Telegram Web Link
ሱራየ እንወድሃለን
ከልብ ስታገለግል በክብርህ ልክ ትከበራለህ ; የእርጋተው ባላባት ገንዘብ ያላማለለው ; የጎንደሮች ባለውለታ ; የአበቄለሽ ፍቅር ተቋዳሺ በ ሄድክበት ሁሉ ጥሩውን ተመኘን

አንዴ ሱራ ኢተርቪው ላይ
ኢትዮጸያ ውስጥ ከፋሲል ውጭ አልጫወትም አለች ታማኞዋ ነብሮ

ከዚ በላይ ፍቅር የትይምጣ 🙏🙏🙏🙏🇵🇪🇵🇪❤️❤️❤️❤️

ከአፍሪካ የማይዘለው የአገራችን ዝውውር ገብያ ማስተማርያ ይቻላላል ¿¿¿
#አስደሳች_ዜና!

የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ሰው ሰራሽ የመጫወቻ ሜዳ የፊፋን የጥራት መስፈርት በማሟላቱ ከአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ ለ3 አመታት የሚቆይ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማግኘቱ ተሰምቷል!

ይህን ፕሮጀክት ከመወጠን አንስቶ ለተግባራዊነቱ በመትጋትና የቅርብ ክትትል በማድረግ ለስኬት ያበቁትን ከማንም በላይ የድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃርን እና ካቢኔያቸውን እንዲሁም ኮንትራቱን ተቀብሎ በከፍተኛ የሙያዊ ብቃት፣ በፊፋ ስታንዳርድ መሰረት ግንባታውን አከናውኖ ያጠናቀቀውን ተቋም(TAN Engineering) አለማድነቅና አለማመስገን ንፉግነት ነው!
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን ከ2011 እስከ 2016 አመት ያገለለለው ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነስርዓት ላይ መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካን ያደረገው ዲሲ ዩናይትድ ስፖርት ክለብ ባለቤት እና አመራሮች በተገኙበት ለመጋቢ ቡድኑ ሎንደን ዩናይትድ በይፋ ፈርሟል::

ፋሲል ከነማ ለሱራፌል ዳኛቸው እንኳን ደስ አለህ በማለት የክብር ሽኝት እና ሽልማት እንዳደረገለት የሚታወስ ሲሆን ቀሪ የእግር ኳስ ህይወቱ የስኬት እንዲሆንለት ይመኛል::

🇦🇹#መልካም_እድል 🔟 #ሱራፌል_ዳኛቸው🇦🇹
. 🇦🇹 #እናመሰግናለን!!🇦🇹

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
#የሙሉ_ሰዓት_ውጤት!!

ተጠናቀቀ | ፋሲል ከነማ 2-1 ሀዋሳ ከተማ 90"
⚽️76’አማኑኤል ገ/ሚካኤል ⚽️41’ታፈሰ ሰለሞን
⚽️88’ቃልኪዳን ዘላለም

🗓️ አርብ የካቲት 22/2016
🕐 1:00
🏟 ድሬዳዋ ስታዲየም

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

🇨🇬#Adwa #VictoryofAdwa #Ethiopia 🇨🇬#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት #የአሸናፊነት_ተምሳሌት #ኢትዮጵያ🇨🇬

@FASILSC
የኢትዮጵያ ፕሪሚዩር ሊግ ደረጃ ሰንጠረዥ ከ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኃላ...
ዐፄዎቹ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርመዋል

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው ፋሲል ከነማ የማጥቃት እና የመከላከል ባህሪ ያላቸው ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
በዘንድሮ የውድድር ዘመን የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተን በመቅጠር ሊጉን የጀመሩት ዐፄዎቹ በ16 ጨዋታዎች 26 ነጥቦችን በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጡ ይታወቃል። ክለቡ በሁለተኛው ዙር የበለጠ ተጠናክሮ ለመቅረብ በሁለቱ የፍፁም ቅጣት ምት ክልሎች ግልጋሎት የሚሰጡትን ሁለት ተጫዋቾች ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ፋሲልን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች ተከላካዩ ሀቢብ መሐመድ ነው። ጋናዊው የቀድሞ አሻንቲ ጎልድ፣ አሳንቲኮቶኮ እና ድሪምስ ተከላካይ ዓምና ኢትዮጵያ መድንን በመቀላቀል የሀገራችንን ሊግ የተዋወቀ ሲሆን በዘንድሮ ዓመት ደግሞ ወደ አዳማ ከተማ አምርቶ ነበር። ተጫዋቹ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከአዳማ ከተማ ጋር ሳይስማማ ቀርቶ ውሉን በማፍረስ ለፋሲል ፊርማውን አኑሯል።

ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ አጥቂው አፍቅሮት ሰለሞን ነው። የእግርኳስ ህይወቱን መነሻ በደደቢት ተስፋ ቡድን ያደረገው አፍቅሮት በዋናው ቡድን የተወሰነ ጊዜ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መድን እና ገላን ከተማ አምርቶ የተጫወተ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ በሀምበሪቾ ቤት ጥሩ ጊዜ አሳልፎ አሁን መዳረሻው ፋሲል ሆኗል።
Soccer Ethiopia

@FASILSC
. #የኢትዮጵያ_ፕሪሚየር_ሊግ_17ኛ_ሳምንት_ጨዋታ
. Ethiopian Premier League..

. ኢትዮጵያ መድን 🆚 ፋሲል ከነማ

🗓️ ቅዳሜ የካቲት 30/2016
🕐 1:00
🏟 ድሬዳዋ ስታዲየም
🏆 ድል ለአፄዎቹ!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
🇦🇹🇦🇹#ደብል_ጃኖ_ማሊያ_በገበያ_ላይ_ዋለ🇦🇹🇦🇹

የብዙሀን ደጋፊዎቻችን ጥያቄ የነበርው ደብል ጃኖ ማሊያ ዛሬ በሁሉም የመሸጫ መደብሮቻችን ለገብያ ቀርቧል።እንደሚታወቀው በዚህ አመት ክለባችን ከሚጠቀምባቸው ሶስት አይነት መለያዎች ውስጥ ቢጫው ማሊያ ለገብያ ቀርቦ የቆየ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ደብል ጃኖ ማሊያ ለሽያጭ መቅረቡን እየገለፅን ለገብያ ያልቀረቡ ቀሪ ማሊያዎችን በቅርብ ጊዜ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን።

🇦🇹የአንዱ ማሊያ የመሸጫ ዋጋ 600 (ስድስት መቶ ብር) ብቻ🇦🇹

🇦🇹#የፋሲል_ከነማ_የደጋፊዎች_ማህበር🇦🇹

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹
እንኳን ደስ ያለን አፄዎቹ አሸንፈናል🇦🇹


@FASILSC🇦🇹
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ጨዋታ የመጀመሪያ አሰላለፍ🇦🇹

ፋሲል ከነማ VS ሲዳማ ቡና

እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
45+1' ጎል

ቃልኪዳን ዘላለም

(ፋሲል ከነማ 1-1 ሲዳማ ቡና)

@FASILSC
የጨዋታ 143 ውጤት !
. #የኢትዮጵያ_ፕሪሚየር_ሊግ_19ኛ_ሳምንት_ጨዋታ
. Ethiopian Premier League..

. ኢትዮጵያ ቡና 🆚 ፋሲል ከነማ

🗓️ ሀሙስ መጋቢት 19/2016
🕛 1:00 ምሽት
🏟 ድሬዳዋ ስታዲየም
🏆 ድል ለአፄዎቹ!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
#የሃዘን መግለጫ!

የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት አረፈ::

መጋቢት 18/2016 ሌሊት ላይ የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

ተጫዋቹ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትውልድ ቦታው አርባ ምንጭ ሌሊት በድንገት ማረፉ ተገልጿል።

ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ መጋቢት 18, 2016 በአርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ከክለቡ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ እና በደጋፊዎቹ ስም በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ:ለወዳጅ ዘመዶቹ :ለባህርዳር ከነማ እግርኳስ ክለብና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
2024/09/29 21:27:24
Back to Top
HTML Embed Code: