Telegram Web Link
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
✝️ #አስቸኳይ_የይድረሱልኝ_ጥሪ_ለመላው_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ልጆች በሙሉ። #ሼር_ሼር_ሼር በማድረግ እንተባበር።

#በዕለተ_ቀኗ_ስለ_ታላቋ_ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ

#በደቡብ_ኦሞ_ሀገረ_ስብከት_በኬንያ_ጠረፍ #ቱርካና_ሐይቅ_በዳሰነች_ብሔረሰብ አካባቢ ለምትገኘው #ለቡቡዋ_ቅድስት_አርሴማ_ቤተክርስቲያን የአጥር ሥራ በሀገር ውስጥ በባሕር ማዶ ላላቹሁ የኦርቶዶክ ተዋሕዶ ልጆች የምዕመናን ምዕመናት በጸሎት፣ ጉልበት፣ በማቴርያልና በገንዘብ የበኩላችንን አስተዋጾ እናድርግ።

ቤተ ክርስቲያኑ ተስርቶ አጥር ለመሥራት ብረት ቆሞ በማቴሪያልና በገንዘብ እጥርት ሳይሠራ እስከ አሁን ስለቆየ በፎቶ እንደምታዩት የከብቶች ማሰማርያ እየሆነ ስለሆነ ወደ ቦታው ጉዞ ለሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል ስለተዘጋጀ በዚህ ጉዞ አጥሩንም በሽቦ ለማጠር ታስባል።

👉 የአጥር ስፍት፦ #400_ሜትር_ነው#1_ጥቅል #ሽቦ_25_ሜትር_ያጠራል። ለዙርያው በሙሉ የሚያስፈልገው #16_ጥቅል_ነው። የአንዱ ጥቅል ዋጋ #19,500 ብር ነው።

👉 ጠቅላላ የሚያስፈልገው ብር፦ 16x19,500=312,000 ብር ነው።

👉 የቻልን አቅሙ ያለን #312_ሰዎች #አንድ_አንድ_ሺህ_ብር_1000 ብር ብልለግስ አጥሩን ሙሉ ለሙሉ እናጥረዋለን።

👉 የኢትዮጵያ ን ግ ድ ባ ን ክ አካውት ቁጥር፦ #1000341945384 (የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ኮሚቴ)

👉የአቢሲኒያ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ #1169289 ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ደ/ኦ/ሀ/ስ/የ/አ/ኮ።

👉 ለበለጠ መረጃ፦ ስለ ሥራ ለማውራት በአገር ውስጥ በባሕር ማዶ ያላችሁ ምዕመናን በነዚህ ቁጥሮች ይደውሉ፦ 0913914917፣ 0934497866፣ 0921605181።
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
#100_ብር_ለሙሴ #challenge

ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት ላቆሙበት #ለሙሴ_አሻግሬ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና የሚያግዝ #የ100_ብር ቻሌንጅ ይቀላቀሉ....

እህቱ ፍሩታ አሻግሬ ከአረብ ሀገር ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች፤ እኛም 100 በመለገስ የሙሴን ሕይወት እናተርፍ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፍሩታ አሻግሬ
1000629004045

ለበለጠ መረጃ
➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929
➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689

(በዚህ መልካም ተግባር የተሳተፋችሁ ወደባንክ ገቢ ያደረጋችሁበትን @natansolo በውስጥ ያስቀምጡልኝ)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[ †  እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም: አባ ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ]


🕊   †  ሥሉስ ቅዱስ   †   🕊

በአንድነቱ ምንታዌ [ሁለትነት] : በሦስትነቱ ርባዔ [አራትነት] የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ : ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው [የማያምንባቸውን] አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም [ዓለምን በእጁ የያዘ] ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

አባታችን አብርሃም በ፺፱ [99] ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ፹፱ [89] ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: [ወይ መታደል!] በጀርባውም አዘላቸው:: [ድንቅ አባት!] ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው::

ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን [ሐይመት] የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::


🕊   †  ታላቁ አባ ሲኖዳ  †   🕊

የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ :-

¤ በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤ በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤ የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤ በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤ የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤ በ፱ [9] ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤ የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሠለስቱ_ደቂቅ አስኬማ: የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ቅናትን [መታጠቂያ] ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤ የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤ በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ፻ [100] ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ
¤ ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ ያለ ዕረፍት ለ፩፻፲፩ [111] ዓመታት ከ፪ [2] ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው::

በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ አርሲመትሪዳ "[ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው::]

ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር:: በዚህች ዕለት በ፩፻፳ [120] ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው አቡነ ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ [ታላቅ ዛፍ] ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::

🕊   † አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ  †  🕊  
[GIYORGIS_OF_SEGLA]

ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ አባ ጊዮርጊስ እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ::

ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው::

ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር ፵፩ [41] ድርሰቶችን ደረሰ:: [መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ]

ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች :-

፩. ሊቀ_ሊቃውንት
፪. በላዔ_መጻሕፍት
፫. ዓምደ_ሃይማኖት
፬. ዳግማዊ_ቄርሎስ
፭. ጠቢብ_ወማዕምር

ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ፷ [60] ዓመቱ በ፲፻፬፻፲፰ [1418] ዓ/ም  በዚህች ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ ፯ [7] ቀን ነው::

የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

🕊

[ †  ሐምሌ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ [ሥላሴን ያስተናገዱ]
፪. ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
፫. ታላቁ አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን ሁሉ አለቃ]
፬. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ [ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ]
፭.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ [ምጥው ለአንበሳ]
፮. አባ መቃቢስ
፯. አባ አግራጥስ

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፪. አባ ባውላ ገዳማዊ
፫. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

" እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ :- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: " [ዕብ.፮፥፲፫] (6:13)

" የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" [ቆሮ.፲፫፥፲፬]  (13:14)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)


🕊         ቅድስት ሥላሴ      🕊

" የቅድስት ሥላሴ ዕምነት የሃይማኖት መጨረሻ ናት፡፡ የሥላሴ ዕምነት መግቢያ በር ወልድ ዋህድ ብሎ ማመን ነው፡፡

የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሥርዓት በዚህ የሥላሴ አርአያ ተመሠረተ፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም ለታመኑ የሕይወት መታወቂያ ማኅተም ነው ለዝንጉዎች ግን የጥፋታቸው ቁልፍ ነው፡፡

ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የሕሙማን መፈወሻ የክፉዎች አጋንንት ማባረሪያ ነው፡፡

ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የአስማተኞችን ወይም የጠንቋዮችን ጥበብ የሚያጠፋና የሟርተኞችን መርዝ የሚያበርስ [ የሚያከሽፍ ] ነው፡፡

ይህ ግሩም የሥላሴ ስም የበሽተኞች መድኃኒት የሙታን ትንሣኤያቸው ነው፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም አሸናፊ የሆኑ የሰማዕታት የገድላቸው ሞገስ የብሩካን ጻድቃን የጸሎታቸው የመልካም መዓዛ ሽታ ነው፡፡

ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የረከሱትን የሚቀድሳቸው የተዳደፉትን የሚያነጻቸው ነው፡፡ ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም እንደ መጎናጸፊያ እጎናጸፈዋለሁ ከእንቁ እንደተሰራ እንደ እራስ ወርቅም እቀዳጀዋለሁ፡፡

በዚህ ግሩም በሆነ የሥላሴ ስም እታመናለሁ በመጎንበስም እሰግድለታለሁ፡፡ ለዚህ ግሩም አስፈሪና አስደንጋጭ ለሆነ የሥላሴ ስም በፊቱ ተንበርክኬ በደስታ እሰግዳለሁ፡፡"

[  ሰይፈ ሥላሴ  ]

🕊

ኃይልየ ሥላሴ !
[  ኃይሌ ሥላሴ ነው ! ]
ወጸወንየ ሥላሴ !
[  አምባ መጠጊያየም ሥላሴ ነው !  ]
በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ !
[ በሥላሴ ስምም ጠላትን /ዘንዶውን/ እቀጠቅጠዋለሁ ! ]

የአብርሃምን ድንኳን የጎበኙ ሥላሴ : የእኛንም ቤት በቸርነታቸው ይጎብኙልን . . . አሜን !

[       🕊   ክብርት ሰንበት   🕊        ]


💖               🕊                💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[ †  እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃን ወከዋክብተ ገዳም አቡነ ኪሮስ: አባ ብሶይ እና አባ ሚሳኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።  † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †   አቡነ ኪሮስ ጻድቅ   †   🕊

† የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው:: በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል::

አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው:: ተወልደው ባደጉባት ሃገር ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል:: ወንድማቸው [ታላቁ ቴዎዶስዮስ] በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው: አሕጉር አቋርጠው ወደ ግብፅ [ገዳመ አስቄጥስ] መጡ::

እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም:: ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ ገብረ ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ:: "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው:: አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ አቡነ በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል::

ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ:: "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል:: ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል::

አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ::

ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ፴ [30] ዓመታት አልቅሰው: ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን: ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር::

ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ፶፯ [57] ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ [ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና] በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ::

ቅዱስ ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም::

🕊  † የበርሃው ኮከብ አባ ብሶይ  †  🕊

† ታላቁ አባ ብሶይ [ቢሾይ] :-

¤ በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ
¤ በመላእክት መሪነት የመነኑ
¤ የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ባልንጀራ
¤ የአባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር የነበሩ
¤ በአጭር ጊዜ የብዙዎች አባት የሆኑ ሰው ናቸው::

† እንቅልፍን የማያውቁ

¤ በ፵ [40] ቀን ብቻ እህል የሚቀምሱ
¤ የጌታችንን እግር በየቀኑ እያጠቡ የሚመገቡ
¤ ፈጣሪያቸውን በጀርባቸው ያዘሉ [ነዳይ መስሎ አግኝተውት]
¤ በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተጉ
¤ በርካታ ጻድቃንን የወለዱ ታላቅ የፍቅር ሰው ናቸው::

በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሰርተው: ቤተ ክርሰቲያንን በንጽሕናቸው አስደስተው: ሐምሌ ፰ [8] ቀን ዐርፈዋል:: ግብፅ ውስጥ የሚገኘው ገዳማቸው ዛሬም ቤተ አበው: ተአምራት የማይለዩትና ተወዳጅ ነው:: ቦታው መካነ ሱባዔ ወመንክራት ነውና::

🕊  †  አባ ሚሳኤል ነዳይ  †  🕊

† መቼም ያ ዘመን [፬ [4] ኛውና ፭ [5] ኛው ክ/ዘመን] እጅግ የተባረከ ነው:: ቅዱሳኑ በብዛት የባለጸጐችና የነገሥታት ልጆች ናቸው:: አባ ሚሳኤልም የኬልቄዶን ንጉሥ ልጅ ሳሉ መንነው በበርሃ ለ፷፭ [65] ዓመታት ተጋድለዋል:: በመጨረሻ ግን በደዌ ምክንያት ወደቁ:: ለ፭ [5] ዓመታት መነኮሳቱ ሲጠይቁዋቸው ቆይተው ሰለቹ::

ከዛም ለ፲፭ [15] ዓመታት ላበታቸው በግንባራቸው እየተቀዳ: ያለ ምንም ምግብ እያቃሰቱ በበዓታቸው ወድቀው ኑረዋል:: ቸሩ አምላክ ግን ፬ [4] ቱን ሊቃነ መላእክት [ሚካኤል: ገብርኤል: ሩፋኤልና ሳቁኤልን] አዞላቸው ሲጠብቁዋቸው ኑረዋል::

በዚህች ቀንም አቡነ_ኪሮስ መጥተው አጽናንተው: ጌታችንንም ጠርተው እንዲያርፉ አድርገዋል:: መላእክት እያጠኑና እየዘመሩ ጻድቁ ቀብረዋቸዋል:: በመቃብራቸውም ላይ ፈውስ የሆነ ጸበል ፈልቁዋል::

†   እግዚአብሔር የእኛን ያይደለ የጻድቃኑን ቅድስና አስቦ ይራራልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[   † ሐምሌ ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. አቡነ ኪሮስ ጻድቅ [አረጋዊና ገዳማዊ]
፪. አባ ብሶይ ጻድቅ [ኮከበ ገዳም]
፫. አባ ሚሳኤል ነዳይ [ጻድቅ]
፬. አባ ቢማ ሰማዕት
፭. አባ በላኒ ሰማዕት
፮. ቅዱሳን አቤሮንና አቶም [ሰማዕታት]

[   †  ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
፪. ኪሩቤል [አርባዕቱ እንስሳ]
፫. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
፬. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ከ፲፪ [12] ቱ ሐዋርያት]

† " በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው:: የኃጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሠቢያ ለበረከት ነው:: " † [ምሳ.፲፥፯] (10:7)

† " እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: " † [መዝ.፴፮፥፳፰-፴፩] (36:28-31)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
2024/09/29 09:22:43
Back to Top
HTML Embed Code: