Telegram Web Link
በአዲስ አበባ ከተማ የ2015 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስከረም 3 ቀን 2015 እንዲሁም የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ነገር ግን በከተማ ደረጃ ወጥ አድርጎ ማስጀምር በማስፈለጉ ፤ ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ለአጀማመሩ ሙሉ ዝግጅታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

መስከረም 3 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች #ማጠናከሪያ_ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

በሁሉም የትምህርት ተቋማት መስከረም 9 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሃደት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ለዩኒቨርስቲ 1ኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ

🌼በተለያዩ ዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጆች የሚገኙት የፍሬሽማን (የ1ኛ አመት ተማሪዎችን) በኦንላይን የጋራ (Common) ኮርሶችን በማስተማር የሚታወቀው A+ Tutorial Class ለ2ኛ ሴሚስተርም ምዝገባ እና ትምህርት መጀመሩን ስናበስራችሁ በደስታ ነው።

🌻ባለፉት አመታት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን ተማሪዎች አስተምሮ አብዛኞቻቸውን ለጥሩ ውጤት ማብቃቱ የማይዘነጋ የA+ ትልቁ ስኬት ነው።

በዚህም ሴሚስተር በሁሉም የትምህርት ዘርፍ👩‍🎓👨‍💻🧑‍⚕👷‍♂ (Department) የ1ኛ አመት 2ኛ ሴሚስተር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።

ጥራት ያላቸው ቲቶሪያል በተብራራ ኖት፣ በድምፅ እንዲሁም በቪድዮ ያቀርባል ከዚያም በተጨማሪ ለተማሪዎቹ የምስክርነት ወረቀት📜 (Certificate) ያበረክታል፣ በየምዕራፉ የተከፋፈሉ ጥያቄዎችን ከነ መልሳቸው ያቀርባል፣ በራሱ መምህራን የተዘጋጁትን ፋይናል ፈተና📑 (Final-Exam) ይፈትናል።

የምዝገባ ጊዜ ሳይጠናቀቅ ፈጥነው ይመዝገቡ!

ለመመዝገብ👇👇👇
@AplusTutorialbot

ለጥያቄና አስተያይት👇
@Ucan_scorebot

ስኬትዎ ከA+ ጋር የተረጋገጠ ነው!

©A+ Tutorial Class

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
መልካም አዲስ ዓመት!!!
Happy New Year!! 2015 E.C
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እነዚህ ከላይ የምታዩዋቸው ስእሎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተሰሩ ናቸው..
“Bidens macroptera yellow Ethiopian new year ethiopian girl , 8k,unreal engine”

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎችን በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገለጸ

ከመስከረም 2015 ዓ.ም. መጨረሻ አንስቶ በሁለት ዙር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጓጓዙበትን የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች በመንግሥት እንደሚሸፈኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማስታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

⚡️ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ መሆኑን አስታውቆ፣ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ለማከናወን የሚያስችለውን ወጪ ለመሸፈን ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድለት ንግግር ላይ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። ፈተናው በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ።

ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው።

በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፦

- ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ ነው።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተመድበዋል። ምደባው ሲዘጋጅ በተቻለ መጠን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲመደቡ ተደርጓል። በአቅራቢያቸው ያለው ዩኒቨርሲቲ በመኝታ ወይም በመፈተኛ ክፍሎች ብዛት ውስንነት ካለበት ወደ ሌላ ዞንና ክልል የመሄድ ዕድል ይኖራል።

- ገጠር አካባቢዎች ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊገጥማቸው ስለሚችል ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ተማሪዎቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ ይጓጓዛሉ።

- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች በመፈተናቸው ምክንያት ግን ወደ ተማሪዎችም ሆነ ወደ ወላጆች የሚሄድ ወጪ አይኖርም።

- ተማሪዎቹ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንዲላመዱት ለማድረግ ሲባል ፈተናው ከሚጀመርበት ቀናት ቀደም ብለው ወደ ዩኒቨርሲቲው ይጓዛሉ። ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ ድምፅም ሆነ ምሥል የሚቀዳና የሚቀርፅ አሊያም ሌላ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው መግባት አይችሉም።

- በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኞችም በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያድሩ ለማድረግ ታቅዷል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
በኦሮሚያ ክልል ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀመር ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀምር የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ወርቅነህ ነጋሳ እንደገለጹት በክልሉ ትምህርት መጀመር የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋል።

የመምህራን ዝግጅት፣ የመማሪያ መጻሕፍት ማዘጋጀትና የትምህርት ቤቶች ዝግጅት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።

የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ይኸው ስራ እስከ መስከረም 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

በዚሁ የትምህርት ዘመን በክልሉ 11 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የገለጹት ዳይሬክተሩ በእስከ አሁኑ ሂደት የተማሪዎች ምዝገባ ከ95 በመቶ በላይ መጠናቀቁን አመልክተዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን ፦
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤
- ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ፈተናው የተማሪዎችን የቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወስን በመሆኑ በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
በ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተመሳሳይ፣ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ከኹሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሙከራ ትግበራ ይጀመራል ሲሉ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ሥራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ለሚጀመረው ትምህርት የተለያዩ ዝግጅቶች ማድረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ሰኞ ዕለት በይፋ ለሚጀመረው ትምህርት በአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ስርዓት እንደሚያካሄድም አመለወርቅ ገልጸዋል።

ተማሪዎች ደስ ብሏቸው የትምህርት ቀኑን እንዲጀምሩ የተለያዩ ዝግጅቶች በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄዱ የገለጹት ኃላፊዋ፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ በክልል ያሉ ትምህርት ቢሮዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ድርጅቶች በትምህርት ቤት ውስጥ መዝናኛ ዝግጅት አዘጋጅተው ተማሪዎችን የመቀበል ሥነ ስርዓት ያካሄዳሉ ብለዋል።

የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ መምህራንን እና ማህበረሰቡ በትምህርቱ የጊዜ ሰሌዳ እና በሥርዓተ ትምህርቱ አፈጻጸም ላይ ውይይቶችን እንዳደረጉ ወ/ሮ አመለወርቅ መጠቆማቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን ያወሱት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዋ፣ በዚህም የትምህርት ቤቶች እድሳት፣ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የመጽሐፍት ማስተዋወቅ እና የትምህርት ጉባዔ የማካሄድ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
* ጥንቃቄ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቃረብን ተከትሎ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል።

" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሸጋገረ " እየተባለ በአንዳንድ የማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ የማይታወቅ በትምህርት ሚኒስቴር ሆነ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያልተገለፀ ነው።

ተማሪዎች ከፈተና ጋር በተያያዘ ማንኛውም አዲስ መረጃ ሲኖር በትምህርት ሚኒስቴር / በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚገለፅ መሆኑን በማወቅ በሀሰተኛ መረጃ ሳትረበሹ ተረጋግታችሁ ዝግጅታችሁን ልታደርጉ ይገባል።

የተማሪ ወላጆችም ትክክለኛና የተረጋገጡ መረጃዎች በትክክለኛ የመስሪያ ቤቶቹ አድራሻ እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚነገሩት መሆናቸውን በማስገንዘብ ልጆቻችሁ እንዳይረበሹ ልታድርጉ ይገባል።

ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲረበሹ እና ብዙ የለፉበት ዝግጅታቸው እንዲደናቀፍባቸው የሚያደርጉ ሀሰተኛ የፈጠራ ወሬዎችን የምታሰራጩ አካላት ድርጊታችሁ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ፤ በትውልድ ላይም አሉታዊ ተፅእኖ ያለው መሆኑን በማወቅ ከድርጊታችሁ ልትታቀቡ ይገባል።

ተማሪዎች ምንጩ የማይታወቅ እና የተለያዩ አካላት ተከታይ ለማፍራት እንዲሁም ሆን ብለው ተማሪ እንዲረበሽ ለማድረግ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩትን መረጃ ወደ ጓደኞቻችሁ ባለመላክ ሀሰተኛ መረጃዎችን ተከላከሉ።
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
በአማራ ክልል በቅርቡ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት❗️

የ2014 /2015 ዓ.ም በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ፈተናው እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ተፈታኝ ተማሪዎች ቀድመው ሊዘጋጁባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ማዕከልም ይሁን በመፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ መገኘት ግዴታ በመሆኑ አድሚሽን ካርድ ፎርም ከሞሉበት ትምህርት ቤት እና ወረዳ በአካል በመገኘት እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲረከቡ፡፡

2. በአድሚሽን ካርዱ ላይ የስም፣ የስትሪም እና የጾታ ወዘተ..ስህተት ካለ በአስቸኳይ ለትምህርት ቤቱ እና ለወረዳው ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እያሳሰብን ይህንን የማያደርጉ ተማሪዎች ካሉ ፈተና ለመውሰድ እንደሚቸገሩ፤

3. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ የትምህርት ቤት ወይም የኗሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት የሚገባ መሆኑ፤

4. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዘው መገኘት ያለባቸው መሆኑ ከዚህ ዉጭ ሌሎች ቁሳቁሶችን በዩኒቨርሲቲ ግቢ እና በመፈተኛ ክፍል መያዝ የተከለከለ መሆኑ፤

5. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ፣ ወረዳው እና ዞኑ በሚያዘጋጀው የጉዞ ፕሮግራም መሰረት ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ መሆኑን በመረዳት ዝግጅት ማድረግ ያለባቸው መሆኑን፤

6. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲሄድ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ልብስ ይዞ የመምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

ይህን መረጃ ሸር በማድረግ ለተማሪዎችና ተማሪ ወላጆች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ትብብራችሁን እንድታደርጉ በተፈታኝ ተማሪዎች ስም ቢሮው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
ባህርዳር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
በነገው ዕለት የ2015 የትምህርት ዘመን ይጀምራል።

በዚሁ ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር 5 ዓመታት ሲያዘጋጅ የቆየው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መተግበር ይጀምራል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው የአዲሱ የትምህርት ስርዓት ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ በሚገኙ 80 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙከራ ደረጃ ይሰጣል።

#ለማስታወሻ - የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ፦

- ከኢንተርናሽናል እና የማህበረሰብ  ትምህርት ቤቶች ውጭ ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ባሉ የግል እና  የመንግስት ትምህርት ቤቶች ይተገበራል።

- ግብረ ገብ ፣ አገር በቀል ዕውቀት ፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናት እና ምርምር ትኩረት ተደርጎባቸው ይሰጣሉ።

- ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል የግብረ ገብ ትምህርት ይሰጣል።

- ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ራሳቸውን የቻሉ የትምህርት ዓይነቶች ሆነው ይሰጡ የነበሩት ኬሚስትሪ ፣ ባዮሎጂ እና ፊዚክስ " ጄኔራል ሳይንስ " ተብለው ይሰጣሉ። ጆግራፊና ሂስትሪም ተቀናጅተው የሚሰጡ ይሆናል።

- ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል ላሉ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል፤ ከ7ኛ ክፍል -12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ ሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራል።

- ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይወስዳሉ።

- 3ኛ ክፍል ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መስጠት ይጀመራል፤ በክልሎቹ ውስጥ በስፋት የሚነገረውን #ተጨማሪ_ቋንቋ በመምረጥ ተማሪዎቹ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲወስዱት ይደረጋል።

-  አጠቃላይ ፈተና በክልል ደረጃ 6ኛ ክፍል ላይ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል።

- የ7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች " ኬሪየር ኤንድ ቴክኒካል ኤጁኬሽን " የተባለ ትምህርት ይሰጣቸዋል። የእርሻ ትምህርት፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስና ጀነራል የሆነውን የሥራና ክህሎት ትምህርት በሙያ ትምህርት ተካቶላቸው ይሰጣቸዋል።

- 11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ጤና ፣ ግብርና፣ የእርሻ ትምህርት፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ቢዝነስ ፣ አካውንቲንግ የመሳሰሉት የሙያ ትምህርትነቶችን እንዲማሩ ይደረጋል። 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከእነዚህ የሙያ ትምህርቶች ውስጥ የመረጡትን ይወስዳሉ።

- የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍልን እንዲሁም ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ያሉ የተመረጡ 5 የትምህርት አይነቶችን መጸሐፍት ዝግጅት ትምህርት ሚኒስቴር ያከናውነዋል ፤ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መፀሐፍት ክልሎች በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው ያዘጋጁታል።
Via. Tikvah
መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ / ኢፕድ የተወሰደ ነው።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2025/02/25 04:17:13
Back to Top
HTML Embed Code: