Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እንኳን ደህና መጣህ!!

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን የአፄዎቹ አሰልጣኝ አድርጎ ከሾመ በኃላ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከቡድናቸው ጋር የሚቀጥሉ እና የማይቀጥሉትን ተጫዋቾች በመለየት ያሳወቁ ሲሆን በለቀቁ ተጫዋቾች ምትክ አዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው እየቀላቀሉ ይገኛሉ:: በቀጣይ በፈረሙ እና ወደ ስብስቡ የሚቀላቀሉ ተጫዋቾችን የፊርማ ውላቸው በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሲፀድቅ በገፃችን የምናሳውቃችሁ ሲሆን ይሄን የተጫዋቾች ዝውውር ሂደት በትዕግስት እንድትጠብቁን ከታላቅ አክብሮት ጋር መልዕክታችንን እናስተላልፋለን::

ዳሽን ቢራ የፋሲል ከነማ የሁልጊዜም አጋር!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ፋሲል ከነማ ጌታነህ ከበደን በይፋ አስፈርሟል

የቀድሞው የብሄራዊ የፊት መስመር እንዲሁም የደደቢት, ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባለፉት አመታት የወልቂጤ ከነማ ተጫዋች አፄዎቹን ተቀላቅሏል

ተጫዋቹ በብዙ ክለቦች ስሙ የተነሳ ቢሆንም ዛሬ ጠዋት ለሁለት አመት ለፋሲል ፈርሟል

እንኳን ደና መጣህ የተሳካ ጊዜ እንዲሆንልህ እንመኛለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
እንኳን ደና መጣህ 🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
የቅድመ ዝግጅት ጥሪ🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

ክለባችን ፋሲል ከነማ ለ2016 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናክሮ ለመቅረብ የተለያዩ ዝውውሮችን በማከናወን የቆየ ሲሆን ከ ሀሙስ ነሀሴ 11 ጀምሮ ታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል መቀመጫውን በማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ያደርጋል።

ስለሆነም አዳዲስ ክለባችን የተቀላቀላችሁ እና ውል ያላችሁ ተጫዋቾች ከላይ በተጠቀሰው ቀን በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን በቆይታችሁም መልካም የዝግጅት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።


@FASILSC
#የዝውውር ዜና

አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ ለ2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ ዝዉዉሮችን በማድረግ የቆዩ ሲሆን መነሻውን በዳሽን ቢራ ስፖርት ክለብ አካዳሚ አድርጎ የተለያዩ ክለብም ተጫውቶ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ላለፉት ሁለት አመታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ተጫውቶ ውጤታማ የነበረውን የመስመር አጥቂ ተጫዋች አማኑኤል ገ/ሚካኤልን ለ 2 አመት ውል የግላቸው አድርገዋል።

አዲሱ የክለባችን የመስመር አጥቂ አማኑኤል እንኳን ደና መጣህ ወደ ታላቁ ፋሲል ከነማ እያልን በቆይታህም መልካም የዝግጅት እና የውድድሮ አመት እንዲሆንልክ እንመኛለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILSC
#የዝውውር ዜና🇦🇹
አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ እየተመሩ 2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ ዝውውሮችን እያደረጉ ሲሆን መነሻውን በአዳማ ታዳጊ ቡድን አድርጎ እንዲሁም በአዳማ ዋና ቡድን ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈው ሁለገቡን የመስመር ተከላካይ እዮብ ማቲያስ ለ2 አመት ውል የግላቸው አድርገዋል።

አዲሱ የክለባችን የመስመር ተከላካይ እዮብ እንኳን ወደታላቁ ፋሲል ከነማ በደና መጣህ እያልን በቆይታህም መልካም የዝግጅት እንዲሁም የውድድር አመት እንዲሆንልክ እንመኛለን።🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
#የዝውውርዜና🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ እየተመሩ 2016 ዓ.ም ጠንክረው ለመቅረብ ዝውውሮችን በማድረግ የቆዩ ሲሆን ላለፉት 2 አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት እንዲሁም በዋልያዎቹ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈውን የተከላካይ መስመር ተጫዋች ጋቶች ፖኖምን ለ 1 አመት ውል አስፈርመዋል።

አዲሱ ፈራሚያችን የተከላካይ አማካኝ መስመር ተጫዋች ጋቶች እንኳን ደና መጣህ ወደ ታላቁ ፋሲል ከነማ እያልን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

በቆይታህም መልካም የልምምድ እና የውድድር ጊዜ ይሁንልክ።


@FASILSC
#አፄዎቹ በሀዋሳ ቅድመ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ!

ለ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ በዝውውር የነቃ ተሳትፎ በማድረግ አስፈላጊ ባሏቸው ቦታዎች ላይ ዝውውሮችን ፈፅሟል::

ከነሃሴ 11 ጀምሮ መቀመጫቸውን በሀዋሳ ከተማ በታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል በማድረግ ዝግጅታቸውን በቀን ሁለት ጊዜ ጠንካራ ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛሉ::

አፄዎቹ ዝግጅታቸውን በተሟላ መልኩ እያደረጉ ሲሆን በጉዳት ልምምድ አቁመው የነበሩት ጌታነህ ከበደ እና ሱራፍኤል ዳኛቸው ካጋጠማቸው ጉዳት አገግመው ከቡድኑ ጋር ልምምድ መጀመራቸው ታውቋል::

በተየያዘም ዜና በዛሬው እለት ለ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለብሄራዊ ቡድን አገልግሎት 4 የክለባችን ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል::
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዎቾችም : አለምብርሃን ይግዛው ሱራፍኤል ዳኛቸው ጋቶች ፓኖም እና ምኞት ደበበ ናቸው::

ዳሽን ቢራ የፋሲል ከነማ የሁልጊዜም አጋር!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹
#የዝውውር ዜና🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ 2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ ዝውውሮችን በማድረግ የቆዩ ሲሆን ያለፉትን ሁለት አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈውን የመሀል ተከላካይ ምኞት ደበበን ለ2 አመት ውል የግለቸው አድርገዋል።

አዲሱ የክለባችን የተከላካይ መስመር ተጫዋች ምኞት ደበበ እንኳን ወደ ታላቁ ፋሲል ከነማ ቤት በደና መጣህ እያልን በቆይታህም መልካም የልምምድ እና የውድድር አመት እንዲሆንልክ እንመኛለን።


@FASILSC
#የዝውውር ዜና🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ 2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ ዝውውሮችን በማድረግ የቆዩ ሲሆን
የቀድሞው የአዳማ የሲዳማ ቡና እንዲሁም ያለፈውን አመት የወልቂጤ ከነማ
የመስመር ተከላካይ ዮናታል ፍስሀን በ3 አመት ውል አስፈርመዋል።

አዲሱ ተከላካይ ዮናታን ፍስሀ እንኳን ወደ ታላቁ ፋሲል ከነማ ቤት በደና መጣህ በቆይታህም መልካም የልምምድ እና የውድድር አመት ይሁንልክ።



@FASILSC
#የአቋም መፈተሻ ጨዋታ

🎯ፋሲል ከነማ🔴⚪️ ከኢትዮጵያ ቡና ☕️


ዛሬ ጳጉሜ 4 - 2015

10:00 አዳማ ዩንቨርስቲ


ተጫዋቾቻችን ወደ አዳማ ተጉዘዋል ድል ለተወዳጁ ክለባችን እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
👉የአቋም መፈተሻ ጨዋታ

              ጨዋታው ተጠናቀቀ

☕️ኢትዮጵያ ቡና 1–0 ፋሲል ከነማ 🔴
                      ሄኖክ (በራስ ላይ )

🏟በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም

@FASILSC
#ፋሲል ከነማ ከወንድማገኝ ማርቆስ ጋ በስምምነት ተለያይቷል!!

ክለባችን ፋሲል ከነማ ከወንድማገኝ ጋ በስምምነት ውሉን ለማቋረጥ ተስማምቷል


በ2014ዓ.ም ክረምት ላይ ከጅማ አባጅፋር በ 2አመት ውል ክለባችን የተቀላቀለው ወንድማገኝ ማርቆስ በቆይታውም በየ ጨዋታው 12 ጨዋታዎችን ለክለባችን አድርጓል።

ኮንትራቱ ሊጠናቀቅ አንድ አመት ቢቀረውም ከክለባችን ጋ ባደረገው ስምምነት ውሉን አቋርጧል።

ወንድማገኝ ማርቆስ ለነበረ ቆይታ ላደረከው አስተዋፆ በክለባችን እና በደጋፊው ስም ከልብ እናመሰግናለን ለቀጣይ አዲስ ስራህም መልካሙን እንዲገጥምህ ከልብ እንመኛለን።


@FASILSC🇦🇹
መልካም አዲስ አመት | 2016 E.C
🌻Happy Ethiopian New Year🌻

እንኳን አደረሳችሁ! አዲሱን አመት የሰላም፣የጤና፣የፍቅር እና የመተሳሰብ ያድርግልን

@FASILSC
#እንቁጣጣሽ🌻🌻🌻🌻

ውድ የፋሲል ከነማ ቤተሰቦች እንኳን ለ2016 የዘመን መለወጫ በአል በሰላም አደረሳችሁ።

አዲሱ አመት የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ ይሁንልን🤲



@FASILSC🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
አዲሱ ዓመት የቤት ስራወቻችንን የምናጠናቅቅበት ጉዞአችን የምንቀጥልበት ለ ክለባችን ከልብ የምናገለግልበት ዘመን ያድርግልን ጥሩ ቤተሰባዊነት እንዳለን በዘመቻወቻችን አረጋግጠናል ።
አንድ ቤተሰብ አንድ ክለብ
🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
ለፋሲላዊያን ቤተሰቦች እንኳን አደረሰቹህ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
2016 የነበረን ህብር አስጠብቀን
ዋንጫው ለአፄው ለማድረስ ያብቃን
የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 20 ይጀምራል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ከመስከረም 20_2016 ዓ.ም ጀምሮ ይከናወናል።

መርሀ ግብሩበአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስ ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የ2016ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመጀመሪያ ዙር በአዳማ እና ድሬዳዋ ከተማ ይደረጋል

የሊጉ የመጀመሪያ ዙር ሙሉ መርሀ ግብር ቀጥሎ ተያይዟል



@FASILSC🇦🇹🇦🇹🇦🇹
2024/09/30 19:30:51
Back to Top
HTML Embed Code: