Telegram Web Link
Audio
ስንክሳር ዘወርሃ ጥር ስምንት(፰)
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
+ +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ
          
+++መልካም ዕለተ ረቡዕ ሰንበት መልካም ቀን+
+++
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ÷ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት"
              የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆላስይስ ሰዎች ፫÷፳፫


👉 ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ :-

            እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ

ለምስጋና በአምላካችን ፊት የምንቀርብበትን በዓለ ጥምቀት በዝማሬ ካሳለፍን በኋላ የቃና ዘገሊላ ዕለት ጥር 12 ከ3 ደብር  ብዛታቸው ከ450 በላይ የሚሆኑ በዝማሬ እያጀቡን የሚመጡ የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት እንግዶቻችንን ጨምሮ ፣ ከ340 ባላይ የህጻናት ክፍል ዘማሪዎቻችን፣ ከ200 በላይ የወጣት ክፍል እና የነባር ቀደምት አባሎቻችንና የአካባቢው ማኅበራትን ጨምሮ ብዛት ያላቸው ነዳያንን አጠቃላይ ከ1500 በላይ ተሳታፊዎችን ጸበል ጸዲቅ በማዘጋጀት የመመገብ ሥራ እንደሚከነወን ይታወቃልና  .     .      .          
         
እርሶም    
                                                                     
የራሳችንን አባላት ጨምሮ እንግዶቻችንን ለማስተናገድ ለመሸኘት እንድንችል ከዚህ ቀደም እንደምታደርጉት ሁሉ በፍቅር እና በመታዘዝ የአቅማችሁን በዓይነትም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንድታደርጉልን ጥሪያንችንን እናስተላልፋለን፡፡

            ለጽ/ቤት ሆነ ለሙያ እና ተራድኦ ክፍል ማስረከብ ይቻላል::

0910 54 43 21 / 0935 20 46 87                   0913 06 98 77  0935 97 43 97
                   
     የኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ጽ/ቤት
                         ጥር ፳፻፲፮ዓ.ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

=>+"+ እንኩዋን ለአበው "ቅዱሳን አባ አብርሃም ወአባ ገዐርጊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ቅዱሳን አብርሃም ወገዐርጊ "*+

+*" ተጋድሎተ ቅዱሳን "*+

=>ቅዱሳኑን የመሰሉ አባቶች "መስተጋድላን" ይባላሉ በግዕዙ:: ለሃይማኖታቸው እስከ ደም ጠብታና እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጋደላቸውን የሚያሳይ ነው:: መጋደል ጐዳናው ብዙ ዓይነት ነው::

+ከራሱ ጋር የሚጋደል አለ:: ከዓለም ጋር የሚጋደልም አለ:: የቅዱሳኑ ተጋድሎ ግን በዋነኝነት ከ2 አካላት ጋር ነው:: በመጀመሪያ ፍትወታት እኩያትን (ኃጣውዕን) ከሚያመጡ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ: ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን ጋር የሚደረግ ትግል ነው::

+በተለይ 2ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔን ይጠይቃል:: የዚህን ቅዱስ ሕይወት ለመረዳት ግን አንድ ነገርን ልብ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ::

+ያለንበት ዘመን ክርስትና በራድ (ቀዝቃዛ) በመሆኑ የቀደሙ አባቶች የጸና ተጋድሎ አንዳንዴ ግራ ሲያጋባን ተመልክቻለሁ:: ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ:: ይኼውም በዘመኑ በርካቶቻችን የረሳነው: ወይም ማስታወስ የማንፈልገው ነገር ይመስላል::

+ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ ተቀብሏል:: ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው:: ፍቅረ መስቀሉን: የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው: የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም::

+ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው:: ጌታችን "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" (ማቴ. 16:18) እንዳለው ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በቃል ሲፈጽሙት እነሆ እንመለከታለን::

+*" ገዳማዊ ሕይወት "*+

=>ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

+ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

+ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

+ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::

+እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

+አባ እንጦንስ አባ መቃርስን: አባ መቃርስ አባ ዮሐንስን ወልደዋል:: አባ ዮሐንስም የታላቁ ገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በጸጋ አገልግለዋል:: አስቄጥስ በምድረ ግብጽ የሚገኝ: በስፋቱና ብዙ ቅዱሳንን በማፍራቱ ተወዳዳሪ የሌለው የዓለማችን ቁጥር አንድ ገዳም ነው::

+ሕይወተ ምንኩሰናም ወደ መላው ዓለም የተስፋፋ በዚህ ገዳም መናንያን አማካኝነት ነው:: በዚህ ገዳም ላይ የሚሾሙ አበው ደግሞ በብዛት መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውና አባታቸውን ቅዱስ መቃርስ ታላቁን የመሰሉ ናቸውና ኃላፊነቱ እጅግ ከባድ ነው::

+በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ተወልደው ያደጉት አባ ዮሐንስ ከመነኑባት ዕለት ጀምረው በፍጹም ተጸምዶና ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ስለ ተገዙ የታላቁ ገዳም አበ ምኔት ሊሆኑ ተገባቸው::

+በአበ ምኔትነት ዘመናቸውም መንጋውን ይጠብቁ ዘንድ ብዙ ደከሙ:: በተለይ ቅዱስ ቃሉን ያስተምሩ ዘንድ ተጉ:: ሕይወተ መላእክትንም ያሳዩ ዘንድ በቃል ብቻ ያይደለ በተግባር ሆነው : ከመንፈሳዊ አብራካቸው ብዙ ቅዱሳንን ወለዱ::

+ከዋክብቱ አባ ገዐርጊ: አባ አብርሃም: አባ ሚናስ: አባ ዘካርያስ . . . የአባ ዮሐንስ ፍሬዎች ናቸውና:: ጻድቁ በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: ከዕረፍታቸው በሁዋላ እንኩዋ መግነዛቸውና የልብሳቸው እራፊ ብዙ ድውያንን ፈውሷል::

+*" ቅዱሳን አብርሃም ወገዐርጊ "*+

=>እነዚህ 2 ቅዱሳን በግብጽ በርሃ ያበሩ የቅዱሱ አባ ዮሐንስ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹ ናቸው:: አስቀድሞ ወደ በርሃ የወጣ አባ አብርሃም ሲሆን እርሱም በምድረ ግብጽ የተባረኩ ሰዎች ልጅ ነው::

+ወላጆቹ በፈቃደ እግዚአብሔር እርሱን ከወለዱ በሁዋላ ብዙ በጐነትን አሳይተዋል:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የችግርና የረሃብ ጊዜ) ነበርና ሃብታቸውን በምጽዋት ጨርሰዋል:: የሚገርመው የቅዱሱ አባት "ነዳያን እየተራቡ ዝም አልልም" ብሎ እየተበደረ ያበላቸው ነበር::

+እርሱ ባረፈ ጊዜም የተባረከች ሚስቱ መልካምን እየሠራች ብዙ ተፈትናለች:: ለባርነት ተማርካ እስክትሔድ ድረስም ታግሣለች:: ቅዱሱን ልጇን አብርሃምንም እንደሚገባ አሳድጋ "ሚስት ላጋባህ" አለችው::

+እርሱ ግን "እናቴ ሆይ! እኔ ይህንን ዓለም አልፈልገውም" ሲል መለሰላት:: ይህንን ስትሰማም ሐሴትን አድርጋ አብርሃምን ወደ በርሃ ሸኘችው:: አባ አብርሃምም ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሔዶ በደብረ አባ መቃርስ መነኮሰ:: ተጋድሎንም በዚያው ጀመረ::

+ሲጾም: ሲጸልይ: ሲጋደልም ዘመናት አለፉ:: በዚህ ጊዜም ታላቁ አባ ገዓርጊ ከዓለም ወደ በርሃ መጥቶ መነኮሰ:: የአባ ዮሐንስ የመንፈስ ልጆች ውስጥም እንደ አንዱ ተቆጠረ:: አባ ገዐርጊን የተመለከተው አባ አብርሃምም ስለ ወደደው አብረው መኖር ጀመሩ::

+2ቱ ቅዱሳንም "በግቢግ" በምትባል በዓታቸው በፍቅር ለፈጣሪያቸው ሲገዙ ዘመናት አለፉ:: በነዚህ ዘመናትም በርካታ ቅዱሳን ከመንፈሳዊ አብራካቸው አፈሩ ከቅድስናቸው ብዛትም ከሰንበት በቀር እህልን አይቀምሱም ነበር::

+የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድ ቀን ከዓለት በተወቀረች በዓታቸው ውስጥ በጸሎት ላይ ሳሉ ወረደላቸው:: የበዓታቸውን ዓለት ሰንጥቆ ሲገባ ታላቅ ግርማና ብርሃን አካባቢውን ዋጠው:: ቅዱሳኑም ለመድኃኒታችን ተደፍተው ሰገዱ::

+እርሱ አነጋግሯቸው: ባርኩዋቸው ዐርጉዋል:: ለምልክትም በዓታቸው እንደ ተሰነጠቀ ቀርቷል:: ዘወትርም በዕለተ ሰንበት ይገለጥላቸው ነበር:: ቅዱሳን አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም በርካታ ተአምራትን ሲሠሩ ኑረዋል::
+አባ አብርሃም ጥር 9 ቀን ሲያርፉ አባ ገዐርጊ ግንቦት 18 ቀን ዐርፎ ተቀብሯል:: በዓታቸው በግቢግም ዛሬ ድረስ በምድረ ግብጽ አለች::

=>አምላከ ቅዱሳን አበው በፍቅሩ ይገለጥልን:: ከአባቶቻች ጸጋ በረከትም አይለየን::

=>ጥር 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ አብርሃም ገዳማዊ
2.አባ ገዐርጊ ጻድቅ
3.ቅዱስ ዲዮስቅርስ ዘሮሜ
4.አባ ኪናፎርያ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
3.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

=>+"+ በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል:: +"+ (ምሳሌ 10:6)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
+ +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ
          
+++መልካም ዕለተ ሐሙስ ሰንበት መልካም ቀን+
+++
Forwarded from Sintu.D
#በጥምቀት_ዙሪያ_የሚነሱ_ጥያቄዎች_እና_መልሶቻቸው
#ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ?
1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/

2. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
በመዝሙር 46/47/፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡

3. አርአያ ሊሆነን፡-
ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ 11፥29/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. 13፥1-17/

4. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ
ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14

#ጌታችን_መች_ተጠመቀ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. 3፥23/

#ጌታችን_ስለምን_በ30_ዓመት_ተጠመቀ?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ. 3፥6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡

ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡

ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ‹‹ይህ ልጄ ነው›› ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ /ማቴ. 3፥16/

#ጌታችን_በዮሐንስ_እጅ_ለምን_ተጠመቀ?

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን ‹‹መጥተህ አጥምቀኝ ›› ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ›› ሲል ነው፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ጌታችንን_በማን_ስም_አጠመቀው?

ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ "ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?" ብሎ ቢጠይቀው ጌታም ‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡

#ዮሐንስ_ጌታን_ሲያጠምቀው_እጁን_ለምን_አልጫነበትም?
- ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል፡፡
- መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል

#ጌታችን_ጥምቀቱን_ለምን_በዮርዳኖስ_አደረገው?
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ.113፥3/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቈላ. 2፥14/

#ጌታችን_ለምን_በውሃ_ተጠመቀ?
እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)

አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)
#ጌታችን_ለምን_በሌሊት_ተጠመቀ?
በኃጢአት ጨለማ ስለነበረ ሕዝብ የጽድቅ ብርሃን እንዲወጣለትና በጨለማ የሚመስል ኦሪት ይኖር ስለነበረ ለሕዝብ ብርሃን የሆነ ወንጌል መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ ኢሳ.9፥2

አንድም ጌታ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ትንሣኤው እንዲሁም ምጽአቱ በሌሊት ነው፡፡ ይኽም የሆነበት ምክንያት፡- ሌሊቱን ተከትሎ የሚመጣው ብርሃን በመሆኑ ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት የመሸጋገራችን ምሳሌ ነው፡፡

አንድም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል የሚወርድ ነውና በጌታ ላይ የወረደው ርግብ እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ባሉ ነበር፡፡ በሌሊት ርግብ የለም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ፡፡

#መንፈስ_ቅዱስ_ለምን_ጌታ_ከውኃ_ከወጣ_በኋላ_ወረደ?
ሀ. ዮሐንስን ያከብሩት ነበርና መንፈስ ቅዱስ የወረደው ለዮሐንስ እንጂ ለጌታ አይደለም ይሉ ነበርና ምክንያቱን ጌታ ውኃ ውስጥ እያለ ከዮሐንስ አልተለየም ነበርና፡፡
ለ. ውኃን የሚባርክ መልአክ እንዳለ ያውቁ ነበርና ውኃውን ለመባረክ አንጂ ለጌታ አይደለም እንዳይባል፡፡
ሐ. ማረፊያ ያጣች ርግብ በባሕር ስትበር አረፈችበት ይሉ ነበርና ሐሳባቸውን በሙሉ ያጠፋ ዘንድ ከውኃ ውስጥ ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Forwarded from 𝕙
"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት ።" ኢያ 3:3

መልካም የከተራ በዓል
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

እንኩዋን "ለጾመ ገሃድ" እና "አባ ታውብንስጦስ" ዓመታዊ የእረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" ጾመ ገሃድ "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::

+"7ቱ" አጽዋማት:-
1.ዓቢይ ጾም
2.ጾመ ፍልሠታ
3.ጾመ ሐዋርያት
4.ጾመ ነቢያት
5.ጾመ ድኅነት
6.ጾመ ነነዌ እና
7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::

+በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለውና ይቆየን:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል::

+ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና:: እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች:: የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን::

+ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል:: ኃጢአትን ለመሥራት: ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም:: እኛ ግን ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2) አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ. 13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን እንጾማለን::

=>"ገሃድ" የሚለው ቃል በቁሙ "መገለጥን : መታየትን : ይፋ መሆንን" የሚያመለክት ሲሆን በምሥጢሩ ግን "የማይታይ አምላክ መታየቱን : የማይዳሰሰው መዳሰሱን" ያመለክታል::

+ወይም በሌላ ልሳን ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም በተዋሕዶ ሰው ከሆነ በሁዋላ ለ30 ዓመታት ራሱን ሳይገልጥ ቆይቶ ነበርና በ30 ዓመቱ ራሱን ለእሥራኤል በዚህ ሰሞን መግለጡን ልብ የምንልበት በዓል ነው::

+መድኃኒታችን ሁሉን ነገር የሚሠራው በጊዜው ነውና ከሥጋዌው በሁዋላ ለ30 ዓመታት: ከስደት መልስ ደግሞ ለ25 ዓመታት የሰውነቱን ምሥጢር በይፋ ሳይገልጥ ቆይቷል:: ያም ሆኖ የሰውነቱን ምሥጢር እርሱ: የባሕርይ አባቱና ቅዱስ መንፈሱ ለድንግል ማርያም ገልጠውላት ታውቀው ነበር:: እርሷ ግን መዝገበ ምሥጢር ናትና ሁሉን ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር:: (ሉቃ. 2:52)

+መድኃኒታችን ከሥጋዌው (ሰው ከሆነባት) ደቂቃ ጀምሮ መግቦቱን አላቁዋረጠም:: ምንም በግዕዘ ሕጻናት ቢኖርም እርሱ በዘባነ ኪሩብ የሚሠለስ ቸር ጌታ ነውና መግቦናል::

+እንደ እሥራኤል ባህል 30 ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ሥግው አምላክ መሆኑን ገለጠ:: የተገለጠውም በጥምቀቱ ሲሆን በዕለቱ ከአብ: ከመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ ልጅነቱን አስመስክሯል:: በባሪያው በዮሐንስ እጅም ተጠምቆ ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶልናል::

+የእዳ ደብዳቤአችን ቀዶ ልጅነታችንን መልሶልናል:: ይህ ሁሉ የተደረገ ለእኛ ነውና በዓለ ኤዺፋንያን (እለተ አስተርእዮቱን) በድምቀት እናከብራለን::

+ነገር ግን ልክ በቅርብ ጊዜ እያየነው እንደሚገኘው በዘፈንና ከአምልኮ ባፈነገጠ መንገድ እንዳይሆን ቤተ ክርስቲያን አበክራ ታሳስባለች:: የመድኃኒታችንን የማዳን ሥራ ከማዘከርና ለእርሱ ከመገዛት ይልቅ ራስን ዘፈን በሚመስል መዝሙር መቃኘቱና ለልብስ ፋሽን መጨነቁ የሚጠቅም አይደለም::

+በዓላት በሚዲያ ታዩ: ተመዘገቡ ብለን ከመዝናናት ትውፊታችንን እያጠፉ ያሉ ድርጊቶቻችን ብንታዘባቸውና ብናርማቸው ይመረጣል:: ስኬታችን ሁሉም ክርስቲያን ለእግዚአብሔር መንግስት መብቃቱ እንጂ በዓል አከባበራችን ዝነኛ መሆኑ አይደለም::

+ጉዳዩ መለኮታዊ እንጂ ፓለቲካዊ አይደለምና ጥንቃቄን ይሻል:: ዛሬ ለታቦተ እግዚአብሔር ክብርን የማይሰጥና ተጋፊ ትውልድን እየፈጠርን ነው:: ካህናትን አለመስማትና ታቦታትን አግቶ አላስገባም ማለት በክርስትና ትርጉሙ ከሰይጣን መወዳጀት ነው:: ስለዚህም በዓል አከከባበራችንን እንታዘብ:: ደግሞም እናርመው::

+*" ጾመ ገሃድ "*+

=>ቤተ ክርስቲያን ጾመ ገሃድን የደነገገች ለ3 ምክንያት ነው:-

1.የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጥሙና እያሰብን በጾም እንድናመልከው::
2.በዓል አከባበራችን እንደ አሕዛብ በተድላ ሥጋ: በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳይሆንና ሰውነታችንን በጾም እንድንገራው::
3.ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዐርብ ሲውሉ እህል በነግህ (በጧት) መቀመስ ስላለበት የእርሱ ቅያሪ (ተውላጥ) እንዲሆን ነው::

+ጾመ ገሃድን የሠሩት አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ ያጸኑት ደግሞ ቅዱሳን ሊቃውንት ናቸው:: አጿጿሙም ጥምቀት ከማክሰኞ እስከ ቅዳሜ ከዋለ በዋዜማው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" እንዲሉ አበው እስከ ምሽት 1 ሰዓት ድረስ ይጾማል::

+በዓለ ጥምቀት እሑድ ሲሆን ዐርብን አዘክሮ: በዕለተ ቅዳሜ ደግሞ ከጥሉላት ተከልክሎ መዋል ይገባል:: በመሳሳይ ሰኞ ቢውል ዐርብን አዘክሮ: ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት (ከሚያገድፉ ምግቦች) ሁሉ ተከልክሎ መዋል ይገባል::

+ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ ነውና የተለየ ግለሰባዊ ችግር እስከሌለ ድረስ ሊጾም ግድ ይላል:: ችግር ካለ ደግሞ ከንስሃ አባት ጋር ሊመክሩ ይገባል::

+*" አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት "*+

=>በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም የተነሳ
+ከልጅነቱ መጻሕፍትን የተማረ:
+በክህነት አገልግሎቱ ለብዙዎች አባት የሆነ:
+በምናኔ ወደ ግብጽ የወረደ:

+በእስክንድርያ አካባቢ አበ ምኔት ሆኖ ብዙ መነኮሳትን የመራ::
+በዘመነ ሰማዕታት የተሰደደ:
+ብዙ አሕጉራትን ዞሮ ያስተማረ:

+በትምሕርተ ክርስቶስ ያላመኑትን አሳምኖ : ያመኑትን ያጸና:
+ሽፍቶችን እየገሠጸ ለንስሃ ያበቃ የነበረ ታላቅ አባት ነው::

+በዘመነ ሰማዕታት ስደትን ታግሦ: በሁዋላም በደብረ ሲሐት ተወስኖ ኑሯል:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::
=>አምላከ ቅዱሳን ፍቅሩን: ምሥጢሩን ይግለጥልን:: ከጾመ ገሃድ በረከትም አይለየን::

=>ጥር 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ጾመ ገሃድ
2.አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት
3.ቅዱስ ኪናርያ
4.ቅድስት ጠምያኒ

=>ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
7.ቅዱስ እፀ መስቀል

=>+"+ እነርሱ እሥራኤላውያን ናቸውና:: ልጅነትና ክብር: ኪዳንም: የሕግም መሰጠት: የመቅደስም ሥርዓት: የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና:: አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና:: ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ:: እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው:: አሜን:: +"+ (ሮሜ. 9:4)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
          አሜን
"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"         
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
         ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

📌 ስንክሳር ዘወርኀ ጥር ፲፩

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ዐሥራ አንድ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሐንስ ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ።

❖ ይችም ዕለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች ትርጓሜውም መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው፤ ልዩ የሆነች የሦስትነቱን ምሥጢር ገልጦባታልና አብ ከሰማይ ሁኖ የምወደው በርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት እያለ ሲመሰክር ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቁሞ ሳለ መንፈስ ቅዱስም በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ሲቀመጥ ይህ አጥማቂው ዮሐንስ እንደመሰከረ።

❖ እንዲህ ሲል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከውኃ በወጣ ጊዜ ወዲያኑ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በጌታችን ራስ ላይ ተቀመጠ ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ነው እርሱንም ስሙት።

❖ በዚች እለት ጌታችን ራሱን ገልጦአልና ከዚህ በፊት ሰላሳ አመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር ግን በዚች እለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ እነሆ የእግዚአብሔር በግ የአለምን ኃጢአት የሚያስወግድ ብሎ መጥምቁ ዮሐንስ እንደገለጠው የከበረ ወንጌል ምስክር ሆነ።

❖ እኔ አላውቀውም ነበር ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁ አለ፤ በዚህም በዓል የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ የጌትነቱ ክብር ተገልጧል እርሱም የአለሙን ሁሉ ኃጢአት ለማስወገድ የሚሠዋ የእግዚአብሔር አማናዊ በግ ነው።

❖ ስለዚህም ይህ በዓል በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ዘንድ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ሆነ በርሱም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ በአከበረው ውኃ ይነጹበታል የተቀበሉትንም ንጽሕና ጠብቀው ቢኖሩ በውስጡ የኃጢአታቸውን ሥርየት ያገኛሉ።

❖ ስለዚህም ከክፉ ነገር ሁሉ ተጠብቀን የፈጣሪያችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የቸርነቱን ብዛት ልናመሰግን ይገባናል እርሱ ስለ እኛ ሰው ሆኖ ከኃጢአታችን አድኖናልና።
ለእርሱም ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።


📌 ጥር 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.በዓለ ኤዺፋንያ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
3.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
4.አባ ወቅሪስ ገዳማዊ
5.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት
6.ቅዱስ እንጣልዮስ ሰማዕት

📌 ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ቅድስት ሐና ቡርክት
#ቃና_ዘገሊላ
ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት(ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡
የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡
በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጇ ወደ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡ እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን አቆይተሃል›› አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡

‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?››
ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል ፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23) በመሆኑም ጌታ አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡ ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡፡ ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡ ይህ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡፡ለአብነት ይሆን ዘንድ ጥቂት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት፡-
የሰራፕታዋ ሴት በ 1ነገ 17÷18 ላይ እንደምናገኘው ልጇ በሞተባት ጊዜ ኤልያስን በሐዘን በለቅሶ እንዲህ ብላ ነበር ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› ትወልጃለሽ ብለህ የወለድኩት ልጅ ምን በድዬህ ምንስ አስከፍቼህ ሞተብኝ? ስትል ነው እንጂ አባባሏ የንቀት ወይም የማቃለል አይደለም፡፡
በጌርጌሴኖን አንድ አጋንንት ያደረበት ሰው ወደ ጌታችን ቀርቦ ‹‹የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› አለው፡፡ እውነት ይህ ቃል የንቀት ይመስላልን? የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ብሎ አምላክነቱን እየመሰከረ ሊያቃልለው ይችላልን? ደግሞስ ላለመጥፋት ፍፁም የሚፈልግ ሰው ሊያድነው ሥልጣን ያለውን ሊንቅ ይችላልን? አይችልም፡፡ ይህ ቃል የሚያመለክተው ምን አጠፋሁ ስለምን ልታጠፋኝ ወደድክ በማለት መፍራት መራዱን ነው፡፡ (ሉቃ 8÷28-29) ስለሆነም ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለው የንቀት አለመሆኑን ከሁለቱ ጥቅሶች መረዳት እንችላለን፡፡ እመቤታችን እና ጌታ በንግግር አልተቃረኑም ንግግራቸው የፍቅር ነበር፡፡ ንግግራቸው የመግባባት ስለነበር ነው ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ካላት በኋላ ዘወር ብላ አገልጋዮቹን የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ያለችው፡፡
‹‹ጊዜዬ አልደረሰም›› ጌታ ይህን ቃል የተናገረው ስለ ብዙ ምክንያቶች ነው፡፡ ጊዜዬ አልደረሰም ማለቱ፡-
እግዚአብሔር ነገሮችን የሚያከናውንበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ተአምር የምፈፅምበት ጊዜዬ አልደረሰም ሲል ነው፡፡
አንድም ጋኖቹ ውስጥ የቀረ ወይን ስለነበረ ባለው ላይ አበርክቶ እንጂ ውኃውን ወደ ወይን አልለወጠውም እንዳይሉ ወይኑ ከጋኑ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡
አንድም ይሁዳ ከሠርግ ቤት ወጣ ብሎ ነበርና ወደ ሠርግ ቤቱ እሰኪመለስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡ ይሁዳ በቃና የገለጠውን ምስጢር ለእኔ ስላላሣየኝ ተከፍቼበት ከተአምራቱ ቢያጎድለኝ በሞቱ ገባሁበት፤ ሸጥኩት እንዳይል ምክንያት ለማሳጣት እንዲህ አድርጓል፡፡
አንድም እውነተኛ የሕይወት ወይን የሆነውን ደሜን የምሠጥበት ጊዜ ገና ነው ሲል፡፡
የድንግል ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሣለ የወይኑን ማለቅ የማይመለከት ሆኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን የእናቱን የድንግል ማርያምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለወይኑ ማለቅ እስክትነግረው ድረስ አንዳች ነገር አላደረገም፡፡ ኋላ ግን የጭንቀት አማላጅ ድንግል ማርያም ስለ ወይኑ አሰበች ልጇ ወዳጇን ለመነች፡፡ እርሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈፀመ፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሣይነግሯት በልብ ያለውን የምታውቅ የምትመረምር እናት ናትና የሠርጉ አስተናባሪዎች ይሄ ጎደለ ሣይሏት የልቦናቸውን ሐዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች፡፡ያስጨነቃቸውንም አርቃለች፡፡ በችግራቸው ደርሳላቸዋለች፡፡ ታዲያ ሳይነግሯት የልቡናን አይታ ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትማ እንዴት አብልጣ አታማልድ?
አምላከ ቅዱሳን ወይነ ቃና ፍቅሩን ያሳድርብን:: ከድንግል እናቱ ምልጃና በረከት አይለየን::
(#ስንክሳር_ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ)
2024/09/30 18:31:21
Back to Top
HTML Embed Code: