Telegram Web Link
#ጭብጨባ
(በተመስገን መሰረት)
.
ጭብጨባ አትውደድ፣ አይምሰልህ የብርታት
ከመውደቋ በፊት......
ቢንቢም መስሏት ነበር፣ አድናቆት የሰጧት፡፡
@Gitemenlenante
።።።።።።ሁሌ አፈቅርሻለው።።።።።።
[አልአዛር] {CJ}

ሁል ጊዜ ስነግርሽ ሁሌ እንደማፈቅርሽ
የፍቅሬን መጠን እኔ ስገልጽልሽ
ካንቺም ዘንድ ስደርስ ልቤ ስትመታ
ውሸት እንዳይመስልሽ አይደለም ጨዋታ
እኔ ያፈቀርኩሽ እስካገኝሽ ሳይሆን እስከ ዘላለም ነው
እኔ ያፈቀርኩሽ እድሜ ዘላለሜን ካንቺ ጋር ልኖር ነው
ላንቺ ያለኝ ስሜት ፍቅሬ የእውነት ነው
ላንቺ ያለኝ ፍቅር የእውነተኛ ነው
እድሜ ዘላለሜን ሁሌ አፈቅርሻለው
@Gitemenlenante
ይድረስ ለኮሮና
እንደምን ነህ ኮቪድ.......... እንዴት ነህ ኮሮና?፣
እኛን አሉ አትበለን .............የለንም በደህና።
***
ዕድሜ ይንሳህና............... ከመጣህ በኋላ፣
ሰው ከሰው እራቀ ............እጅ ከፊት ተጣላ፣
ጥሮ ግሮ መብላት............አፈር ድሜ በላ።
*
ደጅ አድባሩ ሜዳው ........ቀዬው ተናፈቀ፣
ሰው በረንዳን ፈርቶ..........ማጀት ተደበቀ።
*
አለም ተናወጠች............ ተናጋ ሰላሟ፣
እጃችን በውሀ............... እየሳሳ ሟሟ።
**
መሳቅ ታሪክ ሊሆን......... አፋችን ታፈነ፣
በስጋት መነመን............ "ገል"አችን ተነነ።
***
እናም ኮሮናዬ
እኛን እንዳየህን፣
ከሰሪያችን ውጪ ......መመኪያ የሌለን፣
ምስኪን ፍጥረቶች ነን።
*****
በጠባብ ጎጆ ውስጥ ........ሀያ ሁነን ኗሪ"፣
ላንድ ሟች አሰከሬን........ አስር ሺ ቀባሪ።
ሰርጋችን ገበያው....... ቤተ እምነት ተዝካሩ፣
ስብከታችን ህብረት........ ሚሉን "ተደመሩ"።
ወባ ታይፈስ ታይፎድ........... የብሔር በሽታ፣
ሚንጡን ነንና............... እኛ ላይ አትበርታ።
ይልቁንስ ኮቪድ
የእኛን አንተን መናቅ .........."አፉ" በለንና፣
አሳዘኑኝ በለው ...............ለላከህ ሂድና።
@Gitemenlenante
​​​🌹💌...        

"ብታውቂ!"🌺

ከበእውቀቱ ስዩም

😁ስትስቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ፣
መንፈስን ካዚም እስራት እንደምታላቅቂ፣
ብታውቂ!
÷÷÷÷÷
ስትስሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ፣
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ፣
😁ብታውቂ!
÷÷÷÷÷
ስታወሪ!
ዱዳ እንደምታናግሪ፣
መነኩሴውን ከሱባዔ፣
ፈላስፋውን ከጉባዔ፣
እንደምትጠሪ፣
ብታውቂ!
÷÷÷÷÷
እንኳንስ በኔ ልትስቂ፣
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ፣
አይሽ ነበር ስትማቅቂ!!!
@Gitemenlenante
ሲፈቀር የሚባል...
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
"ፈገግ ስትዪ...
ጥርስሽ ምስራቅ ሆነኝ ፣ የፀሐይ መውጫ በር
ከሳቅሽ ሰማይ ላይ ...
ንጋቴን አያለሁ ፣ ተሰቅላ እንደጀንበር።
አንቺ ስትስቂ...
የጨረቃ ገላ ፣ እስኪያልቅ ይሸረፋል
"ሙሉ"
"ግማሽ"
"ሩብ"
እያለ ይጠፋል
ኮከብ እንደ ቅጠል ፣ እግሬ ስር ይረግፋል።"
ብዬሽም አልነበር?
..................................
"ስታኮርፊ ደሞ
ነፍስሽ ምእራብ ነች ፣ መውጫ ለጨለማ
ከኩርፊያሽ ሰማይ ላይ...
ምሽቴን አያለሁ ፣ ንጋቴን ስቀማ።
አንቺ ስታኮርፊ...
ሳቅሽ ሚያደርቃቸው ፣
"ኮከብ ነን" ባይ ሁላ ፣ ይድናል ከመርገፍ
ጨረቃም ሙሉ ነች...
ዳግም ስትስቂ አይታ ፣ ገላዋ እስኪሸረፍ
እስከዚያው ድረስ ግን....
ምን ጨለማ ቢገዝፍ፣
ትንሽ ብርሀንን ፣ አይችልም ማሸነፍ!!"
ብዬሽም አልነበር?
...................................
"ስትስሚኝ ደግሞ...
መለኮት ከንፈርሽ ፣ ከንፈሬን ሲያጠምቀው
ምኔ እንደተነካ ፣ሳይገባኝ ሳላውቀው
ከገነት ደጃፍ ነው ፣ ደርሼ ምወድቀው።
ሲኦል ከቆመ ነፍስ ፣ ገነት የወደቀ አይደል የሚፀድቀው!!?"
ብዬሽም አልነበር?
ግን በቃ አትመኚኝ!!
ይሄን ሁሉ ያልሁሽ...
ስለጠፋብኝ ነው ፣ ልልሽ ያልሁት ነገር!!!
.....................................
አሁን ግን የምልሽ...
"ልቤና አንደበቴ ፣ አይተዋወቅም
አፍቃሪና እውነት....
ሩቅ ለ ሩቅ ናቸው!
ሰማይ ከምድር ላይ ፣ ያን ያህል አይርቅም
ሳፈቅርሽ እንዲህ ነኝ...
የምልሽ ሲጠፋኝ ፣ ያልሁትን አላውቅም!!!
ግን አፈቅርሻለሁ።"
እያልሁሽ አልነበር?
የማይባል የለም! ፣ ይባላል ሲፈቀር!!!!
@Gitemenlenante
የልብ ቅርፅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ፍቅርን ያህል ነገር...
ተሸክሜ ስኖር ፣ በልቤ ትከሻ
"ቃል አጠረኝ" የሚል....
ቃል ካ'ፌ አይወጣም ፣ ላወድስሽ ስሻ።
........................................................
እንደውም ሳፈቅርሽ ፣ ቃል ነው የተረፈኝ
ሁሉ ያጥርብኛል.....
በልብሽ ቅርፅ ውስጥ ፣ መውደድሽ ሲያገዝፈኝ።
...............................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ሰፊ ያልሁት አለም ፣ ባንድ እርምጃ አለቀ
ሳልሄደው ሚደክመኝ...
ተራራና ጋራው ፣ ከግሬ ስር ጠለቀ።
"ሩቅ" ያልሁት ሰማይ..
ሩቅ የሚመስለኝ ፣ ነካሁት በስንዝር
ጨረቃና ፀሀይ....
ከኮከብ ያንሳሉ ፣ ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር።
.......................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ንጉስን ከዙፋን ፣ ማርከው የሚያወርዱ
የሀያላንን አቅም ፣ በጥቅሻ ሚያርዱ
ቆነጃጅት ሴቶች ...
"ቃል አጠረኝ" በሚል ቃላት የተሞሉ
ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር..
ቃል ተገኝቶላቸው ፣ "ፋንጋዎች" ተባሉ።
.........................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
"ቃል አጠረኝ "በሚል...
ባፍቃሪ አንደበት ፣ ቃል ተትረፈረፈ
ሁሉን አሳንሶ...
በልቡ ቅርፅ ውስጥ ፣ ፍቅሩን አገዘፈ
አለሙን ሰርዞ ፣ ፍቅሩን ብቻ ፃፈ!!!
..........................................
ሳፈቅርሽ ይህን አልሁ...
ፍቅርን ተሸክሞ ፣ የሚኖር ልቦና
ሁሉም ከፍቅርሽ ስር ፣ መሆኑን አውቅና
አንቺን ለማወደስ .፣..እኔም ቃል ያጥረኛል
"ቃል አጠረኝ "ማለት...
ቃል እንደሆነ ግን ፣
ፍቅርሽ ይነግረኛል!!!
@Gitemenlenante
///// ይቆጨኝ ነበረ \\\\
ከፍቅርሽ ከፍታ~ ላ'ፍቃሪ ከራቀው፤
ኩራት ከውበት ጋር~ ከተደባለቀው፤
ከሚታየው ርቆ~ የዝናሽ ቅርንጫፍ፤
ከጥላቻሽ አናት~ ከመፈቀርሽ ጫፍ፤
አላፈቅርም ብለሽ፣
አልወድህም ብለሽ፣
እንኳን~ ገፍትረሺው፤
እንኳን መሬት~ ጣልሺው፤
እንኳንም ባንቺ እጅ~ ልቤ ተሰበረ፤
ባላፈቅርሽ ኖሮ~ ይቆጨኝ ነበረ።
[ በለጠ ተክሉ ]
@Gitemenlenante
**** እኔ አንተን ስወድህ****
ልክ እንደ ጠዋት እንቅልፍ
ሰመመን የቃጣው
በአእዋፍ ዜማ የታጀበው
የካህናት ወረብ
ፅናፅል የሞላው
ልክ እንደ ሰማይ ጥግ
ፈክቶ እንደሚበራው
እንደ ምስራቅ
ሰማይ ጨረር የጋረደው
እንደ አዲስ ተስፋ
፣፣፣እኔ አንተን ስወድህ፣፣፣

እንደ ቀትር ፀሀይ
ውሎ እንደሚጣፍጥ
የማለዳ ጀምበር
ለመምሸት የሚያምጥ
እንደ ምሳ ሰአት
ደግሞም እንደ መቅሰስ
አንድ ላይ አጣምሮ
ጉራሽ እንደመቅመስ
ልክ እንደዛ ምሳ
ፍቅር እንደሞላው
የአብይ ፆም ውሎ
አስሮ እንዳሰቃየው

።።።እኔ አንተን ስወድህ።።።

አብረን እንደመሳቅ
ደግሞም እንደማልቀስ
የአንድነት ዋዜማን
አብረን እንደመቁረስ
ምሽት ላይ ተጋግዘን
ዘመን እንደመድረስ
በእሳት በውሀ
በባህር መዋኘት
በውህደት አለም
ባንድ መገናኘት
ምድር ስትሞሸር
ፅሀይ ስትዘቀዝቅ
ኮከቦችን ማየት
ጨረቃንም ማድነቅ
እኔ አንተን ስወድህ
ጠዋትና ማታ ሁሌ ማስታውስህ

Jerry dimple
@Gitemenlenante
ሰላም ውድ የ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች👥 ሰላም ለናንተ ይሁን ዛሬም እንደተለመደው አንድ የቻናላችን ቤተሰብ የግጥም ስራዎቿን ለእኛ ለ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች አድርሳልናለች እኛ የግጥም ስራዎቿን አንድ በ አንድ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል አብራችሁን ሁኑ እናም like በማድረግ በማበረታታት አብሮነታችሁን አሳዩን እንዲሁም የራሳችሁ የግጥም ስራዎች ለቻናላችን ቤተሰቦች ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በ ውስጥ መስመር (Inbox) @AS_CJman 👈 ላይ ማድረስና ማስተዋወቅ ትችላላችሁ የ ገጣሚት #የኤልሳውን የግጥም ስራ ለማየትና ለማንበብ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
።።።።።።።የፍቅር ስሜት።።።።።።።

ቆረጠልኝ ብል ያስብስብኛል
እሱንስ መዝጋት እንዴት ይቻለኛል
ስተኛም አስቤው ስነሳም አስቤው
ልነግረው አስቤ ሳገኘው በድንገት
ድፍረቴ ይጠፋል እንዴት ልግለጽለት
ምናለ ቢረዳኝ ቀድሞ ቢያውቅልኝ
ባይፈልገኝ እነኳን ባያነጋግረኝ
ከፊቴ አይጥፋ ከስሬ አይራቀኝ
እንዴትስ ልንገረው ፍቅሩ ቅኔ ሆኖብኝ

#ገጣሚት_የኤልሳው
@Gitemenlenante
።።።።።።የሰርጋችን እለት።።።።።።

የሰርጋችን እለት
እኔም በ ቬሎዬ ባሌም ሱፍ ከረባት
ቃል ተገባብቶ እስከሞት ሽረት
አምኖኝ ተማምነን በወርቅ ቀለበት
ታድያ ምን ያደርጋል እንዲያ የሰርጌ እለት
አስተኝቶኝ ጠፋ በዛ በለሊት

#ገጣሚት_የኤልሳው
@Gitemenlenante
።።።።።።ሣጣህ - ካጠገቤ።።።።።

ሳጣህ ካጠገቤ ውስጤ ይረበሻል
አእምሮዬ ተናግቶ ማሰብ ይከብደኛል

ቶሎ ተመለስ ይጨንቀኛል ከጎኔ ስጠፋ
እባክህ ናልኝ እጠብቅሀለው በተስፋ

ግን እስከመቼ ነው እንዲህ የምጠብቅ
ምትመጣ መስሎኝ ሁሌ ምጨነቅ

ዳግም ካልተመለስክ ወይ ቁርጡን ንገረኝ
የተስፋ ጭላንጭል ሰተህ እመጣለሁ ብለህ ሁሌ አትሸምግለኝ

አንተማ ሄደሀል ልቤን ባዶ አስቀርተህ
መጣሁ ጠብቂ እያልክ በተስፋ ሞልተህ

በቃ ትቸዋለሁ አንተን መጠበቄን
ተረዳሁ ባዶ ቤት ሲሆን ላትመጣ መሄድህን

እኔማ አልሜ ነበረ ህይወቴን ካንተጋር
ሄደህ ለምትቀረው ላትመለስ ነገር

ጎዳናህን መርጠህ ከሽሸኸኝማ ታድያ ምን ያደርጋል
ይቅናህ ብዬሀለሁ ካላንተ ቢከብድም እኔም ለህይወቴ ማሰብ ልቀጥል

#የኤልሳው
@Gitemenlenante
ህልሜን አደራ!
(በውቀቱ ስዩም)
.
ባይመረመሬ ፥ ጥበብ ተሽከርክሮ
ከወርቃማ ብርሃን ፥ ከብርማ ፀዳል
የተሰራ ሸማ ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ
ከውብ እግሮችሽ ስር ፥ እዘረጋው ነበር
ግና ምንም የለኝ ፥ ከህልሞቼ በቀር፤
:
የኔ ውድ እንግዲህ
ህልሜን እግሮችሽ ስር ፥ ከዘረጋሁ ወዲህ
ዝግ ብለሽ እርገጪ ፥ ዝግ ብለሽ ሂጂ
ህልሜ ላይ ነውና ፥ የምትራመጂ።
@Gitemenlenante
////እጅ አልሰጥም////

የምተኛበትን ፍራሽ ቢወስዱትም
እንቅልፌን ነው እንጂ
ህልሜን አይሰርቁትም
.
ይኸው ዛሬም ድረስ...
.
ሊጥሉኝ ቢጥሩ
መች እኔ እረታለሁ
አስረውኝም ቢሆን
ህልሜን እፈታለሁ

(ልዑል ሀይሌ አንደገጠመዉ)
@Gitemenlenante
2024/09/27 09:33:10
Back to Top
HTML Embed Code: