Telegram Web Link
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
" የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ: ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች:: ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ወንድሞቼ ሆይ! የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት:: ትዕግስትም ምንም የሚጐድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም:: " [ያዕ.፩፥፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
                        †                           

🕊    💖  ቅዱስ   ያዕቆብ  💖    🕊

                         🕊                         

❝  ከሐዋርያት ጵጵስናን የተቀበለ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መሾሙ የቀደመ በሥጋ ዝምድና የጌታችን ወንድም ለኾነ ለያዕቆብ ሰላምታ ይገባል።   ❞


[ አቤቱ የሐዋርያት ተከታዮቻቸው ስለኾኑ ስለ ሰባ ኹለቱ አርድእት ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ። ... ስለ እነርሱ ማረኝ ፤ እኔን አገልጋይኽንም በሀገራቸው ውስጥ ከነርሱ ጋር ዕድል ፈንታዬን ጽዋ ተርታዬን አድርግ ፤ አሜን።

[   ተአምኆ ቅዱሳን   ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

[        ከመልዕክቱ       ]

❝ ወንድሞቼ ሆይ ፥ እምነት አለኝ የሚል ፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል ? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን ? . . . እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ ፤ መልካም ታደርጋለህ ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።

አንተ ከንቱ ሰው ፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን ? ❞ [ ያዕ . ፪ ፥ ፲፬ ] 

🕊

[  † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]


🕊                        💖                     🕊
ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት"

ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው


መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[  † እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †   ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  መድኃኔ ዓለም  †   🕊

† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ፫ ሰዓት [3:00] ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::

በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት [ሦስት ሰዓት ላይ] አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ፮ ሺህ ፮ መቶ ስድሳ ፮ [6,666] ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::

ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ::

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::

በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: [ማቴ.፳፯፥፩ (27:1), ማር.፲፭፥፩ (15:1), ሉቃ.፳፫፥፩ (23:1), ዮሐ.፲፱፥፩ (19:1) ]

ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ [ 27 ] ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት
፳፯ [27] የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::

ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::

በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት ፳፯ [27] ሲመጣ: የመጋቢት ፭ [5] ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት ፭ [5] : የመጋቢት ፲ [10] መስቀል ወደ መስከረም ፲፯ [17] መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::


†  🕊 ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ 🕊  †

በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው:: "ታላቁ መቃርዮስ": "መቃርስ እስክንድርያዊ": "መቃርስ ባሕታዊ"ን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል:: ይህኛው ቅዱስ ደግሞ "መቃርስ ኤዺስ ቆዾስ: መቃርስ ብጹዓዊ: መቃርስ ዘሃገረ ቃው" ይባላል:: ሁሉም መጠሪያዎቹ ናቸው::

ቅዱሱ የ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ሲሆን የቅዱስ ቄርሎስና የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ተከታይ ነው:: ከሕይወቱ ማማርና ከቅድስናው መሥመር የተነሳ አበው አመስግነውት አይይጠግቡም:: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል" እንዳለው:: [መዝ.፺፩]

ዳግመኛ "ወይከውን ከመ ዕጽ እንተ ትክልት ኀበ ሙሐዘ ማይ" [መዝ.፩፥፫] እንዳለው ቅዱስ መቃርስ እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን አፍርቷል:: ከሁሉ አስቀድሞ በበርሃ ኗሪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ስለ ጌታ ፍቅር እንባው እንደ ዥረት እየፈሰሰ:: ራሱን በብረት ዘንግ ይመታ ነበር::

"ቃው" በምትባል ሃገር ዻዻስ ሆኖ በተሾመ ጊዜም ተጋድሎውን አልቀነሰም:: ዻዻስ ቢሆንም የሚለብሰው የበርሃዋን ደበሎ ነው:: ከብቅዓቱ የተነሳ የሕዝቡ ኃጢአት በግንባራቸው ላይ ተጽፎ እየታየው ስለ ወገኖቹ ያለቅስ ነበረ:: በቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሞ አንጀቱ ቅጥል እስኪል ድረስም ያለቅስ ነበር::

ሁልጊዜ ሲቀድስ ጌታችንን ከመላእክቱ ጋር ያየው ነበር:: አንድ ቀንም ጌታ ቅዱስ መቃርስን "ዻዻሱ ሆይ ሕዝቡን ገስጻቸው:: ብትገስጻቸውና ባይሰሙህ እዳው በእነርሱ ላይ ነው" አለው:: ቅዱስ መቃርስም ሕዝቡ ከኃጢአታቸው ይመለሱ ዘንድ ይመክራቸው: ይለምንላቸውም ነበር::

ከዚህ ሁሉ በሁዋላ በጉባኤ ኬልቄዶን [ጉባኤ አብዳን] ፮፻፴፮ ዻዻሳት ንጉሡን ፈርተው ሃይማኖታቸውን ሲክዱ ቅዱሳኑ ዲዮስቆሮስና መቃርስ "ተዋሐዶን አንክድም" በማለታቸው ዘበቱባቸው:: ብዙ አሰቃይተውም ወደ ጋግራ ደሴት አሳደዷቸው::

ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ውስጥ ሲሞት ቅዱስ መቃርስ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ሕዝቡን ሲመክር ያዙት:: ከመሬት ላይ ጥለውም እየደጋገሙ ኩላሊቱን ረገጡት:: ከመከራው ብዛትም በዚህች ቀን ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ:: ቅዱሱ ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል::

አበውም ስለ ቅዱስ መቃርስ ብሎ ጌታ እንዲምራቸው እንዲህ ይጸልዩ ነበር :-

"ሰላም ሰላም ለፈያታዊ ዘቀደሶ::
ሃገረ ጽጌ የአኀዝ ምስለ ጻድቃን በተዋርሶ::
ተዘከረኒ ክርስቶስ አመ ትመጽእ ለተዋቅሶ::
በእንተ መቃርስ ጻድቅ እንተ መጠወ ነፍሶ::
ወበበትረ መስቀል ዘይዘብጥ ርዕሶ::" [አርኬ ዘጥቅምት ፳፯]


†  🕊  አቡነ መብዓ ጽዮን  🕊  †

ሃገራችን ኢትዮዽያ እጅግ በርካታ ቅዱሳንን ስታፈራ አንዳንዶቹ ደግሞ የተለዩ ናቸው:: ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮን በ፲፭ኛው መቶ ክ ዘመን በሽዋ [ሻሞ] አካባቢ የተነሱ ጻድቅ ናቸው:: ገና ከልጅነታቸው የእመቤታችንና የጌታችን ፍቅር የሞላባቸው ነበሩ::

በ፫ ዓመታቸው ከእንግዳ የወሰዷት ስዕለ አድኅኖ ተለይታቸው አታውቅም ነበር:: በወጣትነታቸው ጊዜም ብሉያት ሐዲሳትን: ቅኔንም ጨምሮ ተምረው: ከቤተሰባቸው አስፈቅደው በምናኔ ገዳም ገቡ::

ከዚያ በሁዋላ ያለውን ገድላቸውን ማን ችሎ ይዘረዝረዋል!

በተለይ ዐርብ ዐርብ የጌታን ፲፫ ሕማማት ለማዘከር ሲቀበሉት የኖሩት መከራ እጅግ ብዙ ነው:: ድንጋይ ተሸክመው እንባና ላበታቸው እየተንጠፈጠፈ ይሰግዳሉ:: በድንጋይ ደረትና ጀርባቸውን ይደቃሉ:: ራሳቸውን ይገርፋሉ:: በዋንጫ ሐሞት [ኮሶ] ሞልተው ይጠጣሉ::

ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ወር በገባ በ፳፯ ስለ መድኃኔ ዓለም ጠላ ጠምቀው: ንፍሮ ነክረው ወደ ገበያ ይወጡና ይዘክሩ ነበር:: ከዝክሩ የነካ ሁሉ ይፈወስ ነበር:: ከእንባ ብዛት ዓይናቸው ቢጠፋ ድንግል ማርያም መጥታ ብርሃናዊ ዓይንን ሰጠቻቸው:: ስለዚህም "ተክለ ማርያም [በትረ ማርያም]" ይባላሉ::

ጌታችንም ስለ ፍቅራቸው በአምሳለ ሕጻን ይገለጽላቸው: እርሳቸውም አቅፈው ይስሙት ነበር:: ጻድቁ ተናግረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ ተጋድለው ጌታ በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡበት ስልጣንን ሰጣቸው:: አባታችን ቅዱሱና ጻድቁ መብዓ ጽዮን ከብዙ ትሩፋት በሁዋላ ዐርፈዋል::


†  🕊  አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ 🕊  †

ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም:: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው::" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ:: ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው [ሲያጠምቁዋቸው] "ጽጌ ድንግል" አሏቸው::

ሲመነኩሱም "ጽጌ ብርሃን" ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::

የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን ፩ መቶ ፶ ዓርኬ አድርገው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው [ወለቃ አካባቢ የሚገኝ] ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: በዚህች ቀንም ዐርፈዋል::

አምላከ ቅዱሳን በአማኑኤል ስሙ: በማርያም እሙ: በፈሰሰ ደሙ: በተወጋ ጐኑ: በንጹሐን ቅዱሳኑ ይማረን:: ከመስቀሉና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::

† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን:: 

🕊

[   †  መጋቢት ፳፯ [27] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ [ፍቁረ እግዚእ]
፪. ቅዱሳት አንስት [ከእግረ መስቀሉ ያልተለዩ]
፫. ቅዱሳን ባልንጀሮች [በጌታ ስቅለት ጊዜ ከሞት የተነሱ]
፬. ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
፭. ታላቁ ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት አለቃ]
፮. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት [የኢትዮዽያ ንጉሥ]
፯. ቅዱስ ዕፀ መስቀል 

[   †  ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፪. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፫. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፬. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

" የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" † [፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
የጌታ ስቅለት በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"
ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡”
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡››
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ››
ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ›› 
ቅዱስ አቡሊዲስ ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡››
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[  † እንኳን ለጻድቁ አቡነ ይምዓታ እና ለአበው ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


†  🕊   አባ ይምዓታ ጻድቅ  🕊  †

† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ይምዓታ ከዘጠኙ [ተስዓቱ] ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር :-

፩. የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ::
፪. ዓላማ [የእግዚአብሔር መንግስት] እና
፫. ገዳማዊ ሕይወት ነው::

አባ ይምዓታን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ፬፻፸ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ "ቤተ ቀጢን" ትባላለች::

አባ ይምዓታና ፰ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::

ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ይምዓታ እንደ ገና አቀጣጠሉት::

ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::

ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ይምዓታ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

የነ አባ ይምዓታ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::

- ዸንጠሌዎን በጾማዕት::
- ገሪማ በመደራ::
- ሊቃኖስ በቆናጽል::
- አረጋዊ በዳሞ::
- ጽሕማ በጸድያ::
- ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
- አባ ይምዓታ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ [እዛው ትግራይ] ሆነ::

ጻድቁ ወደ ቦታው ሲሔዱ ወንዝ [ባሕር] ተከፍሎላቸዋል:: ወደ ቦታው ደርሰውም ገዳም አንጸዋል:: በቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠርተው በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል:: የአቡነ ይምዓታ ገዳም ገርዓልታ [በፎቶው ላይ እንደምናየው] እጅግ ድንቅና ማራኪ ነው::

ነገር ግን እዛው ድረስ ሒዶ ለማየት ብርታትን ይጠይቃል:: በተራሮች መካከል ከመቀመጡ ባሻገር የአባቶቻችንን ጽናት የሚያሳይ ድንቅ ቦታ ነው:: ጻድቁ በዚሁ በፎቶው ላይ በምናየው ገዳም ለዘመናት ተጋድለው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::


†  🕊 ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ 🕊  † 

† እነዚህ ቅዱሳን የቁስጥንጥንያ ሰዎች ሲሆኑ የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ዻውሎስም ደቀ መዛሙርት ናቸው:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ በአርዮሳውያን ምክንያት ስደት በሆነ ጊዜ አባ ዻውሎስ: ቅዱስ አትናቴዎስ: ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቅዱስ ሊዋርዮስ ከመንበራቸው ተፈናቀሉ::

በስደቱ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሲያርፍ ቅዱሳኑ አትናቴዎስና ሊዋርዮስ ተመለሱ:: አባ ዻውሎስን ግን በእሥር ቤት ውስጥ ሳለ በንጉሡ ትዕዛዝ አርዮሳውያን አንቀው ገደሉት:: ይህንን ያወቁት 2ቱ ደቀ መዛሙርቱ [መርቆሬዎስና መርትያኖስ] ቅዱስ አባታቸውን ቀብረው ንጉሡን ረገሙት::

አርዮሳዊው ታናሹ ቆስጠንጢኖስም ይህንን በሰማ ጊዜ ፪ቱንም አስመጥቶ በአደባባይ በሰይፍ አስመታቸው:: ይህ ከተከናወነ ከ፶ ዓመታት በሁዋላም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሆኖ በመምጣቱ ሥጋቸውን አፈለሠ:: ቤተ ክርስቲያንንም አንጾ ቀድሶላቸዋል::

† አምላከ አበው ቅዱሳን በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[   † ጥቅምት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. አባ ይምዓታ ጻድቅ [ከተስዓቱ ቅዱሳን]
፪. ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ [ሰማዕታት]
፫. አባታችን ያፌት [የኖኅ ልጅ]

[   †  ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]
፮. ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ

" በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: " † [፩ዼጥ.፫፥፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
ቅምሻ ፩
(ከኤፌሶን ወንዝ ከዲያቆን ሄኖክ መጽሐፍ)
በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ

ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ መኖር ለደከመህ፣ ሕይወት ለታከተህ፣ የሚሰማህ ላጣኸው፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!

ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ ይሉሃል። "በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. ፲፮፥፳፰ አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል። ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል። ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም።

ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ? ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ? "ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. ፲፥፲፰) "ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ" ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? (፩ነገሥ. ፲፱፥፬) ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው" ሲል አልሰማኸውም? (ዮናስ ፬፥፫)

ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም። ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው። አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም:: "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ:: ፩ኛ ቆሮ. ፲፥፲፫

ምናልባት የልብህን መሰበር የኀዘንህን ጥልቀት አይቶ ምቹ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ራስህን እንድትጎዳ ሰይጣን ሊገፋፋህ ይችላል። እንዴት እንዲህ ዓይነት ሃሳብ በልቤ ሊመጣ ቻለ ብለህ አትረበሽ። ሰይጣን ይህንን ክፉ ሃሳብ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለክርስቶስም አቅርቦለታል።

"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር" ብሎ ክርስቶስን እንኳን [ማንነቱን ሳያውቅ] ራሱን እንዲወረውር ሊገፋፋው የሞከረ ደፋር ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ራሱን አይጎዳም። "ጌታ አምላክህን አትፈታተነው" "ሒድ አንተ ሰይጣን" ብለህ ሰይጣንን ገሥፀው። ሰይጣን ክርስቶስን "ከሕንፃ ጫፍ በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አሳይ" ሲለው ክርስቶስ ሰይጣንን ሒድልኝ ብሎ በመገሠጹ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ።

ወንድሜ ሆይ አንተም ሰይጣንን አትስማው ሃሳቡ ራስህን ጎድተህ ከፈጣሪህ እንድትጣላ ሊያደርግህ ነው። ሰይጣንን ከገሠጽከው በእግዚአብሔር ቀኝ ከበጎቹ ጋር ትቆማለህ። አሁን ያለህበት ችግር ያልፋል። የሚሰማህ ክፉ ስሜት መቼም የማይለወጥ አይምሰልህ። ኀዘኑም ፣ ብቸኝነቱም ፣ ተስፋ ቢስነቱም ያልፋል። ጨለማው ይነጋል:: የተዘጋው በር ይከፈታል። ችግሩ ሲፈታ አንተ ከሌለህ ግን ትርጉም የለውም። ስለዚህ ለሚፈታ ችግር የማይቀለበስ ውሳኔ አትወስን:: ራስን ማጥፋት ከጊዜያዊ ችግር ለመሸሽ ሲሉ ዘላቂ ችግር ውስጥ መግባት ነው:: ጊዜያዊ ሕመምን ለማስታገስ የዘላለም ሕመምን ለምን ትመርጣለህ?

"የሞተ ተገላገለ" ሲሉ ሰምተህ እንዳትታለል ሞት ዕረፍት የሚሆነው ራሱ እግዚአብሔር ሲጠራህ ብቻ ነው። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ" ያለው ጌታ ሳይጠራህ ራስን ማጥፋት የዘላለም ስቃይ ያመጣል።

ወዳጄ "በራስህ አንዳች ክፉ አታድርግ" የሕይወትህን ዋጋ ታውቅ ይሆን? አንተ እኮ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ ሲል የሞተልህ ነህ። ሊፈውስህ የቆሰለ፣ ሊያከብርህ የተዋረደ፣ ሊያረካህ የተጠማ፣ ሊያለብስህ የተራቆተ ለአንተ እኮ ነው። ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶአል። አንተን ግን የጠየቀህ እንድትሞትለት ሳይሆን እንድትኖርለት ነው። ለሞተልህ አምላክ እንዴት መኖር ያቅትሃል?

ይቀጥላል ......

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ - የኤፌሶን ወንዝ ገጽ 9-14)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †

[  እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "ሳሙኤል ዘወገግ": "ጸቃውዐ ድንግል" እና "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።   ]


🕊  † አባ ሳሙኤል ዘወገግ  †  🕊

ሃገራችን ኢትዮዽያ ማኅደረ ቅዱሳን [ምዕራፈ ቅዱሳን] እንደ መሆኗ ፍሬ ክብር: ፍሬ ትሩፋት ያፈሩ ብዙ አባቶችና እናቶችን አፍርታለች:: ብርሃን ሁነው ካበሩላት ቅዱሳን መካከል አንዱ ደግሞ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::

በእኛው ሃገር ብቻ ብዙ "ሳሙኤል" የሚባሉ ቅዱሳን በመኖራቸው ስንጠራቸው "ዘእንትን" እያልን ነው:: ለምሳሌም:

- ሳሙኤል ዘዋሊ
- ሳሙኤል ዘወገግ [የዛሬው]
- ሳሙኤል ዘጣሬጣ
- ሳሙኤል ዘቆየጻ
- ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያና
- ሳሙኤል ዘግሺን መጥቀስ እንችላለን:: ሁሉም የመካከለኛው ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች ናቸው::

ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ የተወለዱት በ፲፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው የብዙ ቅዱሳን ቤት የሆነችው ሽዋ ናት:: መንደራቸውም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብዙም አይርቅም::

የጻድቁ ወላጆች እንድርያስና አርሶንያ የሚባሉ ሲሆን ደጐች ነበሩ:: ጻድቁ በተወለደ ጊዜ የቤታቸው ምሰሶ ለምልሞ ተገኝቷል:: አቡነ ሳሙኤል ከልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው በጉብዝናቸው ወራት ይህችን ዓለም ንቀዋል::

የታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው በደብረ ሊባኖስ መንነዋል:: ከ፲፪ቱ ኅሩያን [ምርጦች] አርድእት አንዱ ነበሩና በክህነታቸው ደብረ ሊባኖስን ተግተው ያጥኑ ነበር:: በዚያውም በንጹሕ ልቡና በጾምና ጸሎት ይተጉ ነበር::

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በሁዋላ በደጉ ዻዻስ በአቡነ ያዕቆብ ዘመን ፲፪ቱ ንቡራነ እድ ተመረጡ:: እነዚህ አባቶች በወንጌል አገልግሎት: በተለይ ደቡብና ምሥራቁን የሃገራችን ክፍል ያበሩ ናቸው:: ቅዱሳኑ ሲመረጡም ከአቡነ ፊልዾስ ቀጥለው በ፪ኛ ደረጃ የተመረጡ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::

ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነበር:: ጻድቁ በሃገረ ስብከታቸው ወርደው በሐረርና ሱማሌ አካባቢ ለዘመናት የወንጌልን ዘር ዘርተው እልፍ ፍሬን አፍርተዋል:: አካባቢውንም መካነ ቅዱሳን አድርገውታል::

ቀጥለው ገዳማዊ ሕይወትን ያጸኑ ዘንድ በምሥራቁ የሃገራችን ክፍል በአፋር ሱባኤ ገቡ:: ቦታውም ደብር ሐዘሎ ነበር:: በቦታው ለ፻፶፭ ቀናት ከቆሙ ሳያርፉ: ከዘረጉ ሳያጥፉ: እህል ውሃ ሳይቀምሱ ጸለዩ::

በሱባኤያቸው ፍጻሜ ግን ቅዱስ መልአክ መጥቶ "ሳሙኤል ወደዚያ ተራራ ሒድ:: የስምህ መጠሪያ እርሱ ነውና:: ይህ ግን የሌላ ሰው [የአባ አንበስ ዘሐዘሎ] ርስት ነው" አላቸው:: ጻድቁም ወዳላቸው ተራራ ሒደው ቢጸልዩ ከሰማይ ብርሃን ወረደላቸው::

በመንፈቀ ሌሊት የበራው ብርሃን እስከ ጐረቤት መንደር ሁሉ በመድረሱ የአካባቢው ሰው "ወገግ አለኮ-ነጋ" ብለውዋል:: በዚህ ምክንያት ዛሬም "ደብረ ወገግ" ይባላል:: ይህ ቦታ ዛሬም ድረስ ንጹሕ ልብ ላላቸው አበው በብርሃን ተከቦ ይታያል::

ጻድቁ የወለዷቸው ብዙ ሥውራንም በሥፍራው ይገኛሉ:: ቦታው የአንበሶች መኖሪያ በመሆኑ ጠላት መናንያኑን ማጥቃት አይችልም:: ሳሙኤል ዘወገግም የሚጸልዩት በአናብስት ተከበው ነበር:: በቦታው አንዳንዴም አንበሶች ሲሰግዱ ይታያል ይባላል:: ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ግን እንዲህ በቅድስና ተመላልሰው በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ሱማሌ ክልል ውስጥ በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: የጻድቁ ልደት ሐምሌ ፱ : ፍልሠታቸው ደግሞ ግንቦት ፳፯ ነው::


🕊 † አባ ጸቃውዐ ድንግል † 🕊

እኒህ ጻድቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: የስማቸው ትርጉም "የድንግል ማርያም ወለላ ማር" ማለት ሲሆን ዜና ሕይወታቸው እንደ ስማቸው ጣፋጭ ነው::

የእኒህ ጻድቅ አባታቸው የተመሰከረላቸው ሊቅና የገዳም መምሕር ናቸው:: ምክንያቱም ጸቃውዐ ድንግልን ከወለዱ በሁዋላ መንነዋልና:: አባት የደብረ ዘኸኝ መምሕር ሳሉ ልጃቸው ጸቃውዓ ድንግልን ወደ ገዳሙ ወስደው አሳደጉዋቸው::

በዚያውም ጾምና ጸሎትን: ትዕግስትና ትሕርምትን አስተማሯቸው:: ቅዱሳት መጻሕፍትንም በወጉ አስጠኗቸው:: አባ ጸቃውዐ ድንከግልም በጐውን የምናኔ ጐዳና ከተማሩ በሁዋላ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ::

፵ ዓመት ሲሞላቸው ግን አባታቸው ዐረፉ:: መነኮሳት አበውም ተሰብስበው "ከአንተ የተሻለ የለም" ሲሉ ጸቃውዐ ድንግልን የደብረ ዘኸኝ መምሕር አድርገው ሾሟቸው:: ጻድቁም ቀን ቀን ሲያስተምሩ ይውሉና ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::

በሌሊትም ከባሕሩ ወጥተው የአካላቸው ርጥበት ደርቆ ላበታቸው እስኪንጠፈጠፍ ድረስ ይሰግዱ ነበር:: በዚህ መንገድም ራሳቸውን ገዝተው: መነኮሳትንም ገርተው ያዙ:: እግዚአብሔርም ክብራቸውን ይገልጽ ዘንድ ብዙ ተአምራትን በእጃቸው አሳይቷል::

አንድ ቀን አባ ጸቃውዐ ድንግል መንገድ ሲሔዱ ሁለመናው በቁስል የተመታ አንድ መጻጉዕ ነዳይ ወድቆ አዩ:: ወደ እርሱ ሲደርሱ ምጽዋትን ለመናቸው:: ጻድቁ ግን "የምሰጥህ ነገር የለኝም:: ግን የፈጣሪየን ስጦታ እሰጥሃለሁ" ብለው: በውሃ ላይ ጸልየው ረጩት::

ያ መጻጉዕም አካሉ ታድሶ: እንደ እንቦሳ ዘሎ ተነሳ:: ደስ እያለው: ፈጣሪውንም እያከበረ ወደ ቤቱ ሔዷል:: አባ ጸቃውዐ ድንግልም በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል::


🕊 † ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት † 🕊

ይህ ቅዱስ በዘመነ ሰማዕታት: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዱ ነው:: ቅዱስ ድሜጥሮስ ስቅጣር ከሚባል ደግ ባልንጀራው ጋር በበጐው ጐዳና ሲኖሩ የመከራው ዘመን ደረሰ:: መወሰን ነበረባቸውና ፈጣሪያቸውን ከሚክዱ ሞትን መረጡ::

አስቀድሞም ሲያስተምር በመገኘቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ በንጉሡ እጅ ወደቀ:: ንጉሡ መክስምያኖስም እሥራትን አዘዘበት:: በዚያ ወራት ደግሞ የንጉሡ ወታደር የሆነና በጣዖት የሚመካ አንድ ጉልበተኛ ነበር::

ማንም በትግል አሸንፎት ስለማያውቅ ጣዖታዊው ንጉሥ ይመካበት ነበር:: አንድ ቀን ግን አንድ ክርስቲያን ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቅዱስ ድሜጥሮስን "ባርከኝና ያንን ጣዖታዊ ጉልበተኛ እጥለዋለሁ" አለው::

የቅዱሱን ጸሎትና በረከት ተቀብሎም በንጉሡ አደባባይ ታግሎ ጣለው:: ንጉሡና የጣዖቱ ካህናትም በእጅጉ አፈሩ:: በሁዋላ ግን ይህንን ያደረገው ቅዱስ ድሜጥሮስ መሆኑ በመታወቁ ከባልንጀራው ቅዱስ ስቅጣር ጋር በዚህች ቀን ገድለዋቸዋል::

አምላከ አበው ቅዱሳን ጸጋ ክብራቸውን ያብዛልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[ † ጥቅምት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አቡነ ሳሙኤል ጻድቅ [ዘደብረ ወገግ]
፪. አባ ጸቃውዐ ድንግል [ዘደብረ ዘኸኝ]
፫. ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ስቅጣር ሰማዕት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፬. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
፮. ቅድስት አርሴማ ድንግል
2024/11/16 13:25:45
Back to Top
HTML Embed Code: