Telegram Web Link
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from M.A
በአርማንያ የሚገኘው የቅዱስ ጐርጐርዮስ ቤተክርስቲያን።
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#VisitAmhara

ግሸን ደብረ ከርቤ !

ግሸን ደብረ ከርቤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአንጋፋነታቸው ከሚታወቁት ቅዱሳን ሥፍራዎች አንዷ ናት፡፡

የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ሌሎች የገዳሟን ታሪክ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው ወደ ግሸን ይጓዛሉ፡፡

በተለይ ከመስቀል በዓል እስከ መስከረም 21፣ ጥር 21 እንዲሁም መጋቢት 10 ወደ ግሸን የሚጓዘው ሕዝብ በመቶ ሽዎች ይቆጠራል፡፡

በረከት ለማግኘት፣ ታሪክ ለማወቅ እና ለመፈወስ ግሸን ለእምነቱ ተከታዮች ቀዳሚ መዳረሻ ናት፡፡

በኢትዮጵያ የሀይማኖት ቱሪዝም ታሪክ ብዙ እንግዶችን በማስተናገድ ግሸን ከቀዳሚዎች መካከል ትገኛለች፡፡

ነገ መስከረም 21 ታላቁ የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ክብረ በዓል ይከበራል፡፡

እንኳን አደረሳችሁ !

(Vist Amhara)

#TourismAndPeace  #GishenDebreKerbe #SouthWollo #ReligiousFestival #Ethiopia #LandOfOrigins

@tikvahethiopia
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[  † እንኳን ለአባ አትናቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


†  🕊  አባ አትናቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት 🕊 †   

† 'ዻዻስ' ማለት 'አባት - መሪ - እረኛ' ማለት ነው:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ ፫ [3] ናቸው:: እነሱም ዲቁና: ቅስና: ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ ፱ [9] ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ዽዽስና ነው::

ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር 'ሸክም: ዕዳ' ሲሆን በሰማይ ግን 'ክብር' ነው:: ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን አይመኝም::

ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ - ማንም ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" [፩ጢሞ.፫፥፩] (3:1) ማለቱን ይዞ 'ሹሙኝ' ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ ነው::

አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኳ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ - መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" [ዮሐ.፲] (10) ስለዚህም ክህነት ዽዽስና ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::

አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች ፬ [4] ቱ የበላይ ናቸው::
እነዚህም የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::

እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ ፬፻፵፫ [443] ፬፻፶፩ [451] ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው [የግብጹ] እና የአንጾኪያው [የሶርያው] ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::

የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች:: በተለይ በግብጽ የነበሩ አበው ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ የከፈሉ ናቸውና በልዩ ታከብራቸዋለች::

ዛሬ ያሉትን አቡነ ታውድሮስን ጨምሮ በመንበሩ ላይ የተቀመጡ ፻፲፰ [118] ሊቃነ ዻዻሳት መካከል አብዛኞቹ ደጐች ነበሩ:: ቢያንስ ገዳማዊ ሕይወትን የቀመሱ: ለመንጋው የሚራሩና በየጊዜው እሥራትና ስደትን የተቀበሉ ናቸው::

ከእነዚህም አንዱ አባ አትናቴዎስ ካልዕ ይባላል:: ይህም አባት በመንበረ ማርቆስ ፳፰ [28] ኛው ፓትርያርክ ነው:: የነበረበት ፷ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ቤተ ክርስቲያን ለ፪ [2] የተከፈለችበት: ለተዋሕዶ አባቶች ስደት የታወጀበት ስለ ነበር ወቅቱ ፈታኝ ነበር::

አባ አትናቴዎስ በዚያው በምድረ ግብጽ ተወልዶ: አድጐ: መጻሕፍትን ተምሮ: ምናኔን መርጦ ሲኖር: መጋቤ ቤተ ክርስቲያን አድርገው መርጠውት አንገቱን ደፍቶ ፈጣሪውን ያገለግል ነበር:: በጊዜው ግብጽ ፓትርያርክ ዐርፎባት እውነተኛውን እረኛ ትፈልግ ነበርና የህዝቡም: የሊቃውንቱም ዐይን ወደ አባ አትናቴዎስ ተመለከተ::

ሁሉም በአንድነት ተመካክረውም "አንተ ለዚህ ሹመት ትገባለህ" አሉት:: እርሱ ግን መለሰ "የለም እኔ እንዲህ ላለ ኃላፊነት አልመጥንምና ሌላ ፈልጉ::" ይህ ነው የክርስትና ሥርዓቱ:: የክርስቶስን መንጋ 'እኔ ችየ እጠብቀዋለሁ' ማለት ታላቅ ድፍረት ነውና::

ነገር ግን "ወአኀዝዎ በኩርህ" ይላል - በግድ ሾሙት:: እርሱም የግል ትሩፋቱን ሳያቋርጥ መንጋውን ተረከበ:: በወቅቱ እንደ አሸን ከፈሉ መናፍቃን ሕዝቡን ይጠብቅ ዘንድ ስለ ሕዝቡ ባፍም: በመጣፍም ደከመ:: በፈጣሪ እርዳታም ለ፯ [7] ዓመታት ሕዝቡን ከተኩላ ጠብቆ አካሉ ደከመ:: በዚህች ቀንም ይህችን የመከራ ዓለም ተሰናብቶ ዐረፈ::

† አምላከ አበው አባቶቻችንን ለመንጋው የሚራሩ ያድርግልን:: ከወዳጆቹ ጸጋ በረከትም ይክፈለን::

🕊

[  †  መስከረም ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. አባ አትናቴዎስ ካልዕ
፪. ቅድስት መሊዳማ ድንግል
፫. ቅድስት አቴና ድንግል
፬. ቅዱስ ስምዖን ዘኢየሩሳሌም
፭. ቅዱስ አብርሃም መነኮስ

[    †  ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፪. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፫. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፬. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
፮. ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት

† " ኤዺስ ቆዾስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና:: የማይኮራ: የማይቆጣ: የማይሰክር: የማይጨቃጨቅ: ነውረኛ ረብ የማይወድ: ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ: በጐ የሆነውን ነገር የሚወድ: ጠንቃቃ: ጻድቅ: ቅዱስ: ራሱን የሚገዛ ይሁን:: " † [ቲቶ. ፩፥፯]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
2024/09/30 18:15:32
Back to Top
HTML Embed Code: