Telegram Web Link
ያልወደደ አበደ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
በሰው የደረሰ...
በኔ ላይ እንዳይደርስ ፣ ስፈራና ስቸር
ወድጄሽ እንዳላብድ ፣ ስጠነቀቅ ነበር፡፡
ታድያ ምን ያደርጋል
በከንቱ ፍርሃት ፣ ባክኖ መጠንቀቄ
ዋናው እብደት ነበር ፣ ከመውደድ መራቄ፡፡
@Gitemenlenante
*የናፈቅሽኝ እለት*****
...........................................
...........................................
የሰማይ ደመናን ከሩቅ ተመልክቼ
ውበት ቁንጅናሽን በሀሳቤ ለክቼ
በናፍቆቴ ብሩሽ ጉሙ ላይ ስስልሽ
የሰማዩን አምላክ እውነት ነው የምልሽ
ውቡዋ ሞናሊዛም አትስተካከልሽ......
.................................................
@Gitemenlenante
"ታጥቋል" በተባለ በየዕለት መሳደድ፣
"ባልታወቀ" ገዳይ በካራ መታረድ፣
"ነፍስ ይማር" እያሉ ሞትን መለማመድ።
ሰለቸን! ..... ታከተን!
መረረን! ..... ሰቀቀን!
ደከመን! .... አመመን!

ሜሮን ጌትነት
@Gitemenlenante
#ምንሼ #ነው #ጋሼ
ባለፈው ተዘርፈን ~ ስንደነባበር
አራዳ ነኝ ብለህ ~ ነግረኸን አልነበር
ታዲያስ ያራዳ ልጅ
እኛ ነጋ ስንሞት ~ ጠባ ስንገደል
እዛ እናንተ ግቢ ~ ሁሉ ፒስ ነው አይደል?
አረ ረ ረ …………… ሼ
ያራዳ ልጅ ብዬ ~ እኔ ራሴ አንግሼ
ጀለስካ ነው ብዬ ~ ዙፋኑን ለግሼ
ሞተን አለቅን እኮ ~ ምንሼ ነው ጋሼ
#አረ #ምንሼ #ነው
ያራዳ ልጅ ብለን ~ ፈቅደን እንድትመራን
ቆጥበን ቆጥበን
በጠራራ ፀሀይ ~ ጨቡ ምታሰራን ?
አረ ምንሼ ነው
ባላየ ላሽ እያልክ ~ ምታስጨፈልቀን
ካለፈ በኋላ
ፍሉካ ከች ብለህ ~ በወሬ ምትጨምቀን
#ምንሼ
ያራዳ ልጅ ሆነህ ~ ፋራን ምትወክለው
መቃብራችን ላይ ~ አበባ ም‘ተክለው
#ምንሸት #ነው
መለኛ ነህ ስንል ~ በተስፋ ትንበያ
አረ አታወዛግበን ~ አትሰክሰን በያ

አምነን እንዳንተኛ ~ አራዳ ነው ብለን
ወይ ከተነቃቃን ~ አልባንንም በለን

የአራዳ ልጅ ጭዌ ~ ላራዳ ባይጠፋም
እንዲህ መጨካከን ~ ጨርቆስን አይነፋም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@Gitemenlenante
ሰላም ውድ የ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች👥 ሰላም ለናንተ ይሁን ዛሬም እንደተለመደው አንድ የቻናላችን ቤተሰብ የግጥም ስራዎቿን ለእኛ ለ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች አድርሳልናለች እኛ የግጥም ስራዎቿን አንድ በ አንድ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል አብራችሁን ሁኑ እናም like በማድረግ በማበረታታት አብሮነታችሁን አሳዩን እንዲሁም የራሳችሁ የግጥም ስራዎች ለቻናላችን ቤተሰቦች ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በ ውስጥ መስመር (Inbox) @AS_CJman 👈 ላይ ማድረስና ማስተዋወቅ ትችላላችሁ የ ገጣሚት #ብሌን የግጥም ስራ ለማዳመጥ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Audio
Audio
የ ገጣሚት #ብሌን የግጥም ስራዎች☝️☝️☝️ ከወደዳችሁት like በመስጠት አበረታቱ
በህሊና ቋጥኝ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በህሊና ቋጥኝ ዘልቀው ሲራመዱ
ዳገቱን ለመግፋት ቁልቁል ከወረዱ
ሰማይ ደመና አዝሎ ተስፋን ካረገዘ
በኑሮ አንሳንሳር ላይ ብዙ ከተጓዘ
ሰው የለኝም ብለህ ፍለጋ አትውጣ
ከጠበከው ቦታ ራስህን ስታጣ
በምኞት ጉዞ ላይ ዙሪያህን ብቃኝም
ከአንተነትህ በላይ ሰውም አታገኝም !

ከሶላ
@Gitemenlenante
አስበን🙏🙏 🇪🇹🇪🇹
.
.
ጨለማው አድርቶ
ብርሃን ተውጦ
እምነትና ተስፋ ከስሩ ተሟጦ
ፍቅር ከማህፀን ጨንግፎ ተቋርጦ
ጥላቻ ገንፍሎ ጎልቶ አይኑ ፈጦ
ሰብዓዊነት ጠፍቶ
መለያየት ገጦ
እንባ እያራጨን
ጥርስ እያፋጨን
እንዳንቀር ጠብቀን
አቤቱ አስበን!!

#መአዛ ጥበቡ🌓
@Gitemenlenante
ጣትና ቅጣት

ብዕር ከወረቀት
ጣትም ከቀለበት
ተስማምተው እያረፉ
ምነው የሚስማሙ
ባለጣቶች ጠፉ

©ልዑል ሀይሌ
@Gitemenlenante
#ፀሃዬ

በኑረት ገበታ፤
በቀኔ እኩሌታ፤
ለፍርግርግ ኑሮ፣
በነጋ በጠባ ወበቅሽ ያሸኛል፤
ምፃተኛው ልቤ፣
ባልነገሩት ንግርት፤
"ቀን አለህ" እያለ አካሌን ያሞኛል፣

ግና ከዛች ሰፈር፤
ግና በዛች መንደር፤
የኔ ቢጤ አዝማሪ ለቀን ቅኔ ይቀኛል፣
ግና ከዛች መንደር፣
ባለጊዜ ማምሻሽ "ፀሃይ"ን ይሸኛል፡፡

እናልሽ ፀሃዬ፤
የማልኖረው ህልሜ፣
'ማይመጣው አለሜ፣
~ከሚያስበረግገኝ፣
ምናለ ፈጣሪ ማምሻሽን ባረገኝ፡፡

abiye12
@Gitemenlenante
~የፍቅር -ሀይል~

ከሷ እራቅ ዞር በል፣ ብለው ላስፈራሩኝ
ይባሱን ቀረብኩሽ....
እሷን ማፍቀር አቁም፣ብለው ለዛቱብኝ
ደግሜ አፈቀርኩሽ
ሚሰሩብኝ ሴራ ፣ብርታት እየሆነኝ ይሄው
አለው ከደጅሽ
ገለሀለው ብለው መልዕክትም ቢልኩ
ወደኔ ለመምጣት፣እርምጃ ቢለኩ
እኔ መች ገዶኝ....
ፍርሀቴም ስጋቴም ተመን አልባ ሆኖ
ምንንም አከለ
አንቺን በማፍቀር ውስጥ ሞትን
የማይፈራ ንፁህ ፍቅር አለ!!

ገጣሚ:- ካሊድ አቅሉ
@Gitemenlenante
ናፈቀኝ ሀገሬ
"""""""""""""""
ብዕሬን ሸክፌ
ሀሳብ አጠንፍፌ
ቃላት አጣልፌ
ሄድኩኝ ከወረቀት፤

ቅኔ ልደረድር
ግጥሜን ልሰድር
ከመድብሌ ልከት!

ሀገር ብዬ ጀመርኩ
ሀገሬን ላልጨርስ
ጦማሬን ከትቤ፤

ዋ ብሎ አስፈራራኝ
ከራሴ እያጣላ
አመንትቶ ቀልቤ!
.
.
ለምን አልሽ አለሜ?
.
.
እንደምን ይፃፋል
ስለሀገር ግጥም
ጦቢያ ይሉት ቅኔ፤

ሁሉም አስሮ ይዞት
ዘር የሚሉት ብሂል
የአስተሳሰብ ጠኔ፤

የአባ ጃርሶ ቁጣ
የአቶ መርዕድ ዱላ
የት አለና? ዛሬ፤

የፅዮን ስፍስፍ ልብ
የከድጃ ገር ነፍስ
ርቆ ሄዶ ከኔ፤

የትርንጎ ውበት
የአለሚቱ ምክር
ጠፍቶ ከዘመኔ፤

እንደምን ይፃፋል
ሀገር ይሉት ግጥም
ሀገር ይሉት ቅኔ!
.
.
ጉድ አለ በሀገሬ
.
.
አዬ ጉድ ነው መርዶ
ሰው ከራስ ተሰዶ
ከእምነቱ እረክሶ፤

እሩቅ እሩቅ ሲሄድ
እሳትን ሲላመድ
እያደር ተናንሶ፤

ስክነት ይሉት ጠፍቶ
ሰው እብሪትን ሽቶ
እሳትን ተላብሶ፤

አባት አንገት ደፍቶ
እናትን ሆድ ብሷት
አይኖቿ አልቅሶ፤

እህት በእህቷ
ወንድም በወንድሙ
ጦር ሰይፍ ተማዞ፤

መከባበር ጠፍቶ
ልጂት እናት ንቃ
ልጅ አባቱን አ'ዞ!

ሰው በቁም ታርዞ
ሲሄድ ሲፈረጥጥ
ቁልቁሉን እሩጫ
የእውር ድንብር፤

እንዴት ከግጥሜ ላይ
ጎላ ብላ ትፃፍ
ቅኔ ያላት ሀገር?
.
.
እንዴት? .....እንዴት?
.
.
ወገን ተከፋፍሎ
እገደል ተምሎ
በዘርና በጎጥ፤

በነጮች ሰበካ
ከሀገር ተሰዶ
በድኑን ሲቀመጥ፤

በዳንኪራ ፈዞ
ቁሙን ተገንዞ
ከሀገር ሲፈረጥጥ፤

እና እንዴት ተብሎ
ስለ ሀገር ይፃፍ
ሀገር ትቆላመጥ?
.
.
ተመልከች ዓለሜ
.
.
ሀገር ማለት ሰው ነው
ሰው ነው
ሰው ነው ሀገር፤

ሰው ከሌለ የለም
ሀገር ይሉት ወሬ
ሀገር ይሉት ነገር!

ሰብዕና ጎድሎ
በሌላ ተደልሎ
በቁም ተቀምጦ እሩቅ ከከነፈ፤

ምን ተብሎ ቅኔ
ምን ተብሎ ግጥም
ስለ ሀገር ተፃፈ?
.
.
(እናማ)
.
.
ስለሀገር ያሰብኩት
ብዙ የተለምኩት
ባሸተው ሰንፍጦ
ብቀምስ ጎመዘዘኝ፤

ከእውነቱ ተውኩና
ከተስፋ አጠቀስኩኝ
ብዕሬን አነሳሁ ከወረቀት ልቀኝ፤

ሀሳቤን ሳሰፍር
የሚል ግጥም ፃፍኩኝ
ሀገሬ ላይ ቆሜ ሀገሬ ናፈቀኝ!

(ሀገሬ ናፈቀኝ)

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Gitemenlenante
።።።።አምላኬ ሀገሬን ጠብቃት።።።።።
[አልአዛር] #Alazar

እጅግ ውብ ድንቅ አርገህ በእጅህ ፈጥረሀት
ለዘለአለም የሚኖር ቃልኪዳንህን ሰተሀት
ለአለም ማረፊያ እስትንፋስ አርገሀት
የቀደምት የሰውን ዘር ፍጥረታት
የቀደምት ጀግንነት
የቀደምት አንድነት
የቀደምት ህይወት
አሟልተህ የሰጠሀት
ሀገሬ ሀገራችን እሷም ኢትዮጵያ ናት
ታድያ ታድያ ምነው አሁን ዘነጋሀት
ያ የነበራት ሰላምና አንድነት
በባንዳዎች ክፋዎች ሲነፈግ በድንገት
ምነው ዝም አልካት ምነው ዘነጋሀት
በጥቂት ባንዳዎች ክፋዎች ዝቃጮች
አዕምሮ በሌላቸው ባዶዎች ውራጆች
ቃል የማይገልጻቸው የሰይጣን እረኞች
ክፋት በወረሳቸው የገሀነም ሰዎች
ህሊና በሌላቸው በርካሽ ፍጥረቶች
አስተሳሰብ በሌላቸው ርካሽ ባንዳዎች
ያጎረሰ እጇን ሲነክሱት
ደግ እናትነቷን ሲከዱት
ታድያ ምነው ዘነጋሀት
ካለም የቀደመ ስልጣኔ ያላት
ምድሯ ፈውስ አየሯ ህይወት አርገህ የፈጠርካት
ሀገሬ ሀገራችን እሷም ኢትዮጵያ ናት
ቀስተደመና በመሰለ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ
ውብ ናት ሀገራችን ሁሌም ምታኮራ
እባክህ አምላኬ የቃልኪዳንህን ምድር
እባክህ ጠብቃት የቃልኪዳንህን ሀገር
ሀገር በጥባጮችን ባንዳዎችን ቀጥተህ
የሰይጣን እረኞች ሀገር በጥባጮችን ከምድሯ አውጥተህ
የነበራትን ፍቅርና አንድነት
ህዝቦቿንም ባርከህ ሰላምን ሰጥተሀት
የህዝቦቿን እምባ አብሰህላት
ከፀብ ከጦርነት ከክፋት አርቀሀት
የልጆቿን ጸሎት ሰምተህላት
እባክህ አምላኬ ሀገሬን ጠብቃት

#Alazar{CJ}
@Gitemenlenante
#ሀገር_የከፋት_ለት

በቀን ግፍ ተገፍቶ ለመሄድ ሲገደድ
ሀገር ጸንታ ሳለች ሰው ነበር ሚሰደድ።
ግን እንዲህም ደሞ
ብሶት ከሰው ወርሳ
በእንባ ድጥ ርሳ
ከጫፉም ጫፍ ደርሳ
በጨካኞች ግፊ
አገርም እንደሰው ሲላት ጥፊ ጥፊ
ጨለማን አልብሼ…
ፊቷን ለመሸሸግ ቀኔን እያስመሸሁ
እንባዋን አብሼ…
የተሰበረውን ጥንድ እግሯን እያሸሁ
በጀርባዬ አዝያት ሀገሬን ባሸሸሁ።

ገጣሚ፦ ኢዛና መስፍን
@Gitemenlenante
2024/09/27 02:23:21
Back to Top
HTML Embed Code: