Telegram Web Link
እማማ

ያለን እጅግ በዝቶ ሞልቶ ቢከመርም፥
እንኳን ዘመድ አዝማድ መንገደኛው ሁሉ፤
ከኛ ማእድ ጠግቦ እረክቶ ቢኖርም፥
እኛ ልጆቿ ግን እንኳን በልተን ልንጠግብ
እንኳን ተርፎን ሊፈስ ቀምሰን የምናድረው
ሰርተን ማቅረብ ከብዶን ረሃብሊገለን ነው
እናት ምን እንዳላት ለልጆቿ ስትል ምን እንዳሰናዳች
ለ አብራኳ ክፋይ ምን እንዳስቀመጠች
ታሪኳን ጠያቂ አንድ ልጅ ብታጣ
ቁጭ ብሎቢያንቋርር ቢቋምጥ ቢንጣጣ
ሳይሰራ ቢመኝው እንዲያው ከየት ይምጣ
ጎረቤቱ ብለህ ታሪኳን ጠያቂ
የህይወት ጉዞዋን ከስር መሰረቱ
ከውልደቷ አንሰቶ እስከነ ጽንሰቱ
እህ ብሎ አድምጦ ሰነድ አገላብጦ
ቁጭ ብላ ስተርክ እያያት አፍጥጦ
ሁሉን ቀስሞ ቀስሞ ከአብራኳ ክፋይ
ከስጋዋ ክፋይ በላይ ለሷ አሰቦ
ዘመዶቹን ሁሉ ቢመጣ ሰብስቦ
ዝናዋን የሰሙት ሁሉም ቋመጡላት
ጥንት ስንት ደሞ ፈሶ ቢመኙ ሊከቧት
አልቻል በሎቸው በልጆቿ ብቃት
የወኒያቸው ማማ እላይ በደርሱ
በናታቸው ፍቅር እንኳንስ በቃላት
በፊደል ሊወሱ
እንዲያው ለማሰበም ከቶ በሚያሳሱ
በውድ ጀግኖቿ በሺ ሚጠበቁ
ሁሉም ደጃፎቿ
ከደጃፏ ቀርቶ ጭራሽ ከቅዬዋ
አፉን አሰግስጎ ልጆቿን ሊበላ
ቢመጣ አሰፍስፎ ወገን አሰልፎ
በጥቂት የሚሸሽ ደካማም አልነበር
እስከጥግ ገፍቶ ለ እናቱ ክብር
ሞቱን እንኳን ሳይቀር ከቁቡ ሳይቆጥር
እንኳን ለቀረቧት ላሰቧትም ከቶ ማስፈራሪያ ነበር
ገፍቶ መለሳቸው የተኑሱባትን
በህልውናዋ ያመሰጠሩትን
የግላቸው አርገው ልጆቿን ሊክዱ
አጎንብሰው መተው አጥበዋት ሊሄዱ
ያልሙትን ሁሉ በአጭሩ የቀጡ
ለ'ናታቸው ጓዳ ክብርን የሰጡ
ማንነቷን አውቀው ከማአዷ ጠግበው
ያላት ላይ ጨምረው ቢሰቅሏት አርዘመው
ዛሬ ላይ እንዳትወድቅ ቢጥሩ ከድሮ
ባረገዘች ቁጥር ባእድ ተመሳጥሮ
እንዳያጨናግፍ ጽንሷን አጭበርብሮ
አላሰበም መሰል ለዛሬዋ እማማ
ብትጮህ ብትለፈልፍ አጥታ የሚሰማ
ጉሮሮዋ ደርቆ አቅሟ ሲከዳት
ጉልበቶቿ ዝለው እጇ ሲርበተበት
ማን ይደግፍ ከቶ አለሁልሽ ይበል
በአፉ እየቀባ ያታልላት ጀመር.....
#Tsion
@Gitemenlenante
::::::::::::::::አቻ::::::::::::::::::
እኔና አንተ ማለት
በራሳችን ጊዜ ፍጹም ሳንተያይ
የፈረቃ ቅጥሮች ጨረቃ እና ጸሀይ
የሩቅ ለሩቅ ጓዶች ምድር እና ሰማይ
እሳት እና ውሀ ጸብ እና ገላጋይ
ቬኑስ እና መሬት
በጋ እና ክረምት
አንድ ሆነን አንድ የሆንን
እኔና አንተ እንዲህ ነን
@Gitemenlenante
።።።።።።።በስምንተኛው ሺ።።።።።።።
አይጣል ነው የቁንጫ -ግልምጫ
የትኋን -እርግጫ
የበሬ ቁንጥጫ
የሬት ማጣፈጫ
ለለቅሶ አሙቁልኝ ከደጅ
ለሰርግ ሙሾ አውራጅ
ሰላምታ በስድብ
ፍቅር በድብድብ
ጸብ በመሞጋገስ
እርቅ በመታኮስ
ሰው ዝሆንን አዝሎ
ቤት ዘርቶ አብቅሎ
የሚቻል ሳይቻል የማይቻል ተችሎ ይታየኛል ከሩቅ
በስምንተኛው ሺህ መለከት ሲነፋ ነጋሪት ሲደለቅ
ገጣሚ ኤደን ወልዴ
@Gitemenlenante
እየሔዱ መጠበቅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
‹‹እየሄድክ ጠብቀኝ›› - ስትይኝ ሄጃለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ….
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ…
አክሱምን እንዳየሽ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ጠራቢው እኔ ነኝ!
ያለፍኩት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ሰማይ ጠቀስ ሐውልት - የተፈለፈለ፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
አክሱም ሐውልት ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ጥበብ አለ!!
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ላሊበላን አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ፈልፋዩ እኔ ነኝ፤…
ያለፍሁት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ህንፃ ቤተ-መቅደስ ፤ የተፈለፈለ፡፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
በላሊበላ ውስጥ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ፅናት አለ፡፡
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ትክል ድንጋይ አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
የኔው መቃብር ነው!
ውድቀቴም እዛው ነው! ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ባባራ ዘመኑ፤
የራሱን መቃብር - ለመትከል የቻለ፤
መኖር የሚመስል - መሞትም ያይደለ፤
በጢያ ድንጋይ ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ውድቀት አለ፡፡
ከውድቀቴ ኃላ - ባይንሽ የምታዪው፤
ታምር የሚመስል - ታሪክ የምትይው፤
ምልክት የሚሆን - መንገድ ስላልተውኩኝ፤
ከመሞቴ በፊት..
ውድቀቴን፤
ሽንፈቴን፤
ከመቃብሬ ላይ - እንዲህ ብዬ ፃፍሁኝ፡፡
ሩጫዬን ጨረስኩ፤
ሰው ነኝ - ተሸነፍኩ!!!
እናምልሽ ውዴ….
‹‹እየሔድህ ጠብቀኝ›› - ያልሽው ቃል ስህተት
ነው፤
ቃሉም ገብቶሽ እንደው…
መራመድ መሄድ ነው፤
መሮጥም መሄድ ነው፤
መብረርም መሄድ ነው፤
አንቺ እንድትደርሺብኝ …
እኔ እየሞትሁ - እጠብቅሻለው!!!
@Gitemenlenante
ከሰው መንጋ እንገንጠል
ለአንድ አፍታ እንኳን እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
@Gitemenlenante
-------------ብረት መዝጊያ--------------
አያትሽ መረቁ ይምጣልሽ ማዘንጊያ
ከወንድ በላይ ባል ሚሆን ብረት መዝጊያ
ሸንኮሬም በእልልታ መረቀች ተራዋን
በፈጨችው ስርኩል እየኳለች ዐይኗን
አሜን አልሽ ውቢቱ
አሜን ለወንዱ ባል አሜን ለብረቱ
ጉልቻሽ ተሰራ ትዳርሽ ተጣደ
ባዲስ ጎጆ ፍቅር ቤተሽም ነደደ
ግና መች ገባችው ሸንኮሬና አያትሽ
ብረት ብረት ሲሉ ከሸክላ ወንድ ሁላ
አሜን ያልሽው ባልሽ ሌላ ጉድ አፈላ
አሜን ያልሽው ብረት ሌላ ጉድ ወለደ
ባህሪው ነውና ቶሎ ቶሎ ግሎ ቶልውን በረደ...!!
ሰመረ ጉዕሽ
.......//..........
@Gitemenlenante
፨ ከትውልዱ ማን አስተዋለ

ስለመተላለፋችን ቆስሎ
በአደባባይ ተሰቅሎ
ቁስሉን እያየን በጎልጎታ
ስለሁላችን ተሰቅሎ ጌታ
ደዌያችንን እንደተቀበለ
ከትውልዱ ማን አስተዋለ
በመካከላችን እንዳለ ክርክር
በቅድስቲቱ ህብረት ልዩነት ቢፈጠር
እኔ የጳውሎስ ነኝ እኔ ደግሞ የኬፋ
እኔ የአጵሎስ ነኝ ብለን እንዳንጠፋ
ስለሁሉ የሞተ ባደባባይ የዋለ
ክርስቶስ ነው እንጂ ጳውሎስ እኮ አይደለ
ደሞ! እኔ የክርስቶስ ነኝ ትላለ
ክርስቶስስ መች ተከፈለ
ከትውልዱስ ማን አስተዋለ
በመቅድስናው ደጅ ርኩሰት ሲተከል
የመንፈስ ቅዱስ ሃብት በገንዘብ ሲደለል
ያስተውል ያስተውል፥ አንባቢው ያስተውል
በዚህ በጉባኤ ልዩነት ከታየ
ወንድም በወንድሙ መከራውን ካየ
ከዚሁሉ በኋላ ሊመጣ እንዳለ
ከትውልዱ ማን አስተዋለ
የመንግስታት ቁጣ ርሃብ ቸነፈሩ
የምድር መናወጥ ሲሰማ ባገሩ
የፍቅር መቀዝቀዝ ተላልፎ መሰጠት
በመከራ መኖር እየሞቱ መብዛት
እስር እንግልቱ
ራብና ጥማቱ
አሳርን ሜየቱ
ለዳግም ምጽአቱ ይሄ ሁሉ ነገር እየተስተዋለ
ታዲያ ከትውልዱ ማነው ያስተዋለ
የአዳም ኃጢያቱ የሰው ልጆች ክፋት
ከእንጨቷ በልቶ አምላክነት መሻት
ይህ የጥንቱ በደል እየተስተዋለ
ታዲያ ከትውልዱ ማነው ያስተዋለ
በሰናዖር ሀገር ሰዎች ተሰብስበው
ሰማይ የሚጠቅስ ክፋትን ገንብተው
በአውሬው ከተማ ቦንብና ሚሳኤል እየተስተዋለ
ታዲያ ከትውልዱ ማነው ያስተዋለ
ሰዶም ወገሞራ የጥፋት ተምሳሌት
ተፈጥሮን በሳተ በዝሙት ርኩሰት
በሰይጣን ሰይጥነው በዘመናዊነት
ሲዘፍኑ ሲዳሩ ጥፋት እንደሆነ
አምላኩን በመያዝ ሎጥም እንደዳነ
ያየርኩሰት ግብር ዳግም ከበቀለ
ታዲያ ከትውልዱ ማነው ያስተዋለ
ኸረ ማነው ማነው
እስከ መጨረሻ ጸንቶ የሚድነው
እሞታለው ብሎ እድር እንደገባ
ካምላኩ ሊታረቅ ንስሐ ሚገባ
የፍጻሜው ዘመን አሁን እንደዋለ
ከትውልዱ ማን አስተዋለ

ወልደአብ በላይ
@Gitemenlenante
#እስኪ.....
(ቤዛዊት ከበደ)

ይስቃሉ በሀሣቤ
ይስቃሉ በጉልበቴ
ይስቃሉ በጥረቴ
.
.
ይበላሉ ከማጀቴ
ይጠጣሉ ከማጀቴ
ከእጄ ፍሬ ከደም ላቤ
ይቆርሣሉ ከስኬቴ
.
.
ያደንቃሉ ያን ሀሣቤን
ያደንቃሉ ያን ጉልበቴን
ያደንቃሉ ሙሉ ቤቴን
.
.
እንዲህ እንደዚ እያሉ
ይኖራሉ ከቤቴ ጎን አጥር ጋርደው
ወይ ለወሬ
ወይ ለስርቆት
ወይ ለፅድቅ እንዲመቻቸው::
.
.
እኔም አለሁ
እስኪፀዳ ማድጋዬ
እስኪከዳኝ ቀኝ ጉልበቴ
እስኪጎድል ሙሉ ቀኔ
.
.
ይሀው አለሁ
..
እኔም አለሁ
.
.
ምርቃቴን ይዤ
እርግማኔን ትቼ!!

@Gitemenlenante
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ(ልዑል ሀይሌ)
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
መንገድ ጥረጊልኝ
ይህቺን ብቻ አርጊልኝ!
.
ስምሽን እያነሱ
እንዳያስታውሱኝ
በሞተው ትዝታ
እንዳይቀሰቅሱኝ
ያንቺ አለመሆኔን
ዛሬ እንዳሳያቸው
ጨረቃን ፀሐይን
ምድር አውርጂያቸው
ውቅያኖስ ባህሩን
ሰማይ ስቀያቸው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
የረገጥነው አስፋልት
የሄድንበት መንገድ
ያ ያለፈው ፍቅር
ያ ያለፈው መውደድ
ፍፁም ውሸት ብዬ
እንድሸመጥጠው
ተፈጥሮን አዛቢ
መውደዴን እንድተው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ገደሉን ሙዪና
ተራራውን ናጂው
ደመናን አውርደሽ
አፈሩን ውሰጂው
የረገጥሽው መሬት
አምሮ እንድታይበት
በአበባው ፋንታ
ሳማ ትከይበት
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ያ ሁላ ቃል ኪዳን
ተበትኖ እንዲቀር
አይጥ ሀይቅ ትዋኝ
ዓሳ ሰማይ ይብረር
በህይወት ባሉት ምትክ
ሙታኖች ይነሱ
ነገስታት ይውረዱ
ባርያዎች ይንገሱ
.
ይሄን ካረግሽልኝ
መውደዴን ይቅርና
መኖር አቆማለሁ
በመኖር ብረሳሽ
ባለመኖርም ውስጥ
አስታውስሻለሁ
@Gitemenlenante
ሰላም ውድ የግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች👥 እስቲ ዛሬ ወደ መዝናኛው አለም እንውሰዳችው ዛሬ የተለቀቀዎን የ ያሬድ ነጉን ዞራ የተሰኘውን አዲስ ሙዚቃ🎶 ተጋበዙልን 👍
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👤 Yared negu
🎬 Zora | ዞራ
🕒 04:43
💾 31.08 MB
🌻 እንደምን አደራችሁ 🌻

ዛሬ አሮጌውን 2012 ዓ.ም ጨርሰን 🌻አዲሱን 2013 ዓመትን ልንቀበለው ሰዓታቶች ብቻ ቀርተውናል።

🌻 ታዲያ የበዓል ሸመታና አጠቃላይ የበዓል ዝግጅት እንዴት ይዟችኋል?
🌻 የዶሮ፣ በግ፣እንቁላል፣ ቅቤ መሰል የበዓል ፍጆታዎች አቅርቦትና ዋጋ በእናንተ አካባቢ ምን ይመስላል?

#ልብ ይበሉ በዓልን ተንተርሶ ብዙ ሰዎች ወደ ገበያ ስፍራዎች የሚያቀኑበት ወቅት ነው። ጊዜውም የኮቪድ 19 መሆኑ ተገንዝበን ራሳችንን መጠበቅ አንርሳ መልዕክታችን ነው።

መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ ይሁንላቹ !
Channel photo updated
2024/09/27 11:28:13
Back to Top
HTML Embed Code: