Telegram Web Link
ናፈቀኝ ሀገሬ
"""""""""""""""
ብዕሬን ሸክፌ
ሀሳብ አጠንፍፌ
ቃላት አጣልፌ
ሄድኩኝ ከወረቀት፤

ቅኔ ልደረድር
ግጥሜን ልሰድር
ከመድብሌ ልከት!

ሀገር ብዬ ጀመርኩ
ሀገሬን ላልጨርስ
ጦማሬን ከትቤ፤

ዋ ብሎ አስፈራራኝ
ከራሴ እያጣላ
አመንትቶ ቀልቤ!
.
.
ለምን አልሽ አለሜ?
.
.
እንደምን ይፃፋል
ስለሀገር ግጥም
ጦቢያ ይሉት ቅኔ፤

ሁሉም አስሮ ይዞት
ዘር የሚሉት ብሂል
የአስተሳሰብ ጠኔ፤

የአባ ጃርሶ ቁጣ
የአቶ መርዕድ ዱላ
የት አለና? ዛሬ፤

የፅዮን ስፍስፍ ልብ
የከድጃ ገር ነፍስ
ርቆ ሄዶ ከኔ፤

የትርንጎ ውበት
የአለሚቱ ምክር
ጠፍቶ ከዘመኔ፤

እንደምን ይፃፋል
ሀገር ይሉት ግጥም
ሀገር ይሉት ቅኔ!
.
.
ጉድ አለ በሀገሬ
.
.
አዬ ጉድ ነው መርዶ
ሰው ከራስ ተሰዶ
ከእምነቱ እረክሶ፤

እሩቅ እሩቅ ሲሄድ
እሳትን ሲላመድ
እያደር ተናንሶ፤

ስክነት ይሉት ጠፍቶ
ሰው እብሪትን ሽቶ
እሳትን ተላብሶ፤

አባት አንገት ደፍቶ
እናትን ሆድ ብሷት
አይኖቿ አልቅሶ፤

እህት በእህቷ
ወንድም በወንድሙ
ጦር ሰይፍ ተማዞ፤

መከባበር ጠፍቶ
ልጂት እናት ንቃ
ልጅ አባቱን አ'ዞ!

ሰው በቁም ታርዞ
ሲሄድ ሲፈረጥጥ
ቁልቁሉን እሩጫ
የእውር ድንብር፤

እንዴት ከግጥሜ ላይ
ጎላ ብላ ትፃፍ
ቅኔ ያላት ሀገር?
.
.
እንዴት? .....እንዴት?
.
.
ወገን ተከፋፍሎ
እገደል ተምሎ
በዘርና በጎጥ፤

በነጮች ሰበካ
ከሀገር ተሰዶ
በድኑን ሲቀመጥ፤

በዳንኪራ ፈዞ
ቁሙን ተገንዞ
ከሀገር ሲፈረጥጥ፤

እና እንዴት ተብሎ
ስለ ሀገር ይፃፍ
ሀገር ትቆላመጥ?
.
.
ተመልከች ዓለሜ
.
.
ሀገር ማለት ሰው ነው
ሰው ነው
ሰው ነው ሀገር፤

ሰው ከሌለ የለም
ሀገር ይሉት ወሬ
ሀገር ይሉት ነገር!

ሰብዕና ጎድሎ
በሌላ ተደልሎ
በቁም ተቀምጦ እሩቅ ከከነፈ፤

ምን ተብሎ ቅኔ
ምን ተብሎ ግጥም
ስለ ሀገር ተፃፈ?
.
.
(እናማ)
.
.
ስለሀገር ያሰብኩት
ብዙ የተለምኩት
ባሸተው ሰንፍጦ
ብቀምስ ጎመዘዘኝ፤

ከእውነቱ ተውኩና
ከተስፋ አጠቀስኩኝ
ብዕሬን አነሳሁ ከወረቀት ልቀኝ፤

ሀሳቤን ሳሰፍር
የሚል ግጥም ፃፍኩኝ
ሀገሬ ላይ ቆሜ ሀገሬ ናፈቀኝ!

(ሀገሬ ናፈቀኝ)

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Gitemenlenante
።።።።አምላኬ ሀገሬን ጠብቃት።።።።።
[አልአዛር] #Alazar

እጅግ ውብ ድንቅ አርገህ በእጅህ ፈጥረሀት
ለዘለአለም የሚኖር ቃልኪዳንህን ሰተሀት
ለአለም ማረፊያ እስትንፋስ አርገሀት
የቀደምት የሰውን ዘር ፍጥረታት
የቀደምት ጀግንነት
የቀደምት አንድነት
የቀደምት ህይወት
አሟልተህ የሰጠሀት
ሀገሬ ሀገራችን እሷም ኢትዮጵያ ናት
ታድያ ታድያ ምነው አሁን ዘነጋሀት
ያ የነበራት ሰላምና አንድነት
በባንዳዎች ክፋዎች ሲነፈግ በድንገት
ምነው ዝም አልካት ምነው ዘነጋሀት
በጥቂት ባንዳዎች ክፋዎች ዝቃጮች
አዕምሮ በሌላቸው ባዶዎች ውራጆች
ቃል የማይገልጻቸው የሰይጣን እረኞች
ክፋት በወረሳቸው የገሀነም ሰዎች
ህሊና በሌላቸው በርካሽ ፍጥረቶች
አስተሳሰብ በሌላቸው ርካሽ ባንዳዎች
ያጎረሰ እጇን ሲነክሱት
ደግ እናትነቷን ሲከዱት
ታድያ ምነው ዘነጋሀት
ካለም የቀደመ ስልጣኔ ያላት
ምድሯ ፈውስ አየሯ ህይወት አርገህ የፈጠርካት
ሀገሬ ሀገራችን እሷም ኢትዮጵያ ናት
ቀስተደመና በመሰለ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ
ውብ ናት ሀገራችን ሁሌም ምታኮራ
እባክህ አምላኬ የቃልኪዳንህን ምድር
እባክህ ጠብቃት የቃልኪዳንህን ሀገር
ሀገር በጥባጮችን ባንዳዎችን ቀጥተህ
የሰይጣን እረኞች ሀገር በጥባጮችን ከምድሯ አውጥተህ
የነበራትን ፍቅርና አንድነት
ህዝቦቿንም ባርከህ ሰላምን ሰጥተሀት
የህዝቦቿን እምባ አብሰህላት
ከፀብ ከጦርነት ከክፋት አርቀሀት
የልጆቿን ጸሎት ሰምተህላት
እባክህ አምላኬ ሀገሬን ጠብቃት

#Alazar{CJ}
@Gitemenlenante
#ሀገር_የከፋት_ለት

በቀን ግፍ ተገፍቶ ለመሄድ ሲገደድ
ሀገር ጸንታ ሳለች ሰው ነበር ሚሰደድ።
ግን እንዲህም ደሞ
ብሶት ከሰው ወርሳ
በእንባ ድጥ ርሳ
ከጫፉም ጫፍ ደርሳ
በጨካኞች ግፊ
አገርም እንደሰው ሲላት ጥፊ ጥፊ
ጨለማን አልብሼ…
ፊቷን ለመሸሸግ ቀኔን እያስመሸሁ
እንባዋን አብሼ…
የተሰበረውን ጥንድ እግሯን እያሸሁ
በጀርባዬ አዝያት ሀገሬን ባሸሸሁ።

ገጣሚ፦ ኢዛና መስፍን
@Gitemenlenante
ክብር ደማቸው ገብረው አጥንታቸውን ከስክሰው ለሀገር አንድነት ለሀገር ሉአላዊነት ለህዝብና ለሀገር መከታ ለሆነው ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት 😍😍😍😍😘😘😘😘
@Gitemenlenante
#ወቶአደር

የሀገር መመኪያ ~ የህዝቦች ሰላም
ጠላት ለመመከት ~ በፅናት ሚቆም
የወገኑን ሞት ~ ቀድሞ የሚካፈል
የፍቅር ተምሳሌት ~ ችግርን የሚችል
ቤተሰቡን ትቶ ~ ከሞት የሚጋፈጥ
ለህይወቱ ማይሳሳ ~ ሀገሩን የማይሸጥ
ሚከፈለው ደሞዝ ~ ህይወት የማይተካ
ተሰማርቶ ሚኖር ~ በበረሀ ጫካ
የኢትዮጵያን አርማ ~ ከፍ አድርጎ ሚያፈካ
እርሱ ነው ወቶአደር ~ ጠላትን ማረሻ
መጥቀሙን እንጂ ~ ጥቅሙን የማይሻ
ለአገሩ ሰርቶ ~ ለሀገሩ ሚሞት
ወቶአደር ሲኖር ነው ~ ኢትዮጵያ ሚያምርባት
07/03/13

ዳዳ coffee
@Gitemenlenante
#ውዝግብ_2

አራሚም
ታራሚሚ ባልተበየነለት
እንደልቡ ዘመን
ወላድ በሬው በዝቶ...
እንዳገር ተዛመን
ስልቻ ባነሰው ፥ የሀተታ ስብስብ
በቢላዋ ምላስ
እየተመተረ...... ነጭ የወሬ ስብ
ግንባር ስጋ ያሉት
ቁልፍልፉ ወጥቶ ..... ከማደናገሩ
በጠየቁ ቁጥር.........ብዙ በቆፈሩ
ጥያቄ ያጭራል ፥ የመልስ ዳር ዳሩ ።

አብርሀም_ተክሉ
@Gitemenlenante
እረኛዬ 🐑🐑
---------

በማለዳ ማልደህ
በቀትር ቀትረህ
በለሊት እንቅልፍህ
ድካም ሳይበግርህ
ታሰማራኛለህ በለምለሙ ስፍራ
ጠግቤ እንዳድር ለነፍሴ ስትራራ

ከሰላሜ ማዕድ ጎሎ እንዳልጠቁርብህ
ግጦሽ እንዳላየ ስቤ እንዳይከሳብህ
በአውሬ ተበልቼ ነፍሴ እንዳትቀጠፍ
ከኋላዬ ሳይሆን ከፊቴ የምታልፍ
አስቀድመህልኝ ሞትህን ከሞቴ
አሻራ አኖርክልኝ የእግርህን ኮቴ

በጨለማ ቢሆን ጉዞዬ መንገዴ
በእሳት እያለፍኩ ጨሼ አለመንደዴ
ነበልባሉ አልፈጀኝ ጎርፉ አላሰጠመኝ
እሳቱን በውሃ እያጠፋህልኝ
በውሃ ላይ አቁመህ በ'ታምር አስኬድከኝ

አይኖቼ ታውረው
ህዋሶቼ ታስረው
ብርሀን የምትሆነኝ
የነፃነት ዋሴ
አለኝታዬ ለኔ ጠበቃ የነፍሴ

ሞት ጥላ አጥልቶብኝ
ጠላቶች ከበውኝ
ሀገር ሰላም ብዬ የምረማመደው
አንተ እረኛዬ ጎሳይ ሆነኸኝ ነዉ
ከማመስገን ሌላ ምን እከፍልሃለሁ
ክብሬን ሁሉ ውሰድ
ከብረህ ታይ ብያለሁ
አመሰግናለሁ! 🙏🙏

#መአዛ ጥበቡ🌓
@Gitemenlenante
# ሀገር_ማለት_ሰው_ነው

ሁሉም ተገንጥሎ ~ አንድ እኔ እንኳን ብቀር
በተረፋት መሬት ~ በቀረቻት አፈር
አስቀጥላታለሁ ~ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@Gitemenlenante
#ኣንድ_ያልተረዳኸው

በሴት ልጅ እንባዋ
ከሞላው ገምቦዋ
ከዚያ ከምታዝለው ስትል ላንተው ጥማት
ክብሯን ማጉደልህ ነው እህቴን ያመማት

#Ezana_Mesfin
@Gitemenlenante
_ እሚኝ

የምወድሽን ያህል ፥ አንቺ እኔን ባትወጂኝ
ፍቅሬ ከጤፍ አንሶብሽ...እፍ ብለሽ ብትሰጂኝ
ለመግፋትሽ የተገፋሁ ፥ እኔስ ታዲያ ፥ ምኔ ሞኙ
እንዳልነበርሽ መኖር ጀመርኩ ፥ ተፋታሁኝ ከሙጥኙ ።
................. አብርሀም_ተክሉ
@Gitemenlenante
"ደስታ የገደለዉ"
__________________

ሲያድለኝ ወደድኩኝ
ሲያድለኝ አፈቀርኩ
ፍቅሬን ለማሳየት
እጅጉን ተቸገርኩ
ስንት ምኞት ተመኘሁ
ስንት አበባ ቀጠፍኩ
ሃሎ ማለት አቅቶኝ
ስንት ሰላምታ ሰሰትኩ
ለመዉደድ ለፍቅር
እንዲህ ከሆንኩልሽ
ሀሳቤን ተረድተሽ
እሽ ያልሽኝ እለት
ቀብረሽኝ ሂጅና
መርዶ ንገሪያቸው
ምነዉ ያሉ እንደሆን
ደስ ደስ ደስ ብሎት
እኔን ስላገኘ ደስታ አፍኖት ሞተ
ብለሽ ንገሪያቸዉ፡፡
@Gitemenlenante
ናፈቅሽኝ እለት

የሰማይ ደመናን ከሩቅ ተመልክቼ
ውበት ቁንጅናሽን በሀሳቤ ለክቼ
በናፍቆቴ ብሩሽ ጉሙ ላይ ስስልሽ
የሰማዩን አምላክ እውነት ነው የምልሽ
ውቡዋ ሞናሊዛም አትስተካከልሽ
@Gitemenlenante
ነጠብጣብ ሐሳቦች
(በእውቀቱ ስዮም)
.
.
ሰማይ ከሚመክን ፤ይጸንስ መከራ
ያርግፍ ! ያርግፍ! ያርግፍ ! መኣት እያፈራ
የ’ሣት ዛፍ ባለበት ፤ ሰደድ አያስፈራ
.............
ከሐምሌት ጋር ሞቷል፤ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፤ አለመሆን የለም
ሸክም ጸጋ ሆኗል፤ ጸጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ፤ ትከሻህን አስፋ!
............
አንድ ሕልም እንደ ጠጅ፤ እየደጋገሙ
ንግር ፤ትንቢት ሳይሆን፤ ታሪክ እያልለሙ
ተኝቶ መነሣት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሣት
ነፍሴን እንቆቅልሽ
(ከስብስብ ግጥሞች)
@Gitemenlenante
////አስፈራኸኝ///


ቀድመህ ወደድከኝ ....እሺ ወደድከኝ
እንደወደድከኝ .... ባይንህ ነገርከኝ
እየወደድከኝ..... እየፈለከኝ
ቀርበህ ለመንገር .... ምነው ፈራኸኝ?
እጆቼን መያዝ ..... እየተመኘህ
በፍርሀት ሲርድ ..... መለ አካልህ
አይኖቼን ደፍረህ ...... ማየት ካቃተህ
ወይ አልቀረብከኝ ..... ወይ እኔ አልራኩህ
ከሩቅ ስታየኝ ..... ከሩቁ ሳይህ
ላታስጨርሰኝ .... እያሰጀመርከኝ
እውነት አንተ ልጅ .... ፈርተህ አስፈራኸኝ

///***ሀና ሰዋለ***///
@Gitemenlenante
"መምጣት እና መሄድ"
ግጠም ያልሽኝ ጊዜ
ስንኝ ቋጥሪያለሁ
ቅኔን ተቀኝቼ ባንቺ ደስታ ሲቃ
ዜማ አንቆርቁሪያለሁ
ግጠም ያልሽኝ ጊዜ
ሰማይን እንደ ሸራ
ደመናን እደቀለም
ስንቴ ከነ አክናፍሽ
በምናብ ስያለሁ
ያ ዉብ ጊዜ አልፎ
ተወኝ በቃ ስትይ
ዜማ አንቆርቁሬ
ሙሾ ደርድሪያለሁ
ደመናን አጥቁሬ
ዶፍ እያዘነብኩት
ይሄዉ ስየሻለሁ
ሰትመጪም ስትሄጅም
መች አርፌ አዉቃለሁ፡፡

by:- Aby the quen
@Gitemenlenante
ልረሳሽ ብጠጣ አይኔ እየሰከረ
ጭራ
ሽ ሁለት አርጎ ያሳየኝ ጀመረ

#ፒፒ ሀይሉ
@Gitemenlenante
በሀገር ፍቅር ስሜት ግርማ ሞገስ ተላብሰህ
ሀገሬን ማን ደፍሮ ሊነካት ወታደር አንተ እያለህ
አልአዛር[CJ]
@Gitemenlenante
2024/09/26 22:51:48
Back to Top
HTML Embed Code: