Telegram Web Link
Forwarded from 📚📖 ከመጻሕፍት አንደበት 📖 📚 (Ãbdü "Muslim vacation is Fisebililah")
አድዋ ያልገባው
(ተጻፈ በ ሰይፈ ተማም)

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
ያልገባው ነጻነት
የአድዋ ጀግኖች የተዋደቁለት
ይመስለው ይሆናል ለሱ ለመጨመር አንዲት የ'ረፍት ለት
ካላንደር የዘጋት አንዲት 24 ሰዓት

«እፎይ ስራ የለም
አቦ ክላስ የለም አድዋ ነው ዛሬ
ፊልሜን መኮምኮም ነው እግሬን አጣምሬ
ጣል ያንን አትበሉኝ አልጥልም ደፍሬ»

እንዴት ያል ነገር ነው?
ለዚህ ነበር እንዴ
እነ አባ ቃኘው ያነሱት ጎራዴ?

ጣልያንን ጥለን አነ አንቶኔሊን
እነ አልቤርቶኒ እነ ማንፍሬዲኒ
ሽቅብ የሚጓዙት ደሞ እነ አልፔኒ
ጠቅላይ ጦር አዛዡ ዋናው ባራቲየሪ
ይህን ሁሉ ጥልያን
ጥለን ጣጥለን
ኳስ እያየን አለን
(እነማንን? እነባላቶሊን ጥቁሩን ጣልያን)

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
ያልገባው ነጻነት
የአድዋ ጀግኖች የተዋደቁለት
ይመስለው ቢሆንስ እንደው ከንቱ ልፋት
ስልጣኔን መግፋት

(ከዚህ ስልጣኔ ምኒልክ የታየው
የናት፣ የርስት እና የዕምነት መነጠቅ ነው።)
ታካች ሰው ምንግዜም ልፍስፍስ ነውና
ሂወት አልባ ዝመና
የሰነፍ ፍልስፍና
የወቅቱ ሰዎች መብት
አርነት፣ ግዕዝ፣ ነጻነት
በድህነት ታክተን
ሰሞነኛ ብቻ አይተን
በማያልም ህልማችን
ወቀስን ጀግናችንን
ሚዛናችንም ስቶ
በህንጻ በዳስ ሲለካ
የነጻነት ኩራትስ እንዴት በገንዘብ ይለካ?
የዘመናዊነት ጤዛነት
ላይናችን እስኪታያት
ባሉታ የታሸ የጥልያን ልገሳ
አንዳች ሳያስቀምጥ
ያለንን ሁላ ሊያነሳ?
ለዚህ ነበር አንበሳው ከያለበት የተነሳ
እንደመብረቅ እያገሳ

ግን አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
የአድዋጀግኖች የተዋደቁለት
ምን ይገርማል ከቶ ባይገባው ነጻነት
አላየውምና ተነጥቆ በጉልበት

አንዳንድ ግዜኮ
የውሃንም ጠዓም
ይቻላል ማጣጣም
ጠላም ውሃ ነበር በጌሾ ቢቆጣም
አዲሱ ኢትዮጵያዊ ነጻነትን እንዲያውቅ
ላንዲት ጀምበር ብቻ ውብ ሃገሩን መንጠቅ
ያኔ አያስችለውም ይህ የጀግና ውላጅ
ከጠላቱም አልፎ አለምንስ ቢፈጅ
ፈዞ ቢታይ ዛሬ - ልቡ
ያድዋ ግማጅ

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
ያልገባው ነጻነት
አገሩን ከሰጠ በእጅአዙር አዙሮ
ባለፋ ምኒልክ ከተራራው ጓሮ

አባ ዳኘው የልጅልጅ ልጅ ልጁን ቢያየው
ዘራፍብሎ የሚሸሸው
ኢትዮጵያዊነት ሲጎድለው
ኳስ ና ፊልም ሲያፈዘው
ምን ይል ይሆን ማየት ቢችል ያድዋው ጀግና አባ ቃኘው?
ምን ይል ይሆን ሰራዊቱ
ምንትል ይሆን እናቲቱ
ምንትል ይሆን ምድሪቱ
ምንይል ይሆን ሰማይቱ
ኧረ ምን ትል ይሆን ጣይቱ
መጋደሉ መዋጋቱ
ከረፍት ቀን የዘለለ
ሆኖ ካልታየ ውጤቱ
ለዘመነኛ ወጣቱ
ምንትል ይሆን ብርሃነ ኢትዮጵያ
ጠሃይቷ ጣይቱ?
ተጠየቅ አንተ ዘረ ብርቱ

ባመጣልህ ተሽከርካሪ
ከስንቱ ጋር ሲነታረክ
ስትዋከብ ስትገጭ ቢያይክ
ምንይልክ ይሆን ምኒልክ?
መገናኛን ቢያስብልክ
ዛሬ ይዘህ በኪስክ
ቦሌ ሆነህ ንፋስ ስልክ
ስትቀጥፍበት ቢያይክ
ምንይልክ ይሆን ምኒልክ?
ቢኖር ምን ይላል ዛዲያ
የሴጣን ስራነው ሲሉኝ
በሰማሁ ከማለት ወዲያ
ላለበሰህ ነጻ መንፈስ
ወቀሳህን ብታደርስ
ያኔነው እምዬ ሚያለቅስ

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
ቢመስለው ምናልባት ይህ አድዋ ማለት
እንደነ መቅደላ የጦርነት ፍጅት
የመድፍ ጋጋታ የሙታን ክምችት
የተራራ ርችት
ቢመስለው ምናልባት
አድዋን እራሷን ለምን አንጠይቃት

የአድዋ ተራሮች
እኩይ ሃሳብ
እንደባብ ሲሳብ
ከውጫሌ ካብ
ደሞም
የኢትዮጵያ መንፈስ
አትረብሹኝ ብሎ ሲፈስ
ሲውተረተር ሲገሰግስ
ሲንደረደር ሲገማምስ
ሲግተለተል ሲደማምስ
ሲንቦለቦል ሲያተራምስ
ወዲአ ላይ ሲርመሰመስ

ኢጣልያ ባገሩ ላይ ሲያምርበት
ባየ ግዜ
የቸኮለ በሌጣው
ያልቸኮለ በኮርቻው
እየተሰካ እየፎከረ እየተንደቀደቀ ገባበት

የአድዋ ተራሮች ላፍታ ልሳን ቢኖራቹ
ከዚህ ውጪ የምትሉን ስንት ጉድ ነው ያያቹ?

ይህ አዲሱ ትውልድ ይህ አዲሱ ወጣት
የአድዋ ጀግኖች የተወደቁለት
ምስጢሩ የገባው ለት
ቢመስለውም እንኳ ለሱ ለመጨመር
አንዲት የ'ረፍት ለት
ካላንደር የዘጋት አንዲት 24 ሰዓት
እያመሰገነ እፎይ እያለ ነው በነጻነት ኩራት
ሃገሩን ሚያያት
ያኔ ይንደላቀቅ ይረፍ እግሩን ሰቅሎ
ይሴብህ እያለ ለዓድዋው ውሎ

@Arthabesha
@Arthabesha
👆👆👆👆👆👆
THE ART OF BEING HUMAN | ሰው የመሆን ጥበብ
በ ቡድን የተዘጋጀ የጥበብ ኤግዚቢሽን

ተዘጋጀ :- በ '23 art studio and teyem art center'
መቼ :- አርብ ከ መጋቢት 8 - ሰኞ መጋቢት 11
የት :- @SABEGN ቦሌ አትላስ ከ ሳፋየር አዲስ ፊት ለፊት
የኛዋ ግጥም ሲጥም በ ቦታው ትገኛለች ፣ የመክፈቻ ፕሮግራሙን ትመራለች፣ ክፍት መድረክ አለን ፣ ከመሃላችን የሚያቀነቅኑም ይኖራሉ ::


#SABEGN #GitemSitem
Forwarded from LinkUp Addis
LinkUp is excited to announce that Chewata Awaqi will be joining us at LinkUp Bazaar this Saturday with their variety of games free for all to enjoy as they shop and mingle. On Sunday Gitem Sitem's open mic will be available for all attendees to sing and share their talents. Enjoy the games, live performances, poetry readings and more with your friends and family this weekend. Entrance is free.

@linkupaddis
Forwarded from Afro Century Events (rutha Jo)
Afro Century Events is inviting aspirant female stage managers to apply for an opportunity to participate in a stage management training at Makossa Fest happening at the Venue in Addis Abeba.

Complete and submit the online application form https://forms.monday.com/forms/3f77de98beb92d3d5ab0e158b0e10e63?r=euc1  by April 6.
Cologne-based author Navid Kermani will read from "Wonder Beyond Belief: On Christianity" and talk about his work and his travels.
📅 - 4 April 2023 at 6.00pm,
📍Goethe-Institut Addis Abeba.
Kermani is one of Germany's most influential intellectuals and has been awarded, among other prizes, the Peace Prize of the German Book Trade, the most important literary award in the German-speaking world.

The reading will take place in German and Amharic
Conversation- in English.

Official author's website: www.navidkermani.de
ሰላም የግጥም ኣጣሚያን የተነፋፈቅን አይመስላችሁም ?
ተነፋፍቀን አንቀርማ !
ግጥም ሲጥም የሸፍታዋ ተመልሳለች
ነገ ረቡዕ መጋቢት 27
በ ሸፍታ ሬስቶራንት
በ መቶ [ 100] ብር ብቻ


#krinfudethiopia #shifta #linkupaddis #poeticsaturdays #heransyoga #hibreqal
አሁንም ግጥም ሲጥም

የሽፍታዋ ልዩ ክፍት መድረክ ወሯን ጠብቃ ከች ብላለች።

የምትጽፉ፣ የምትዘፉኑ፣ የምትስሉ፣ የምትገጥሙ፣ የምትኮምኩም ሆናችሁ የምትኮመኩሙ እንድትገኙበትም እንድታቀርቡበትም ተጋብዛችኋል።

መግቢያ 100 ብር ብቻ
12:30 ላይ እንጀምራለን


#krinfudethiopia #shifta #Arada #linkupaddis #poeticsaturdays #heransyoga #hibreqal #jubalgraphics
Yes, it's been a year! Atmosphere invites you to the one year anniverasy of creativity, food, drinks, entertainment and fun. Let's take a trip down memory lane tonight with Gitem Sitem, Chewata Awaqi and a special performance by the DJ and Masinko duo Airwan and wonde. Come celebrate this special day with us at the new location.

https://maps.app.goo.gl/MKGgJcpnm3igRK68A

@atmosphere251
ሰላም እንዴት ናችሁ የግጥም አጣምያን
ግጥም ሲጥም የ ሽፍታዋ በ ክፍት መድረኳ መጥታለች
የፊታችን ረቡዕ ግንቦት 30 : ከ 12ሰዓት ጀምሮ ሽፍታ ሬስቶራንት እንገናኝ!

#shifta #kirunfuddigitals #linkupaddis #poeticsaturdays #hibreqal #jubalgraphics
በአማርኛችን ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሲባል የምንሰማው ኤአይ ስነ-ግጥምን ጨምሮ በተለያዩ የጥበብ ዘርፎች ዙሪያ በርካታ ፈተናዎችን ከዕድሎች ጋር ይዞ መምጣቱ ብዙዎችን እንዳከራከረ አለ።

በርካቶች፣ ማሽን መጻፍ የሚችለው ግጥም ሰዋዊ ስሜት ይጎድለዋል፣ የሰውን ምናብና የፈጠራ አቅም ሊደርስበት አይችልም ሲሉ ይሞግታሉ።

እናንተስ ምን ትላላችሁ?
ልታጋሩ የወደዳችሁትን በክፍት መድረካችን ላይ እያቀረባችሁ ሰዋዊ ስነ-ግጥምን የማንገስ አቅማችሁን ለኩበት።

Some say that the rise of artificial intelligence (AI) has sparked debates about its potential impact on various creative domains, including poetry.
(MIT Technology Review)

Critics argue that AI-generated poetry lacks the emotional depth and personal experiences that human poets bring to their work, suggesting that it may never fully replace human creativity.
(The New York Times)

What do you say?
We have a test run while you perform yours this wednesday?
at Shifta
(GitimSitem)
Forwarded from LinkUp Addis
Gitem Sitem has organized an Open Mic Circle. Happening this Wednesday 5 July 2023, this open mic circle seeks to answer the question of whether or not AI lacks the emotional depth and Personal experience poets bring to their work. Open to the public, this Gitem Sitem serves as a test run. This event is taking place at Shifta starting from 6:30pm.

Get daily updates on the LinkUp App: https://linkupaddis.com/explore

@linkupaddis
ድምጽ ማጉያው እናንተን በመጠበቅ ላይ ነው።
ይህ ክፍት መድረክ ለአዳዲስ አጣሚያን፣ ዜመኞች፣ ራፐሮች፣ ኮማኪዎች እና ጨዋታ አዋቂዎች እንዲሁም ድጋፉን የማይሰስት ታዳሚ ፊት አዲስ የፈጠራ ሥራዎችን ለሞመከር ወደ ኋላ ለማይሉ የተከየነ ነው።

የሽፍታ ሰው ይበለን

Grab the mic and pour your soul into it.
This open mic event is for all the up and coming poets, singers, rappers, comedians, storytellers and all the artists who won't miss a chance to experiment an art form infront of a supportive audience.

Join us this Wednesday at Shifta
2024/09/27 02:23:04
Back to Top
HTML Embed Code: