Telegram Web Link
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
                        †                             

  †   🕊   ክብርት ሰንበት   🕊   †

❝ የሰው ልጆች ያርፉባት ዘንድ ሰንበትን አዘጋጀ፡፡ ለጻድቃንም ለኃጥአንም ፣ ለሞቱትም በሕይወት ላሉትም ፡ የሰው ልጆች ያርፉባት ዘንድ ሰንበትን አዘጋጀ፡፡

የክርስቶስ ሰንበቱማ እርሷ ናት ፣ ለልዑልም የስሙ ማደሪያ ናት፡፡ ዛሬስ በሰማያት ያለች ተስፋችንና ሕይወታችን በዚህች በተቀደሰች ቀን ነው ፣ በርሷ በሚያርፉባት በሰንበት ቀን፡፡ ❞

[    ቅዱስ ያሬድ    ]

🕊

[ መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪ እና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ማደሪያ [ ምልክት ] የሆንሽ የብርሃን ቀን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ በገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል፡፡ ኃጥአንም ከደይን በአንቺ ይወጣሉ፡፡ ]

[   አባ ጽጌ ድንግል   ]

†                      †                      †
💖                   🕊                   💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                         †                         


💖  [ ሥላሴ ተመስገን ! ]



†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
🕊

[ † እንኳን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ የተድላና የደስታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† በዚሕች ቀን ለ፵ [ 40 ] ዓመታት በመላው ዓለም የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት የተከፈቱበት ቀን ይታሠባል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ :-

- አበው ተስፋ ሲያደርጓት
- ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት
- ሱባኤ ሲቆጥሩላት
- ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል::

† ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :-

- በመጸነሱ ተጸንሳ
- በመወለዱ ተወልዳ
- በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ
- በጥምቀቱ ተጠምቃ
- በትምሕርቱ ጸንታ
- በደሙ ተቀድሳ
- በትንሣኤው ከብራ
- በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ
- በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች::

† አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በመላው ዓለም ዞረው በብዙ ድካም የሠሯት ቤተ ክርስቲያን ለ፪፻ [200] ዓመታት እጅግ የበዙ መከራዋችን አሳልፋለች:: በ፪፻፷፭ [265] ዓ/ም የመጣባት መከራ ግን በዓለም ታሪክ እስካሁን አልታየም:: የወቅቱ ኃያላን ነገሥታት [ዲዮቅልጢያኖስና መክስምያኖስ] ዓለምን ለ፪ [2] ተካፍለው ክርስቲያኖችን የማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ::

በመጀመሪያም በዓለም ያሉ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት እንዲቃጠሉ ካልሆነም እንዲዘጉ : በፈንታቸው ደግሞ አዽሎን: አርዳሚስ የተባሉ ጣዖቶች እንዲተኩ ትዕዛዝ ተሰጠ:: ለ፵ [40] ዓመታት ክርስቲያን ስለሆኑ ብቻ ሚሊየኖች ተገደሉ: ታሰሩ: ተሰቃዩ: ተሰደዱ:: መጻሕፍት ተቃጠሉ: አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ወደሙ::

በአባቶቻችንና እናቶቻችን ላይ ልንናገረው ከምንችለው በላይ ጭንቅና መከራ ደረሰ:: ነገር ግን ቅዱሳኑ ያን ሁሉ ችለው ጸኑ:: ፵፯ [47] ሚሊየን የሚያሕሉትን ደግሞ ሰይፍና እሳት በላቸው:: በዛ ዘመን አንድ ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት ከአሕጉር አሕጉር መሔድን ይጠይቅ ነበር::

ከዚሕ ሁሉ በኋላ ግን እግዚአብሔር "ግፍ ይበቃል" ሲል በ፫፻፭ [305] ዓ/ም ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ:: መክስምያኖስን በጦርነት ሲማርከው አውሬው ዲዮቅልጢያኖስ ግን አብዶ ሞተ:: ይህ ከተደረገ ከዓመታት በኋላ [በ፫፻፲፫ [313] ዓ/ም] ታላቁ ቆስጠንጢኖስ የዓለም መሪዎችን በዚሕች ቀን ጠርቶ አዋጁን በአዋጅ ሻረው:: "ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ:: በፈንታው ደግሞ ሁሉም ጣዖት ቤቶች ይዘጉ" አለ::

በሺሕ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን በወርቅ አስለበጠ:: በዚሕ ምክንያት ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን "ዕለተ ትፍሥሕት [የደስታ ቀን]" ተብላ ትከበራለች::

† ቸሩ አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ይሠውርልን:: ከበረከቷም ያድለን:: ትውልዱ ደካሞች ነንና ከማንችለው ፈተናም ይጠብቀን::

🕊

[ † ሰኔ ፲ [ 10 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፪. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት [ከታላላቆቹ ሶፍያዎች አንዷ ናት]
፬. ቅዱሳት ሰማዕታት ደባሞንና ብስጣሞን [የቅድስት ሶፍያ ልጆች]
፭. ቅዱስ አውሎጊስ ሰማዕት
፮. ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፫. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ]
፭. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
፮. ቅዱስ ዕፀ መስቀል

" ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ:: ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ:: ኢየሩሳሌምስ እርስ በርሷ እንደ ተገለጠች ከተማ ተሠርታለች . . . ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ:: ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ:: " † [መዝ.፻፳፩፥፩-፱] (121:1-9)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

💛

[     ክፍል አንድ     ]

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

የመጀሪያ ጸሎቱ  ፦

❝ አቤቱ አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ አንጻኝ በአንተ ፊት ምንም መልካም ሥራ ያልሠራሁ ኃጢአተኛ ነኝና አቤቱ አንጻኝ፡፡ ከክፉ ነገር ሁሉ አውጣኝ ጠብቀኝ ፥ ከእኔ ጋርም ሁን ብቻዬን ነኝና አትተወኝ አትለየኝ ፤ የኃጢአተኛን አንደበቴን በድፍረት ከፍቻለሁና ቅዱስ የሆነውን ስምህንም አመሰግናለሁ፡፡ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡ ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
                          †                       

🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞

🕊

❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

❝ እግዚኦ መኑ ከማከ ሙታነ አንሣእከ በቃልከ እግዚኦ መኑ ከሚከ ሕይወተ ወሀብከ ሰላመ ለነ ጸጎከ እግዚኦ መኑ ከማከ ንግበር በዓለ ፋሲካ ኵልነ ምስለ ጻድቃኒከ ኅቡረ ፤ ❞

ትርጉም

[ ጌታ ሆይ እንዳንተ ማነው ! ? በቃልህ ሙታንን አነሣህ ፣ ጌታ ሆይ እንዳንተ ማነው ! ? ሕይወትን ሰጠህ ለኛም ሰላም አደልህ ጌታ ሆይ እንዳንተ ማን ነው ! ? የፋሲካን በዐል ከጻድቃንህ ጋር በጋራ በመሆን ሁላችን እናከብራለን። ]

[ ድጓ ዘፋሲካ ]

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ማር ገላውዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †  ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት  †   🕊

† ቅዱስ ገላውዴዎስ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘ በድሮው የሮም ግዛት በአንጾኪያ [አሁን ሶርያ ውስጥ] ነው:: አባቱ አብጥልዎስ የሮም ቄሣር የኑማርያኖስ ወንድም ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ያደገው በቤተ መንግሥት ውስጥ ነው::

ወቅቱ መልካምም ክፉም ነገሮች ነበሩት:: መልካሙ ነገር በቤተ መንግሥት አካባቢ ይኖሩ የነበሩት ልዑላኑ አብዛኞቹ በፍቅረ ክርስቶስ የታሠሩ ነበሩ:: ከእነዚህ መካካከል "ቅዱስ ፋሲለደስ: ቅዱሳኑ :- ፊቅጦር: ቴዎድሮስ: አባዲር: አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: እስጢፋኖስ . . ." ነበሩ:: ቅዱሳቱ "ማርታ: ታውክልያ: ኢራኢ: ሶፍያ. . ." ነበሩ::

አስቸጋሪው ነገር ደግሞ ነጋ መሸ ኑሯቸው ጦርነት ነበር:: የዘመኑ የፋርስና የቁዝ መሪዎች ጦረኞች ነበሩና ዕለት ዕለት ፍልሚያ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ገላውዴዎስ የተመሠከረለት አርበኛና የተባረከ ንጹሕ ክርስቲያን ሆኖ አድጓል:: ከልጅነቱ ጀምሮ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናቱ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት ታሽቷል:: እርሱ የነገሥታቱ ቤተሰብ ነው:: ማዕዱ በየዓይነቱ ሞልቶ ካልመሸ እህል አይቀምስም:: ጸሎቱ ስሙር: ስግደቱ ከምድር: አኗኗሩ በፍቅር ሆነ:: በዚያውም ላይ በድንግልናው የጸና ኃያል ነበር::

በጊዜው የቅዱስ ገላውዴዎስን ያህል መልኩ ያማረ [ደመ ግቡ] በአካባቢው አልነበረም:: ይህ ግን ሊያታልለው አልቻለም:: ሁሉ በእጁ ቢሆንም ለእርሱ ግን ብቸኛ ምርጫው ሃይማኖተ ክርስቶስ ነበር::

ቅዱስ ገላውዴዎስ ለጦርነት ወጥቶ ሲመለስ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ሃይማኖቱን ክዶ: ሕዝቡን ለጣዖት ሲያሰግድ: ክርስቲያኖችን ሲገድል ደረሰ::

†  ቅዱሱ ኃያል የጦር ሰው ነውና ንጉሡን መግደል ሲችል ተወው:: በዚያ ሰሞንም ለገላውዴዎስ ሁለት ምርጫዎች ቀረቡለት :-

፩. ክርስቶስን ክዶ የንጉሡ ተከታይ መሆን:
፪. በክርስትናው ደሙን ማፍሰስ::

የቅዱሳኑ ምርጫቸው የታወቀ ነውና ታስሮ ወደ ግብጽ ተጋዘ:: በዚያ ከመኮንኑ ጋር ስለ ሃይማኖት ተከራክረው መኮንኑ ስለተበሳጨ ቅዱሱን በረዥም ጦር ጐኑን ወጋው:: ዘለፍ ብሎ ነፍሱን ሰጠ:: ሕዝበ ክርስቲያኑ በድብቅ መጥተው የቅዱሱን ሥጋ ሽቱ ቀብተው: ከዝማሬ ጋር ገነዙት:: የጓደኛው እናት ቅድስት ሶፍያ መጥታ ወደ ሶርያ ወስዳዋለች::

† ተወዳጅ: ኃያል: ቡሩክና መልካም ሰው ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት በሆነባት በዚሕች ዕለት በመላው ኦርቶዶክሳውያን ይከበራል::

† አምላካችን የቅዱሱን መንኖ ጥሪት: ትዕግስት: ጸጋና በረከት ያሳድርብን:: አሜን::

🕊

[ † ሰኔ ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት [ሕይወቱ መላእክትን የመሰለ]
፪. አንድ ሺ ሰማንያ ስምንት ሰማዕታት [የቅዱስ ገላውዴዎስ ማኅበር]
፫. አባ ክርዳኑ ሊቀ ጳጳሳት
፬. እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮጵያዊት [የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እህት]
፭. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዳሴ ቤቱ [ግብጽ]

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፫. ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
፬. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ

" የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ:: ሰባኪው :- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል:: " † [መክ. ፲፪፥፩-፱]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

           #ሰኔ ፲፩ (11) ቀን።

እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ነገረ ማርያምን ወደ ግእዝ ቋንቋና አራቱ ወንጌልን ወደ ተለያየ ቋንቋ ለተረጎሙት #ለአቡነ_መዝሙረ_ድንግል ለዕረፍታቸው በዐልና #በግብጽ_ቤተ_ክርስቲያ_ጨምር_ቅድስና ለተሰጣቸው #ለአብረ_ገብረ_ኢየሱስ_ለዕረፍታቸው በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                       ✝️ ✝️ ✝️
#አቡነ_መዝሙረ_ድንግል፦ የተባሉት ጻድቅ አገራቸው ጎጃም ነው፤ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ባለ ውለታ ናቸው። ጻድቁ በአምስት ሊቃውንት እየተመሩ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራቱን ወንጌላት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም በግእዝ፣ በአረማይክ፣ በዕብራይስጥና በዐረብኛ ጽፈው በአራት ዓምት ያዘጋጁ ታላቅ አባት ናቸው። ዛሬም በሞጊና ገዳም ይገኛል።

ከዚህም ሌላ ነገረ ማርያምንም በግእዝና በዕብራይስጥ አዘጋጅተው ጽፈውታል። ሌሎችንም በርካታ መጻሕፍት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች እየተረጎሙ ጽፈው ያስቀመጡ ነበር። በጣም ጸሎተኛ፣ ደራሲ፣ ባሕታዊ፣ ጻድቅና መናኝ የሆኑት አቡነ መዝሙረ ድንግል ዐርፈው የተቀበሩት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነው። ከአቡነ መዝሙረ ድንግል እግዚአብሔር አምላክዐ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!።

                        ✝️ ✝️ ✝️
#አቡነ_ገብረ_ኢየሱስ፦ የተባሉት ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በአገራችን ብዙ ተአምራትን በማድረግ ወንጌል ሲሰብኩ ከኖሩ በኋላ የግብጽ ገዳማትን ለመሳለም ወደ ግብጽ ወርደው አባ መቃርስ ገዳም ገቡ። ከዚያም ወጥተው በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ገብተው በዚያ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ። አቡነ ገብረ ኢየሱስ ታላቅ የሆነ ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባት ስለሆኑ በዚህም ግብጻውያን ይቀኑባቸው ነበር።

ስልሳ ስድስተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ገብረ ክርስቶስ ባረፉ ጊዜ ኤጲስቆጶሳቱ ተሰብስበው ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወደ አስቄጥስ መጥተው ለከበረች ሹመት የሚገባውን እየመረመሩ ሁለት ወር ተቀመጡ። በዚህም ጊዜ በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ለሚኖሩት ለጻድቁ አቡነ ገብረ ኢየሱስ የታዘዘ መልአክ ተገልጦላቸው "ለኤጲስ ቆጶሳቱ ለዚህች ለከበረች ሹመት የሚገባው ስሙ ገአርጊ የሚባል በመካከላችሁ አለና እርሱን ሹሙት አትዘኑ" በላቸው ብሎ ነገራቸው። አቡነ ገብረ ኢየሱስም "ከመካከላችሁ ስሙ ገአርጊ የሚባል ጻድቅ አለና እርሱን ሹሙት" ብለው መልአኩ የነገራቸውን መልእክት ነግረዋቸው አባ ገአርጊን ስልሳ ሰባተኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾመዋቸዋል።

አባ ገአርጊም ስማቸው አባ ቄርሎስ ተብሎ ከተሾሙ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ አገልግለዋል። በወቅቱ የነበረው የግብጻውያኑ ንጉሥ በጣም ብዙ ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም አቡነ ገብረ ኢየሱስ ሄደው በድፍረት አስተምረውትና ገሥጸውት በአንድ ሚስት ብቻ እንዲጸና አድርገውታል። የጻድቁ አባታችን ገዳላቸው በጣና ይገኛል። ሰኔ11 ቀን ዐርፈው የተቀበሩት ግን በዛው በግብጽ በቊስቋም ገዳም ነው። ግብጻውያን የቅድስና ማዕረግ ሰጥተዋቸው ታቦት ቀርጸውላቸው በዓላቸውን በሚገባ ያከብሩላቸዋል። ከአቡነ ገብረ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
"በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

              #ሰኔ ፲፩ (11) ቀን።

እንኳን በጦርነት ድል አድራጊው ከቤተ መንግሥት ወገን ለሆነ #በንጽሕናው_የመላእክት_አርያ_ላለው #ለከበረ_ሰማዕት_ለቅዱስ_ገላውዴዎስ ለተጋድሎው ፍጻሜ #ለዕረፍቱ_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ #በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ ስም በእስክንድርያ ከተማ ከሠራችበት #ከአርባ_ሰማዕታት #ከቅዳሴ_ቤተ_ክርስቲያንና #ከእስክንድርያ_ሊቀ_ጳጳሳት
#ከቅዱስ_ክርዳኑ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                       ✝️ ✝️ ✝️
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ገላውዴዎስ፦ ይህ ቅዱስ ምድራዊ መንግሥትንና የዚህን ዓለም ክብር የናቀ ነበረ መልካም ገድልንም ተጋደለ። የማይጠፋ ሰማያዊ መንግሥትንና የማያልቅ ክብርንም ወረሰ።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብጥልዎስ ነው እርሱም ለሮሜ ንጉሥ ለኑማርያኖስ ወንድሙ ነው መልኩም እንደ እስራኤል ያዕቆብ ልጅ እንደ ዮሴፍ ውብ ነበር። እርሱም በጦርነት ላይ የበረታ ነበር። የአንጾኪያ ተወላጆችም ይመኩበት ነበር። ስለ ደም ግባቱና ጽናቱ በሁሉ ዘንድ የተወደደ ነበር። እርሱንም ከመውደዳቸው ብዛት የተነሣ ጠላቶችን ድል እንዳረጋቸው እነርሱም ድል ሁነው በውርደት በብዙ ድንጋጤ ከፊቱ እንደሸሹ አድርገው ሥዕሉን ሥለው በከተማው መግብያ በር ላይ ያኖሩት ነበር።

ቅዱስ ገላውዴዎስ የቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር ያነብ ነበር። የሮሜ ንጉሥም ዜናውን ሰምቶ ሊያየው ወደደ ልጁ ገላውዴዎስንም ይልክለት ዘንድ ወደ አባቱ ላከ እርሱም ላከለት። በደረሰም ጊዜ በደስታ ሊቀበለው ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋራ ወጣ በአየውም ጊዜ ደስ ተሰኘበት የሮሜ ከተማ ሰዎች ሁሉም ደስ አላቸው። ከእነዚያ ወራቶችም በኋላ ከቊዝ አገር ሰዎችና ከአርማንያ ታላቅ ጸብ ተነሣ ይህም ቅዱስ ገላውዴዎስ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ታምኖ ወደ እነርሱ ወጣ ድልም አደረጋቸው ንጉሣቸውንም ያዘው ጣዖታቶቻቸውንም ሰበራቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ተመለሰ ዲዮስቆሮስም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክዶ አምልኮ ጣዖትን በአጸና ጊዜ እጅግ አዘነ ፊቅጦር የሚባል የኅርማኖስ ልጅ ወዳጅ ነበረው ሁልጊዜም የመጻሕፍትን ቃል ይሰሙ ነበር ስለ ነፍሳቸውም ድኅነት ያነቡ ነበር።

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ያፈሱ ዘንድ ተስማሙ። በዚያ ጊዜም ሰይጣን በሽማግሌ አምሳል ታያቸው ያዘነላቸውም መስሎ እንዲህ አላቸው "ልጆቼ ሆይ መልካምች ጐልማሶች ናችሁ የነገሥታት ልጆችም ናችሁ። ስለ እናንተ እፈራለሁ አዝንላችኋለሁም እኔም ከንጉሡ ጋር ትስማሙ ዘንድ ለአማልክትም ታጥኑ ዘንድ እመክራችኋለሁ ሲአዝዛችሁም ትእዛዙን አትተላለፉ እናንተም ክርስቶስን በቤታችሁ አምልኩት ይህ ንጉሥ ኃይለኛ ርኅራኄም የሌለው ጫካኝ ነውና" አላቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር የሚነጋገራቸው ሰይጣን እንደሆነ አስገነዘባቸው "ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሐሰት አባት ሆይ ከእኛ ራቅ አንተ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ሕግ ትቃረናለህና" አሉት። ያን ጊዜም መልኩን ለውጦ እንደ ጥቁር ባሪያ ሆነ እንዲህም አላቸው "እነሆ ከንጉሥ አጣልቼ ደማችሁን እንዲአፈስስ አደርገዋለሁ" ሰይጣኑም ይህንን ብሎ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ሔዶ "ፊቅጦርና ገላውዴዎስን ካልገደልካቸው በአንተ ላይ ይነሣሉ አንተንም ገድለው መንግሥትህን ይወስዳሉ እነርሱም የመንግሥት ልጆች ናቸውና" አለው።

ስለዚህም ንጉሡ ወደ ቅዱስ ገላውዴዎስ ልኮ ወደርሱ አስመጣው ለጣዖታቱም እንዲሠዋ ለመነው የአባቱንም ሹመት ይሾመው ዘንድ ቃል ገባለት ሰምቶም አልታዘዘለትም። ንጉሡም ክፉ ቃልን ሊናገረው አልደፈረም ቅዱስ ገላውዴዎስ ግን በድፍረት ይናገረው ነበር ያለ መፍራትም ንጉሡንና የረከሱ አማልክቶቹን ሰደበ። ኅርማኖስም ቅዱስ ገላውዴዎስን ወደ ግብጽ እንዲልከውና በዚያ እንዲገድሉት ንጉሡን መከረው እርሱ እንደ ልጄ እንደ ፊቅጦር ዐመፀኛ ነውና።

ንጉሡም ወደ እንዴናው ገዥ እንዲህ ብሎ ጻፈ "ገላውዴዎስ ትእዛዛችንን አልተቀበለም ቃላችንንም አልሰማም አንተም ወደ ትዕዛዛችን ይመለስ እንደሆነ በብዙ ድካም ሸንግለው ይህ ካልሆነ ራሱን በሰይፍ ቁረጥ"። ቅዱስ ገላውዴዎስ ወደ እስክንድርያ ይወስዱት ዘንድ ንጉሡ እንደ አዘዘ በአወቀ ጊዜ የእኅቱ ባል የሆነ ሲድራማኮስን ጠርቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን በማመን እንዲጸና ወገኖቹንም እንዲያጸናቸው አደራ አለውና በሰላምታ ተሰናበተው።

ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስም በደረሰ ጊዜ አርያኖስ አይቶ ደነገጠ ተነሥቶም እጁን ሳመው እንዲህም ብሎ ለመነው "ጌታዬ ገላውዴዎስ ሆይ ይህን ሥራ አትሥራ የንጉሥንም ትዕዛዝ አትተላለፍ። ቅዱስ ገላውዴዎስም እንዲህ ሲል መለሰለት "ንጉሥ ያዘዘህን ልትፈጽም እንጂ በነገርህ ልታስተኝ አልተላክሁም" አለው። መኰንኑም እስከሚቆጣ ድረስ እንዲህ እርስበርሳቸው ይነጋገሩ ነበር በመኰንኑም እጅ ጦር ነበር ቅዱስ ገላውዴዎስ ወጋው ነፍሱንም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ሰኔ 11 ቀን ሰጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ምዕመናንም መጥተው የቅዱስ ገላውዴዎስን ሥጋ ወሰዱ በመልካም አገናነዝም ገነዙት ከቅዱስ ፊቅጦር ሥጋ ጋርም በሣጥን ውስጥ አኖሩት። የስደቱም ዘመን እስኪሚፈጸም ጠበቁት።

ከዚህም በኋላም የቅዱስ ፊቅጦር እናት ቅድስት ሶፍያ ወደ እንዴናው አገር መጣች የቅዱሳን ገላውዴዎስንና የፊቅጦርን ሥጋቸውንም ወስዳ ወደ አንጾኪያ አደረሰች። የቅዱስ ገላውዴዎስ ሥጋ አስዩጥ በሚባል አገር ይኖራል የሚልም አለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ መስተጋድል በቅዱስ ገላውዴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላሀሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 11 ስንክሳር።

                         ✝️ ✝️ ✝️
"#ሰላም_ለቅዳሴ_ቤትከ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_መድኃኒነ። በእስክንድርያ ዘኮነ። ኀቤከ እግዚኦ አንቃዕዶና አዕይንተነ። ከመ ተሀበነ እምቅኔ ኃጢአት ግዕዛነ። ንጸንሐከ ንሕነ እምዘመን ዘመነ። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_11

                         ✝️ ✝️ ✝️
#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወኢትፈርህ እምግርማ ሌሊት። እምሐፅ ዘይሠርር በመዓልት። እምግብር ዘየሐውር በጽልመት"። መዝ 90፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 5፥1-11፣ 1ኛ ጴጥ 5፥7-12 እና የሐዋ ሥራ 16፥35-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥16-32። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም አቡነ ገብረ ኢየሱስ፣ አቡነ መዝሙረ ድንግልና የቅዱስ ገላውዴዎስ የዕረፍት በዓል። በሁላችንም ይሁንልን።
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
2024/09/27 16:22:53
Back to Top
HTML Embed Code: