Telegram Web Link
አፄዎቹ ከ ጦና ንቦች

ዛሬ 7:00

ሀዋሳ ዮኒቨርስቲ ስታዲየም


@FASILSC
ተጫዋቾቻችን ወደ ሜዳ እየገቡ ነው
መልካም እድል እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
ጨዋታው ጀምሯል

ፋሲል ከነማ 0-0 ወላይታ ዲቻ
ጎል ተቆጥሮብናል 😕

እናሸንፋለን በፋሲል ሙሉ እምነት አለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
ወላይታ 2-1 ፋሲል
#ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከበዛብህ መለዮ ጋር ተለያይቷል!

ክለባችን ፋሲል ከነማ ከመሐል አማካዩ በዛብህ መለዮ ጋር ውል ለማቋረጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል::

በ2010 ክረምት ላይ ከወላይታ ዲቻ አፄዎቹን የተቀላቀለዉ አማካዩ ላለፉት 6 ዓመታት ፋሲል ከነማን በብቃት ያገለገለ ሲሆን በተለይ አፄዎቹ በ2013 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ሲያነሱ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ካደረጉ ተጫዋቾች መካከል ይገኝበታል።

በዛብህ መለዮ ከክለባችን ፋሲል ከነማ ጋር እስከ ዓመቱ መጨረሻ የሚያቆየዉ የኮንትራት ዉል ቢኖረዉም ሁለቱ አካላት ባደረጉት ስምምነት ተጫዋቹ ዉሉን በማቋረጥ ሌላኛዉን የሊግ ክለብ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል::

በዛብህ ከክለባችን ጋር ለነበረህ ቆይታ በፋሲል ከነማ እና በደጋፊዎቻችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን መልካሙን ሁሉ እንመኝልሃለን::
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ።
በዛብህ መለዮ (በዜ )እናመሰግናለን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
#ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከታፈሰ ሰለሞን ጋር ተለያይቷል!

ክለባችን ፋሲል ከነማ ከመሐል ሜዳ ተጫዋቹ ታፈሰ ሰለሞን ጋር ውል ለማቋረጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል::

ባሳለፍነዉ ዓመት መጀመሪያ አፄዎቹን የተቀላቀለዉ አማካዩ የ2015 የዉድድር ዓመትን በአፄዎቹ ቤት ያሳለፈ ሲሆን በቆይታዉም ፋሲል ከነማን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና በ CAF የኮንፌደረሽን ጨዋታዎች ከመወከልም ባለፈ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከመሐል ሜዳ እየተነሳ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ታፈሰ ከክለባችን ፋሲል ከነማ ጋር እስከ ዓመቱ መጨረሻ የሚያቆየዉ የኮንትራት ዉል ቢኖረዉም ሁለቱ አካላት ባደረጉት ስምምነት የተጫዋቹ ዉል ሊቋረጥ ችሏል::

ታፈሰ ሰለሞን ከክለባችን ጋር ለነበረህ ቆይታ በፋሲል ከነማ እና በደጋፊዎቻችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን መልካሙን ሁሉ እንመኝልሃለን::
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ።

ታፈሰ ሰለሞን (ታፌ) ስለነበረን ጊዜያዊ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
#ከድር ኩሊባሊ (ኩሊ ጎንደሬዉ) እናመሰግናለን !

ክለባችን ፋሲል ከነማን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በመሐል ተከላካይ እና በተከላካይ አማካይ ቦታ በቋሚነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለዉ ኮትዲቯራዊዉ ተከላከይ ከድር ኩሊባሊ ከፋሲል ከነማ ጋር ያለዉ ዉል መጠናቀቁን ተከትሎ ከክለባችን ጋር ተለያይቷል።

በቅፅል ስሙ ኩሊ ጎንደሬዉ እየተባለ የሚጠራዉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ፤ ሜዳ ላይ ያለዉን አቅም አሟጦ በመጫዎት እና በአልሸነፍ ባይነቱ በአፄዎቹ ደጋፊዎች በእጅጉ ይወደዳል። ከዚህም ባለፈ ተጫዋቹ ከክለባችን ጋር ባሳለፋቸዉ 5 የዉድድር አመታት በጣት ከሚቆጠሩት ዉጭ በበርካታ ጨዋታዎች ላይ በቋሚነት ማገልገል ችሏል።

ኩሊባሊ ፋሲል ከነማ ወደ ሊጉ ካደገ በኋላ የፕሪሚየር ሊግ፣ የጥሎ ማለፍ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ሲያሳኩ ከፍተኛ ግልጋሎትን የሰጠ ሲሆን አፄዎቹ ኢትዮጵያን ወክለዉ በአፍሪካ መድረክ የCAF ቻምፒየንስ ሊግና ኮንፌደረሽን ጨዋታዎች ላይ በቋሚነት በመሰለፍ ድንቅ 5 ዓመታትን ማሳለፍ ችሏል።

ከድር ኩሊባሊ ከክለባችን ጋር ለነበረህ ቆይታ በፋሲል ከነማ እና በደጋፊዎቻችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን መልካሙን ሁሉ እንመኝልሃለን::
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ።

ከድር ኩሊቤሊ(ኩሊ ጎንደሬው) ስለነበሩን ጊዚያት እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏
# አስቻለው ታመነ (አስቼ አማቻችን እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በሄድክበት ሁሉ የተሻለውን እንመኛለን
ፋሲል ተሳትፎበት የነበረው ሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ውድድር በ መቻል የበላይነት ተጠናቀቀ
የመጀመሪያው ሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ባለቤት መቻል እንኳን ደስ አላቹህ ።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1498 የመውሊድ በዓል በስላም አደረሳቹህ።
🕌🕌🕌🕌

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ ደመራ እና መስቀል በዓል አደረሳቹህ።


ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የፊታችን እሁድ ይጀምራል ።
1,ፋሲል ከነማ ክለብ አመራሩ
ክለባችን ፋሲል የነበሩትን የደጋፊወች ጥያቄ በመመለስ ታላላቅ እና ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን በመድረግ እንዲሁም ከዚ በፊት የሊጉን ዋንጫ ተቆዳሽ እንድንሆን እና ፋሲል አስፈሪ እና ጠንካራ የሀገራችን ክለቦች ተርታ እዲሰለፍ የረዳን የጠንክሮ መስራት ምሳሌው አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ዳግም ወደ ቤቱ በማስመለስ እንዲሁም የፋሲል ከነማ ብዙ ጊዜ የሚታማበት የደጋፊወች አያያዝ በ 20,000 መታወቂያ ማውጣት ዘመቻ ጠንከር ያሉ ስራወች ተሰርተው ለሎሎች ክለቦች ምሳሌ ሁነንበታል እዲሁም ፋሲልን ወደቤቱ መመለስ የ ፋሲለደስ እስቴዲየም ማደስ ማስጀመር ጥሩ ጅማሮ ታይቶበታል ከፋሲል አመራሮችን የተሻሉ ስራዎችን በዚ ክረምት እደተሰሩ ሁሉም ደጋፊ የማያምንበት ነው
2,ፋሲል ከነማ ደጋፊወች
ከደጋፊወች በኩል በዚህ አመት ትኩረት ሰጥተን ልሰራ የሚገባን መታወቂያችን በማውጣት ; ስብናችን በማስተካከል ከእያንዳንዳችን ክለባችን መጥፎ ስም ከመስጠት ልንቆጠብ ይገባል ; የክለብ መለያ ማልያ ልናከብር እና በጥሩ ሁኔታ ልንይዝ ያገባል ማልያ ማክበር ክለብ ማክበር ነው ።
3,ፋሲል ከነማ አስጨፋሪወች
ከዚህ ቀደም ክለባችን የሚታወቅበት ዘርፍ ነበር አስጨፋሪው ጃኖ በመልበስ ጡም ዜማወችን ለደጋፊዎቹ ሲያስጨፍሩ ግጥሞችም ይባል የሚያሰኙ እና ለ አፍ የሚቀሉ አሰልች ያልሆኑ ባጠቃላይ የተለፋበት መሆኑን የሚያሳውቁ ነበር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትኩረት ማነስ ያን ውበታችን እያጣነው እና የማይናበብ ጭፈራወችን አሰልቺ (ድግግሞሽ የሚበዛበት ) የክለብን ትልቅነት የማይመጥን አደጋገፎችን እያየን ነው እና ይህ ቤት ሙሉ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራ ወሳኝ የ አንድ ክለብ ምንነት( image) ማሳያ ነው

አመቱ የክለባችን እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣ
አመቱ የፋሲል ነው
#ኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ የፊታችን መስከረም 20 ይጀምራል ።

የአንደኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ቅ/ጊወርጊስ በ አፍሪካ ቻምቺዮንስ ሊግ እንዲሁም ባህርዳር ከነማ በ አፍሪካ ኮንፌድሬሽን ሀገራችን ወክለው ከምድብ ድልድል ውስጥ ሳይገብ ቀርተዋል። ሁለቱንም ክለቦች ሀገራችን ወክላቹህ ጥሩ ተሳትፎ ስላደረጋቹ እናመሰግናለን።።🙏🙏🙏

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ 🇵🇪🇵🇪
የሲዳማ ቡናው አማካኝ አቤል እንዳለ በመጨረሻወቹ ሰዓታት የ አፄወቹን ስብስብን ተቀላቅሏል
አቤልን እንዳለ ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ወደ ደደቢት ከዛም ቅ/ጊወርጊስ ከዛም ኢ/ያ ብና ከዛም ሲዳማ ብና ብዙ ልምዶችን የያዘው አቤል እንዳለ የሁለት አመት ኩንትራት ይፈርማል ።

ንግስናው ነው ቦታችን⚽️⚽️ 🔴⚪️🔴⚪️
አቤላ እንኳን ደህና መጣህ🇵🇪🇵🇪🇵🇪
የጫዋታ ቀን !!🔴⚪️🔴⚪️
ደጋፊዎች የተለመደው ድጋፋቹህን በስምጥ ሸለቆዋ ንግስት አዳማ (ናዝሬት) እንገናኝ ።
ፋሲል ካለ ድል አለ ። 🇵🇪🇵🇪🇵🇪
የዘንድሮው ፋሲል ይለያል በመንፈስ; በአስተዳደር; በጥንካሬ ;በስፖርታዊ ጨዋነት ; በማሸነፍ ስነ ልቦናችን ጎፈሬን ለብሰን ተከስተናል ። ይህን ጥምረት ማየት ያጎጎል

ማሸነፍ ምርጫችን ነው !!
የፋሲል ነኝ ብለህ ንገረው💪💪💪

@FASILSC
2024/09/30 23:47:09
Back to Top
HTML Embed Code: