Telegram Web Link
ተፈታኞች ከነገ ጀምሮ ይገባሉ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከነገ ሐምሌ 16 ጀምሮ ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ።

ተፈታኝ ተማሪዎች ከሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚጓዙት በተዘጋጅላቸው ተሽከርካሪዎች ነው።

ተፈታኞች ዩኒፎርማቸውን መልበስ ፤ ብርድልብስና አንሶላ ይዘው መገኝት ይጠበቅባቸዋል። 

ወደ መፈተኛ ተቋማት ቆሎ፣ ጭኮ፣ በሶ የመሳሰሉ ደረቅ ምግቦችን ይዞ መግባት የሚፈቀድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ ሞባይል፣ አይፓድ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉ እንዲሁም ማንኛውም ጌጣጌጥ ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

ተማሪዎቹ ከቤታቸው ሲወጡ፦
- መታወቂያ ፣
- አድሚሽን ካርድ
- የት/ቤት ዩኒፎርም መያዛቸውን እንዳይረሱ ፤ ወላጆችም ይህንን እንዲያስታውሷቸው ጥሪ ቀርቧል።

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ይሰጣል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ!

የ2015 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።

በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቃል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ 8ኛ ክፍል ውጤት ወጣ!

" ተማሪዎች ውጤታችቸውን በ https://aa.ministry.et/#/result ላይ በመግባት ማየት ይችላሉ " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዛሬው እለት የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል።

50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል እንደሚዘዋወሩ የተገለፀ ሲሆን የተለያየ የአካል ጉዳት  ላለባቸው ተማሪዎች  የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑ ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ 73,385 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደው 70.6% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸው ተነግሯል።

61,840 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 50,812 የሚሆኑት ማለትም 82.16 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።

ተማሪዎች ውጤታችቸውን በ https://aa.ministry.et/#/result ላይ Registration number ና first name በማስገባት መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#Oromia

የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ።

የኦሮሚያ ክልል የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም  ስማቸውን እና የID. ቁጥራቸውን በማስገባት ዉጤታችሁን ማየት እንደሚችሉ ቢሮው አሳውቋል።

Website:- https://oromia.ministry.et/#/result

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016  የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር
 
ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።

የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ  ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከመስከረም 7- 10/2016 ዓ.ም ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና #በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 % በታች ሆኖ ወደከፍተኛ ትምህርት መግባት ያልቻሉ እና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ ሴሚስተር የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸው ይታወቃል።

የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና የሚሰጠው ተማሪዎቹ በተቋማት እና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና ወስደው በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው።

#MoE

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እንኳን  ለ 2016 ዓ.ም  አዲሱ  አመት በሰላም  አደረሰን!!

መጪው ዘመን  የሰላም  የፍቅር   የአብሮነት  የስኬት  የመፅናናት  የዕውቀት  የማስተዋልና  የደስታ እና  የስኬት  ዘመን  ይሁንልን ።

መልካም አዲስ ዓመት!!

Wishing you all Happy New Year 2016 E.C!

🌼🌻🌼🌿🇪🇹🌿🌼🌻🌼
" ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን ሰኞ መስከረም 7 /01/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ።

ቢሮው ይህን ያሳወቀው የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ለህዝብ ካሰራጨ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መልዕክት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ " የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 14 /1/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #የተሳሳተ ነው " ብሏል።

ቢሮው በየትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ እንደተሰራጨ በግልፅ አላሰፈረም።

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረገው የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት #ሀገር_አቀፍ የትምህርት ካላንደር መሰረት ከመስረም 7 እስከ 11/2016 ዓ/ም ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።

መስከረም 14 ደግሞ የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ካላንደሩ ላይ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ #የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረግ ብሏል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው መሰረት የ2016 ዓ/ም ትምህርት ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም ተቋም እንደሚጀምር #አስረግጦ ተናግሯል ፤ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ይህን እንዲያውቀው ብሏል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" እስካሁን ውጤት አልተገለፀም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እስካሁን #አልተገለፀም ሲል አሳውቋል።

ተፈታኞችና መላው የትምህርት ማህበረሰብ #በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በፀጥታና ሌሎች ምክንያቶች ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ፈተናቸውን መውሰዳቸው ይታወቃል።

የነዚህ ተማሪዎችን ፈተና ውጤት በሐምሌ 2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች ጋር አብሮ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም " እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል " የአገልግሎቱ ከፍተኛ ኃላፊ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ  ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በዌብ ሳይት 👉 https://eaes.edu.et/

በአጭር የጽሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም 👉 https://www.tg-me.com/eaesbot

#MoE

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የአሁኑ ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑን ከቀናት በፊት መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ በወረቀት ነው የሚሰጠው።

ይህ የፈተና አሰጣጥ አካሄድ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ፣ በመንግሥት በጀት ፣ በትምህርት ቢሮዎች ላይ ጫናውን እንደሚቀንስ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አመልክቷል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶቹ እየተደረጉ ሲሆን የሶፍትዌር ስራው ከወዲሁ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የዘንድሮውም ምዝገባ በኦንላይን ሲሆን፣ ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ ይደረጋል ፤ በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ ይሄዳል ተብሏል።

የተሻሉ የፈተና አዘጋጆች፣ ፈተናዎች እንዳይሰረቁ የሳይበር ጥበቃ፣ የደህንነት ካሜራዎች ፣ የተቋማት ትብብር (ኢንሳ፣ ፈተናዎች አገልግሎት) ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የፈተና ህትመት ዝግጅት ከዚህ ቀደሙም በተሻለ መልኩ ጠንካራ ስራ በጋራ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ እራሳቸውን ለመመዘኛ ፈተናው ብቁ እና ዝግጁ እያደረጉ መሄድ ያለባቸው ሲሆን መምህራን፣ ወላጆች፣ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተማሪዎችን እያገዙ ለፈተናው እንዲዘጋጁ ማደርግ አለባቸው።

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ገብተው ባለፉት ሁለት ብሄራዊ ፈተናዎች ማለትም በ2014 እና 2015 ከተፈተኑት አጠቃላይ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥተው ያለፉት እጅግ ጥቂት ናቸው።

በ2014 ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 30,034 ወይም 3.3 በመቶ ብቻ ሲሆኑ በ2015 ፈተና 845,099 ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ የቻሉት 27,267 ወይም 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

በተለይ ፈተናው በየአካባቢው ካሉ ትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ ወጥቶ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገበው ውጤት ብዙሃኑን ያስዳነገጠ እንዲሁም የትምህርት ስርዓቱ ያለበትን አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ያመላከተ ሆኗል።

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#ብሔራዊ_ፈተና

ባለፉት ሁለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት ግን እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው።

ምን የተቀረ ነገር ኖሮ ነው ? የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑን በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ማብራሪያ ሰጥታዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" የፈተናው ክብደ እና ቅለት ከሆነ ምንም የተቀየረ ነገር የለም።

የፈተና አሰጣጥ እና ዝግጅት ሂደት አለ፤ እራሱን የቻለ ሳይንስ አለው በጣም እንዳይከብድም በጣም እንዳይቀልም።

እስከ ዛሬ ሲሰራ ከነበረው ምንም የተለየ ነገር የለም። የተለየው ፈተና አሰጣጡ ነው።

ፈተና አሰጣጡ ያመጣው ለውጥ ምንድነው ከተባለ ፤ ከዚህ በፊት ፈተናዎች በየትምህርት ቤት ነው የሚሰጡት ፈተና መታተም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ፣ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ፈተናዎቹ ይሰረቃሉ።

ፈተና ሲሰረቅ የነበረው በተደራጀ መልክ ነው በክልሎች ፈታኞች በየክልሉ ሲሄዱ ትልቅ ግብዣ ተደርጎ ጉቦ ተሰጥቷቸው ተማሪዎቹ እንዲኮራረጁ ይደረጋል። ውጤቱ ትርጉም ያለው አልነበረም።

እኔ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣሁ ጊዜ በሁለተኛው ሳምንት ፈተና ሰጥተን ነበር በድሮው አሰጣት ፎርማት ያኔ ነው የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ ነው ብለን ፖሊሲ ያደረግነው ፣በወቅቱ ፈተና አሰጣጡን አልቀየርንም ነበር ያኔ ያለፈው 48% ነው። አንዳንድ ክልሎች 70-80 በመቶ አሳልፈዋል።

በምንም አይነት የተማሪዎቹ ችሎታና ብቃት አይደለም። ... መሰረቅ መኮረጁን ለማወቅ ዳታውን ከተታትሎ ማግኘት ይቻላል፤ ግልፅ ነው።

ፈተናው እራሱ የተማሪዎች ችሎታና ብቃት መለኪያ አልነበረም። ያንን ነው የቀየርነው። ከምንም በፊት የሰራነው በተማሪዎች ጭንቅላት ውስጥ በስርቆት፣ በማጭበርበር  ፣ ሌላ ሰው በማስፈተን ፣ በመኮረጅ የሚገኝ ትምህርት የለም የሚል ነው። ይሄን አውቀው እንደ ችሎታቸው እንዲያጠኑ ነው ያደረግነው።

የዛ ውጤት፣ እንደ ሀገር ያለንበትን ልክ ነው ያሳወቀን። በዚህም ይሄ ነው የትምህርት ስርዓቱ ካልን በኃላ ሪፎርሞችን በተግባር አውለን አንድ ትውልድ ቢበላሽብን ቀጣዩን እንዴት እናድናለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው። "

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በ2014 እና በ2015 በድምሩ 1,741,619 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውስደዋል። ከነዚህ ውስጥ ያለፉት በድምሩ 57,301 ተፈታኞች ናቸው።

በዚህ ልክ ተፈታኝ ተማሪዎች መውደቃቸው ዜጎችን ያስደነገጠ ቢሆንም ከነዚህ ተማሪዎች በፊትም ፈተናው አሰጣጡ በዚህ መንገድ ቢሆን ውጤቱ ከዚህ እንደማይለይና የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት ከታች ጀምሮ የመጣ እንደሆነ የሚገልጹ በርካቶች ናቸው።

ለዚህ ውድቀት ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነት እንዳለበትና ተማሪዎቹን ከሚያስተምሯቸው መምህራን ብቃት አንስቶ ፣ የትምህርት ቤቶች የጥራት ጉዳይ፣ የግብዓት አቅርቦት ሁሉ ሊፈተሽ የሚገባው እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑ ይነሳል።

via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
እባክዎ ይህንን የ 5 ደቂቃ ቅጽ በመሙላት እንድታግዙን በትህትና እንጠይቃለን

Dear Free Education Ethiopia subscribers,

We are deeply committed to enhancing and elevating the quality of service we provide to you. Your feedback is invaluable to us. Please assist us by taking a moment to fill out this 5-minute form.

HERE IS THE LINK
#Urgent

ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን መረጃ በአስቸኳይ እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ተቋማቱ በየፕሮግራሙ ያሉ ተማሪዎች መረጃን እስከ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም እንዲልኩ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።

በተጠቀሰው ጊዜ መረጃውን የማያሳውቅ የትምህርት ተቋም ተፈታኝ ተማሪ እንደሌለው እንደሚታሰብ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የመውጫ ፈተና በመንግሥት እና በግል ተቋማት በድምሩ 150,184 ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ወስደው 61,054 ተፈታኞች ወይም 40.65 በመቶዎቹ ማለፋቸው ይታወሳል።

(በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጄና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
2023 የታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸናፊ የሆነው የ14 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሔማን በቀለ 25,000 ዶላር ተበረከተለት።

በአሜሪካ ቨርጂንያ ነዋሪ የሆነው ታዳጊ ሔማን ሽልማቱን ያገኘው የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚያስችል ሳሙና በመፍጠሩ ነው።

ሳሙናው በአነስተኛ ዋጋ ($.50) ለገበያ የሚቀርብ መሆኑ ተመልክቷል።

"ታዳጊዎች በዓለም ላይ መልካም ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ አምናለሁ" የሚለው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪው ሔማን፤ ለባዮሎጂ እና ቴክኖሎጂ ትምህርት አይነቶች ሁሌም ልዩ ፍላጎት እንደነበረው ይገልፃል።

ውድድሩ የፈጠራ ሃሳቡን ለማውጣትና ውጤታማ እንዲሆን ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረለት ገልጿል።

ላለፉት አራት ወራት በውድድሩ ለመጨረሻ ዙር ከደረሱ ሌሎች ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ጋር America’s Top Young Scientist ለመባል ብርቱ ፉክክን ሲያደርግ ቆይቷል።

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የፈጠራ ውጤቱን የበለጠ በማበልፀግና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በማቋቋም ሳሙናውን ለሚፈልጉ ሰዎች በአነስተኛ ዋጋ ለማቅረብ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

USA Today በሔማን በቀለ ላይ የሠራውን ሰፊ ዳሰሳና የምስል ዘገባ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፦

https://www.usatoday.com/story/news/health/2023/10/23/virginia-teenager-heman-bekele-america-top-young-scientist/71288776007/?fbclid=IwAR0HNycYzn2ii4gAg4iIYSHQ5gm7yUh1oRW7hWTHNPYEiAUQMKYfX-OV-2I


VIa TIKVAH

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
#MoE

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች #የዩኒቨርሲቲ_ምደባን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ

የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-

1. በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1,000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

2. የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

3. የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡

4. የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞችና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5. በተቋማት የጾታ ተዋፅኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋፅኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል።

6. የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ያግዛል፡፡

7. የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር ያግዛል፡፡

8. የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው፡፡ በመሆኑም በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡

9. በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡

10. ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል።

11. የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል ዕድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምትውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል።

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#Update

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ከታች የተዘረዘሩ ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፦

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ
6. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
The Pan Africa Youth Leadership Program (PAYLP) is a three-week exchange from April 6-April 27, 2024 in the United States for high school students and adult mentors. The primary program themes are civic education, community service, entrepreneurship, and youth leadership development.  Participants live with host families for the majority of the exchange and engage in leadership and civic education workshops, community service activities, visits to local schools and community organizations, project planning and development, and local cultural activities with American peers. Participants return home with action plans to bring their exchange experience to their home communities in the form of a wide range of community service projects.   
Apply here https://t.ly/-8Q9z
@addisamcenter
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ነጥብ ማምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል።

በሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የማካካሻ ትምህርት ለሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ፤ የማካካሻ ትምህርቱ ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ ያዛል።

በዚህም ተቋማቱ ከጥር 1 ጀምሮ በቀሩት ወራት ትምህርቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ መስጠት እንዳለባቸው ተገልጿል።

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
🎄 እንኳን ለክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ 🎄 

⚜️ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም ገና እያልን፤ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንሎት እንመኛለን። ⚜️ 


🎁በድጋሚ ለሁላቹም መልካም ገና🎁

🎄 Merry Christmas! 🎄

We welcome the birth of Christ with peace and joy. May this holiday season bring us joy and blessings.

🎁Wishing you a wonderful celebration!🎁

#stay safe
#Free education Ethiopia
2024/12/23 06:05:32
Back to Top
HTML Embed Code: