Forwarded from የ እግዚአብሔር እና የድንግል ማርያም ልጆች (Seleshi)
የእግዚአብሒር ሰላም ከእናተ ጋር ይሁን።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው
ከሞት ይበልጥ ኃያል መሆኑን አረጋግጧል።
ይህ በመሆኑም ሞቱና ለፍርድ ሲቀርብ
የገለጠው ዝምታ በውስጡ ካለው ፍርሐት አልመሆኑን እንረዳለን።
ቢናገር ኖሮ አፈቸውን በማስያዝ አድማጮቺን
ማሳመን ይችል ነበር። ይሁን እንጂ የእርሱ ዓለማ ይህ አልነበረም። የእርሱ ዓለማ እኛን ነጻ
ማውጣት ነበር። ስለሆንም ከመሰቀል ላይ
እንዲወርድ በጠየቁት ጊዜ መውረድ
ቢችልም እንኳ ምንም ዓይነት መልስ አልሰጣቸውም። የእርሱ ብቸኛ ዓለማ ስለ እኛ
ሕማምን ተቀብሎ በመሞት የኃጢአትን ዋጋ
በእኛ በመክፈል ለእኛ ስረየትና ድኅነት
ማስገአት ነበር።
የክሮስቶስ ዝምታ ድካም አለመሆኑን ትንሣኤው አረጋግጧል።
የትንሣኤው ኃይል ክርስቶስን በድካም ለሚወነጅሉት ወይም ስቅለቱ የአቅም የማጣቱ
ምልክት እንደ ሆነ አድርገው ለማያስቡ ሰዎች
ሁሉ ብርቱ ምላሽ ነው።
ትንሣኤው ዝምታ የላቁ ዓለማዎች እንዳሉት
አረጋግጧል። እርሱ ዝም ያለው ራሱን ለእኛ
ሊሰጠን ስለ ወደደ ነው። ቢናገር ኖሮ ለፍርድ
ያቀረብት ጠላቶቹን አፍ በማስያዝ አድማጮቹን ማሳመን ይችል ነበር።
ራሱን ቢከላከል ኖሮ የተከሰሰባቸውን ያለ ምንም ጥርጥር ያሸንፍ ነበር።
ከዚህ ሌላ ገና የአስራሁለት ዓመት ብላቴና ሳለ
ይናገራቸው የነበሩት ቃላት ኃይል እነርሱ ራሳቸው በመደነቅ መስክረውለታል።
"ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል
ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጢይቃመቸውም
በመቅደስ አገኙት የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ።" ሉቃ 2:46-
47። አድማጮቹም ቢሆኑ በሥልጣን መናገሩን
በአግራሞት መስክረውለታል። "....ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን
እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበረ። " ማቴ
7:28-29። ከዝህ ከፍል የምንረዳው ጌታችን
በአስራሁለት ዓመቱ በአይሁድ መምህራን
መካከል ሲነጋገር እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው የነበረ አምላካችን ነው።
በትንሣኤው ከሞቱ ይበልጥ ኃያል መሆኑን
አረጋግጦልናል። በአንድ ልጅህ በርሱ ያለ ክብርና ጽንዕ ሐአንተ ይገባል ከእርሱ ጋራ
ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም
ለዘላለም ለዘለአለሙ አሜን። መልካም ጊዜ።

ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል።
በራሱ ኃይል ስልጣን።
የእግዚአብሔር ሰለም ከእናተ ጋር ይሁን።
የጌታችን የመደኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
ሞቱ በራሱ መሥዋዕትነት እንጂ በኃይል ወይም በግዳጅ አለመሆኑ ትንሣኤው አረጋግጧል።የክርስቶስን ትንሣኤ ማመን ማለት በእርሱ ፍቅር በእርሱ ምሥዋዕት ሆኖ
መቅረብና በእርሱ የሰው ልጆችን ከሞት ባርነት
ነጻ ማውጣት ማመን ነው። ከዚህ ተጨማሪ
በእርሱ ኃይል አስቀድሞ ስለራሱ በተናገራቸው
ቃላትና ከእግዚአብሔር ጋር አንድ በመሆኑ
ማመን ነው። ይህ ኃይል በሥጋው ሞቶ በመለኮቱ ሕያው የሆነው የአንድዬ የአምላካችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው።
ይህ ኃይል ለዮሐንስ በራዕዩ እንደሚከተለው
የተነገረው የአንድዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል
ነው።".....አትፍራ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እንሆም ከዘላለም አስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ
የሞተና የሲዖል መክፈቻ አለኝ።"ራእ 1:8።
ስለዚህ ኃይል አንድዬ ሐዋርያውን ቅዱስ
ጴጥሮስን በሐምሣኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ
በወረደባቸው ጊዜ ሰክረዋል የሚል ቃል
ከአይሁድ በተነገረባቸው ጊዜ እንዲህ ብሎ
አናግሮታል"እግዚአብሔር ግን የሞትና ጣር
አጥፍቶ አስነሰው ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።" ሐዋ 2:24። ዳዊትንም ትንቢት
አናግሮታል"...ነፍሴን በሲዖል አትተዋትምና
ቅዱስ መበስበስን ያይ ዘንድ አተሰጠውም። "
መዝ 15: 8-11።ቅዱስ ጳውሎስም ፦
"....ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት
እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው
እናውቃለንና። " ሮሜ 6 :9። ስለዚህ የጌታችን
ትንሣኤ የሚያስተምረን ወደፊት የማይምት ሞት የማይገዛው አምላካችን ነው። አለም ያላት
አምላክ ግን "የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን
አሳብ አሳወረ" 2ኛ ቆሮ 4:4 ተብሎ እንደተነገረ
አለም ያላት አምላክ ወደውጭ የሚጣል እና የሚፈረድበት ነው። ዮሐ 12:31-32 ራእ 20:10። መልካም ጊዜ።

Forwarded from Bketa @¥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥር በዚች ቀን የከበሩ ጻድቃን ሠለስቱ ደቂቅ አናንያ አዛርያ ሚሳኤል የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።
❖ እሊህም ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም ልጆቹ ናቸው ዳንኤልም የእኅታቸው ልጅ ነው በምርኮ ጊዜም ከእስራኤል ልጆች ጋራ ተማርከው ወደ ባቢሎን ወረዱ፤ ከእስራኤል ልጆች ምርኮ ውስጥ በመብልና በመጠጥ እያስተማረ አሳድጎ በሠራዊቱ መካከል ጭፍሮቹ ያደርጋቸው ዘንድ ነውር ነቀፋ የሌለባቸውን ወጣቶች ንጉሥ መረጠ፤ እሊህም ከተመረጡት ውስጥ የተቆጠሩ ሆኑ የእኅታቸው ልጅ ዳንኤልም፤ ምግባቸውን በሚሰጡአቸው ጊዜ አረማውያን ከአረዱአቸው ውስጥ መብላትን አልወደዱም ከንጉሥ ማዕድም ከሚመጣ ከሥጋው እንዳያበላቸውና እንዳያጠጣቸው አለቃውን ለመኑት።
❖ እግዚአብሔርም በባለሟሎች አለቃ ፊት ቸርነቱን አደረገላቸው፤ የባለሟሎች አለቃም ንጉሡ ጌታዬን እፈራዋለሁ የምትበሉትንና የምትጠጡትን ምግባችሁን ስለ አዘዘ ከባልንጀሮቻችሁ እናንተን ከስታችሁ ቢያያችሁ ንጉሥ ራሴን ይቀጣኛል አላቸው፤ በእነርሱ ላይ የተሾመ አሚሳድን እንዲህ አሉት እኛን ባሮችህን ዐሥር ቀን ፈትነን ከምድር ዘር ሽምብራን ይስጡን እንበላ ዘንድ ውኃንም እንጠጣ ዘንድ፤ ቃላቸውንም ሰምቶ ዐሥር ቀን ፈተናቸው ዐሥር ቀንም ከአለፈ በኋላ የንጉሡን ማዕድ ከሚመገቡ ከእነዚያ ልጆች ይልቅ ሰውነታቸው ወፍሮ መልካቸውም አምሮ ታየ።
❖ ከዚህ በኋላ አሚሳድ የሚበሉትን ምግብ የሚጠጡትን ወይን እየወሰደ ለአራቱ ሁሉ ልጆች ሽምብራ ይሰጣቸው ነበር፤ እግዚአብሔርም ዕውቀትንና ጥበብን መጻሕፍትን በማንበብ ሁሉ ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ያዘዘው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ወደርሱ አመጡአቸው የባለሟሎችም አለቃ ወደ ንጉሡ ወደ ናቡከደነፆር አገባቸው።
❖ ንጉሡም ጠየቃቸው በሰው ሁሉ ዘንድ እንደ አናንያና እንደ ዳንኤል እንደ ሚሳኤልና እንደ አዛርያ ያለ አልተገኘም በንጉሡም ፊት ቆሙ፤ ንጉሡም የፈለገውን የምክርና የጥበብን ነገር ሁሉ በግዛቱ ካሉ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሰዎች ሁሉ ይልቅ በነሳቸው ዘንድ ዐሥር እጥፍ አገኘ፤ ንጉሡም እጅግ ወደዳቸው በባቢሎን አገር ሁሉ ላይ ገዢዎች አድርጎ ሾማቸው።
❖ ንጉሥም ጣዖትን ከወርቅ ባሠራ ጊዜ ሰዎችን ሁሉ እንዲሰግዱለት አዘዛቸው፤ ሦስቱ ልጆችም ለዚያ ጣዖት ባልሰገዱ ጊዜ የሚቀኑባቸው ወደ ንጉሥ ነገር ሠርተው በንጉሥ ፊት አቀረቧቸው ስለ አልሰገዱለትም ጠየቃቸው እነርሱም እኛስ ለሠራኸው ለወርቅ ምስል አንሰግድም አሉት፤ ንጉሥም ተቆጥቶ ከምትነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ።
❖ እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ የእሳቱን ነበልባል አጠፋው በጥዋት ጊዜ እንደሚቀዘቅዝ በእሊህ በሦስቱ ልጆች ዘንድ እንደ ጥዋት ውኃ ቀዝቃዛ አደረገው፤ ከዚያም የእሳቱ ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ከፍ ከፍ ብሎ በውጪ ያሉትን አቃጠላቸው እሊህን ሠለስቱ ደቂቅን ግን ምንም አልነካቸውም፤ ይህን ድንቅ ሥራ አይቶ በፊታቸው ሰገደ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔርንም አመነ ለእሊህም ልጆች ሹመታቸውን ከፍ ከፍ አድርጎ ክብርን ጨመረላቸው።
❖ ከዚህም ዓለም የሚወጡበት ጊዜ ሲደርስ በበዐታቸው እየጸለዩ ሳሉ ሰግደው ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ፤ ወዲያውኑ ታላቅ ንውጽውጽታ በባቢሎን አገር ሆነ፤ ንጉሡም ፈርቶ ስለ ምን ይህ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ብሎ ዳንኤልን ጠየቀው ነቢይ ዳንኤልም ይህ ሦስቱ ልጆች ስለ አረፉ ከዓለም ለመውጣታቸው ምልክት ነው ብሎ ነገረው።
❖ ንጉሡም ወደርሳቸው ደርሶ ታላቅ ኀዘንን አዘነ ከዝሆን ጥርስም ሦስት ሣጥኖችን እንዲሠሩላቸው በሐር በግምጃ ልብሶች ገንዘው ቅዱሳኑን በሣጥኑ ውስጥ እንዲያኖሩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዛቸውም አደረጉ፤ ሁለተኛም የወርቅ ሣጥን ሠርተው እርሱ በሚሞት ጊዜ ሥጋውን በውስጡ አድርገው በከበሩ ሠለስቱ ደቂቅ መካከል እንዲያኖሩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉለት።
❖ ከዚህ በኋላ የከበረ አባት አባ ቴዎፍሎስ በእስክንድርያ ሊቀ ጵጵስና በተሾመበት ወራት በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ሠራ ሥጋቸውን ወደዚያች ቤተ ክርስቲያን ሊያመጣ ወዶ ሥጋቸውን እንዲያመጣለት አባ ዮሐንስ ሐፂርን ወደ እርሳቸው ሀገረ ባቢሎን ላከው፤ ወደ ባቢሎን ሀገርም በደረሰ ጊዜ ወንዞቿን አየ በውስጧ ከቶ ሰው አልነበረም የወርቁ ምስልም በዚያ አለ፤ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም የቅዱሳን ሥጋ ወደአለበት አደረሰው የንጉሡም ሥጋ በመካከላቸው ነበረ፤ ሥጋቸው በአለበትም ቦታ ሰገደ፤ እንዲህም ብሎ በማልቀስ ጸለየ የከበራችሁ አባቶቼ ሆይ የከበረ አባት ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ በስማችሁ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ሥጋችሁን በውስጧ ሊያኖር እኔን ልኮኛልና ከእኔ ጋራ ትሔዱ ዘንድ ፈቃዳችሁ ይሁን።
❖ በዚያን ጊዜ እንዲህ የሚል ቃል ከሥጋቸው ወጣ ለሃይማኖት አባት ለአባ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው የድካምህን ዋጋ እግዚአብሔር ይስጥህ ነገር ግን እኛን እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ሥጋዎቻችን ከንጉሡ ሥጋ እንዳይለዩ እግዚአብሔር ስለአዘዘን ከዚህ አንወጣም ድካሙንም ከንቱ አናደርግም፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከብርበት ዕለት በሌሊት መብራቶችን ይሰቅሉ ዘንድ እንዲአዝ በውስጣቸውም ዘይትና ፈትል እንዲያደርጉ በእሳት ግን አይለኩሱአቸው፤ እኛም ከዚያ ደርሰን በእኛ የእግዚአብሔር ኃይል በዚያ ይገለጣል ብለህ ንገረው አሉት።
❖ አባ ዮሐንስ ሐፂርም ተመልሶ እንደነገሩት እንዴትም እንዳዘዙት ሁሉንም ለአባ ቴዎፍሎስ ነገረው እርሱም ሠለስቱ ደቂቅ እንዳዘዙ አደረገ፤ በዚችም በግንቦት ወር በዐሥር ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከብርበት ሌሊት የከበሩ ሠለስቱ ደቂቅ ተገለጡ ያለ እሳትም መብራቶችን አበሩ ሊቀ ጳጳሳቱና ለዚህ ጸጋ የታደሉ ሁሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ እርከን ላይ ሲዞሩ ሠለስቱ ደቂቅን አዩአቸው በየአይነቱ በሆነ ደዌ የታመሙ ብዙ በሽተኞችም ከቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ መገለጥ የተነሣ ያን ጊዜ ተፈወሱ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
🛎 በዚችም ቀን አብርሃም ፀራቢ በሰማዕትነት አረፈ ይህም ቅዱስ የሰማዕት ቴዎድሮስ ገዳም ተብላ ከምትጠራ ከመርቅያስ አገር ሰዎች ነው፤ ወላጅ እናቱም የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ሃይማኖት እንዲማር ለመምህር ሰጠችው፤ ጌታችንም ዐይነ ልቡናውን ገልጦለት ትምህርቱን ሁሉ የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ ተማረ።
❖ ከዚህም በኋላ መጾም መጸለይና መስገድ ጀመረ ዘጠኝ ዓመትም በሆነው ጊዜ ከደንጊያ የሚሠራ የውኃ መሔጃ መጥረብን ተማረ በዚህም ብዙ ገንዘብ አከማቸ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች የሚመጸውት ሆነ፤ በአንዲት ዕለትም በሌሊት ሲጸልይ የዚችን ዓለምና በውስጧ ያለው ሁሉ ኃላፊ መሆኑን አሰበ፤ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ ስም ምስክር ሆኖ መሞትን ወደደ።

❖ በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶት ጽና አትፍራ አንተ ጠላቶችህን ድል አድርገህ የሰማዕትነትን አክሊል ትቀበላለህና አለው፤ ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን ወደ ተጠመቀባት ወደ ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ በሥዕሉ ፊት ቁሞ ጸለየ፤ በርሱም ዘንድ ሰውነቱን አደራ አስጠበቀ ወደ መኰንኑም ወጥቶ ክርስቲያን እንደ ሆነ ታመነ፤ ያንጊዜም ከከባዶች እንጨቶች ጋራ የኋሊት አሥረው ከረኃብና ከጽምዕ ጋራ ከፀሐይ ውስጥ ጣሉት፤ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ጌታችን ተገለጠለት፤ ሰላምታም ሰጠው ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግም ቃል ኪዳን ሰጠው።
❖ ከዚህ በኋላም መኰንኑ ራሱን እንዲቆርጡት አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ራሱ እኔ ክርስቲያን ነኝ እያለች ሦስት ጊዜ በተራራው ላይ በረረች ሃምሳ ምዕራፍ ያህልም ሒዳ ከባሕር ወደቀች፤ ከዚህም በኋላ ሆዱን ሰንጥቀው ባሩድና ሙጫ ዘይትን መልተው ከእሳት ውስጥ ጣሉት፤ እሳቱ ግን ምንም አልነካውም ከዚህም በኋላ በየጥቂቱ ከትፈው በእንቅብ አድርገው ከባሕር ውስጥ ጣሉት፤ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ከራሱ ጋራ አንድ ሆኖ እንደ ቀድሞው እስና በሚባል አገር በባሕሩ ወደብ ታየ ምእመናንም ወስደው በታላቅ ክብር ቀበሩት።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሰማዕት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
📌 ግንቦት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ሠለስቱ ደቂቅ ቅዱሳን (አናንያ: አዛርያና ሚሳኤል)
2. ቅዱስ አብርሃም ጸራቢ (ሰማዕት)
3. አባ ሚካኤል ገዳማዊ
4. አባ ይስሐቅ ግብጻዊ
📌 ወርሐዊ በዓላት
1. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3. ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
6. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
7. ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† "ናቡከደነፆርም መልሶ:- መልአኩን የላከ : ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን : የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን : በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ::" †††
(ዳን. 3:28)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
(ዳን. 3:28)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Forwarded from ✝️ የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ✝️ (ኆኅተ ጥበብ ሰ/ት/ቤት)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም
🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፩
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚች ቀን የቅዱስ ዮስጦስ ሚስት ቅድስት ታውክልያ በሰማዕትነት አረፈች።
❖ በየካቲት ዐሥር እንደ ተጻፈ የእስክንድር ገዢ እርስበርሳቸው ከአለያያቸው በኋላ ቅድስት ታውክልያን ወደ ሀገረ ፃ ወሰዱዋት፤ በሀገረ ፃ መኰንንም ፊት የመኰንኑ እስክንድርያን መልእክት በአነበቡ ጊዜ መንግሥታቸውን ትተው እንዴት ከመንግሥታቸው ሞትን መረጡ ብሎ አደነቀ።
❖ ከዚህ በኋላ መኰንኑ ሸነገላት ብዙ ታላላቅ ቃል ኪዳኖችንም ገባላት፤ የከበረች ታውክልያም እኔ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር መንግሥቴን ተውኩ ከልጅነት ባሌም ተለየሁ በልጆቼም አልተጽናናሁም ለመሆኑ አንተ የምትሰጠኝ ስጦታ ምን ያህል ነው ብላ መለሰችለት፤ ይህንንም ሰምቶ ታላቅ ግርፋት እንዲገርፉዋት አዘዘ የሥጋዋም ቊርበት እስከሚቆራረጥ ገረፉዋት።
❖ ከዚህ በኋላም ከእሥር ቤት አስገቡዋት የእግዚአብሔርም መልአክ ተገለጠላትና ቊስሎቿን አዳናት፤ እሥረኞችም አይተው አደነቁ ብዙዎቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት አገፉ፤ የምስክርነቷ ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለከበረች ታውክልያ ተገልጾላት አጽናናት ከክብር ባለቤት ጌታችንም የተሰጡዋትን ቃል ኪዳኖች ነገራት።
❖ በዚያን ጊዜም ራስዋን ይቆርጡ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች፤ ምእመናን ሰዎች መጥተው ለወታደሮች ብር ሰጥተው የቅድስትን ሥጋ ወሰዱ በመልካም መግነዝም ገንዘው የስደቱ ወራት እስኪፈጸም በሣጥን ውስጥ አኖሩዋት፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✍️ በዚችም ዕለት የከበረ ኤጲስቆጶስ አባ በፍኑትዮስ አረፈ፤ ይህም ከታናሽነቱ በአባ መቃርስ ደብር በአስቄጥስ ገዳም መነኰሰ ታላቅ ተጋድሎንም በመጋደል ብዙ ትሩፋትን ሠራ፤ አዘውትሮ ይጾም ነበረ ቅጠላቅጠልን ይበላል እንጂ በእሳት የበሰለ አይበላም በገዳሙ ውስጥም መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ተምሮ ቅስና ተሾመ በዚያም ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ እነሆ ትሩፋቱና ጽድቁም በሁሉ ዘንድ ታወቀ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊላታዎስም ልኮ ወደ እርሱ አስመጥቶ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾመው።
❖ ኤጲስቆጶስነትም ከተሾመ በኋላ ቅዳሴ በሚቀድስ ጊዜ ካልሆነ በቀር ከቶ ልብሱን አልለወጠም ቅዳሴውንም ሲፈጽም ከጠጉር የተሠራውን ማቅ ይለብሳል፤ እንዲህም የሚጋደልና የሚጸመድ ሆኖ ኖረ በዚህ ሁሉ ዘመንም ከመነኰሳት ጋራ ያገለግል ነበረ በታመመ ጊዜም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀው።
❖ የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኢጲስቆጶስነት ስለተሾምኩ ጸጋህን በውኑ ከኔ ታርቃለህን ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ወደርሱ መጥቶ አስተውል ዕወቅ አንተ በገዳም ሳለህ በታመምክ ጊዜ የሚጎበኝህ የለም ወይም የሚአገለግልህና ለደዌህ መድኃኒትን የሚሰጥህ አታገኝም ነበር፤ ሰለዚህ እግዚአብሔር የሚረዳህና ደዌውንም ከአንተ የሚያርቅልህ ሆነ፤ ዛሬ ግን እነሆ አንተ በዓለም ውስጥ ነህ በአንተ ዘንድ የሚጐበኝህና የሚአገለግልህ አለ ለደዌህም መድኃኒትን የምትሻውንም ምግብ ታገኛለህ አለው።
❖ ይህም አባት በኤጲስቆጶስነት ሹመት ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ የሚያርፍበትም በቀረበ ጊዜ ካህናቱንና ዲያቆናቱን መምህራኑን ጠራቸው፤ የአብያተ ክርስቲያናትንም ንዋየ ቅዱሳታቸውንና ገንዘባቸውን ሁሉ ሰጣቸው እንዲህም አላቸው ዕወቁ እኔ ወደ እግዚአብሔር እሔዳለሁና እንደሚገባም በመካከላችሁ እንደ ኖርኩ እናንተ ታውቃላችሁ፤ ለኤጲስቆጶስነት ሹመቴም እጅ መንሻ ከሚአመጡልኝ እንኳ አንድ የብር አላድ እንዳልሠወርኩ በፊቱ ልቆም ያለኝ የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኔ ላይ ምስክርን ይሁን አላቸው።
❖ ይህንም ሰምተው አለቀሱ ተሳለሙትም እንዲባርካቸውና በክብር ባለቤት ጌታችንም ዘንድ መራዳቱን እንዳይረሳ ለመኑት እርሱም ባረካቸው፤ እግዚአብሔርም ያክብራችሁ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጽናችሁ ይህንንም ብሎ በሰላም አረፈ፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
🛎 በዚችም ቀን የባሌ መምህር አባ አሴር በሰማዕትነት አረፈ ይኸውም በንጉሥ ወናግ ሰገድ ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም ወርዶ ሳለ መጀመሪያ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡ። በኋላም የጌታችን እግር በቆመበት በኢየሩሳሌም መግቢያ በእሳት አቃጠሉት።በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
🛎 በዚች ቀንም ቅድስት አናሲማ አረፈች ይቺም ቅድስት በደናግል ገዳም መንኵሳ ራስዋን እብድ አስመስላ ኖረች፤ በሌሊትም በጾምና በጸሎት ሥጋዋን በመቅጣት ራሷን ታሠቃያለች ሰዎችም በሚያዩዋት ጊዜ ራስዋን አእምሮዋን እንደሳተች ታስመስላለች መበለቶችም ይሰድቧታል።
❖ እግዚአብሔርም ገድሏን ለአባ ዳንኤል ገለጠ፤ እርሱም ከደናግል ገዳም ሔዶ ትሩፋቷንና ገድሏን ሁሉ ለእመ ምኔቷ ነገራት እርሷም ለእኀቶች መነኰሳይያት ነገረቻቸው ከዚያችም ዕለት ወዲህ አከበሩዋት፤ እርሷም ስለ አዋረዱዋትና ስለ አጐሳቈሉዋት እኀቶችን እያመሰገነች ደብዳቤ ጽፋ ትታ ከንቱ ውዳሴን በመጥላቷ ተሠውራ በሌሊት ወጥታ ወደ ዱር ሸሸች በዚያም በሰላም አረፈች።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
🛎 በዚችም ቀን በዲዮቅልጥያኖስ መንግሥት ዘመን ቅዱስት ኤፎምያ በሰማዕትነት አረፈች፤ የዚችም የእናቷ ስም ቴዎድርስያኒ ነው እርሷም የክብር ባለቤት ክርስቶስን የምታምንና የምትፈራው ናት፤ ሰይጣንም ክርስቲያኖችን በማስገደድ ለጣዖት እንዲያሰግድ አንቲሂጳጦስን በአነሣሣው ጊዜ ይቺን ቅድስት ኤፎምያን ከብዙ ክርስቲያኖች ጋራ አሥረው አመጡዋት፤ አንቲሂጳጦስም ለአማልክት ሠዊ አላት፤ እኔ ከክብር ባለቤት ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አልሠዋም የአባቶቼን ተስፋ ለማግኘት ልቤ የጸና ነውና አለችው።
❖ ያን ጊዜ አንቲሂጳጦስ ተቆጥቶ ዐጥንቷ እንዲሰበር ሕዋሳቷ ሁሉ እንዲለያይ ከሠረገላ መንኰራኩር ውስጥ ይጨምሩዋት ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ አዳናት ሁለተኛም ነበልባሉ አርባ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ እስከሚል እሳትን አንድደው ከውስጡ ይወረውሩዋት ዘንድ አዘዘ፤ በእሳቱ መካከልም ቁማ ጸለየች እየጸለየችም በደኅና ወጣች ብዙዎችም በጌታ አምነው በሰማዕትነት አረፉ።
❖ ከዚህም በኋላ እስከ ማግሥት ከወህኒ ቤት ጨመራትና በማግሥቱ ወደ ሸንጎ አወጧት እርሱም ለአማልክት ሠዊ አላት፤ ቅድስት ኤፎምያም ሣቅ ብላ እኔስ ለማይናገሩ ደንጊያዎች አልሠዋም አለችው፤ አንቲሂጳጦስም ሰምቶ ሥጋዋን ይገፉ ዘንድ መቃጥን ያላቸው አራት ደንጊያዎችን እንዲያመጡ አዘዘ፤ ሁለተኛም አራዊት ከአሉበት ኲሬ ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዝዞ ከዚያ ወረወሩዋት፤ አራዊት ግን ተሸክመው አውጥተው ከውኃው ዳር አቆሙዋት፤ ደግሞ ስለታሞች ደንጊያዎችንና ሰይፎችን በመሬት ውስጥ እንዲተክሉ ተቆራርጣ ትሞት ዘንድ በላያቸው እንዲያስሮጡዋት አዘዘ ሩጣም ተሻገረች ምንም የነካት

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Bketa @¥
✨✨✨✨✨✨✨✨ ✨✨✨✨✨✨✨✨
✥ ቅዱስ ያሬድ ✥
✥መላእክት ምስጋናቸው እረፍታቸው ፣ እረፍታቸው ምስጋናቸው ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ እግዚኣብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግናሉ፡፡ ቤተክስቲያንም አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ናትና ይህን አብነት በማድረግ ልዑል እግዚኣብሔር ሃያ አራት ሰዓት የሚመሰገንበትን የምስጋና ሥርዓት ዘርግታለች፡፡ሕያው እግዚኣብሔር የአዳም ልጆች በመላእክት ምስጋና እንዲያመሰግኑት በመውደዱ ሰማያዊውን ምስጋና ይማር ዘንድ ቅዱስ ያሬድን መረጠ፡፡
👉ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊው ሊቅ
ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ.ም ኣክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ ያሬድ ማለት መውረድ ማለት ነው ፡፡ ሰማያዊውን ጣእመ ዜማ ወደ እኛ የሚያወርድ ነውና፡፡‹‹ዋይ ዜማ!!! ዘሰማዕኩ እመላእክት ቅዱሳን ›› ‹‹ ከሰማይ ከቅዱሳን መላእክት የሚያስደንቅ ዜማ ሰማሁ›› በማለት እንደተናገረ በኣክሱም መጽሓፍትን እያስተማረ ሳለ ከሰማያውያን መላእክት ጣእመ ዜማን ተማረ፡፡
በተመስጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተነጠቀ፡፡ በዚያም መላእክት ልዩ ጣእም ባለው የዜማ ድምፅ ሲያመሰግኑ ሲዘምሩና ሲያሸበሽቡ አየ፡፡ ከጣዕመ ዜማውም የተነሣ ተደነቀ፡፡ የእግዚኣብሔርን ስም እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን በጠራ ጊዜ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ተገለጸለት፡፡ ተመልሶም ወደ ምሥራቅ ዞሮ እጁንም ዘርግቶ ‹‹ ሃሌ ሉያ ለአብ ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፣ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን . . . ›› ብሎ በኣክሱም ከተማ ሙራደ ቃል /የቃል መውረጃ/ በተባለችው ሥፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ ዜማን በዐውደ ምሕረት ያሰማ የዜማ ደራሲ ነው፡፡
👉የቅዱስ ያሬድ አስተዋጽኦ
📌ዓለም ከሚያውቃቸው የዜማ ደራስያን ከሞዛርትና ከሌሎችም አስቀድሞ ቅዱስ ያሬድ ግእዝ፣ እዝል ፣ አራራይ በተሰኙ የዜማ ስልቶች የማይሰለችና ዘመን ተሸጋሪ ዜማን፣ የዜማ ምልክቶችንና የተለያዩ ድርሰቶችን በመድረስ ሃገራችን የዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሃብት ባለቤት እድትሆን ኣድርጓል፡፡
📌📌 ቅዱስ ያሬድ በሰዓታት ፣በወራትና በዘመናት የተከፋፈሉ ድንቅ ምስጋናዎችን ከብሉያትና ከሐዲሳት ንባብና ምሥጢር ለቤተክርስቲያን እንደ ሰምና ወርቅ ኣስማምቶ የአገልግሎት ሥርዓትን የሠራ የቤተ ክርስቲያን ዓምድ ነው፡፡
📌📌 የቅዱስ ያሬድ ዜማ ድንቅና ጥልቅ የነገረ ሃይማኖት አስተምህሮት ፣ የቅዱሳት መጽሓፍትን ንባብ ትርጓሜ እንዲሁም የታሪክ ምስክርነትን የያዘ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ድርሰት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዛሬ በጉባኤ ቤት ለዜማ ትምህርት ቤተክርስቲያን የምትገለገልበትን ሥርዓተ ትምህርትና የመማሪያ መጽሓፍትን የደረሰ ሊቅ ነው፡፡ ድረሰቶቹም ምዕራፍ ፣ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ዝማሬና መዋሥዕት ይባላሉ፡፡
📌📌ቅዱስ ያሬድ በአክሱም በመምህሩ በጌዴዎን ወንበር ተተክቶ መጽሓፍተ ብሉያትና ሓዲሳትን ኣስተምሯል፡፡ ከኦቡነ አረጋዊና ከኣፄ ገብረ መስቀል ጋርም በመሆን በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎት በጣና ቂርቆስ ፣ በዙር ኣባ ኣቡነ ኣረጋዊ ገዳም እንዲሁም ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ እስከ ብርብር ማርያም በመሄድ ያስተማረ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡
አጠቃላይ በሥነ ጽሑፍና በቋንቋ እድገት በነገረ መለኮትና በታሪክ ትምህርት እንዲሁም በሥርዓተ ጸሎት የቤተ ክርስቲያን ኣንድነት በማስጠበቅ ረገድ ጽኑ መሠረትን የጣለ ታላቅ ሊቅ ነው፡፡
👉 የቅዱስ ያሬድ ምናኔ
📌📌 ቅዱስ ያሬድ የሕይወት ዘመኑን በጸሎትና በብሕትውና ለማሳለፍ ወደ ሰሜን ተራራ ምድረ ጸለምት በመሄድ /በሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት በበየዳ ወረዳ በሚገኝ ሥፍራ/ ብርድ በጸናበት በረዶ በሚፈላበት በሐዊ ተራራ በጽሙና ተቀምጧል፡፡ በዚያም ጉባኤ ዘርግቶ ትምህርት አስፋፍቶ ለሃያ ሁለት ዓመታት ኣስተምሯል፡፡
📌📌ቅዱስ ያሬድ ዘመኑን ሁሉ በማኅሌት እግዚኣብሔርን በማገልገል በጣእመ ዜማው ዲያብስን ድል መትቶ በዚያው በሓዊ ተራራ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ ገብቶ ግንቦት 11 ቀን በሰባ ኣምስት ዓመቱ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ ተለይቷል(ተሰውሯል)፡፡ ቤተክርስቲያንም ቅድስናውንና ኣማላጅነቱን ኣምና በስሙ ጽሌ ቀርጻ፣ ቤተክርስቲያን አንጻ ፣ ድርስቶቹንም የቤተክርስቲያን መገልገያና የስርዓተ ኣምልኮ መፈጸሚያ አድርጋ እየተጠቀመችባቸው ተገኛለች፡፡
በምናኔ በኖረበት ሥፍራም በስሙ ገዳም ተገድሞ መናንያን አሰረ ፍኖቱን ተከትለው ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ በረዶውንና ውርጩን ታግሠው በስሙ እየተማጸኑ ይኖራሉ::
እንኳን አደረሳችሁ
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

Forwarded from ✞ገድለ ቅዱሳን✞
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ †††
††† ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን : ክብራችን : ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን?
*አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም)::
*ልቡናው የቅድስና ማሕደር::
*ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው::
*እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ!
ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- "ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ : ሙሉ አካሏ ነው::"
††† የሊቁ ዜና ሕይወት በጥቂቱ †††
††† ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ:: ሊቁ በሕጻንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር:: ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም:: በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ::
ምን ትምሕርት ባይገባው ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር:: አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው:: ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ::
ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው:: ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና::
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ : ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ:: ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ:: እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው::
ካህኑ ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ:: በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር::
ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት:: ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት : ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት:: ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር : ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ:: ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት::
ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ:: ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ:: ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ : ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ::
††† ቅዱስ ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት:-
1. አምስት ያሕል መጻሕፍትን ጽፏል::
2. በጣና ቂርቆስ : በዙር አባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል::
3.በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ ኑሯል::
††† በ576 (571) ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል::
††† አባቶቻችን:-
*ጥዑመ ልሳን
*ንሕብ
*ሊቀ ሊቃውንት
*የሱራፌል አምሳያ
*የቤተ ክርስቲያን እንዚራ
*ካህነ ስብሐት
*መዘምር ዘበድርሳን
*ማኅሌታይ
*ልዑለ ስብከት
እያሉ ይጠሩታል::
††† የቅዱሱ ጸሎትና በረከት ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን::
††† ግንቦት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ
2.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
3.ቅዱሳን ክርስቲናና ይስሐቅ (የቅዱስ ያሬድ ወላጆች)
4.ቅድስት ታውክልያ እናታችን (ንግሥናን ንቃ ሰማዕት የሆነች)
5.ቅድስት ኤፎምያ ሰማዕት
6.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
7.ቅድስት አናሲማ ገዳማዊት
8.አባ በፍኑትዮስ ገዳማዊ
9.አባ አሴር ሰማዕት (ኢትዮዽያዊ)
10.አባ በኪሞስ ጻድቅ
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
††† "እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ:: እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ:: በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደሆነ አላውቅም:: እግዚአብሔር ያውቃል:: ወደ ገነት ተነጠቀ:: ሰውም ሊናገር የማይገባውን: የማይነገረውን ቃል ሰማ::" †††
(2ቆሮ. 12:2-5)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+°✝ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ✝°+
=>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ
ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ?
ምንስ
እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ
ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ
አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን
እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::
<< ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? >>
+ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ
ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ::
እነርሱ
ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው::
ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ
አደገ:: ገና
በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና)
ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::
+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም
አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ
ትምሕርት ይህ
ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2
ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ
ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::
+ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና
እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ
መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ
ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ
ሲኖር
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ
ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ::
ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን
ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::
+ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ
ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ
ራዕየ
ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ
ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው
ሳይታክት:
ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና
ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ
አንክሮ
ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና
ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::
+ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ
በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው
ወደውታልና
የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ
ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል
የለም::
ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር::

+ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት
ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ
መካከል "
አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ
የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ
10 ዓመት
አቁሞታል::
+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ
ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም
ይሔው
ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት
ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ
አወገዛት::
እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ
አጋዘችው::
+በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/
ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት
እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና
ለቅሶ ተደረገ::
+አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ
(ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ
ታጥቆ ሲጸልይ
ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ
ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ
ተመለከተ::
+ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ:
ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን
እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ
እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ"
አላቸው::
ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::
+በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ:
መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ
በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ
ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም::
ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ"
ብሎ በጉባኤ
መካከል ጠየቀው::
+"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ
ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ
አላወቃትም'
ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ
ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::
+"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ
የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ
ይቀያየራል::
እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ
መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::
+'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ
ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ
መልክ
ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::
+አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ
ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም
ሰምተው ሁሉም
ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ
ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::
+ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ
አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ!
እሰግድ
ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም
የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን
ምስጋናም
ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ
ወጥተዋል::
+ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን:
ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት
የተነሳ ታላቅ
ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን
ባርኳል::
✔ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
*አፈ በረከት
*አፈ መዐር (ማር)
*አፈ ሶከር (ስኳር)
*አፈ አፈው (ሽቱ)
*ልሳነ ወርቅ
*የዓለም ሁሉ መምሕር
*ርዕሰ ሊቃውንት
*ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
*ሐዲስ ዳንኤል
*ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
*መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
*ጥዑመ ቃል - - -
+እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ
ይክፈለን::
+ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56
ዓመታት
በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት
ተፈጽመዋል::
+እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ
በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት
ቃል ኪዳን
ተቀብላለች::
❖ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር
ያድለን::
❖ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የዓለም ሁሉ መምሕር)
2አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ (ፍልሠታቸው)
3.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ (ቃል ኪዳን
የተቀበለችበት)
4.አባ አብርሃም ዘደብረ ሊባኖስ
5.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
6.እስክንድር ንጉሠ ኢትዮዽያ
7.ቅዱስ መስቀል (የተአምር በዓሉ)
8.አባታችን ያሬድ (የማቱሳላ አባት)
9.ቅዱስ ሚናስ ዲያቆን❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት2፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ
3፡ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
5፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
6፡ ቅዱስ ላሊበላ
7፡ ቅድስት መስቀል ክብራ
++"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም
ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር
አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች
አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት
ሁሉም ያበራል::
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን
አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት
ይብራ:: +"+ (ማቴ.
5:13-16)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ
መካከል "
አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ
የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ
10 ዓመት
አቁሞታል::
+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ
ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም
ይሔው
ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት
ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ
አወገዛት::
እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ
አጋዘችው::
+በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/
ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት
እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና
ለቅሶ ተደረገ::
+አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ
(ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ
ታጥቆ ሲጸልይ
ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ
ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ
ተመለከተ::
+ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ:
ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን
እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ
እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ"
አላቸው::
ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::
+በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ:
መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ
በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ
ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም::
ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ"
ብሎ በጉባኤ
መካከል ጠየቀው::
+"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ
ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ
አላወቃትም'
ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ
ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::
+"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ
የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ
ይቀያየራል::
እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ
መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::
+'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ
ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ
መልክ
ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::
+አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ
ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም
ሰምተው ሁሉም
ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ
ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::
+ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ
አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ!
እሰግድ
ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም
የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን
ምስጋናም
ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ
ወጥተዋል::
+ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን:
ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት
የተነሳ ታላቅ
ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን
ባርኳል::
✔ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
*አፈ በረከት
*አፈ መዐር (ማር)
*አፈ ሶከር (ስኳር)
*አፈ አፈው (ሽቱ)
*ልሳነ ወርቅ
*የዓለም ሁሉ መምሕር
*ርዕሰ ሊቃውንት
*ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
*ሐዲስ ዳንኤል
*ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
*መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
*ጥዑመ ቃል - - -
+እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ
ይክፈለን::
+ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56
ዓመታት
በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት
ተፈጽመዋል::
+እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ
በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት
ቃል ኪዳን
ተቀብላለች::
❖ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር
ያድለን::
❖ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የዓለም ሁሉ መምሕር)
2አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ (ፍልሠታቸው)
3.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ (ቃል ኪዳን
የተቀበለችበት)
4.አባ አብርሃም ዘደብረ ሊባኖስ
5.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
6.እስክንድር ንጉሠ ኢትዮዽያ
7.ቅዱስ መስቀል (የተአምር በዓሉ)
8.አባታችን ያሬድ (የማቱሳላ አባት)
9.ቅዱስ ሚናስ ዲያቆን❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት2፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ
3፡ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
5፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
6፡ ቅዱስ ላሊበላ
7፡ ቅድስት መስቀል ክብራ
++"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም
ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር
አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች
አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት
ሁሉም ያበራል::
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን
አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት
ይብራ:: +"+ (ማቴ.
5:13-16)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Forwarded from ✞ገድለ ቅዱሳን✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ቅዱስ አርሳኒ +"+
=>ቅድስት ሃይማኖት እዚህ ዛሬ እኛ ጋር የደረሰችው
በበርካታ ሰማዕታትና ጻድቃን ደም ነው:: ቅድስት ቤተ
ክርስቲያን
ግድግዳዎቿ እንጨትና ድንጋይ እንዳይመስሏችሁ:: አጽመ
ቅዱሳን ነው እንጂ::
+ቅዱሳን ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስን እንደ እኔ እና እንደ
ዘመኑ ትውልድ በከንፈራቸው የሚሸነግሉ አልነበሩም::
እነርሱ
በፍጹም ልባቸው ስለ ፍቅሩ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ
እንጂ:: በቅድስናቸው ከተመሰከረላቸው ቀደምት ቅዱሳን
አንዱ ደግም
ቅዱስ አርሳንዮስ ነው::
+ቅዱሱ የተወለደው በ345 ዓ/ም ሮም ውስጥ ነው::
በወጣትነቱ ይሕ ቀረህ የማይሉት የጥበብና የፍልስፍና
ሰው ነበር::
በተለይ በትልቁ የሮም ቄሳር ቴዎዶስዮስ ዘመን በቤተ
መንግስት አካባቢ የተከበረና የንጉሡ ልጆች መምሕር
ነበር::
አኖሬዎስና አርቃዴዎስን ቀጥቶ ያሳደጋቸውም እርሱ ነበር::
+በድንግልና እስከ 40 ዓመቱ ድረስ ሮም ውስጥ ቆየ::
ከዚህ በኋላ ግን ስለ ሰማያዊ ነገሮች ሲያስብ መልዐኩ
በሕልም ወደ
ግብፅ ሒድ አለው:: በመጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ቀጥሎ
ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ መነኮሰ:: በቆይታ ግን
ብሕትውና ምርጫው
ሆነ::
+ቅዱስ አርሳኒ በእነዚሕ ነገሮቹ ይታወቃል:-
1.በምንም ምክንያት ከማንም ጋር አያወራም:: (ለ60
ዓመታት በአርምሞ ኑሯል)
2.በቤተ መቅደሱ ግድግዳ ተጠግቶ እንባውን ሲያፈስ
የርሱን አካል አርሶ በመሬት ላይ ሲፈስ ይታይ ነበር::
ከእንባው ብዛት
ቅንድቦቹ ተላልጠው አልቀው ነበር::
3.በርካታ ድርሳናትን ደርሷል:: ብዙዎቹ ዛሬም ግብጽ
ውስጥ አሉ::
4.ሸንጎበቱን ወደ ደረቱ አዘንብሎ ስለሚቆም ማንንም ቀና
ብሎ አያይም ነበር::
5.ለጸሎት አመሻሽ 11:00 አካባቢ ላይ ይቆምና ጸሎቱን
የሚጨርስ ፀሐይ ግንባሩን ስትመታው ነው::
6.ሁል ጊዜ ራሱን "አንተ ሰነፍ (ሐካይ) እያለ ይገስጽ
ነበር::
7.በገዳማውያን ታሪክ የርሱን ያሕል በቁመቱ ረዥም
አልተገኘም ይባላል:: የራሱ ጸጉር በጀርባው የወረደ ሲሆን
ጽሕሙን
በስዕሉ ላይ እንደምታዩት ነጭና እስከ መታጠቂያው
የወረደ ነበር::
+እነዚህ ግን በጣም ጥቂቶቹ ናቸው::
+ቅዱስ አርሳንዮስ አካሉ በተጋድሎ ደቆ: ለ60 ዓመታት
በግሩም መንፈሳዊነት ኑሮ በ100 ዓመቱ በዚሕች ዕለት
ዐርፏል::
❖አምላካችን እግዚአብሔር ከታላቁ የቅድስና ሰው አርሳኒ
በረከት አይለየን::
=>ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አርሳንዮስ - አርሳኒ (ጠቢብ ገዳማዊ)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
=>+"+ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል:: ደግሞ
ተገርቷል:: ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው
አይችልም:: የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት
ነው:: በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን:: በእርሱም እንደ
እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን::
ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ:: ወንድሞቼ ሆይ
ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም:: +"+ (ያዕ. 3:7-11)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❖ ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ቅዱስ አርሳኒ +"+
=>ቅድስት ሃይማኖት እዚህ ዛሬ እኛ ጋር የደረሰችው
በበርካታ ሰማዕታትና ጻድቃን ደም ነው:: ቅድስት ቤተ
ክርስቲያን
ግድግዳዎቿ እንጨትና ድንጋይ እንዳይመስሏችሁ:: አጽመ
ቅዱሳን ነው እንጂ::
+ቅዱሳን ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስን እንደ እኔ እና እንደ
ዘመኑ ትውልድ በከንፈራቸው የሚሸነግሉ አልነበሩም::
እነርሱ
በፍጹም ልባቸው ስለ ፍቅሩ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ
እንጂ:: በቅድስናቸው ከተመሰከረላቸው ቀደምት ቅዱሳን
አንዱ ደግም
ቅዱስ አርሳንዮስ ነው::
+ቅዱሱ የተወለደው በ345 ዓ/ም ሮም ውስጥ ነው::
በወጣትነቱ ይሕ ቀረህ የማይሉት የጥበብና የፍልስፍና
ሰው ነበር::
በተለይ በትልቁ የሮም ቄሳር ቴዎዶስዮስ ዘመን በቤተ
መንግስት አካባቢ የተከበረና የንጉሡ ልጆች መምሕር
ነበር::
አኖሬዎስና አርቃዴዎስን ቀጥቶ ያሳደጋቸውም እርሱ ነበር::
+በድንግልና እስከ 40 ዓመቱ ድረስ ሮም ውስጥ ቆየ::
ከዚህ በኋላ ግን ስለ ሰማያዊ ነገሮች ሲያስብ መልዐኩ
በሕልም ወደ
ግብፅ ሒድ አለው:: በመጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ቀጥሎ
ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ መነኮሰ:: በቆይታ ግን
ብሕትውና ምርጫው
ሆነ::
+ቅዱስ አርሳኒ በእነዚሕ ነገሮቹ ይታወቃል:-
1.በምንም ምክንያት ከማንም ጋር አያወራም:: (ለ60
ዓመታት በአርምሞ ኑሯል)
2.በቤተ መቅደሱ ግድግዳ ተጠግቶ እንባውን ሲያፈስ
የርሱን አካል አርሶ በመሬት ላይ ሲፈስ ይታይ ነበር::
ከእንባው ብዛት
ቅንድቦቹ ተላልጠው አልቀው ነበር::
3.በርካታ ድርሳናትን ደርሷል:: ብዙዎቹ ዛሬም ግብጽ
ውስጥ አሉ::
4.ሸንጎበቱን ወደ ደረቱ አዘንብሎ ስለሚቆም ማንንም ቀና
ብሎ አያይም ነበር::
5.ለጸሎት አመሻሽ 11:00 አካባቢ ላይ ይቆምና ጸሎቱን
የሚጨርስ ፀሐይ ግንባሩን ስትመታው ነው::
6.ሁል ጊዜ ራሱን "አንተ ሰነፍ (ሐካይ) እያለ ይገስጽ
ነበር::
7.በገዳማውያን ታሪክ የርሱን ያሕል በቁመቱ ረዥም
አልተገኘም ይባላል:: የራሱ ጸጉር በጀርባው የወረደ ሲሆን
ጽሕሙን
በስዕሉ ላይ እንደምታዩት ነጭና እስከ መታጠቂያው
የወረደ ነበር::
+እነዚህ ግን በጣም ጥቂቶቹ ናቸው::
+ቅዱስ አርሳንዮስ አካሉ በተጋድሎ ደቆ: ለ60 ዓመታት
በግሩም መንፈሳዊነት ኑሮ በ100 ዓመቱ በዚሕች ዕለት
ዐርፏል::
❖አምላካችን እግዚአብሔር ከታላቁ የቅድስና ሰው አርሳኒ
በረከት አይለየን::
=>ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አርሳንዮስ - አርሳኒ (ጠቢብ ገዳማዊ)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
=>+"+ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል:: ደግሞ
ተገርቷል:: ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው
አይችልም:: የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት
ነው:: በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን:: በእርሱም እንደ
እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን::
ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ:: ወንድሞቼ ሆይ
ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም:: +"+ (ያዕ. 3:7-11)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር