Telegram Web Link
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖   መስከረም ፳፫ [ 23 ]    ❖

[  ✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን ወሰማዕት አውናብዮስና እንድርያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞  ]


† 🕊 ቅዱሳን አበው አውናብዮስ ወእንድርያስ 🕊

፬ኛው መቶ ክ/ዘ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዘመነ ከዋክብት ይባላል:: ምናልባትም በዓለም ላይ ላለፌት ፩ ሺህ ፭ መቶ ዓመታት ያንን ዘመን መልሶ ማየት አልተቻለም::

-  ያ ዘመን ብዙ ሰማዕታት ነበሩበት::
-  ያ ዘመን ብዙ ሊቃውንት ነበሩበት::
-  ያ ዘመን ብዙ ጻድቃን ነበሩበት::
-  ያ ዘመን ብዙ ደናግል ነበሩበት::
-  ያ ዘመን ብዙ መነኮሳት ነበሩበት::
-  ያ ዘመን ብዙ ባህታውያን [ግኁሳን] ነበሩበት::

ዘመኑ ዘመነ ብርሃን ነው:: እልፍ አእላፍ ቅዱሳን በዚህ ዘመን አብርተዋልና:: ጠላት ሰይጣንን ከቦታው አሳድደው አስጨንቀውታል:: በዚህ ዘመነ ብርሃን ከወደ ምሥራቅ ካበሩ ከዋክብት መካከል ደግሞ በዚህ ዕለት አባቶቻችን ቅዱሳን አውናብዮስና እንድርያስን እናዘክራለን::

ቅዱሳኑ ባለ ብዙ ሃብት ነበሩ:: ከሰማዕታት: ከጻድቃን: ከደናግል: ከሊቃውንቱም አሉበት:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

በተጠቀሰው ዘመን በቅዱስ ጊዮርጊስ ሃገር በልዳ ከከበሩ ወገኖች ተወልደዋል::

የቅዱሳኑ ወላጆች ክርስቲያኖች: በዚያውም ላይ ባለ ሥልጣኖችና ሃብታሞች ነበር:: ልጆቻቸውን [አውናብዮስንና እንድርያስን] ሥጋዊውንም: መንፈሳዊውንም ትምሕርት አስተምረዋቸዋል:: ወጣት በሆኑ ጊዜ ወላጆቻቸው የዚህን ዓለም ነገር ሲያስቡላቸው: እነሱ ግን የተሻለውን እድል ያስቡ ነበር::

ዘወትር ገድላተ ቅዱሳንን ያነቡ: ዜና አበውን ይሰሙ ነበርና ይመንኑ ዘንድ ልቡናቸው አወካቸው:: በአንዲት ሌሊት ግን በመንፈስ ቅዱስ አጋዘዥነት ወስነው: ከሃገራቸው ልዳ ወጥተው ወደ ገዳም ሔዱ::

ክብር ለቅዱሳኑ አባ ሮማኖስና አባ በርሶማ ይሁንና ወቅቱ በሶርያ ምድር ገዳማዊ ሕይወት ተስፋፍቶ: ብዙ አድባራት በበርሃ ውስጥ ነበሩ:: ፪ቱ ቅዱሳንም በአንዱ ገዳም ውስጥ ገብተው አገለገሉ::

ተጋድሏቸውን እያበረቱ እስከ ምንኩስና ደረጃም ደረሱ:: ተጋድሏቸው በጾም: በጸሎትና በትእግስት ብቻ አይደለም:: በትሕትና በፍቅር በደግነትና በመታዘዝም ጭምር ነበር እንጂ::

የምንኩስናና የገዳማዊ ሕይወት ጠላት 'ፍቅረ ዓለምና ፍትወት እንስሳዊት' ናቸው:: አንድ ሰው ከዚህ ዓለም ቁሳቁስ ሳይርቅ መናኝ መሆን አይችልም:: ቅዱሳኑ ግን በመንኖ ጥሪት ይህችን ዓለም ከነኮተቷ ናቁዋት: አቃለሏት::

የሥጋ ፈቃዳቸውን ያጠፉ ዘንድ ሰውነታቸውን በጾምና በጸሎት: ዕረፍትም በማሳጣት ቀጧት:: እግዚአብሔር ደግሞ ስለዚህ ፈንታ ጸጋውን አበዛላቸው:: ቅዱሳኑ በሶርያ ገዳማት ለዘመናት ከተጋደሉ በሁዋላ ወደ ግብጽ ለመውረድ ወሰኑ:: ምክንያታቸው ደግሞ :-

፩ኛ. ከውዳሴ ከንቱ ለመራቅ
፪ኛ. ከቅዱሳን አበው ለመባረክ እና
፫ኛ. ለተሻለ ተጋድሎ ለመብቃት ነበር:: እየጸለዩ እያመሰገኑም ግብጽ: ቀጥሎም ገዳመ አስቄጥስ ደረሱ::

ታላቁ ርዕሰ መነኮሳት አባ መቃርስን ፊት ለፊት ቢያገኙት ደስ አላቸው:: ሐሴትንም አደረጉ:: እግዚአብሕርን በማደሪያዎቹ ማግኘት ይቻላልና:: የታላቁ ቅዱስ ደቀ መዝሙር ሆነው: በድንግልና ተጠብቀው: በተጋድሎ በርትተው በቦታው ለ፫ ዓመታት ቆዩ::

እግዚአብሔር ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ፈልጐአቸው ነበርና በዚያ ሰሞን በከተማ የነበሩ ሊቃውንት ወደ ገዳም መጡ:: ገዳማውያንንም ዻዻስ ስላረፈብን "የምንሾመው መልካም እረኛን ስጡን" አሏቸው::

ገዳማውያኑ ሱባኤ ገብተው ቢጠይቁ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ አውናብዮስን መረጠ:: አበውም ቅዱሱን ዽዽስና ሲሾሙት ወንድሙን እንድርያስን ረዳት አደረጉት:: ፪ቱ ቅዱሳን ከበርሃ ወደ ከተማ መውጣታቸውን ተከትሎ ተጋድሏቸውን ለማበርታት ወሰኑ::

ምክንያቱም ለአንድ ገዳማዊ ከተማ ውስጥ ከመኖር በላይ ፈተና የለምና:: ቅዱሳኑ ቀን ቀን ድውያንን ሲጠይቁ: ሙታንን ሲቀብሩ: ሕዝቡን ሲያስተምሩ: ሥጋውን ደሙን ሲያቀብሉ ውለው ሌሊት ይጋደላሉ::

ለፈቃደ ሥጋቸው ሳያደሉ እንዲህ ባለ ቅድስና ኖረው ደግሞ ሌላ ፈተና መጣ:: የከተማው ሃገረ ገዢ አረማዊ በመሆኑ "ለጣዖት ስገዱ: ክርስቶስን ካዱ" ይል ጀመር:: ቅዱሳኑ ሕዝቡን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ሊያስተምሩ ወደዋልና መኮንኑን "ተው! ተሳስተሃል" አሉት::

በዚህ ምክንያትም ብዙ ስቃይ ገጠማቸው:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት ሰማዕት ሆነዋል:: ጌታም ስለ ድንግልናዊ ሕይወታቸው: ስለ ወንጌል አገልግሎታቸውና ስለ ሰማዕትነታቸው ፫ አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል::

አምላከ አበው ቸርነቱን ይላክልን:: የቅዱሳኑን በረከትም ያሳድርብን::

🕊

[  † መስከረም ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን ጻድቃን አውናብዮስ ወእንድርያስ [ሰማዕታት]
፪. ቅዱስ ጐርጐርዮስ መንክራዊ
፫. ቅድስት ቴክላ ድንግል
፬. ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሰማዕት

[   †  ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፫. ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን [ንጉሠ እሥራኤል]
፬. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፭. ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
፮. አባ ሳሙኤል
፯. አባ ስምዖን
፰. አባ ገብርኤል

" በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: " [፩ዼጥ.፫፥፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[  †  እንኩዋን ለቅዱስ ጐርጐርዮስ መነኮስ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና ለቅዱስ አድሊጦስ ሐዋርያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]


† 🕊 ቅዱስ ጐርጐርዮስ መነኮስ 🕊

በዚህ ስም ተጠርተው: ለምዕመናን አብርተው ያለፉ አባቶቻችን ብዙ ናቸው:: ለምሳሌም :-

-  ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
-  ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
-  ጐርጐርዮስ ዘሮሜ
-  ጐርጐርዮስ መንክራዊ
-  ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
-  ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓትን መጥቀስ እንችላለን::

ከእነዚህ ዐበይት ጐርጐርዮሶች አንዱ ገዳማዊው ቅዱስ ዛሬ የሚከበረው ነው:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ የተወለደው በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን በላይኛው ግብጽ አካባቢ ነው:: ወላጆቹ እጅግ ባለ ጠጐች በመሆናቸው የሚፈልገውን ሁሉ አሟልተው አሳድገውታል::

በተለይ ደግሞ ሥጋዊ [የዮናናውያንን ጥበብ] እንዲማር አድርገው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሰደውታል:: በዚያም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ከሥርዓቱ ጋር አጥንቶ እጅግ አንባቢ ስለ ነበረ አናጉንስጢስ [አንባቢ] ሆኖ ተሾመ::

አንባቢ በሆነባቸው ዘመናትም ወጣ ገባ ሳይል ያገለግል ነበርና ጣዕመ መንፈስ ቅዱስ አደረበት:: ስለዚህም አንደበቱ ጥዑም [ለዛ ያለው] ነበር:: ትንሽ ቆይቶም አበው 'ይገባሃል' ብለው ዲቁናን ሾሙት:: አሁንም ታጥቆ ያለ ዕረፍት ማገልገሉን ቀጠለ::

ዘመኑ ነጫጭ ርግቦች [የተባረኩ መነኮሳት] የበዙበት ነበርና ቅዱስ ጐርጐርዮስ አዘውትሮ ወደ ገዳም እየሔደ ይጐበኛቸው: በእጆቻቸውም ይባረክ ነበር:: በተለይ ሊቀ ምኔት ታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ [አባ ባኹም] በቅርቡ ነበርና ሁሌ እየሔደ ይጨዋወተው ነበር::

ትንሽ ቆይቶ ግን ቅዱሱ የምናኔ ፍላጐቱ እየጨመረ ሔደ:: አንድ ቀን ከገዳም ውሎ ሲመለስ ወላጆቹ ጥያቄ ጠየቁት:: "ልናጋባህ እንፈልጋለንና ምን ትላለህ?" አሉት:: እርሱም ጭራሹኑ እንደማይፈልግ መለሰላቸው:: ሊያሳዝኑት አልፈለጉምና ድጋሚ አልጠየቁትም::

ትንሽ ቆይተውም ተከታትለው ዐረፉ:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወላጆቹን ቀብሮ: ሃብት ንብረቱን ሸጦ ጉዞ ጀመረ:: ወደ አባ ዻኩሚስ ደርሶም ያን ሁሉ ገንዘብ በታላቁ ቅዱስ ፊት አፈሰሰው:: "ምን ላድርገው ልጄ?" ቢለው "አባቴ! ፈጣሪህ ያዘዘውን" አለው::

አባ ዻኩሚስም መነኮሳት በመብዛታቸው ቤት አልነበረምና ብዙ ቤቶችን አነጸበት:: የቅዱሱ ገንዘብ ገዳም ከታነጸበት በሁዋላ ምናኔን አንድ ብሎ ጀመረ::

ቅዱሱ ባጭር ታጥቆ: በጾምና ጸሎት: ውሃ በመቅዳት: በመጥረግ: ምግብ በማዘጋጀት: እግዚአብሔርንም አበውንም አስደሰተ:: ቅዱሱ ምንም ቢናገሩት አይመልስም:: ማንንም ቀና ብሎ አያይም::

"እሺ" ከማለት በቀር ትርፍ ቃል አልነበረውም:: በጸሎት እንባው: በስግደት ደግሞ ላቡ ይንቆረቆር ነበር:: ፍቅሩ: ትዕግስቱ: ትሕትናውና ታዛዥነቱ እጅግ ብዙ ዓለማውያንን ማረከ:: ስለ እርሱ የሰሙ ኃጥአን ሔደው ምንም ሳይናገራቸው በማየት ብቻ ይማሩ ነበር:: ፊቱ ብሩህ: ደግና ቅን በመሆኑ እርሱን ማየቱ በቂ ነበር::

ለ፲፫ ዓመታት በገዳመ ዻኩሚስ ከተጋደለ በሁዋላ ወደ ገዳመ ቅዱስ መቃርስ ከ፪ኛው አባ መቃርስ ጋር ተጉዋዘ:: በዚያም በዓት ወስኖ ከሰው ጋር ሳይገናኝ ፯ ዓመታትን አሳለፈ:: በጸጋ ላይ ጸጋ: በበረከት ላይ በረከት ሆኖለት በ፳፪ኛ ዓመቱ አባቶችን ሰበሰባቸው::

መንገድ ሊሔድ መሆኑን ነግሯቸው "በጸሎት አስቡኝ" አላቸው:: በማግስቱ በዚህ ቀን ሲመጡ ግን በፍቅር ዐርፎ አገኙት:: መነኮሳትም በክብር ገንዘው: ከበረከቱ ተሳትፈው: በታላቅ ዝማሬ ቀብረውታል::


†  🕊 ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 🕊  †

ኢትዮዽያዊቷ ቅድስትእናት ክርስቶስ ሠምራ ቅንነቷ: ደግነቷና ቅድስናዋ እጅግ የበዛ ነው:: አንድ ቀን ግን ገና በትዳር ውስጥ እያለች: ከአገልጋዮቿ አንዷን ትጠራትና ታዛታለች:: ያቺ አገልጋይ ግን የታዘዘችውን ጀሮ ዳባ ልበስ ብላ ሳትታዘዛት ትቀራለች::

ደጋግማ ብትነግራትም ልትሰማት አልቻለችም:: ያን ጊዜ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልትገስጻት ብላ ጠጠር ብትወረውርባት ያች አገልጋይ ወድቃ ሞተችባት:: ቅድስቲቱ እጅግ ደንግጣ አለቀሰች:: የምታደርገውንም አጣች::

ወዲያው ግን ፈጠን ብላ: ወገቧን ታጥቃ ትጸልይ ጀመረች:: "ጌታየ ሆይ! ከሞት አስነሳልኝና ዓለምን ትቼ በቀሪ ዘመኔ አንተን አገልለግልሃለሁ" ብላ ፈጣሪን በብዙ እንባ ተማጸነችው:: ያን ጊዜም አገልጋዩዋ ከሞት ተነሳችላት::

ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ጊዜን አላጠፋችም:: ልጆቿን በቤት ትታ: ሃብትን ብረቷን ንቃ: አንድ ልጇን አዝላ: ቤቷን እንደ ተከፈተ ትታው ወደ ገዳም ወጣች:: በዚህ ዕለትም [መስከረም ፳፬ ቀን] ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባች::


†  🕊 ቅዱስ አድሊጦስ ሐዋርያ 🕊 †

ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው በግሪክ አቴና [ATHENS] ውስጥ ሲሆን በነገድ እሥራኤላዊ ነው:: በአደገባት አቴና ከተማ ሥርዓተ ኦሪትን ከወገኖቹ: የግሪክን ፍልስፍና ደግሞ ከአርዮስፋጐስ ተምሯል:: መድኃኔ ዓለም ዘመነ ስብከቱ ሲጀምር ግን አድሊጦስ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ አደመጠው: ተማረከበትም::

ወዲያውም "ጌታ ሆይ! ልከተልህ?" ሲል ጠየቀው:: ልብን የሚመረምር ጌታም ፈቅዶለት ከ፸፪ቱ አርድእት ደመረው:: ከዚያም ከጌታችን ዘንድ ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ: ለወንጌል አገልግሎት ተሠማርቶ በርካታ አሕዛብን አሳምኗል:: በመጨረሻም ተወልዶ ባደገባት አቴና በዚህች ቀን ገድለውታል::

አምላከ ቅዱሳን በትእግስት: በፍቅርና በትሕትና ይሸልመን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

🕊

[  †  መስከረም ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ገዳማዊ
፪. ቅድስ ክርስቶስ ሠምራ [ደብረ ሊባኖስ የገባችበት]
፫. ቅዱስ አድሊጦስ ሐዋርያ [ከ፸፪ቱ አርድእት]
፬. አቡነ ሰላማ

[   †  ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት [መምሕረ ትሩፋት]
፪. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፫. አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
፬. ቅዱስ አጋቢጦስ [ጻድቅ ኤዺስቆዾስ]
፭. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፮. ፳፬ቱ "24ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ሱራፌል]
፯. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም [ኢትዮዽያዊ]

" ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር አያቀናናም:: ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም:: ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል። ሁሉን ያምናል:: ሁሉን ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል::" [ቆሮ.፲፫፥፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
በቤተክርስቲያን የጽጌ ማኅሌት እንጂ የጽጌ ጾም የሚባል ነገር የለም¡
━━━━━━━✦༒🌻 ༒✦━━━━━━━ 

📌 ሙሉ ይነበብ

የደብረ ሊባኖስ አገልጋይ የሆኑ አንድ አባት ከወንድሞች ጋር ሆነን ቅድመ ቅዳሴ ተምረን፣ ተመክረንና አድምጠን እንወጣበት በነበረበት ጉባኤ ቤት በተለየ መልክ በመጪው "የጽጌ ጾም" ስለሚገኘው በረከት እየነገሩን  አባቶች በልዩ ፍቅር ተጠብቀው እንዴት እንደተጠቀሙባት እየነገሩን እንድንዘጋጅ  ይመክሩን ጀመር ። በቸኮለ ማቅኛ (ድፍረት በነዳው አንደበት) ድንገት ማረም አማረኝና  «በቤተክርስቲያን ወርኃ ጽጌ ፣ ዘመነ ጽጌ ፣ ማኅሌተ ጽጌ  እንጂ የጽጌ ጾም የሚባል ነገርኮ የለም አባታችን!» አልኳቸው። 

አልተናደዱም ግን አዘኑ። በትካዜ እጅጉን ዝግ ባለ ድምጽ "እንዲያ እያላችሁ ነው ምታስተምሩት? " አሉኝ። "ለምን መሰልዎት አባታችን… " ብዬ ለማስረዳት እኔ የጽጌን ጾም ንቄና አጥቅቼ ሳይሆን የፈቃድ ጾም ስለሆነ እያልኩ ላብራራ ስንደረደር በከንቱ መውተርተሬን ገትተው እንዲህ አሉ "ተወው የኔ ልጅ አባቴ ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ብሎሃል «ጾም ታጸምም ኵሎ ፍትወታት ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና» #ጾም_የሚባል_የሌለው_በዓለ_ሃምሳ_ብቻ_ነው። ቀንበር አለዘብን ብላችሁ ሸክም አታክብዱ፤ መብል ሥጋን ያገዝፋል ጾም ግን ሰውነትን ያቀላል …  ዛሬማ ፍቅር በራቀበት፣ ተስፋ በመነመነበት፤ ትውልድ እያለቀ ፣ እምነት እየደረቀ  ያለጊዜዋ ምድርን ልታሳልፉ  ጾም የለም እያላችሁ መስበክ ጀምራችኋላ? " ተግሳጹ ከጅራፍ በላይ የሚያም ነበር!  ያኔ  ኅሊናውን ዋሻ፣ አንደበቱን ጋሻ አድርጎ ራሱን የሚከላከል «ሰው» በተፈለገው ልክና በተገቢው መንገድ መጥፋቱ እያስጨነቃቸው  «ምላሱ የሰላ አእምሮው የላላ» ከልክ በላይ የሚፈነጭ የኔቢጤው በየቦታው "ጾመ ጽጌን" ማውገዙ  እጅጉን ሕመም እንደሆነባቸው አስረድተው በአላዋቂነት ስለሰጠሁት ማቅኛ ይቅርታዬን ተቀብለው አለፉኝ። 

ከቅዱስ ያሬድ የነገሩኝን እያሰላሰልኩ 
ጾመ … ጻመወ …  ጸመወ … (ጾመ፣ መከራ ተቀበለ፣ ዝም አለ) የሚለውን ዘር እየቆጠርኩና እያዛመድኩ   ጿሚ፣ ጸማዊ፣ ጽምው ለመሆን በመጣር ከጽሙና መንደር ደርሶ መቆጠብ ያለውን ዋጋ እየመዘንኩ ተመለስኩ።

ባለ ብዙ መልእክት ሆኖ "«ጾም ታጸምም ኵሎ ፍትወታት ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና» አለ አባቴ ቅዱስ ያሬድ" ያሉት በውስጤ ተመላለሰ። 

ጾም የሥጋን ፍላጎቶች ሁሉ ጸጥ ታደርጋለች። ለወጣቶችም ዝምታን ታስተምራቸዋለች።  (እውነት ነው እርጋታ፣ ዝምታ፣ ጽሙና…  የጾም ውጤት ነው) 

በቤተክርስቲያናችን የበዙ የጾም ቀናት አሉን፤ በዓመት ውስጥ በአጠቃላይ ወደ ፪፻፷ ገደማ ይደርሳሉ ከእነዚህ ውስጥ ወደ ፩፻፹ የሚጠጉ ቀናት ለሁሉም አማንያን እንደ ግዴታ በአዋጅ አጽዋማት ውስጥ ተካትተዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በካህናቱ እና ሌሎች  ምዕመናን በቀኖና፣ በፈቃድ…  የሚጾሟቸው ናቸው። መናንያኑ ግን ከዓመት እስከ ዓመት የዱር ዕፀው ቅጠላ ቅጠል ከውኃ ጋር ሰንበትና በዓለ ፶ እየቀመሱ ከዓመት እስከ ዓመት ይጾማሉ። 

【 Ethiopian Christians observe an extraordinary number of fast days, generally reckoned to be about 250. Of these approximately 180 are obligatory for all believers, while the rest are observed by the clergy and other particularly devout individuals. In addition to the organized calendric fasts, throughout the history of the Ethiopian Church there were ascetics renowned for their extreme fasting, often subsisting on little more than wild plants and water.】  ⇝ Sergew Hable Selassie “Worship in the Ethiopian Orthodox Church” & "The Church of Ethiopia: a Panorama of History and Spiritual Life" 

ቅዱስ ያሬድ ሌላ ምክርም አለው ፦ 

"በፍኖተ ጽድቅ ፍትሑ ለእጓለ ማውታ ወአነሂ እትመየጥ ኀቤክሙ ለሣህል ከመ ፈለገ ሰላም ዛቲ ጾም በቍዔት  ባቲ ትፈሪ ጽድቅ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና ወታበጽሕ ውስተ አዕምሮ ዚአሁ" 

በእውነት መንገድ ለድሃ-አደግ ፍረዱ (የተቸገረውን እርዱ)  እኔም ወደእናንተ ለይቅርታ እንደ ሰላም ወንዝ እመለሳለሁ፤  ጥቅም የሚገኝባት  ይህች ጾም ጽድቅን የምናፈራባት ለወጣቶች እርጋታን የምታስተምር እርሱን ወደማወቅ የምታደርስ ናት ። 

የተዋህዶ ዓይን የኢትዮጵያ ብርሃን ቅዱስ ያሬድ ሌላም ምዕዳን ይጨምራል 

ጾም ቅድስት ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና ዛቲ ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ተመጠወ ሙሴ ሕገ እግዚአብሔር ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ኤልያስ ዓርገ ውስተ ሰማያት ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ዳንኤል ድኅነ እምአፈ አናብስት ጾም ቅድስት ሶስና ድኅነት እምዕደ ረበናት ጾም ቅድስት ዓቀመ ኢያሱ ፀሐየ በገባዖን ጾም ቅድስት ጳውሎስኒ ይቤ ትግሁ እንከ አኃውየ በጾም ወበጸሎት ዛቲ ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ጾም ቅድስት ትሚህሮሙ ለወራዙት ጽሙና። 

ቅድስት ጾም ለወጣቶች እርጋታ ዝምታን ታስተምራቸዋለች።  ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት። በዚህች በተቀደሰችዋ ጾም  ሙሴ የአምላኩን ሕግ ተቀበለባት፤  ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት። በዚህች ቅድስት ጾም ኤልያስ ወደ ሰማይ ዐረገባት ፤  ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት። በዚህች ቅድስት ጾም ዳንኤል ከአንበሶች አፍ ዳነባት በዚህች ቅድስት ጾም ሶስና ከመምህራኑ ክስ ተርፋለች በዚህች ቅድስት ጾም ኢያሱ በገባዖን ፀሐይን አቆመ ። ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት! ጳውሎስ እንዲህ አለ ‘ እንግዲህ ወንደረሞቼ በጾምና በጸሎት ትጉ’ ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት። በዚህች በተቀደሰችዋ ጾም … ቅድስት ጾም ለወጣቶች እርጋታ ዝምታን ታስተምራቸዋለች። 

ደራሲውም እንዲህ ሲል መክሮናል 

… ማርያም ታቦት ጽላተ ኪዳን ሐዲስ፣ 
ቅብዕኒ ርጢነ ጾም እስከ ሰኮና እግር ወርእስ፣ 
እስመ ጾም ትፌውስ ሕማማ ለነፍስ። 

ለሐዲስ ኪዳን ጽላት ታቦቱ ፡ ማርያም አንቺ ነሽና
የጾም መድኃኒቱን ቀቢኝ ፡ ከራስጠጉር እስከ እግር ሰኮና
የነፍስ ሕመም የሚፈወስ ፡ በጾም «በጸሎት» ነውና። 

እንግዲህ ከአባቴ ይኼን ያዝኩላቸው በቤተክርስቲያናችን ጾም የሌለው ለበዓለ ሃምሳ ብቻ ነው። ይልቅ ሰውን በማንጠቅምበት አልፎም ለማያድንም ምክንያት ጾመ ጽጌን አንንቀፋት።

"ወዝኬ ዘሰ ዘይሜህር ዘእንበለ ይኅሥሡ እምኔሁ ወዘእንበለ ምክንያተ ድልወት ለበቁዔተ ሰማእያን ውእቱኬ አብድ ወአኮ ጠቢብ ➺ ይኸውም አስተምረን ሳይሉት እና ሰሚዎቹን የሚጠቅምበት ምክንያት ሳይኖረው ላስተምራችሁ የሚል ሰው አላዋቂ ነው እንጂ አዋቂ አይባልም፡፡ ሰነፍ እንጂ ጠቢብ አይባልም" (ፊልክስዩስ) 

እንኳን ለጽጌ ጾም አደረሰን አደረሳችሁ። በማኅሌት የታጀበውን ተወዳጁን ዘመነ ጽጌ ወርኃ ጾም ተደርቦበት የበረከት ዋጋና በጎ ምላሽ የሚያሰጠን ያድርግልን። 
ከቴዎድሮስ በለጠ
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                          †                          

🌼  [   🕊    ወርኃ ጽጌ    🕊   ]  🌼

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ ከመስከረም ፳፮ [ 26 ] እስከ ኅዳር ፮ [ 6 ]

“እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ”

[ ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን እያቀፍሽው በተአምርና በንጽሕና ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ድንግል ማርያም ሆይ ከልቅሶ ከሐዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ ፤ መልካማዬ ከደስተኛው ገብርኤልና እንዳንቺ ርኅሩኅ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ ]

 🕊

[ አባ ጽጌ ድንግል ]

🌼🌼      🌷🌷🌷      🌼🌼                     
                    
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[  † እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው አሸጋግሮ ለቅዱስ ዮናስ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]


† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† ስንዱ እመቤት ቤተ ክርስቲያን [ሃገራችን] ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት መጸው [ጽጌ] : ሐጋይ [በጋ] : ጸደይ [በልግ] ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::

ዘመነ መጸው /ወርኀ ጽጌ/ ጥቢ እየተባለም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ምድር በአበባ የምታጌጥበት: ክረምት የተለፋበት አዝመራ የሚደርስበት በመሆኑ ደስ ያሰኛል:: በጊዜውም :-

፩. የእመቤታችን የቅድስት ድንግል_ማርያም ስደቷ ይታሠባል:: እርሷ ስለ እኛ :-

-  የሕይወት እንጀራን ተሸክማ መራቧን::
-  የሕይወት መጠጥን ይዛ መጠማቷን::
-  የሕይወት ልብስን አዝላ መራቆቷን::
-  ሙቀተ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለውን ተሸክማ ብርድ መመታቷን እናስባለን::
-  ዘመኑ የበረከት ነው::

፪. በሌላ በኩል ጊዜው ወርኀ ትፍሥሕት [የደስታ ወቅት] ነው:: በክረምት የደከመ ዋጋውን አግኝቶ: በልቶ: ጠጥቶ ደስ ይለዋልና:: ያልሠራው ግን ከማዘን በቀር ሌላ እድል የለውም:: ይኼውም ምሳሌ ነው::

ዘመነ ክረምት የዚህ ዓለም ምሳሌ: ዘመነ መጸው ደግሞ የመንግስተ ሰማያት:: በዚህ ዓለም ምግባር ትሩፋትን የሠራ በወዲያኛው ዓለም ተድላን ሲያደርግ ሰነፎች ኃጥአን ግን እድል ፈንታቸው: ጽዋ ተርታቸው ከግብዞች ጋር የመሆኑ ምሳሌ ነው::

በወርኀ ትፍስሕት እንደ ሊቃውንቱ እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባል::

"ድኅረ ኀለፈ ክረምት ወገብአ ዝናም: ዘአስተርአይከ እግዚኦ ጽጌያተ ገዳም :
አፈወ ሃይማኖት ነአልድ ወፍሬ ምግባር ጥዑም :
አትግሃነ ለስብሐቲከ ከመ ትጋሆሙ አዳም :
ለጽብስት ንሕብ ወነአስ ቃሕም::"

† የዘመናት ባለቤት ዘመነ መጸውን ወርኀ ትፍስሕት ያድርግልን::

🕊

🕊  †  ቅዱስ ዮናስ ነቢይ  †  🕊

† ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው:: በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ግን ፯ ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል:: [፩ነገ.፲፯፥፲፯] እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች::

ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ፰፻ ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ::

"ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ [ገራገር] የለምና እንቢ አለ [ሰምቶ ዝም አለ]:: እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ ተርሴስ ኮበለለ::

ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሸት እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ :- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው::

ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ፫ ቀን እና ሌሊት ኖሮ: ሙስና [ጥፋት] ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ [ምሳሌ] ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው::
"ወበከመ ነበረ ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: [ማቴ.፲፪፥፴፱]

ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት [እጣ ወድቆበታልና] "የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው::

እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ፫ ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ፫ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው::

ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ:: የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል::

የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቋ ነነዌ ከ፫፻ ዓመታት በሁዋላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም ፻፸ ዓመት ነው::

† አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

🕊

[  †  መስከረም ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ጸአተ ክረምት [የክረምት መውጫ]
፪. ቅዱስ ዮናስ ነቢይ
፫. ቅዱስ እንጦንዮስ
፬. ቅድስት በርባራ
፭. ሐዋርያት ዼጥሮስ ወዻውሎስ
፮. ቅዱስ ዕፀ መስቀል

[  †   ወርሐዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. አቡነ አቢብ [አባ ቡላ]
፮. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
፯. ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ

" ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ:: " † [ማቴ.፲፪፥፴፱]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊                        💖                       🕊   

  [       🕊  እንኳን አደረሳችሁ   🕊       ]

    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🌼

እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለልጇ ለወዳጇ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለመድኃኒታች ለኢየሱስ ክርስቶስ ለስደታቸው መታሰቢያ ለፈቃድ ጾም [ለጽጌ ጾም] በሰላም አደረሰን።


[ 🕊    ወርኃ ጽጌ   🕊 ]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም ፳፮ [ 26 ] ቀን እስከ ሕዳር ፮ [ 6 ] ቀን ያለው ፵ [ 40 ] ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን [ ዘመነ ጽጌን ] ታከብራለች፡፡ ይህ ፵ [ 40 ] ቀን የእመቤታችንና የጌታችንና የአምላካችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡

በዚህ በወርኃ ጽጌ [ በዘመነ ጽጌ ] የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ [የፈቃድ] የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ ፯ [ 7 ] ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ [ሉቃ.፯፥፵፯] እንዲል፡፡

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች እመቤታችን ከልጇ ጋር በስደት የተቀበለችውን መከራና የደረሰባትን ሀዘን እየሰቡ በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ከእመቤታችን ጸጋንና በረከትን ያገኛሉ፡፡

ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" [ማቴ.፮፥፲፮] የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር !

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


🕊                        💖                       🕊
2024/11/16 13:30:24
Back to Top
HTML Embed Code: