Telegram Web Link
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
@Gitemenlenante
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማፍቀር መለኪያው ልብ ሆኖ ሳለ
ስንት ሠው ወደቀ ልፈትን እያለ
መተማመን እንጂ ፍቅርን የሚያዘልቀው
ለፍቅር ፈተና ውሀ በወንፊት ነው
....
ግን ይሄን እወቂ
....
ፈላጊሽ ቢበዛ የኔሁኚ የሚልሽ
ልብሽ ነው ፈራጁ መራጪው ራስሽ
ባንቺነትሽ ልኬት ሚዛኑን ባልደፋ
ያበራሁት ፍቅርሽ ይኖራል ሳይጠፋ
....
ግን ይሄን እወቂ
....
ሳላልፍ ከቀረሁኝ ከብዶኝ ሳላጠና
በመውደድ ጥያቄ በፍቅር ፈተና
ሀዘኔ እንዳይበዛ ወድቀሀል አትበይኝ
ዝምታም መልስ ነው በቃ ዝም በይኝ
@Gitemenlenante
😍😍እኔ እወድሻለሁ❤️❤️


እኔ እወድሻለሁ
ታስሮ እንደመፈታት
እንደጣኦስ ውበት
እንደዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ
ደርቦ እንደመምታት፤

እኔ ወድሻለሁ
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት
ግማሽ እንደመውረስ፤
እኔ ወድሻለሁ.
እንደመቅደስ ዕጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
እኔ ያንች ቡዳ
ያንች ልዝብ ሰይጣን ፡፡

(አዝማቹ የገ/ክርስቶስ ደስታ ነው)

በዕውቀቱ ሥዩም
የማለዳ ድባብ
@Gitemenlenante
።።።።።።።።ምሉዕነት።።።።።።።።
ጥርሷ እንደበረዶ የነጣ ያማረ
ጸጉሯ እንደሀር ፈትል የተሽቀረቀረ
ዓይኗ ከውሀ ብይ በእጅጉ የጠራ
የፊቷ ገጽታ ከሩቅ የሚጣራ
ወገበ ቀጭኗ አንገተ ሰልካካ
መላ ሰውነቷ ልብን የሚነካ
አንደበ ርቱዕ እውነት ተናጋሪ
ለፍቅር የቆመች የሰው ልጅ አክባሪ
እስቲ ፈልጉልኝ ብዬ ብነግራቸው
ስዕል ስለው መጡ ሰው ስለጠፋቸው
@Gitemenlenante
።።።።።።።በነታይታ ዘመን።።።።።።።
በነታይታ ደጃፍ ከጎዳናው መሀል ሞት እየጨፈረ ዳንኪራ እየመታ
በለቅሶ ታጅቦ በሰቆቃ አጊጦ በሀዘን አሸብርቆ በእንባ እየተረታ
ጉልበቱ ዝሎበት ከመሬት ላይ ወድቆ
ክፉኛ ቆሳስሎ በደም ተጨማልቆ
አቅሙ ከሽፎበት ሲወድቅ ሲነሳ
በነታይታ ዘመን ላግዝህ ከማለት ቀድሞ ተሽቀዳድሞ ፎቶ ነው የሚያነሳ
#ኤደን ወልዴ
@Gitemenlenante
"ንድፍ"
በ ሜሮን ጌትነት
ሀገር ያውቅ የለም ወይ
የፈጣሪን ስሌት
ወንድን የማነፁን
አስቀድሞ ከሴት
የኔ ኃላ መሆን
ያንተ ፊት መፋጠር
ምኑ ነው የሚያስደንቅ
የታል አዲስ ነገር?
እኔን በዋናነት
ሲሰራኝ አልሞ
አንተን ንድፍ አ´ረገህ
ጫረህ አስቀድሞ ።
@Gitemenlenante
ስላስከፉኝ ሰዎች ልጽፍ አሰብኩና
ይቅር ብዬ ተውኩት እኔም ያስከፋውት ሰው አይጠፋምና
#Alazar
@Gitemenlenante
🌱🌱🌱🌱🌱…………………
#በቀለች

ከኮረብታዉ አናት
እንዲያዉ ለነገሩ፣በዉትፍትፍ ጭራሮ
ቤቷን ቀልሳለች፣ጀምራለች ኑሮ።

ከኮረብታዉ ግርጌ፣ወገቡን ሊነካ
የዛፍ መተሻሸት፣ዉበት አለዉ ለካ።

ከዛፎቹ ጀርባ በስፋት የፈራዉ የትርንጎ ፍሬ
ለወገቧ ማማር፣ለጭኖቿ መጉላት፣ሆነላት ፍካሬ።

ከትርንጎ መሀል፣የወይን ጉራማይሌ
ያቆነጃል ከንፈር፣ያሳምራል ዳሌ።

ተፈጥሮ ባሏ ነዉ፣ወንድ አታዉቅም እሷ
በአይን ያልታረሰ፣ድንግል ነዉ ቀሚሷ።

ፈጣሪ ወንድሟ፣ፈጣሪ ዘመዷ
ክፋት አይታ አታዉቅም፣ቀና ነዉ መንገዷ።

ህልም አይቼ ማታ

እንደዚች አይነት ሴት፣በቀለች ከተማ
ስሟ በቀለች ነዉ፣ያባቷ ከተማ።
ውሂብ ገ/እየሱስ
@Gitemenlenante
።።።።።።።።እውነትን ፍለጋ።።።።።።።።
ጸሀይዋ ደብዝዛ ጨረቃም ሳትታይ
ፅልመት ቦታ ይዞ በጠቆረ ቀን ላይ
ባኮረፈ ሰማይ ጎርፍ እምባ በሚጥል
በጨቀየ ምድር በውርጭ በሚያቃጥል
ቀኑ ሲደበዝዝ በቁር በሀሩር
ከጨለማ አድማስ ውስጥ ብቻውን የሚኖር
ተነጥሎ ወጥቶ ከመንጋዎች መሀል
እሱ ሰው ማን ይሆን እውነትን ፍለጋ ዋጋ የሚከፍል
#ገጣሚት_ኤደን_ወልዴ
@Gitemenlenante
Channel photo updated
(እናት)

እምዬ እናቴ
የኔ የግል ሀብቴ
ተቀምጠሽ ከጎኔ
እያየውሽ ባይኔ
ላኑርሽ ዘላለም ህይወቴ ነሽ ለኔ
ስታዘዝሽ ልኑር
ህይወቴ እንዲሰምር
ምክርሽ ህይወቴ ነው
ቁጣሽ ተስፋዬ ነው
ደስታሽ አለሜ ነው
እምዬ አበባዬ ካንቺ ጋራ ኖሬ
ምንም ሳልደብቅሽ የውስጤን ዘርዝሬ
ሀዘኔን ደስታዬን ላንቺ ተናግሬ
ልኑር ካንቺ ጋራ
ህይወቴ እንድትበራ

@Gitemenlenante
. ተ ረ ት ተ ረ ት .
-----------------------------
ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ሰው ነበረ
በሀብቱ የከበረ
ውልደቱም እድገቱም የሆነ አሜሪካ
ባለው ነገር ሁሉ ጭራሽ የማይረካ
ሲሞላለት ሆዱ 'ሀምበርገሩን' በልቶ
'ጋዴሚት' ይለዋል አልጋው ላይ ተኝቶ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
በጣም የተማረ
በቃኝን የማያውቅ የጣልያን ተወላጅ
ሁሌም ለአዲስ ነገር ጠዋት ማታ 'ሚባጅ
'ፒዛና ፓስታውን' ጥርግርግ አድርጎ
ይተኛል ጥሩ እንቅልፍ 'ባፋንኩሎ' ብሎ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
ህልሙ የሰመረ
ጀርመን ነው ሀገሩ
'ምርጥ ዘር' ነው ዘሩ
'ቮግ ቮረስቱን' በልቶ ሞልቶለት አዱኛ
'ሻይሰ' ብሎ ነው ሁሌም የሚተኛ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
የተመራመረ
ጃፓን ተወለደ
በሮቦት አደገ
ቀን ሲሰራ ውሎ
ሩዙን ቀቅሎ
'ሱሺ' ጠግቦ በልቶ
'ባጋይሮ' ብሎ ያነጋል ተኝቶ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
አጥቶ የተቸገረ
ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ያደገ ኩራት ነው 'ራቱ ዛሬም ሆነ ነገ
ቢጠግብም ባይጠግብም ቆሎውን ቆርጥሞ
'ተመስገን' ይለዋል መደብ ላይ ተጋድሞ።

ተረት ተረት ...
እግዜር ከመንበሩ ወደ ምድር ወርዶ
ይጎበኝ ነበረ በየቤቱ ሄዶ
ከእነኚያ ከአራቱ ቆዳቸው ከነጣ
ከየአንደበታቸው መልካም ነገር ቢያጣ
ጥቁሩ ሲያመሰግን የፈለገው ሞልቶ
ያጎደለባቸው አንድ የሆነ ነገር እንዳለ ገምቶ
ሊጨምርላቸው ነጮቹጋ ሄደ አበሻውን ትቶ።

ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ።
-------------------------------
በሜሮን ጌትነት
@Gitemenlenante
2024/09/27 07:28:33
Back to Top
HTML Embed Code: