Telegram Web Link
😭 በመናገሻ ገነተ ጽጌ (በአራዳ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመ ነውር 😭

😭 #ጥር_30_ዕለተ_ሐሙስ_ከምሽቱ_6:00 ሰዓት ላይ ያለ ማዘዣና ያለ ዕውቅና ሕግን በተላለፈ መልኩ በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ የየፖሊስና የፌደራል ልብስ የለበሱ ጥይት የታጠቁ አካላት ሰተት ብለው በመግባት ድፍረት የተመላበትን ተግባር ፈጽመዋል።

😭 የዕለቱን የጥበቃ አካላት በማስፈራራትና በመዛት "በቤተክርስቲያኑ ውስጥ መሳሪያ ተቀምጧል" በሚል የዲያቆናትና ካህናትን ቤት ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ እየበረገዱ ሕጋዊ የሆኑ (የቤ/ክ ሎጎ ያለባቸውን) ባንዲራዎች እያወረዱ በመውሰድ እንዲሁም በአካባቢው ምዕመናን የተገዙ ከ250 ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን የቤ/ክ ሎጎ ያለባቸውን ብዛት ያላቸውን ባንዲራዎች : የታቦት ማሳመሪያ የዲኮር ዕቃዎች በእግር እየረገጡ ክብራቸውን ባዋረደ መልኩ ተወስደዋል።

😭 የፖሊስና የፌደራል አካል ነን ብለው የመጡት አካላት ግቢውን በሚያውክ መልኩ ስለገቡ በጊዜው የነበሩ አካላት ወደ አስተዳዳሪው በመደወል እንዲመጡ ለማደረግ የቻለ ሲሆን የሕግ አካላት ነን ያሉት ግን አስተዳዳሪውን በማዋከብና ለብዙ ዓመታት የቤ/ክ እና የሀገር ቅርስ ያለበትን ሙዚየም ክፈቱ እስከማለት ለመጠየቅ ችለዋል የደብሩ አስተዳዳሪ ግን " ሕዝብና አገልጋዮች በሌሉበት ለዚያውም በዕኩለ ሌሊት አልከፍትም" በማለት አቋማቸውን አሳይተዋል።

😭  ይህ የቤ/ክን እና የምዕመናንን ክብር ባልጠበቀና እንደ ወንጀለኛ በዕኩለ ሌሊት መፈጸሙ ነውር ሆኖ ሳለ በካህናትና ዲያቆናቱ ላይ የተፈጸመው እንግልት ደግሞ እጅጉን አሳፋሪ ነበር በጊዜውም የነበሩ የአይን ምስክሮች እንደነገሩን አንዳንድ ካህና በተፈጸመው አዝነው አምርረው እስከማልቀስ ደርሰዋል።

😭 በቀጣይነትም ዳግም ይህ ነገር ለመፈጸሙ ምንም ዋስትና ስለሌለን የቤ/ክኑ አስተዳደር አካል ፥ የሰ/ት/ቤቱ አመራር ፥ የአካባቢው ወጣትና ምዕመናን በጋራ በመሆን ጉዳዩን በባለቤትነት የፈጸሙት አካላት የወሰዷቸውን ንብረቶች እንዲመልሱና የፈጸሙት የቤተ ክርስቲያንን ክብር የተገዳደረ መሆኑን እስከሚመለከት አካል ሔደው ሊጠይቁ ይገባል።

😭 አሁን ላይ ማንም እየተነሳ መሳሪያ አንግቦ ሕገ መንግሥቱን በተጻረረ መልኩ ቤ/ክ ድረስ ገብቶ የፈለገውን ነገር እያደረገ ነገም ካህናት ብቻ የሚነኩትን ቅዱሱን ታቦትና ንዋየ ቅዱሳቱን ላለመንካቱ ምንም ዋስትና የለንም።

😭 የደብሩ አስተዳደር የሰንበት ት/ቤቱ አመራርና አባላት የአካባቢው ወጣቶችና ምዕመናን በኃላፊነት ከመላው ምዕመን ጋር የተፈጸመውን ተግባር አውግዘን የተወሰዱ ንብረቶች ተመልሰው የተፈጸመውን ተግባር ልንጋፈጥ ይገባናል።

👉 ስለ መናገሻ ገነተ ጽጌ (አራዳ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያገባኛል 💒
† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ አጋቦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ †††

††† ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱሱ ሐዋርያ ሃብተ-ትንቢት የተሠጠውና በዘመነ ሐዋርያት (በቀላውዴዎስ ቄሳር ጊዜ) በዓለም ላይ ከባድ ረሃብ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረና በርካታ ክርስቲያኖችን ከረሃብና ከሞት የታደገ ትልቅ ሐዋርያ ነው:: (ሐዋ. 11:27)

በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመናገሩም "ሐዋርያ ትንቢት" ተብሏል:: በአገልግሎቱ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎችን ወደ ክርስትና በመሳቡ የተበሳጩ አይሁድም በዚህች ቀን ገድለውታል:: በተቀደሰ ሥጋው (መቃብሩ) ላይ ብርሃን ሲወርድ ያየች አይሁዳዊት ሴትም በክርስቶስ አምና ተሰውታለች::

††† የአባታችን በረከት ይደርብን::

የ††† ካቲት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አጋቦስ ነቢይ: ሐዋርያና ሰማዕት
2.አባ ዘካርያስ ትሩፈ ምግባር

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ነጎድጓድ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፊያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ

††† "በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ:: ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነስቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ:: ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ::
ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው: እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ::
እንዲህም ደግሞ አደረጉ:: በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት::" †††
(ሐዋ. ፲፩፥፳፯)

††† "ስለ እኛ ትጸልዩ ዘንድ ይገባቹሃል: ለሁሉ መልካም ነገርን እንደምትወዱና እንደምትሹ እናምናለን::" †††
(ዕብ. ፲፫፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Audio
ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት አራት(፬)
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
Forwarded from Bketa @¥
“ብዙ እናቶች ስቃይ ካለበት የወሊድ ሰዓት በኋላ ልጆቻቸውን ሌሎች እንዲመግቡላቸው ለእንግዶች ይሰጣሉ። ክርስቶስ ግን እኛ ልጆቹን በብዙ መከራ እና ስቃይ በመስቀል ላይ ከወለደን በኋላ ሌሎች እስኪመገቡን ድረስ አይተወንም። በገዛ ሥጋ እና ደሙ እየመገበ ራሱ ያሳድገናል። በዚህ ሁሉ መንገድም ከራሱ ጋር አንድ ያደርገናል።”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

††† እንኩዋን ለአባታችን "አባ ብሶይ ዼጥሮስ" እና "ቅዱስ ዕብሎይ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† አክርጵዮስ †††

በዚች ቀን የእስክንድሪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አክርጵዮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አስረኛ ነው። ይህም አባት እግዚአብሄርን የሚፈራ ንፁህ ቅዱስ ነው ።

በእስክንድርያ አገርም ቄስ ሆኖ የሚያገለግል ነበር ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ በአረፈ ጊዜ የእስክንድር አገር ህዝብና ኤጲስቆጶሳቱ መረጡት በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

ከዚህም በኃላ እንደ ሀዋሪያት መልካም ጉዞን ተጓዘ የእግዚአብሄርን ሀይማኖት ህይወት የሆነ ህጉንም እያስተማረ ቅዱሳት መፅህፍትንም እያነበበላቸውና እያስተማራቸው መንጋዎቹን ይጠብቃቸው ነበር ሁል ጊዜም ይመለከታቸዋል አንድ የብር አላድን ወይም አንድ የወርቅ ዲናርን ጥሪት አላኖረም ከእለት ምግቡ ከቁርና ከሀሩር ስጋውን ከሚሸፈንበት ልብስ በቀር ምንም አላከማቸም።

በዚህም ተጋድሎ አስራ ሁለት አመት ኑሮ ጌታችንንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

+*" ቅዱስ ዕብሎይ "*+

=>አባ ዕብሎይ በቀደመ ሕይወቱ ለ40 ዓመታት በኀጢአት የኖረ: እግዚአብሔር ለንስሃ ሲጠራው "እሺ" ብሎ : ለ40 ዓመታት በንስሃ ሕይወት ተመላልሶ በበርሃ የተጋደለ: እንባው እንደጐርፍ ይፈስ የነበረ: አጋንንትንም ድል የነሳና ለፍሬ: ለትሩፋት የበቃ ቅዱስ አባት ነው:: እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶለታል::

<< ባርያ ሆኖ ያለ ኀጢአት: ጌታ ሆኖ ያለ ምሕረት የለምና ይቅር በለን !! >> (የአባ ዕብሎይ የንስሃ ጸሎት)

+*" አባ ብሶይ (ዼጥሮስ) "*+

=>ብሶይ (ቢሾይ) በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተለመደ
የቅዱሳን ስም ነው:: በተለይ በምድረ ግብ በዚህ ስም
ሰማዕታትም : ጻድቃንም ተጠርተውበታል:: ከእነዚህ
ቅዱሳን (ከገዳማውያኑ) አንዱ የሆነው አባ ብሶይም
(አንዳንዴ አባ ዼጥሮስም ይባላል) የዘመነ ጻድቃን ፍሬ
ነው::

+ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ቤት ናት:: ያ ማለት ራሳቸውን
ለክርስቶስ የለዩ ሰዎች ይኖሩባታል:: እነዚህ ሰዎች
ከተለያየ ጐዳና እና ማንነት ሊመጡ ይችላሉ:: ቢያንስ ግን
በንስሃ የታጠቡ መሆናቸው ወደ ተቀደሰው አንድነት
እንዲገቡ ትልቅ መሠረት ይሆናቸዋል::

+ቅዱሳንም አንዳንዶቹ ከእናታቸው ማኅጸን ሲመረጡ :
ሌሎቹ ደግሞ ከኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ሆነው
ይታያሉ:: ደስ የሚለው ደግሞ በንስሃ ከታጠቡ በሁዋላ
በፍጹም ልባቸው በመጋደላቸው እነሆ በሰማያዊ አክሊል
ተከልለዋል::

+አባ ብሶይ ዼጥሮስም ከኃጢአት ተመልሰው ለቅድስና
ከበቁ ቀደምት አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱ ተወልዶ
ባደገባት ምድረ ግብጽ የታወቀ ሽፍታ : ዝሙተኛና ክፋቱ
የተገለጠ ሰው ነበር:: ለብዙ ዘመናት በእንዲህ ካለ ግብሩ
መላቀቅ ባይችል እግዚአብሔር ጥሪውን ላከለት::

+የአምላካችን የጥሪ መንገዱ ብዙ ነውና ለእርሱ ደዌን
ላከለት:: መቼም ወደድንም ጠላንም በሽታ ወደ
እግዚአብሔር የሚያቀርብ ጥሩ ፈሊጥ (አጋጣሚ) ነው::
ዛሬም ቢሆን ዘለን : ዘለን ስንሰበርና የሐኪም መፍትሔ
ሲጠፋ የግዳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት (ወደ ጸበሉ)
እንቀርባለንና:: አምላካችን ስለዚህ ጥበቡ ይክበር
ይመስገን::

+ቅዱስ አባት ብሶይም በሽፍትነትና በኃጢአት ኑሮ ሳለ
ለሞት የሚያበቃ ደዌ ደርሶበት የአልጋ ቁራኛ ሆነ::
ኃይሉም ደከመ:: በእንዲህ እያለም በራዕዩ ያየው ነገር
ፍጹም አስደነገጠው::

መላእክት ነፍሱን ወስደው መካነ ኩነኔን ካሳዩት በሁዋላ
አለቀሰ::

+ይልቁን ሌቦችና ዝሙተኞችን ከ4 ሲቆራርጣቸው ስላየ
ፈጽሞ አዘነ : ተጸጸተ:: ፈጣሪውንም ዕድሜ ለንስሃ
እንዲሰጠው ተማጸነ:: ጌታንም "አምላኬ ሆይ! ከበሽታየ
ብታድነኝ : ዳግመኛ አልበድልህም:: ዓለምን ሁሉም ንቄ
አገለግልሃለሁ" ሲል ተማጸነው::

+እግዚአብሔርም ሰምቶት ፈጥኖ ፈወሰው:: አባ ብሶይም
እንደ ቃሉ በፍጹም ልቡ ንስሃ ገብቶ መነነ:: በገዳመ
አስቄጥስ (ግብጽ) ለ38 ዓመታት ሲኖር የላመ የጣመ
በልቶ : ከሞቀ መኝታ ተኝቶ አያውቅም::

+ሰውነቱን ይቀጣት ዘንድም እስከ 30 ቀን ያለ እህል ውሃ
ይጾም ነበር:: በዘመኑ ሁሉም የሴት መልክን አላየም::
ንስሃን የሚወድ ጌታም ጸጋውን አብዝቶለት ብዙ ድርሳናትን
ጽፏል:: የሚገርመው ደግሞ ከትህትናውና ቅድስናው
የተነሳ የእያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ተገልጦ ይታየው ነበር::

+ቅዱሱ አባታችን ብሶይ ዼጥሮስ በንስሃና በቅድስና
ሕይወት እንዲህ ተመላልሶ በዚህች ቀን ዐርፎ በገዳሙ
ተቀብሯል:: የድካሙን ዋጋም አድልዎ ከሌለበት :
ከእውነተኛው ፈራጅ ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተቀብሏል::

=>አምላከ ቅዱሳን ዕድሜ ለንስሃ : ዘመን ለፍስሐ
አይንሳን:: ከክብረ ቅዱሳንም ያካፍለን . . . አሜን !!

=>የካቲት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
2.ቅዱስ አባ ብሶይ ጻድቅ
3.አባ አክርዽዮስ
4."49" አረጋውያን ሰማዕታት (ፍልሠታቸው)
5.ቅዱስ አሞኒና ሚስቱ ቅድስት ሙስያ (የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች)
6.አባ ኖብ ጻድቅ : መነሳንሱ ዘወርቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

=>አምላክ በበረከታቸው ይባርከን::

=>+"+ መቶ በግ ያለው : ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7)

†ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
†ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር አሜን †
Audio
ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት አምስት(፭)
@SinkisarZekidusan2
"ላለማመን እንጂ ለማመን በዙሪያችን ብዙ ምስክሮች አሉልን"

ዓይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔርን መኖር የሚክዱ ተመራማሪዎች የራሳቸውን እውቀት መነሻ በማድረግ የእግዚአብሔርን አለመኖር ከነገሩት በኋላ "እስኪ አንተ እግዚአብሔር መኖሩን በተጨባጭ አስረዳን?" ሲሉ ጠየቁት። ቅዱስ ዲዲሞስ ተመራማሪዎቹ ጭልጥ ብለው መሳሳታቸውን ቢያውቅም በጥሞና ያዳምጣቸው ነበር እንጂ አልተበሳጨም። ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት "ምሽት ተመልሳችሁ ኑ" አላቸው።

እነርሱም የቀጠሮአቸውን ሰዓት አክብረው ምሽት ተመልሰው መጡ። ቅዱስ ዲዲሞስም "እስኪ ወደላይ አንጋጣችሁ የሰማዩን ገጽታ ተመልከቱ" አላቸው። እነርሱም እንዳላቸው ሰማዩን ተመለከቱ። እርሱም "በሰማይ ላይ ምን ምን ይታያችኋል?" አለ። እነርሱም "ከዋክብት" ብለው መለሱለት። እርሱም "በስጋዊ አይናችሁ የማየት ችሎታ እነዚህን ክዋክብት በቀን ማየት ትችላላችሁን?" አላቸው። እነርሱም "አንችልም" አሉት። እርሱም "ለምን ማየት ያቅታችኋል?" ሲል ጥያቄውን በጥያቄ ደገመላቸው። እነርሱም "ምክንያቱም ከዋክብትን ለማየት የግድ መምሸት አለበት" አሉት። እርሱም "በእርግጥ ትክክል ናችሁ የመለሳችሁት ምላሽ ትክክል ነው። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እንደምናውቀው የተሰወረውን ነገር ለማግኘት ብርሃን ያስፈልጋል እነዚህን የምታዩአቸው ከዋክብት ለማየት ግን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ ሊኖር የግድ ነው። እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔርንም ለማየት ቁሳዊ ነገርን ማየት በሚቻልበት በሳይንስ መሳሪያና ፍልስፍና ሳይሆን በእምነት ብቻ ማረጋገጥ እንደሚቻል ልነግራችሁ እወዳለሁ።" በማለት አስረዳቸው።

 በድጋሚ "በሰማያት ገጽታ ላይ ከዋክብት እንደሚታዩ ነግራችሁኛል። ይሁን እንጂ እኔ ዓይነ ሥውር ስለሆንኩ በምን ታረጋግጥሉኛላችሁ?" ሲል አዲስ የጥያቄ ርዕስ ከፈተላቸዉ። እነርሱም ግራ ተጋብተው ምላሽ አጡ፤ እናም ከመናገር ይልቅ ዝምታን መረጡ። እርሱ ግን የእኔ ዓይነ ስውርነት የከዋክብቱን አለመኖር አያረጋግጥም፤ እኔ አየሁም አላየሁም ከዋክብቱ ዘወትር አሉ። እኔም ምንም ዐይነ ሥውር ብሆንም እንኳን ከዋክብቱን ሳልመለከት እናንተ አይታችሁ በነገራችሁኝ ምስክርነት ብቻ የከዋክብቱን መኖር አምኜ ተቀብየዋለሁ አላቸው። እኔ አንዳች ከዋክብት ሳልመለከት የከዋክብቱን መኖር እንዳመንኩ እናንተም በሥጋዊ አይናችሁ ባትመለከቱም እንኳን በእምነት እግዚአብሔር መኖሩን አታምኑምን? ብታምኑ መልካም ነው።" ሲል በትሕትና ጠየቃቸው። እነርሱም በጥያቄ መልክ ያቀረበላቸውን አስተሳሰቡን እና ምስክርነቱንም ተቀብለው የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት አረጋገጥን አሉት። በዚህ የክርክርና የውይይት ሁኔታ ዓይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ (በትሕትናውና በድክመቱ) የተናገሩትን አድምጦ የእነርሱን ዕውቀታቸውንና አስተሳሰባቸውን ተጠቅሞ ክብራቸውን ሳይጋፋ የእግዚአብሔርን መኖር በማሳመን ረታቸው። ክርክራቸውም በዚህ ተደመደመ።

(#ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ "የሕይወት መንገድ" በመምሕር ሰለሞን በቀለ ከተተረጎመ መጽሐፍ የተወሰደ)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን

✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ቀናችንን በጸሎት እንጀምር


🔔 ስንክሳር ዘወርኀ የካቲት ፯


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት ሰባት በዚች ቀን የእስክንድርያ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት እለእስክንድሮስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ሦስተኛ ነው።

❖ ይህም አባት ታሮን በሚባል ገዳም መነኰሰ ትርጓሜውም የአባቶች ገዳም ማለት ነው በጌታችንም ፈቃድ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ እርሱ የተማረ አዋቂ ጻድቅ ሰው ነበረና።

❖ በሹመቱ ወራትም ብዙ መከራ ደረሰበት የግብጽ ንጉሥ ልጁን ሹሞ በመንግሥቱ ላይ አሠለጠነው እርሱም በአስቄጥስ በረሀ ያለውን የመነኰሳቱን ገዳማት አፈረሳቸው።

❖ ከክፋቱና ከክህደቱ ብዛት የተነሣ ከምስር በስተሰሜን ወዳለች ገዳም ገብቶ በዚያ አምላክን የወለደች የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን አየና ይች ምንድን ናት አለ እርሷም በሽልማት ሁሉ የተሸለመችና ያጌጠች ናት በልብሶቿም ላይ ያማረ የሐር ልብስ ነበረ ስዎችም የክርስቶስ እናት የሆነች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሥዕል ናት አሉት እርሱም ተሳድቦ የረከሰ ምራቁን በፊቷ ላይ ተፍቶ ደኅና ከሆንኩ ክርስቲያኖችን ፈጽሜ አጠፋቸዋለሁ አለ ዳግመኛም በክብር ባለቤት በጌታችን ክርስቶስ ላይ የስድብ ቃልን ተናገረ።

❖ ሌሊትም በሆነ ጊዜ የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ታላቅ ራእይን አየ በነጋም ጊዜ ለአባቱ እንዲህ ብሎ ነገረው ዛሬ በዚች ሌሊት ታላቅ መከራና ብዙ ቅጣት ደረሰብኝ ታላቅ ዙፋንንም አየሁ በላዩ የተቀመጠበት ሰው እጅግ የሚያስፈራ የሚያስደነግጥ ነው ፊቱም ከፀሐይ ይበራል የብዙ ብዙ የሆኑ ሠራዊት የጦር መሣሪያ ይዘው በዙሪያው ቁመው ነበር እኔና አንተም እሥረኞች ሁነን በኋላው ቁመን ነበር እኔም በዙፋን ላይ የተቀመጠው ማነው ብዬ ጠየቅሁ ትላንት አንተ የዘበትክበት የክርስቲያን ንጉሥ ክርስቶስ ይህ ነው አሉኝ ከዚህም በኋላ የጦር መሣሪያ ከተሸከሙት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ ጐኔን በጦር ወጋኝ ጦሩንም ከጐኔ ውስጥ አላወጣውም፤ አባቱም ሰምቶ ደነገጠ እጅግም አዘነ ያ ልጁም ወዲያውኑ ታመመ አንደበቱም ተዘግቶ በክፉ አሟሟት ሞተ።

❖ ዳግመኛም ከአርባ ቀን በኋላ አባቱ ሞተ፤ በርሱም ፈንታ ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም ክርስቲያኖችን እጅግ አሠቃያቸው ይህንንም አባት ሊቀ ጳጳሳት እለእስክንድሮስን አብዝቶ አሠቃየው ከሕዝቡ ሦስት ሺህ የወርቅ ዲናር ለምኖ እስከ ሰጠው ድረስ ጌታችንም ይህን ንጉሥ ፈጥኖ አጠፋው።

❖ ከዚህም በኋላ አሁንም ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም ሊቀ ጳጳሳቱን ይዞ እንደ ቀድሞው ሦስት ሺህ የወርቅ ዲናር እንዲሰጠው ፈለገ እርሱም ከወገኖቼ እስከምለምን ታገሠኝ ብሎ ማለደው ንጉሡም ቀጠሮ ሰጠውና ይለምን ዘንድ ወደ ላይኛው ግብጽ ወጣ።

❖ በተራራ ላይ አንድ ገዳማዊ ሰው ነበር ከእርሱም ጋር ሁለት ደቀ መዛሙርት አሉ በተራራውም በአንድ ቦታ እንዲቆፍሩና እንዲጠርጉ አዘዛቸው ወርቅን የተመላ አምስት ማሰሮ አገኙ አንዱን ሸሽገው አራቱን ወደ ገዳማዊ መምህራቸው አመጡ እርሱም ይረዳበት ዘንድ እንዲስጡት ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ላካቸው፤ እነርሱ ግን እነዚያን የወርቅ ማሰሮዎች ይዘው ተመልሰው ወደ ዓለም ገቡ የምንኵስና ልብሳቸውንም ጥለው ሚስት አገቡ በዚያም ወርቅ ወንዶችና ሴቶች ባሮችን እንስሳትንም ገዙ።

❖ የዚያችም አገር አስተዳዳሪ ያዛቸው ገንዘብንም ከወዴት እንዳገኙ በመግረፍ መረመራቸው እነርሱም አምስት የወርቅ ማሰሮዎችን እንዳገኙ አመኑ መኰንኑም ለንጉሥ የጭፍራ አለቃ አሳልፎ ሰጣቸው እርሱም ወደ ንጉሥ አቀረባቸውና አምስት የወርቅ ማሰሮ እንዳገኙ አስረዳው ንጉሡም ጭፍሮቹን ልኮ የሊቀ ጳጳሳቱን ቤት በረበረ የአብያተ ክርስቲያናት ከሆነ ከንዋየ ቅድሳት ያገኘውን ሁሉ ወሰደ ሊቀ ጳጳሳቱንም አሠረውና ወርቅን የተመሉ አራቱን ማሰሮዎች ደግሞም ሦስቱን ሽህ የወርቅ ዲናር አምጣልኝ አለው እርሱም ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ገንዘብ ምንም ምን የለኝም አለው ወደ ሕዝቡ ልኮ ሦስቱን ሽህ የወርቅ ዲናር አምጥተውለት እስከ ሰጠው ድረስ አልተወውም ይህንንም ክፉ ንጉሥ ጌታችን አጠፉው።

❖ ከዚህም በኋላ ከእርሱ የከፋ ሌላ ንጉሥ ተሾመ እርሱም የሐሰተኛውንና የርኵሱን ነቢይ ስም በከበረ መስቀል ፈንታ በእጆቻቸው ውስጥ እንዲአትሙ የክርስቲያንን ወገኖች አስገደዳቸው፤ ይችም ምልክት የመለኮትን ነገር የሚናገር ወንጌላዊ ዮሐንስ የተናገራት ትንቢት ናት ይህም ክፋ ንጉሥ ወደ ሀገሮች ሁሉ ይህን እንዲአደርጉ አዘዛቸው ሊቀ ጳጳሳቱንም እንዲሁ ያደርግ ዘንድ አዘዘው።

❖ ሊቀ ጳጳሳትም ይተወው ዘንድ ብዙ ለመነው አልተቀበለውም ዳግመኛም እስከ ሦስት ቀን ይታገሠው ዘንድ ለመነው ከዚህም በኋላ ደግሞ እንዳይጥለውና ወደዚህ ወደረከሰ ሥራ እንዳያስገባው ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ማለደ ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በጥቂት ደዌ ጐበኘው ወደ ቤቱ እስክንድርያ ይሔድ ዘንድ እንዲአዝዝለት

❖ ጉሡም ከለከለው ሰለ እጅ ኀትመት ምክንያት ለመፍጠር ሰለ መሰለው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገለጠለትና ነገ ታርፋለህ አለው እርሱም አርድእቱን እግዚአብሔር ነገ ስለሚጐበኘኝ አርፋለሁና መርከብን አዘጋጁ አላቸው፤ አንዳለውም በማግሥቱ አረፈ ሥጋውንም በመርከብ ተሸክመው ወስደው ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሥጋ ጋር ቀበሩት።

❖ በዚህም አባት አለእስክንድሮስ ዘመን በግብጽ አገር ለሚኖሩ መለካውያን ስሙ አንስጣስዮስ የሚባል ሊቀ ጳጳሳት ነበራቸው ያዕቆባውያን ምእመናንን ይወዳቸዋል ስለዚህም ወገኖቹ መለካውያን ተጣሉት፤ እርሱም ነፍሱን ያድን ዘንድ አስቦ ወደዚህ አባት አለእስክንድሮስ መጥቶ ከሥልጣኑ በታች በመሆን የሚታዘዝ ሆነ እለእስክንድሮስም አንስጣስዮስን በእርሱ ፈንታ የሊቀ ጵጵስናውን ሥልጣን ይዞ መንጋውን ይመራ ዘንድ እርሱ ግን ከመነኰሳት እንዳንዱ ሁኖ በገዳም ይኖር ዘንድ እንዲተወው ለመነው።

❖ አባ አንስጣስዮስም አልወደደም እንዲህም አለ ይህን የምሻ ከሆነ አኔ እስከ ዛሬ ሊቀ ጳጳሳት አልነበርኩምን ላንተ ደቀ መዝሙርህ ሁኜ ላገለግልህ ወደድኩ እንጂ አለ፤ በመካከላቸው ከተደረገው ከብዙ ልመና ከብዙ ምልልስም በኋላ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ አንስጣስዮስ ፈቀደ በአንዲትም ሀገር ላይ ኤጲስቆጶስነትን ሾመው፤ መንጋውንም እንደሚገባ በጎ አጠባበቅን ጠበቀ፤ አባት እለእስክንድሮስም በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር የኖረው ሃያ አራት ዓመት ከስድስት ወር ነው እግዚአብሔርንም አገለገለው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑን ለዘላለሙ አሜን።
2024/10/01 04:44:32
Back to Top
HTML Embed Code: