Telegram Web Link
🇮🇱🇱🇧 እስራኤል ደቡብ ሊባኖስ ላይ በፈፀመችው ጥቃት 492 ሰዎች መሞታቸውን የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋ ማዕከል አስታውቋል

"በጥቃቱ 35 ህጻናት እና 58 ሴቶችን ጨምሮ 492 ሰዎች ሲገደሉ 1,645 ቆስለዋል" ሲል መግለጫው ገልጿል።

💥 ቀደም ሲል ሰኞ እለት የእስራኤል መከላከያ ሃይል በሊባኖስ ንቅናቄ ሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ተናግሯል።

📱የእስራኤል የአየር ጥቃት መሰንዘር የጀመረው ባለፈው ሳምንት በሊባኖስ በገመድ አልባ መሳሪያዎች ፍንዳታ ከተከስተ በኋላ ነው። በይፋዊ መረጃዎች መሠረት በፍንዳታው 37 ሰዎች ሲሞቱ  ከ3,000 በላይ ሰዎች ደገሞ ቆስለዋል።

👆ከማህበራዊ ድረ-ገጾች የወጡ ምስሎች በሊባኖስ በበካ ሸለቆ በደቡብ እና በሰሜን የእስራኤል ጥቃት ያስከተለውን ውጤት ያሳያል።
🇸🇳 በሴኔጋል የባህር ዳርቻ የ30 ስደተኞች አስከሬን የያዘች ጀልባ መገኘቱን የሀገሪቱ ጦር ሃይሎች የፕሬስ አገልግሎት አስታውቋል

🚤 "እሁድ መስከረም 22 ቀን የሴኔጋል የባህር ሃይል ከዳካር የባህር ዳርቻ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በርካታ አስከሬኖች መገኘታቸውን መረጃ ተነግሮት ነበር ። ወዲያውኑ ወደ አካባቢው የተላከው ካዮር የተሰኘው የደህንነት ጀልባ ወደ ስፍራው በማቅናት የዳካር ወደብ ተጎትታ የነበረን ጀልባ አግኝቷል
ሲል መግለጫው አክሏል።

ሶስት የፈጣን ጀልባዎች የዶክተሮች፣ የእሳት አደጋ ተከላካዮች እና የጤና ባለስልጣናት ቡድን ጭኖ ወደ ሥፍራው ደርሷል። የአካላታቸው የመበስበስ ሁኔታ የመለየት ስራውን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል።

እንደ ጦር ሃይሉ መረጃ በድምሩ 30 ሰዎች ሞተዋል። የሞቱት ሰዎች ስደተኞች ናቸው ተብሏል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የደብረ ሊባኖሱ የጦር ተዋጊ መኮንን እና መነኩሴ አባ ገብረ እንድርያስ
"መ/ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም አለም ያለ ሁሉ መልእክቱን ለማግኘት የሚፈልጉ ሰዎችን መርዳት ግዴታው ነው፡፡ ከብርቱ ቅጣት መፍሰስ ጀምሮ ሰዎች ለመዳን ይጥራሉና ! ማምለጫውን ማሳየት ግዴታው ነው፡፡ በዚህም ለመነገድ የሚሞክር ይቀጣበታልና አገልግሎቱን በነጻ ይስጥ፡፡ ውሳኔው ወደ አፈጻጸም ተሻግሯልና ያልጠበቅናቸው አገሮች ሕዝቦች የሚጠፉ ሲጠፉ የሚተርፉ ምህረት ሲሹና ማምለጫ ሲፈልጉ በየትም ያለ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ልጅ በትህትና፣ በቅንነት፣ ራስን ዝቅ በማድረግ፣ መርዳት ዋናው ተግባርና ግዴታው ነው፡፡

› በትምክህት የሚናገር የሚያደርግ የሚመጻደቅ ብርቱ ቅጣት ይጠብቀዋልና ከዚህ አጸያፊ ስራ ይቆጠብ፡፡"

🟥 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 3 ገጽ 39 ፥ ተጻፈ መጋቢት 19/2001ዓ.ም ።
Audio
መልክአ አቡነ ገብረ ማርያም ዘሐንታ
Audio
መልክአ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት
🇮🇱🇱🇧 የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ላይ አዲስ ጥቃት ሰነዘረ

ቪዲዮ 1፡ በደቡብ ሊባኖስ ውስጥ በሚገኘው Qsaibe ከተማ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ያስከተለውን መዘዞች ያሳያል

ቪዲዮ 2 እና 3፡ ከቤይሩት 30 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው በማኢስራ ከተማ ላይ የደረሰው የቦምብ ጥቃት ያሳያል

ቪዲዮ 4 እና 5፡ በደቡብ ሊባኖስ ውስጥ በሳይዳ ከተማ አቅራቢያ በዛህራኒ የነዳጅ ዴፖዎች አጠገብ የደረሰው ጥቃት ያሳያል።

ቪዲዮዎቹ ከማህበራዊ አውታረመረቦች የተገኙ ናቸው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇨👨‍🚒 ኪቶ በከባድ የእሳት አደጋ ተውጣለች

የኢኳዶር ዋና ከተማ የሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ሲሆን እሳቱን ለመከላከል የእሳት አደጋ ሠራተኞች እና የጦር አውሮፕላኖች ተሰማርተዋል።
በትራፊክ አደጋ የ55 ሰዎች ሕይወት አለፈ። (updated)

ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ55 ሰዎች ሕይወት አለፏል፡፡በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ እንደገለጹት

አደጋው ዛሬ ቀን 7 ሠዓት ላይ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፈታታ ቀበሌ መከሰቱንም አረጋግጠዋል፡፡የተከሰተው አደጋ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2024/09/26 03:30:44
Back to Top
HTML Embed Code: