Telegram Web Link
የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ተሰምቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፤ በኮቪድ -19 እና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት በተቀመጠለት ጊዜ አለመጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

በመሆኑም የ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር ትምህርት ከሐምሌ 20 እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲቆይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲዎቹ ሐምሌ 20 እና 21/2014 ዓ.ም ምዝገባ በማከናወን፥ ትምህርት ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም መጀመር እንዳለባቸው ተገልጿል።

ለተማሪዎቻቸው አስቀድመው ጥሪ ያደረጉ ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ማስተካከያ እያደረጉ መሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለማወቅ ችሏል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
በ2015 የትምህርት ዘመን ከመመሪያው ውጭ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ተባለ❗️

በመጭው የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ከመመሪያው ውጭ ወርሐዊ የክፍያ ጭማሪ ማድረግና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያ እንዳይጠይቁ የአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳስቧል።

ከመመሪያው ውጭ የክፍያ ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል የተባለ ሲሆን መመሪያው በ2014 ዓ.ም ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ጭማሪ እንዳያደርጉ ያዛል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ተቋማት ግንባታን ለማስጀመር ሰመራ ገቡ‼️

ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት ሰመራ ከተማ በሚገኘው ሱልጣን አሊ ሚራህ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ሚኒስትሩ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ በተመረጡ አካባቢዎች አሸባሪው ህወሃት ወረራ ፈጽሞ በነበረበት ወቅት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን የመልሶ ግንባታ መርሃ ግብር ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በይፋ ያስጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

ሚኒስቴሩ ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት እስከ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ድረስ ግብረ-ህይል አቋቁሞ የተለያዩ ስራዎችን መስራቱ ይታወቃል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ስቴም ፓወር (STEMpower) ከቪዛ (Visa) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት 4 ዙሮች ከ600 በላይ ሰልጣኞችን አሳትፏል።

ስልጠናውን ከተከታተሉ ሰልጣኞች መካከል የፈጠራ ሀሳባቸውን ወደ መሬት በማውረድ ሥራ የጀመሩ እና ለመጀመር በሂደት ላይ ያሉ ሰልጣኞች ይገኙበታል።

አሁን ደግሞ 5ተኛ ዙር ሥልጠና ለመስጠት ምዝገባው እየተካሄደ ነው።

የሥልጠናው ፕሮግራም የሚያካትተው ፦

• የተከታታይ 6 ቀን የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ሥልጠና

• 3 ወር የንግድ ማበልጸግ እና ማማከር አገልግሎት (Business Development and Consultation, Coaching and Pitching)

• 9 ወር የተለያየ የማማከር ድጋፍ, ክትትል እና ሜንቶርሺፕ

• ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

- የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

- በግብርና፣ ጤና፣ አገልግሎት፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ እና ሌሎችም ዘርፎች የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

- ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ ሐምሌ 22 2014 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3PK7LY2

#StemPower #VISA

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ፡፡

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 64.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት ሆናል፡፡

ለውጤቱ መመዝገብም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ቢሮው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናውን እያቀረበ

ከሰኞ ማለትም ከ18/11/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታችሁን በቀጣይ በምናሳውቃችሁ አድራሻ አማካኝነት ኦላይን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የአዲስ አበባ ት/ቢሮ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" የተቀመጠው አድራሻ በአግባቡ ስለማይሰራ ውጤታችንን ማየት አልቻልንም " - ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘንድሮው የስምንተኛ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል።

ቢሮው ተማሪዎች ውጤታቸውን https://aaceb.gov.et/%e1%8b%a88%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8b%89%e1%8c%a4%e1%89%b5/ ወይም aaceb.gov.et ላይ በመግባት ማየት እንደሚችሉ ገልጾ ነበር።

ነገር ግን ቢሮው ይፋ ያደረገው ውጤት መመልከቻ አድራሻ በትክክል ስለማይሰራ ውጤት ለማየት እንዳልቻሉ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች አሳውቀዋል።

በመሆኑም ፤ የከተማው ትምህርት ቢሮ አድራሻው ላይ ያለውን ችግር እንዲያርም /እንዲያስተካክል እንዲሁም ለህዝብ ይፋ ከመደረጉ በፊት ተገቢውን ፍተሻ ማለፉን ሊያረጋግጥ ይገባል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 29 /2014 ዓ/ም በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ፈተና ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይፋ በተደረገው መረጃ ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፤ 85.5% ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል ለመዛወር ችለዋል።

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ከ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጋር ተያይዞ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ተማሪዎች ቅሬታቸውን ወደ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በአካል በመሄድ ማቅረብ እንደሚችሉ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አበበ ቸርነት ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ ውጤት ወደየትምህርት ቤቶች መላኩን የገለጹት ኃላፊው፤ በተፈጠረው የኔትወርክ መጨናነቅ ምክንያት ውጤታቸውን ማየት ያልቻሉ ተማሪዎች ወደትምህርት ቤታቸው በመሄድ ማየት እና መውሰድ ይችላሉ ብለዋል፡፡

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" ፈተናው የሚቀር አይደለም " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

* ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተማሪዎቻችሁን አዘጋጁ !

የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም መሰጠት ይጀምራል። ይህን በተመለከተ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ ከሰጡት ማብራሪያ ፦

" ... በሙሉ አቅማችን እየተዘጋጀን ነው። የሚቀር ነገር አይደለም ፤ 2015 ትምህርት ዘመን ማብቂያ ላይ ፤ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብሎ ዲግሪ የሚሰጥበት ነገር ሀገሪቱን በጣም ክፉኛ ጎድቷታል የሚል እምነት አለን።

ይሄንንም ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች ጋር፣ ከግል ኮሌጆች ፕሬዜዳንቶች እና ኃላፊዎች ባለቤቶች ጋር ፣ ከዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ያደረግንበት ነው።

ይሄ አዲስ ሀሳብ አይደለም አተገባበሩ ነው አዲስ የሆነው። ከዚህ በፊት ተሞክሮ ተቃውሞ ስለንበር ነው የተተወው።

የህግና የህክምና ትምህርቶችን ብቻ እንዲሰጡት አድርጎ አሁንም እየተሰጡ ሌሎች በሙሉ ተትተው ነበር።

አሁን ግን በአጠቃላይ ከከፍተኛ ትምህርት ጥራት ችግር ጋር በተገናኘ ምንም ልንወጣው የማንችለው እና ያን ጥራት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲዎቹ በራሳቸው ባስተማሩበት እና እራሳቸው በሰጡት ፈተና ብቻ የሚለኩበት ሁኔታ ከጀርባው ያለ ጠንካራ የሞራል መሰረት ይጠይቃል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ እራሳቸው ድግሪ ስንሰጥ ለማህበረሰቡ ይሄ ሰው እንዲህ እንዲህ አይነት ትምህርቶችን፣ እውቀቶችና ክህሎቶች አሉት ብለን ነው እየነገርን ያለነው።

... ከዚህ በፊት አንዱ የነበረው ችግር ማሳለፍ የሚባል ነገር አለ። ዝም ብሎ ማሳለፍ ምክንያቱም ተማሪዎች ከወደቁ የትምህርት ክፍሉን ድክመት ያሳያል እየተባለ ሲሳራበት የነበረው ነገር ምን ያህል ሀገሪቱን እንደጎዳት አሁን ለውይይትም የሚቀርብ አይደለም።

እኔ በዚህ ጉዳይ ባለፉት ሰባት (7) ወራት በትምህርት ዘርፍ ከሚሰሩ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች የግል ኮሌጆች ባለቤቶች እንደዚህ አይን ያወጣ የለም መሆን የለበትም የሚል ክርክር አልሰማሁም። ሁሌ የሚሰማው ለምን በኛ ጊዜ ? ለምን ባንተ ጊዜ ለምን በሌላውስ ሰው ጊዜ የሚለውን ልትመልስ አትችልም ይሄ ዝም ብሎ ደረቅ ክርክር ነው።

በአንድ በሆነ ጊዜ መጀመር አለበት ምክንያቱም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ላይ እየደረሳ ያለው ጉዳት ሀገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ነው። ይሄንን ዝም ብለን ማለፍ አንችልም ብለን እየሄድንበት ነው።

ለተማሪዎችም ፣ ለወላጆችም፣ ለቤተሰብም አንድ (1) ዓመት የመዘጋጃ ጊዜ ሰጥተናል። ለኮሌጆችም ተማሪዎቻቸውን እንዲያዘጋጁበት ጊዜ ሰጥተናል ይሄን ጊዜ በደንብ ተጠቅመው ስራቸውን መስራት አለባቸው።

ይሄ የመውጫ ፈተና የተማሪዎች ፈተና ብቻ አይደለም። ከተማሪዎች በላይ የትምህርት ክፍሎች፣ የኮሌጆች ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ፈተና ነው። ምን እያደረጉ ነው ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚለውን እንደትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ የምናገኘው ፤ እነዚህ ኮሌጆች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በእርግጥም ተማሪዎችን እያበቁ ነው ? ወይስ የዲግሪ ወፍጮ ቤት እንደሚሏቸው ዝም ብሎ ጊዜ እያስቆጠሩ ድግሪ የሚሰጡ ናቸው የሚለውን የምንለይበት ነው።

ስለዚህ የሚቀር አይደለም። ሁሉም እንደማይቀር አውቆ የተሰጠውን የመዘጋጃ ጊዜ በደንብ ተጠቅሞ ትምህርትን በደንብ አስተምሮ በደንብ አስጠንቶ ቢያዘጋጅ ነው የሚሻለው "

©ኢፕድ/ቲክቫህ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

" ...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው።

ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው። "

@Free_Education_Ethiopia
“የሰላም ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት እየተሰራ ነው” - ሰላም ሚኒስቴር

የሰላም ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት በማድረግ ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ስራ ለመስራት መታሰቡን የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ መሪ አስፈፃሚ ዶ/ር አወቀ አጥናፉ በተለይ ለሳይበር ሚዲያ ተናገሩ።

ሀገር በቀል የሆኑ የሰላም እሴቶች እና ባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓቶችን ያካተተ ስርዓተ ትምህርት ለመቅረጽ ምክክር እየተደረገ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#የ2015 ትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር

በአዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ሪፎርም መሠረት በ2014 ዓ.ም በተመረጡ የአንደኛ እና የመካከለኛ ደረጃ የሙከራ ትምህርት ቤቶች የተዘጋጁት የመማሪያ ማስተማሪያ መጻሕፍት ሙከራ ተካሂዶባቸው ወደ መሉ ትግበራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮው፡

1) የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም መምህራንን በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በማስተዋወቅ አዲሱ ቀርዓተ-ትምህርት በ2015 ዓ.ም. ተግባራዊ እንዲደረግ እንዲሁም

2) በዚህ ሸኚ ደብዳቤ ተያይዞ በተላከው የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የ2015 ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ እንዲደረግ አሳስባለሁ፡፡ | ብርሃኑ ነጋ ( ፕሮፌሰር ) የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Free Education Ethiopia ️︎
Photo
የ2015 ትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር

* በክፍል ውስጥ የመደበኛ ትምህርት መስከረም 9/ 2015 ይጀምራል።

* የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና (ሚንስትሪ) ከሰኔ 5 - 9/ 2015 ዓ.ም ይሰጣል።

* የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከግንቦት 21 - 25/ 2015 ዓ.ም ይሰጣል።

* ሰኔ 30/ 2015 ዓ.ም የዓመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።

መልካም የትምህርት ዘመን !!


የአዲስ አበባ ከተማ ት/ቢሮ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የፈተና ቀን እስኪደርስ ለምን ይጠብቃሉ

FRESHMAN የሁለተኛ ሴሚስተር የ MID TERM ፈተና ዝግጅቶን ከኛ ጋር በ 15 ቀን ያጠናቁ

@Premiumtutor

ብልሆች ቀድመው ይገኛሉ ኑ አብረን እንቅደም!
COMING SOON ❗️
በመጪው 2015 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የመውጫ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።

በ2015 ዓ.ም መጨረሻ መተግበር በሚጀምረው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ከሰሞኑን የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለአዲስ ዘመን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ሚኒስትር ዴኤታው ካነሳሷቸው ሃሳቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው

• የመውጫ ፈተና ምዘና የሚሰጠው ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ብቻ ነው።

• በግልም ሆነ በመንግስት የትምህርት ተቋም የሚማር ተማሪ ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ሲያልፍ ብቻ ነው፡፡

• የመውጫ ፈተናው የሚዘጋጅበት፣ የሚያዝበት እና የሚሰራጭበት ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

• በየዓመቱ ከ150 እስከ 180 ሺህ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ተማሪዎችን ምዘና ለመስጠት የሚያስችል አቅም አለ፡፡

• የሙያ ማኅበራት አቅማቸው ሲጎለብት የሙያ ፈተና ይሰጣሉ፤ የመውጫ ፈተና ሥራን ከመንግስት ይረከባሉ።

• ፈተናውን የሚያሰናዱ ተቋማትና መምህራን ዝግጅት ሥራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ፡፡

• የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጸኝነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እየተሰራበት ነው።

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2025/02/25 10:22:07
Back to Top
HTML Embed Code: