Telegram Web Link
ሁለተኛ አጋማሽ ተጀመረ

46

ፋሲል 0-0 ሲዳማ

@FASILSC
80

ፋሲል 0-0 ሲዳማ


@FASILSC
ጎልልልልልልል


ጊትጋቱ በራሱ ላይ
ሪፖርት | ፋሲል ከነማ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል

በምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ ዐፄዎቹ ጊት ጋትኩት በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠራት ግብ ሲዳማ ቡናን 1-0 በመርታት የመጀመሪያ ድላቸውን አሳክተዋል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ተጠባቂው የሲዳማ ቡና እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ ሲደረግ በአቻ ውጤቶች ጨዋታቸውን አጠናቀው ለዛሬው ጨዋታ የተገናኙት ሁለቱ ቡድኖች ካለፈው የጨዋታ አቀራረባቸው ውስጥ በተመሳሳይ በሦስት ተጫዋቾች ላይ ቅያሪን አድርገዋል። ፋሲሎች እዮብ ማቲያስ ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል እና ይሁን እንዳሻውን አሳርፈው ዮናታን ፍሰሀ ፣ ቃልኪዳን ዘላለም እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስን ሲያስገቡ በሲዳማ ቡና በኩል በዛብህ መለዮ ፣ እንዳለ ከበደ እና ቡልቻ ሹራ አርፈው ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ እና አቤኔዘር አስፋው ተተክተው ገብተዋል።
ቀዝቃዛ በነበረው የመጀመሪያ አጋማሽ የመጀመሪያ 20 ደቂቃዎች ሲዳማዎች በፈጣን ቀጥተኛ ኳሶች ከራሳቸው የሜዳ ክፍል ለመውጣት ሲሞክሩ ፋሲሎች በአንጻሩ በርካታ ስኬታማ ቅብብሎችን በማድረግ እና የኳስ ቁጥጥር ብልጫ በመውሰድ የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረት አድርገዋል። ሆኖም 10ኛው ደቂቃ ላይ በሲዳማ ቡና በኩል ማይክል ኪፖሩል በፋሲል ከነማ በኩል ደግሞ ሱራፌል ዳኛቸው ከሳጥን አጠገብ ሙከራ አድርገው ሁለቱንም ግብ ጠባቂዎቹ በቀላሉ ይዘዋቸዋል።

በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል መድረስ የቻሉት ዐፄዎቹ 19ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታውን ለመምራት እጅግ ተቃርበው ነበር። በፈጣን ሩጫ ከሳጥኑ የቀኝ ክፍል ላይ የደረሰው ቃልኪዳን ዘላለም ጥሩ ሙከራ አድርጎ የግቡ የግራ ቋሚ መልሶበታል። በሴኮንዶች ልዩነትም ጌታነህ ከበደ ሳጥን ውስጥ ያደረገውን ሙከራ የመሃል ተከላካዩ ደስታ ደሙ ተደርቦ አምክኖበታል።
አልፎ አልፎ ፋሲሎች ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ደርሰው የሚያደርጉትን ቅብብል ስህተት በመጠቀም በፈጣን የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ የግብ ዕድል ለመፍጠር የሚሞክሩት ሲዳማዎች ጨዋታው ወደ ዕረፍት ሊያመራ በተጨመሩ የባከኑ ደቂቃዎች ውስጥ ግብ የሚያስቆጥሩበት ወርቃማ አጋጣሚ አግኝተው ነበር። ከሲዳማ ቡና የግብ ክልል በረጅሙ የተሻማውን ኳስ የፋሲል ተከላካዮች ግብ ጠባቂው ከጀርባ ይይዘዋል ብለው በመዘናጋት የተውትን ኳስ በጥሩ ሩጫ ያገኘው ማይክል ኪፖሩል ከማቀበል አማራጭ ጋር ከግብ ጠባቂ ጋር ቢገናኝም ዒላማውን ባልጠበቀ ሙከራ አባክኖታል።

ከዕረፍት መልስ ጨዋታው በኳስ ቁጥጥሩ ብልጫ ለመውሰድ በሚደረገው ብርቱ ፉክክር ጨዋታው በመጠኑ ተሻሽሎ ሲቀጥል የአጋማሹ የመጀመሪያ ዒላማውን የጠበቀ ሙከራም 53ኛው ደቂቃ በሲዳማዎች አማካኝነት ተደርጓል። አበባየሁ ዮሐንስ ከሳጥን ውጪ አክርሮ በመምታት ያደረገውን ሙከራ ግብ ጠባቂው ሚኬል ሳማኬ መልሶበታል።
ፋሲል ከነማዎች በተለይም በቀኙ የማጥቂያ መስመራቸው ተደጋጋሚ ፈጣን የማጥቃት ሸግግሮች ወደ ሳጥን ቢደርሱም ንጹህ የግብ ዕድል ለመፍጠርም ተቸግረው ተቸግረዋል። ሆኖም 68ኛው ደቂቃ ላይ ግን ጨዋታውን መምራት የሚችሉበት ዕድል አግኝተው ነበር።ጌታነህ ከበደ ቃልኪዳን ዘላለም በግሩም ዕይታ ሰንጥቆ ባቀበለው ኳስ ከግብ ጠባቂ ጋር ቢገናኝም ያደረገውን ሙከራ ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉ መልሶበት የግብ ዕድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

መጠነኛ ፉክክር እየተደረገበት የቀጠለው ጨዋታ እየተቀዛቀዘ ሄዶ በመጨረሻ 10 ደቂቃዎች ግን ድጋሚ ተጋግሎ ቀጥሏል። 80ኛው ደቂቃ ላይ ጌታነህ ከበደ ከመሃል በተሰነጠቀለት ኳስ ከሳጥን አጠገብ በድጋሚ ጥሩ የግብ ዕድል ቢያገኝም በዘገየ ውሳኔ ሳይጠቀምበት ሲቀር በአንድ ደቂቃ ልዩነት በሲዳማ ቡና በኩል ተቀይሮ የገባው ይስሃቅ ካኖ ከሳጥኑ የቀኝ ክፍል ላይ ጥሩ ሙከራ አድርጎ ግብ ጠባቂው ሚኬል ሳማኪ መልሶበታል።
ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ ግን 88ኛው ደቂቃ ላይ ፋሲሎች የማሸነፊያ ግብ አስቆጥረዋል። ተቀይሮ የገባው ኤልያስ ማሞ ያገኘውን የቅጣት ምት ወደ ሳጥን ሲያሻግረው የሲዳማው የመሃል ተከላካይ ጊት ጋትኩት በግንባሩ ገጭቶ ለማስወጣት ሲሞክር ተጨርፎ ራሱ ግብ ላይ አርፏል። ጨዋታውም በፋሲል ከነማ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ውጤቱም ለዐፄዎቹ የመጀመሪያ ድል ሆኖ ተመዝግቧል።

@FASILSC
አፄዎቹ የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዘገቡ !

በሶስተኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

- የፋሲል ከነማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጊት ጋትኩት በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ያጠናቀቁት አፄዎቹ የውድድር አመቱ የመጀመሪያ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

ቀጣይ ጨዋታ

እሁድ  ጥቅምት 18

ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@FASILSC
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፋሲል ከነማ ከ ሲዳማ ቡና
የጨዋታ ሃይላይት ይህን ይመስላል

አሸንፈናል🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
እናመሰግናለን በዛብህ መለዮ🇦🇹🇦🇹🇦🇹

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማህበር ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከነማ በነበረው ጨዋታ ላይ ለበዜ እንዝርቷ ማስታዎሻ አበርክተዋል።



@FASILSC
ና ና ፋሲሌ ና ና (2)
🇵🇪🇵🇪
ሱራ የ ቀይ እና ነጩ 🔴⚪️🔴⚪️
#ቀጣይ ጨዋታ

ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጽያ ቡና

ጥቅምት 17_2_2016

9:00

🏟 አዳማ ሳይንስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ


እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILSC
#የጨዋታ ቀን

ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና

ቅዳሜ 17 -2-2016

አዳማ ሳይንስ

እናሸንፋለን ግምትዎን ያስቀምጡ🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILSC
ፋሲል ከነማ የመጀመሪያ አሰላለፍ

እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
ጎልልልልልልልልልልልልልልል ፍሲል ከነማ
አማኑኤል ገ/ሚኬኤል ጎልልልልል
ጎልልልልል ፋሲል

ደገመው አማን🇦🇹🇦🇹🇦🇹
የሙሉ ሰአት ውጤት

ፋሲል 2-0 ቡና

አማኑኤል 54,80



@FASILSC
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን ያሸነፈበት ጨዋታ ጎሎቹ ይሄን ይመስላል


እንኳን ደስ ያለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILSC
#ቀጣይ ጨዋታ🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

ፋሲል ከነማ ከ ባህርዳር ከነማ

አርብ ጥቅምት 23-2-2016

9:00

🏟 አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ

እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILSC
ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከነማ የመጀመሪያ አሰላለፍ

እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹




@FASILSC
2024/09/29 19:23:05
Back to Top
HTML Embed Code: