Telegram Web Link
ፋሲል ተሳትፎበት የነበረው ሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ውድድር በ መቻል የበላይነት ተጠናቀቀ
የመጀመሪያው ሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ባለቤት መቻል እንኳን ደስ አላቹህ ።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1498 የመውሊድ በዓል በስላም አደረሳቹህ።
🕌🕌🕌🕌

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ ደመራ እና መስቀል በዓል አደረሳቹህ።


ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የፊታችን እሁድ ይጀምራል ።
1,ፋሲል ከነማ ክለብ አመራሩ
ክለባችን ፋሲል የነበሩትን የደጋፊወች ጥያቄ በመመለስ ታላላቅ እና ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን በመድረግ እንዲሁም ከዚ በፊት የሊጉን ዋንጫ ተቆዳሽ እንድንሆን እና ፋሲል አስፈሪ እና ጠንካራ የሀገራችን ክለቦች ተርታ እዲሰለፍ የረዳን የጠንክሮ መስራት ምሳሌው አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ዳግም ወደ ቤቱ በማስመለስ እንዲሁም የፋሲል ከነማ ብዙ ጊዜ የሚታማበት የደጋፊወች አያያዝ በ 20,000 መታወቂያ ማውጣት ዘመቻ ጠንከር ያሉ ስራወች ተሰርተው ለሎሎች ክለቦች ምሳሌ ሁነንበታል እዲሁም ፋሲልን ወደቤቱ መመለስ የ ፋሲለደስ እስቴዲየም ማደስ ማስጀመር ጥሩ ጅማሮ ታይቶበታል ከፋሲል አመራሮችን የተሻሉ ስራዎችን በዚ ክረምት እደተሰሩ ሁሉም ደጋፊ የማያምንበት ነው
2,ፋሲል ከነማ ደጋፊወች
ከደጋፊወች በኩል በዚህ አመት ትኩረት ሰጥተን ልሰራ የሚገባን መታወቂያችን በማውጣት ; ስብናችን በማስተካከል ከእያንዳንዳችን ክለባችን መጥፎ ስም ከመስጠት ልንቆጠብ ይገባል ; የክለብ መለያ ማልያ ልናከብር እና በጥሩ ሁኔታ ልንይዝ ያገባል ማልያ ማክበር ክለብ ማክበር ነው ።
3,ፋሲል ከነማ አስጨፋሪወች
ከዚህ ቀደም ክለባችን የሚታወቅበት ዘርፍ ነበር አስጨፋሪው ጃኖ በመልበስ ጡም ዜማወችን ለደጋፊዎቹ ሲያስጨፍሩ ግጥሞችም ይባል የሚያሰኙ እና ለ አፍ የሚቀሉ አሰልች ያልሆኑ ባጠቃላይ የተለፋበት መሆኑን የሚያሳውቁ ነበር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትኩረት ማነስ ያን ውበታችን እያጣነው እና የማይናበብ ጭፈራወችን አሰልቺ (ድግግሞሽ የሚበዛበት ) የክለብን ትልቅነት የማይመጥን አደጋገፎችን እያየን ነው እና ይህ ቤት ሙሉ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራ ወሳኝ የ አንድ ክለብ ምንነት( image) ማሳያ ነው

አመቱ የክለባችን እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣ
አመቱ የፋሲል ነው
#ኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ የፊታችን መስከረም 20 ይጀምራል ።

የአንደኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ቅ/ጊወርጊስ በ አፍሪካ ቻምቺዮንስ ሊግ እንዲሁም ባህርዳር ከነማ በ አፍሪካ ኮንፌድሬሽን ሀገራችን ወክለው ከምድብ ድልድል ውስጥ ሳይገብ ቀርተዋል። ሁለቱንም ክለቦች ሀገራችን ወክላቹህ ጥሩ ተሳትፎ ስላደረጋቹ እናመሰግናለን።።🙏🙏🙏

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ 🇵🇪🇵🇪
የሲዳማ ቡናው አማካኝ አቤል እንዳለ በመጨረሻወቹ ሰዓታት የ አፄወቹን ስብስብን ተቀላቅሏል
አቤልን እንዳለ ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ወደ ደደቢት ከዛም ቅ/ጊወርጊስ ከዛም ኢ/ያ ብና ከዛም ሲዳማ ብና ብዙ ልምዶችን የያዘው አቤል እንዳለ የሁለት አመት ኩንትራት ይፈርማል ።

ንግስናው ነው ቦታችን⚽️⚽️ 🔴⚪️🔴⚪️
አቤላ እንኳን ደህና መጣህ🇵🇪🇵🇪🇵🇪
የጫዋታ ቀን !!🔴⚪️🔴⚪️
ደጋፊዎች የተለመደው ድጋፋቹህን በስምጥ ሸለቆዋ ንግስት አዳማ (ናዝሬት) እንገናኝ ።
ፋሲል ካለ ድል አለ ። 🇵🇪🇵🇪🇵🇪
የዘንድሮው ፋሲል ይለያል በመንፈስ; በአስተዳደር; በጥንካሬ ;በስፖርታዊ ጨዋነት ; በማሸነፍ ስነ ልቦናችን ጎፈሬን ለብሰን ተከስተናል ። ይህን ጥምረት ማየት ያጎጎል

ማሸነፍ ምርጫችን ነው !!
የፋሲል ነኝ ብለህ ንገረው💪💪💪

@FASILSC
#የጨዋታ ቀን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

ፋሲል ከነማ ከ ሀዋሳ ከተማ

ዛሬ መስከረም 26 -1 - 2016ዓ.ም

9:00

🏟 አዳማ ሳይንስ ዩንቨርስቲ ስታዲየም

እናሸንፋለን!!🇦🇹


@FASILSC
በአፄወቹ ደጋፊ ተመስገን ሰጠኝ እና በ ኢትዮጵያ ፒርሜርሊግ ደጋፊዎች ጥምረት የተደረገ ቃለ ምልልስ ።


ጥምረት:- ሙሉ ስም?

ደጋፊ:- ተመስገን ሰጠኝ

ጥምረት:- ክለባቹ በውድድር አመቱ ስኬታማ ጊዜ ያሳልፋል ብለህ ታስባለ?

ተመስገን:- እንደ ደጋፊ ጥሩ ዓመት እናሳልፋለን ብዬ አስባለው። ከአሰልጣኝ ቅጥር ጀምሮ ጥሩ ጥሩ ዝውውሮች አሳክተናል በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እምነት አለን ጥሩ ግዜ ይኖረናል።

ጥምረት:- ዛሬ በምታደርጉት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ከክለባቹ ምን እንጠብቅ?

ተመስገን:- በዛሬው ጨዋታ ለክለባችን አዳዲስ የሆኑ  ተጫዋቾች እንዲሁም አዲስ አሰልጣኝ ነው ያለን ሁሉንም አብረን እምናይ ይሆናል።

ጥምረት:- ክለባቹ በደጋፊዎች ታጅቦ እንዲጫዋት ምን ስራ እየተሰራ ነው?

ተመስገን:- ክለባችን በደጋፊዎች ታጅቦ እንዲጫወት ደጋፊ ማህበሩ እና ከተማ አስተዳደሩ በቅንጅት እስታዲየማችን ታድሶ ወደ ድሮ አፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ድባብ ለመመለስ እየተሰራነው።በድባብ የሚታማ ደጋፊ አደለም የትም  ስታዲየም ልዩ የሆነ ደጋፊ አለን።

ጥምረት:- በቀጣይ የውድድር አመት ደጋፊዎችን ወደ ገንዘብ ለመቀየር  መሰራት አለበት የምትለው ነገር ካለ?

ተመስገን:- ደጋፊውን ወደ ገንዘብ ለመቀየር የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማህበር ከአሁን በፊት የመታወቂያ ዘመቻ፣ባዛር፣የጎዳና ላይ እሩጫ ወ.ዘ.ተ ሲሰራ ቆይቷል አሁን በተሻለ ይቀጥላል።

ጥምረት:-በዚ የውድድር  አመት ምን አይነት ቡድን እንዲኖራቹ ትፈልጋለህ?

ተመስገን:- ምንም ጥርጥር የለውም የዋንጫ ቡድን እንፈልጋለን።

ጥምረት:- ስለጥምረቱ ያለህ አስተያየት?

ተመስገን:- ጥምረቱ ድንቅ ስራ እየሰራ ነው። የእግር ኳስ ክለባትን እርስ በእርስ የሚያቀራርብ በመሀላችን መከባበር፣መደጋገፋ እንዲኖር ያደረገ ነው በርቱ።

ጥምረት:- የዛሬ ጨዋታ ግምት?

ተመስገን:- 3 ለ 1 እናሸንፋለን ጌታነህ ከበደ ለፋሲል ከነማ የመጀመርያ ጎሉን ያስቆጥራል።
⚪️🔴⚪️🔴
ና ና ፋሲሌ ና ና 🇦🇹🇦🇹

ምንጭ -ጥምረት

@FASILSC
👉የሶከር ኢትዮጵያ ከፋሲል በኩል ለ 9:00 ሰዓቱ ጨዋታ ግምገማ
🇵🇪🇵🇪🇵🇪
ባለፈው የውድድር ዓመት ወደ ሊጉ ካደጉ በኋላ ደካማ የሚባል የውድድር ዓመት ያሳለፉት ዐፄዎቹ ዘንድሮ ያደረጓቸው ለውጦች ከወዲሁ ለዋንጫ ከታጩ ቡድኖች ውስጥ እንዲካተቱ አድርጓቸዋል። አምና በአሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ የኋላ ኋላ ደግሞ በአሸናፊ በቀለ ስር እየተመሩ ዓመቱን ያገባደዱ ሲሆን ክለቡ ከለመደው የውጤት ጉዞ አንፃር መዳከሙን ተከትሎ በመጨረሻዎቹ የሊግ ጨዋታዎች ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ውላቸው የተጠናቀቁትን የቀድሞው አሰልጣኛቸው ውበቱ አባተን በድጋሚ መልሰው በመቅጠር በርካታ ትልልቅ ዝውውሮችን ፈፅመው ዘንድሮ በሊጉ ከተጠባቂ ክለቦች ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል። የ2015 የሊግ ተሳትፏቸውን በደረጃ ሰንጠረዡ 5ኛ ላይ በ43 ነጥቦች ተቀምጠው የፈፀሙት ዐፄዎቹ በቀድሞው አሰልጣኛቸው የዝውውር መስኮቱ ላይ በንቃት ተሳታፊ ነበሩ። እንደ ጌታነህ ከበደ ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል ፣ ኤልያስ ማሞ ፣ እዮብ ማቲያስ ፣ ጋቶች ፓኖም ፣ ዮናታን ፍሰሀ እና ቃልኪዳን ዘላለምን እንዲሁም የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችንም ጭምር በማካተት በተጨማሪነትም ረዳት አሰልጣኝ እና የቪዲዮ ተንታኝን ጭምር በመቅጠር ክለቡ በሀዋሳ ዝግጅቱን ለወራት ሲሠራ ቆይቷል። በሀዋሳ ክለቡ በቆየበት ወቅት ካደረጋቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ባሻገር በሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ላይ ተሳትፎም ነበር። በዚህ ውድድር ላይ ቡድኑ የቅንጅት ችግሮች ፍንትው ብለው ሲንፀባረቁበት የነበረ ቢሆንም ቡድኑ በሒደት በጌታነህ ከበደ በጥልቀት ለመጫወት ሲጥር ግን የተለየ መልክን ተላብሶ ያስተዋልን ሲሆን ምን አልባት በነገው ጨዋታ የነበሩበትን ችግሮች በነበሩት የዝግጅት ቀናት ካስተካከለ በማያጠራጥር መልኩ በርካቶቹ ተጫዋቾች ልምድ ያላቸው ከመሆኑ አንፃር ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል።

ስራህ ምስክርነት ሲያገኝ ያስደስታል
ልካችን ዋንጫ ነው 💪💪💪

መልካም ዕድል ፋሲሌ⚪️🔴⚪️🔴

ምንጭ- ሶከር ኢትዮጵያ

@FASILSC
እናሸንፋለን በፋሲል ሙሉ እምነት አለን
ጨዋታ ተጀምሮል
ሀዋሳ 0-0 ፋሲል
1'
2024/09/29 23:27:16
Back to Top
HTML Embed Code: