Telegram Web Link
#የመቁረጫ_ነጥብ

የአቅም ማሻሻያ (ረሜዲያል) የመቁረጫ ነጥብ፦

- የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 263

- የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 227

- የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 220

- የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 190

- የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 210

- የታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 210

- የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 180

- የታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 👉 180

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#Update

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና  ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ  የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

(የአቅም ማሻሻያ የመቁረጫ ነጥቡን ከላይ ይመልከቱ)

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ12ኛ_ክፍል_ማጠናቀቂያ_ፈተና_ወስደው_የማለፊያ_ውጤት_ያላመጡ_ተማሪዎች_1.pdf
4.9 MB
ሙሉ ማብራሪያ የያዘ ሰነድ

የ12ኛ-ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት ማስፈፀሚያ ሰነድ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ለ 2015 የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 13 - 14.

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 15 - 16.

ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 20-21.

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 15 - 16

ባህር ዳር ዩንቨርስቲ - የካቲት 20 - 22

ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ Online ምዝገባ የካቲት 20-26.
(  የመግቢያ ቀንየካቲት 27-28 )

ያልጠሩ ዩኒቨርስቲዎች ዛሬ እና ነገ ይጠራሉ።

የ Remedial ተማሪዎች ምደባ በዚህ ሳምንት ይከናወናል። ወደ ዩኒቨርስቲ የምትገቡባት ቀን ሩቅ ስላልሆነ ተዘጋጁ።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ጉዳዩ ፡ የነፃ የትምህርት ዕድልን ይመለከታል

👉ጠብታ አምቡላንስ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የመጀመሪያውን የግል የኢመርጀርሲ ሜዲካል ቴክኒሽያን ባለሙያ ደረጃ 4 ማሰልጠኛ ተቋም የሆነውን ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅን በመክፈት ከፍለው ለመማር አቅም የሌላቸው ወጣቶች የነፃ ትምህርት እድል በመስጠት አሰልጥኖ በጠብታ አምቡላንስ ቅድመ ሆስፒታል ድንገተኛ የህክምና አገልግሎት እና በጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ነው::

👉ኮሌጁ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም በግል ኮሌጆች ከፍለው መማር የማይችሉና የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ ውስን ሰልጣኞች በመመልመል የነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይጋብዛል ።

የመግቢያ መስፈርቶች

👉1. ከ2011 - 2013 ባለው የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና ውጤታቸው ለወንዶች ከ293 በላይ ለሴት ከ278 በላይ ያመጡ፡፡

👉2. የ2014 ዓ.ም ተፈታኞች በ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የቴ/ሙ/ የመግቢያ ነጥብ ያለው/ያላት፡፡

👉3. ዕድሜ ከ30 ዓመት ያልበለጠ/ያልበለጠች፡፡

👉4. የኮሌጁን መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል የምትችል፡፡

👉5. ከፍለው ለመማር የማይችሉ መሆኑን የሚገልጽ ከሚኖሩበት ቀበሌ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

👉6. ለሴት ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ይሰጣል

👉7. ስልጠናውን ለ20 ወራት በመደበኛ ፕሮግራም

👉የምዝገባ ጊዜ ከየካቲት 20 እስከ መጋቢት 2 /2015 ዓ.ም

👉የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቦታ ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ አድራሻ 22 አካባቢ እየሩሳሌም ህንጻ ፊት ለፊት ዮናስ ሆቴል ጀርባ

👉ለምዝገባ ሲመጡ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ ፣ትራንስክሪፕት ፣ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል ።

የፈተናው ጊዜ ከምዝገባ በኋላ ይገለጻል፡፡

Via: የየካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የ2015 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ በመሆኑ የሚያገለግለው ለ2015 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች የሚስተናገዱት በ2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል ተብሏል።

(የ2015 ዓ/ም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ALX Data Analytics
📅 Deadline: March 27, 2023
📍 ALX

Seize the opportunity to become a Data Analyst. Our beginner-friendly and accessible program is perfect for anyone regardless of educational background or math skills.

Apply now at and unlock your full potential in a growing industry! Limited Enrollment.

Enroll: https://bit.ly/3kzfSNm
.
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
#MoE

" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድሚያ የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሀዱ ዘግቧል።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡

ከሀምሳ በመቶ በታች ካመጡት ተማሪዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ አመት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሪሜዲያል እንዲወስዱ የተወሰነ ሲሆን ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚንስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት የሚፈልጉ የግል ከፍትኛ የትምህርት ተቋማትም በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም የማስተማሪያ ሰነዱ ለተማሪዎቹ ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ማስተማር የሚችሉት ይሄንን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ለአሀዱ በሰጡት ቃል አመላክተዋል

Via ahadu
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Free Education Ethiopia ️︎
Photo
" ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ ይቆያሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ፤ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የላቀ ውጤት ላመጡ 273 ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዓብይ አህመድ፣ የእዉቅናና ሽልማት ማበርከታቸው ይታወሳል።

በዚሁ እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለእነዚህ ተማሪዎች በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የትምህርት እድል/ Scholarship / እንደተገኘ መግለፃቸው አይዘነጋም።

ከዚህ የትምህርት እድል ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የትምህርት እድሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥረት የተገኘ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ተማሪዎቹ ከመስከረም/2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲማሩ መመቻቸቱን ገልጿል።

ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ ያሉትን ግዜያት #የእንግሊዝኛ_ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ እንድቆዩ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎች የተፈጠረላቸዉ እድል በቀጣይ እየተፈጠረ ላለዉ በዉድድር ላይ የተመሰረተ  ዓለም ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ምሩቃንንና ሳይንትስቶችን ፣ ቴክኖሎጂስቶችን፣ መሪዎችን  የመፍጠሪያ ልዩ  እድል መሆኑን የገለፀው ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ በሄዱበት የሀገር ስምና ገጽታ ናቸዉ ብሏል።

የተፈጠረዉ የትምህርት ዕድል በጣም ጥሩ እድል መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ነገር ግን ዕድሉ ለተፈጠረላቸዉ ተማሪዎች #እንደግዴታ የሚወሰድ አይደለም ሲል አሳውቋል።

ተማሪዎቹ መማር የምፈልገዉ በሀገር ዉስጥ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ነዉ ብለዉ ካሰቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሌለ ተገልጿል።

ተማሪዎቹ በተባበሩት ኤሜሬትስ በየትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ሊማሩ ይችላሉ ?

🏫 የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ

የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ደረጃ 284ኛ ላይ ሲገኝ በአረብ ወሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ዉሰጥ ደግሞ አምሰተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቀመጫውንም አል አይን በተባለችው የአቡ ዳቢ ከተማ ሲሆን ካሉት ዩኒቨርስቲዎችም በእድሜ ትንሹ ነው።

🏫 አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ ፦

አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዉስጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች በሰባተኛነት የተቀመጠ ሲሆን  የሚሰጣቸው የትምህርት አይነቶችም በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል መሰረት ነው። በአለም አቀፍ ተማሪዎችም ተመራጭ የሆነ ዩኒቨርስቲ ነው።

🏫 ካሊፋ ዩኒቨርስቲ ፦

ካሊፋ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ደረጃ 211ኛ ላይ ሲገኝ በ2021 በተሰጠው የዩኒቨርስቲዎች ደረጃ ደግሞ በአረብ ዉሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ውሰጥ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ለትርፍ ያልተቋቋመ ትኩረቱን ሳይንስ ላይ አደረጎ በ2007 የተመሰረተ ዩኒቨርሰቲ ነው። ዩኒቨርሰቲው በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል የተቃኘም ጭምር ነው። በውሰጡ ሶሰት ኮሌጆች፣ ሶሰት የምርምር ኢኒስቲቲዩቶች፣ 18 የምርምር ማእከላት እና 36 ዲፓርትመንቶችን በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ይዟል።

🏫 ዪኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ፦

ዪኒቨርሰቲ ኦፍ ሻርጃ በ 1997 የተቋቋመ ሲሆን በመካከለኛው እሩቅ ምሰራቅ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የትምህርት ተቋም ለመሆን አልሞ እየሰራ ያለ ዩኒቨርሰቲ ነው።

🏫 ዛይድ ዩኒቨርስቲ ፦

በ1998 የተመሰረተና በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ስመ ጥር የሆነ ዩኒቨርሲቲ ነው።

https://www.topuniversities.com

#ትምህርት_ሚኒስቴር
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" የውጭ የትምህርት እድል ያገኛችሁ ተማሪዎች ወደ ተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ ግቡ " - ትምህርት ሚኒስቴር

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ያመጡና የውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል /Scholarship/ የተሰጣቸው 273 ተማሪዎች ቀደም ሲል በትምህርት ሚኒስቴር ወደተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ትምህርት ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ተማሪዎቹ የውጪ ሀገር ትምህርቱ የሚጀመረዉ ከመስከረም/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ ቀደም ሲል ወደተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ነው ሚኒስቴሩ ያሳሰበው።

ለውጪ ሀገር ትምህርታቸው የሚያግዝ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ቀደም ሲል ከተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር የሚፈጸም መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዚህ ጉዳይ በተናጠል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የሚመጣ ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ግልጿል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" ትምህርት ቤቶቹን በመጪው ሚያዝያ ወር እንደገና ለመክፈት ዕቅድ ተይዟል " - UNICEF

በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን እንደገና ለመክፈት ዕቅድ መውጣቱ ተገልጿል።

በትግራይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከመራቃቸው ባለፈ መምህራንም ለሁለት ዓመታት ደመወዝ አልተከፈላቸውም

ትምህርት ቤቶቹን በመጪው ሚያዝያ እንደገና ለመክፈት ዕቅድ እንደተያዘም (UNICEF) የትምህርት ኃላፊ ቻንስ ብሪግስ ተናግረዋል።

"በትግራይ ሙሉ በሙሉ የትምህርት ሥርዓቱ ፈርሷል"ያሉት ቻንስ ብሪግስ " ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ2.3 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው የሚያሳይ መረጃ አለን" ብለዋል

በመቐለ ከባለቤታቸው እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ነዋሪ የሆኑት አቶ መንግሥት ገብረመድኅን የእርስ በርስ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት ሁለቱ ልጆቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ነበር።

" የአየር ጥቃቶች እና የድሮን ጥቃቶች ድምጽ ይሰማሉ። ህጻናቱን ጠመንጃ ይዘው የሚሄዱ ወታደሮችንም ያያሉ። እነሱንም ለማስመሰል ይሞክራሉ። " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

" ደመወዛችን አየተሰጠን ስላልነበር ልጆቻችን ምን እንደምንመግባቸው ያስጨንቀን ነበር ስለዚህ እነሱን በማስተማር ላይ ማተኮር ፈታኝ ነበር። ነገር ግን ትናንትና ደመወዜን ተቀበልኩ፣ አሁን ለልጆቼም ልብስ እና ምግብ መግዛት እችላለሁ " ብለዋል

በትግራይ በነበረው ጦርነት ከዛም በፊት በነበረው የኮቪድ19 ወረርሽኝ ሚሊዮኖች ተማሪዎች  ከትምህርት ገበታቸው ርቀዋል መምህራን ደግሞ በጦርነት ምክንያት ደሞዝ ሳይከፈላቸው ቆይቷል

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
" የመውጫ ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና እንዲወስድ የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

250 ሺህ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመጪው ሐምሌ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።

ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና እንዲወስድ የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተናው #በኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡ #ኢፕድ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2024/12/23 19:08:31
Back to Top
HTML Embed Code: