንያ
2. "150" ቅዱሳን ሰማዕታት (ፋርስ (ኢራን) ውስጥ የተሰየፉ)
3. አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት

📌 ወርሐዊ በዓላት
1. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2. ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳት
3. አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4. አቡነ ኪሮስ
5. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
††† እንኳን ለብጹዐን ጻድቃን: ቅዱስ ዞሲማስ እና አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ብጹዐን ጻድቃን †††

††† በዚህ ቀን ብሔረ ብጹዐን ውስጥ የሚኖሩ ጻድቃን ይታሠባሉ::
በሃይማኖት ትምሕርት 5 ዓለማተ መሬት አሉ:: እነሱም አቀማመጣቸው ቢለያይም ከላይ ወደ ታች:-
1.ገነት (በምሥራቅ)
2.ብሔረ ሕያዋን (በሰሜን)
3.ብሔረ ብጹዐን (ብሔረ - አዛፍ - እረፍት) {በደቡብ}
4.የእኛዋ ምድር (ከመሐል) እና
5.ሲዖል (በምዕራብ) ናቸው::

††† ከእነዚሕ ዓለማት ባንዱ የሚኖሩ የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን:-
*ኃጢአትን የማይሠሩ::
*ለ1,000 ዓመታት የሚኖሩ::
*ሐዘን የሌለባቸው::
*በዘመናቸው 3 ልጆችን ወልደው (2 ወንድና አንድ ሴት) ሁለቱ ለጋብቻ: አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት የሚያውሉ ሰዎች ናቸው::

††† ቅዱሳኑ ወደዚሕ ቦታ የገቡት በነቢዩ ኤርምያስ እና በቅዱስ እዝራ ዘመን ሲሆን አንዴ የተወሰኑት በዘመነ ሰማዕታት ወጥተው በዚሕ ቀን ተሰይፈዋል::

††† በመጨረሻ ግን በሐሳዌ መሲሕ ዘመን ወጥተው ሰማዕትነትን ይቀበላሉ::

††† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረቱና ይቅርታው ለምናምን ሁሉ ይደረግልን:: ከደግነታቸውም በረከትን አይንሳን::

+*" አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ "*+
=>አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ :
እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ
ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት
ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ "ስብሐት ለአብ
: ስብሐት ለወልድ : ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው
አመስግነዋል፡፡
+የስማቸው ትርጓሜ "የአብ : የወልድ : የመንፈስ ቅዱስ
እስትንፋስ" : አንድም "የክርስቶስ እስትንፋስ" ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ
እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን
ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት
ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው
ዐውቀዋል፡፡
+በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ
ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን
ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ
መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን
ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት
እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት : ለአባቶች
መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን
በማውጣት አገልግለዋል፡፡
+አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት
ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው
ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና
ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት
ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ
ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና
ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተ ክርስቲያን
አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመስዋዕት
ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋል፡፡
+አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል
ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡
ጌታንም በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ
መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ
ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ
ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ ሁሉንም የኢትዮጵያን
ቅዱሳት ገዳማትንም ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ
የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው
ነበር፡፡
+ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን
እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያስነሱ
ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ
ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው
የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ
ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን
ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት
የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
+ጻድቁ ወደ ደብረ አስጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ
ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
አውግዤሻለሁ፡፡ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ
አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን
አቁመዋል፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አስጋጅ ሲደርሱ
ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ
ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት
ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት
አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡
+በአምላክ ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ፣
በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ
መልክአ ኢየሱስ ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤
እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል
ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች
በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ
የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡
በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት
ይደግማሉ፡፡
+ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን
ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ
ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔ ዓለምን
የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን
የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም
የሆነች ጸሎት "ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም" ብሎ
የሚጠራጠር ቢኖር ግን መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡
+ጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ታህሳስ 9 ቀን ተወልው
ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ (ገድለ አቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስ)
=>አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ሃገራችንን
ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ሚያዝያ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
3.ቅዱስ ዞሲማስ ገዳማዊ (ብሔረ ብጹዐንን ያየ እና ዜናቸውን የጻፈ አባት)
4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሕጻን ሰማዕት (ገና በ10 ወር ዕድሜው ሰማዕት የሆነ)
5.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
3.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)

††† "ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ::" †††
(1ዼጥ. 1:13-15)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
+++በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን+++

የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ቻናል ተከታታዮቻችን ከዚህ ስር የተለቀቀውን መልእክት አይታችሁና አንብባችሁ የቻላችሁትን ያህል ታደርጉ ዘንድ ሁሉን በሚችል በቸሩ እግዚአብሔር የሁላችን እናት በሆነች በቅድስት ድንግል ማርያም እና በምትወዷቸው ቅዱሳን ሁሉ ስም እንማጸናችኋለን+ 👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Bketa @¥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን

📌 ስንክሳር ዘሚያዚያ ፲
አንድ
አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈ ቅዱስ ስም ሚያዝያ በዚች ቀን የታላቅ አባት የአባ ዕብሎ ረድእ ቅዱስ ይስሐቅ አረፈ።


❖ የዚህን ዓለም ጣዕም ንቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ገብቶ መነኮሰ፡፡

❖ ለታላቁ አባት ለአባ ዕብሎይም ረድእ ሆኖ 25 ዓመታት ሲያገለግለው ኖረ፤ ሥጋውም እስኪደርቅ ድረስ በጽኑ ተጋድሎ ኖረ፤ በቅዳሴና በጸሎት ጊዜ ጸጥታን ገንዘብ አደረገ፡፡

❖ የቁርባን ቅዳሴ ጸሎት እስኪፈጸም ድረስ ሁለት እጆቹን የኋሊት አስሮ ራሱን አዘንብሎ እያለቀሰ ይቆማል፡፡

❖ በረከትን ከእርሱ ሊቀበሉና በጸሎቱ ሊማጸኑ ብዙ መነኮሳት ወደ ቅዱስ ይስሐቅ መጥተው ‹‹ከሰው ለምን ትሸሻለህ›› ቢሉት እርሱም ‹‹ከሰይጣን እንጂ ከሰው የምሸሽ አይደለሁም፤ አንድ ሰው መብራት እያበራ በነፋስ ውስጥ ቢቆም መብራቱ እንደሚጠፋ ሁሉ እኛም በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ ልባችን ብሩህ ሆኖ ሳለ ከሰው ጋር ተገናኝተን እርስ በእርሳችን በተነጋገርን ጊዜ ልባችን ይጨልማል›› ብሎ መለሰላቸው፤ ይኽም ቅዱስ በገድሉ እግዚአብሔርን ደስ አሰኝቶ ሚያዝያ 10 ቀን በሰላም ዐርፏል፡፡

ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን


📌 በዚችም ዕለት ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰብዓኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ገብርኤል አረፈ።

❖ ይህም ቅዱስ የምስር አገር አለቆች ከሆኑት ከልጆቻቸው ውስጥ ነው፤ በግብጽ ባለች በቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያንም ዲቁና ተሾመ ዐዋቂና ጥበበኛም ስለሆነ ጸሐፊ ሁኖ ብዙዎችን መጽሕፍቶች ጻፈ የሚበዙትንም በዐረብና በቅብጥ ቋንቋ ተረጐመ።

❖ ከመሆኑ በፊት ሁሉን አይቶ በመንፈስ ቅዱስ የሚናገር የእግዚአብሔር ጸጋ በላዩ ያደረች ሶርያዊ አባ ዮሴፍ የሚባል አንድ አረጋዊ ሰው ነበረ።

❖ አረጋውያን መነኰሳትና ኤጲስቆጶሳት ወደርሱ ተሰብስበው ለዚች ለከበረች የሊቀ ጵጵስና ሹመት ማን እንደሚሻል ይገልጥላቸውና ይነግራቸው ዘንድ ለመኑት።

❖ እርሱም የታሮይክ ልጅ አንድ ሰው አለ ብሎ መለሰላቸው ምልክቱንም አመለከታቸው መነኰሳቱና ኤጲስቆጶሳቱም በዚህ ወደው ተስማሙ ከዓመተ ሰማዕታትም በስምንት መቶ ዓመት የካቲት ሃያ አንድ ቀን ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

❖ ወደ አስቄጥስ ገዳምም በሔደ ጊዜ መታመንን ጨመረ ይቺም በባስልዮስ ቅዳሴ ፍጻሜ ከመለኮቱ ጋር አንድ ሆነ የምትል ናት፤ መለኮቱ ከትስብእቱ ተጨመረ ብሎ እንዲህ እንዳያስብ መነኰሳቱ ስለፈሩ እኛስ ልማዳችን እንዲህ አይደለም አሉት።

❖ ከብዙ ምርምርም በኋላ ይች ቃል ከሚከተላት ያለ መለያየት ያለ መጨመርና ያለ መደባለቅ ከሚለው ጋራ ተሰራች በበጎ አቀባበልም ተቀብለዋት እስከዚች ቀን ጻንታ ኖረች።

❖ በሹመቱ ወራትም ብዙዎች በጎ ሥራዎች ተሠሩ ሙታንን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይቀብሩዋቸው በውግዘት ከለከለ ሁለተኛም ዕቁባቶችን በእነርሱ ዘንድ ያኖሩትን አውጥተው እንዲሰዱ አወገዘ።

❖ ይህም አባት ስለሙታን ርስትና ስለሌሎች ሥራዎች የሕግና የሥርዓት መጽሐፍን ደረሰ። ከቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትም ብዙዎችን ተረጐመ በዘመኑም ኃምሳ ሦስት ኤጲስቆጶሳትንና ብዙ ካህናትን ሾመ ነገረ ግን ከእርሳቸው አንድ አላድ እንኳ አልተቀበለም።

❖ የግብጽ ንጉሥም በግፍ ከእርሱ ገንዘብ ሽቶ አሠቃየው እንዲጠባበቁትም ሰላዮችን በላዮ አኖረ፤ ጸሐፊዎችና ሹሞች ከሕዝቡም ታላላቆች ከሕዝቡም ሆነ ከአብያተ ክርስቲያናት ወይም ከገባሬዎች ምንም ምን እንዳል ወሰደ በአወቁ ጊዜ ስለዚህ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር ሰብስበው ስለርሱ ለንጉሡ ሰጡት ።

❖ የዕረፍቱም ጊዜ ሲቀርብ እግዚአብሔርም ትሩፋቱንና ጽድቁን ለሰው ሊገልጽ ወደደ ጥቂትም ታመመ ብዙ ካህናትና መነኰሳትም ወደ ርሱ እንደ መጡ በሌሊት ራእይ አየ፤ እነርሱም ወንጌሎችን መስቀሎችንና ማዕጠንቶችን በእጆቻቸው ይዘዋል።

❖ እንዲህም አሉት እኛ ልንጐበኝህ መጣን ከዓመትም ፍጻሜ በኋላ ወደአንተ ተመልሰን መጥተን ከእኛ ጋራ እንወስድሃለን፤ በነቃም ጊዜ ከእርሱ ዘንድ ላሉ መነኰሳትና ኤጲስቆጶሳት ለካህናትም እንዴት እንዳየ ነገራቸው ከደዌውም ዳነ።

❖ ከዓመት ፍጻሜም በኋላ ጥቂት ታመመ አስቀድመው ወደርሱ መጥተው የነበሩትን ካህናትና መነኰሳት ደግሞ አያቸው ሰላምታም ሰጡት፤ ከእንርሱም ጋራ ደስ አለው በዚያን ጊዜም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጥቶ በሰላም አረፈ በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ዓሥራ አራት ዓመት ከኖረ በኋላ ነው።


በረከቱም ረድኤቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን



📌 ሚያዝያ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱስ አባ ይስሐቅ ገዳማዊ (የታላቁ ዕብሎይ ደቀ መዝሙር)

2. አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት



📌 ወርኀዊ በዓላት
1. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ

2. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ

3. ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ

4. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ

5. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)

6. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት

7. ቅዱስ ዕፀ መስቀል
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Bketa @¥
5 ነጥቦች ስለ ገብርሔር

1. የመክሊቱ ጌታ ጥያቄ "ምን ያህል አትርፈሃል?" አይደለም። ነገር ግን "በቅንነትና በታማኝነት ለማትረፍ ምን ያህል ሠርተሃል?" ነው።
ባለ 5ቱና ባለ 2ቱ ያተረፉት መጠንን ሳይሆን ታማኝነትን ነው። አንደኛው 5፣ ሌላኛውም 2 ቢያተርፉም የሁለቱም ሽልማት ግን ‘መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ የሚል ቃል ነው። ባተረፉት የመክሊት ቁጥር ልዩነት ልክ ሳይሆን በታማኝነታቸው አንድ ዓይነትነት ምክንያት አንድ ዓይነት ሽልማትን ተሸልመዋል።

2. ባሮቹ "ስጠን፣ ያስፈልገናል" ብለው ለምነውት ሳይሆን "ባሮቹን ጠርቶ..." እንደሚያስፈልጋቸው አውቆ መክሊትን ሰጥቷቸዋል። እኛ ባሮቹ ለእኛ ከምናስበው በላይ እርሱ ለእኛ የሚያስብልን ነው። እንደ ዐቅማችን የሚያስፈልገንንም አይነፍገንም።

3. ምንም የማይሰጠው ባሪያ የለም። ጌታችን ሁልጊዜም ጽድቅን ለማትረፍ ቢያንስ አንድ መነሻ መክሊትን ለሁሉም ይሰጣል። "ለኔ ምንም ስላልሰጠኝ" ብሎ ሰበብ ማቅረብ አይቻልም። ይልቁንስ "የተሰጠኝ ምንድን ነው?" ብሎ መክሊትን መፈለግ ያሻል።

4. ባለ አንድ መክሊቱ ጥፋቱ ምንድን ነው?ከገብርሔር ታሪክ ቸልተኝነት፣ ስንፍና እና ገለልተኝነት እጅግ ክፉ ኃጢአቶች መሆናቸውን እንረዳበታለን። ያ ባሪያ ክፉ የተባለው መክሊቱን ተዘርፎ፣ ወይም ጥሎት፣ ወይም ጠፍቶበት ሳይሆን በቸልተኝነት ወይም በስንፍና ምክንያት ስላላተረፈበት ነው። መክሊቱን ግን እንደ ተቀበለው መልሷል። በመክሊት ማትረፍ እንጂ መክሊትን እንደ ተቀበሉ መመለስ ትርጉም የለውም። መክሊቶቻችንን ለበተንንና የት እንዳሉ ለማናውቅ፣ ከክፉው ባሪያ ለከፋን ለእኛ ወዮልን!

5. ጌታ መጠየቅ ሲጀምር ከባለ 5ቱ ነው። አብዝቶ የተቀበለ አብዝቶ ተጠያቂ ነው።

ዲ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተ ብርሃን
2024/09/28 10:24:54
Back to Top
HTML Embed Code: