Telegram Web Link
አሳዛኝ መረጃ‼️
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ 03 ቀበሌ ቤተሆር ላይ ትናንት ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከስቶ  የ48 አርሶደሮችን እህል ማውደሙን የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል። የእሳቱ መንስኤም አልታወቀም ብለዋል።
አዩዘሀበሻ
================
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መሬት ርዕደት
ዛሬ 02/05/2017 ከረፋዱ 4:50:30 ሰኮንድ ገረጅ ና መገናኛ መካከል የመሬት መንቀጥቀጥ ተሠምቷል ።
በእሳት እየጋየች ያለችው ሎስ አንጀለስ ከሳተላይት ስትታይ ይሄንን ትመስላለች። እሳት የማታዩበት ክፍል ነዶ ነዶ አመዱ የቀረ ቅንጡ መንደርና ሌላው ተራራማ ክፍል ነው።
ከቀናት በፊት በነዚህ ቤቶች አዲስ አመቱን አስመልክተው እቃ ለመቀየርና ቤት ለማሳመር ሲደምሩ ሲቀንሱ የነበሩ ሰዎች ነበሩባቸው። ዛሬ ያ ሁሉ ሽርጉድ ቀርቶ በመቶ ሺዎች ስደተኛና መኖሪያ አልባ ሆነዋል።    
አለን ያልነውና የተመካንበት ሁሉ በቅፅበት ዶግ አመድ በሚሆንበት  በዚህ አለም ከእግዚአብሔር በቀር ሊመኩበት የሚችሉት አንዳች ነገር የለም።
🟢🟡🔴
ጥር 2 | በዚህች ቀን፦

በግፍ የተገደለው የጻድቁ አቤል መታሰቢያ ነው።


ይኸውም የአባቶች ሁሉ አባት የአዳም ልጅ ነው። አቤልና ቃየል በጎለመሱ ጊዜ ቃየል መንታውን ኤልዩድን ያገባ ዘንድ ፈለገ። መልኳ ያማረ ነበርና።

አዳምም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ ጭንቅ ሆነበት። ቃየልንም አብራህ የተወለደች እኅትህን ታገባት ዘንድ አይገባህም። አለዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቅርቡና መሥዋዕቱን ለተቀበለው ይሁን አለው።

እግዚአብሔርም የአቤልን መሥዋዕት ተቀበለ። የአቤል መንትያ እኅቱ አቅሌማ መልኳ ያማረ አልነበረምና ቃየል በቅናት ወንድሙ አቤልን ገደለው።


በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ጥር 2 የታላቁ ቅዱስና ሊቀ ሰማዕታት ማር ጊዮርጊስ የልደት በዓሉ ነው፡፡

አባቱ ዘሮንቶስ/አንስጣስዮስ እናቱ ቴዎብስታ/አቅሌስያ ይባላሉ።


ስንክሳሩ በአጭሩ ‹‹የሕርቃሎስም ልጅ ሕልምን የምትተረጉም ነቢይት ሳቤላ በሰማዕትነት ዐረፈች›› በማለት የጠቀሳት #ቅድስት_ሳቤላ_ሰማዕት ዕረፍቷ ነው፡፡

ከክርቶስ ልደት 500 ዓ/ዓ በፊት የተነሣች፣ እስራኤላዊ የዘር ሐረግ ህርቃል ህርቃሎስ ለሚባል ሰው ልጁ የሆነች፣ ኤፌሶናዊት 292 እድሜ የኖረች ነቢይት ነች። ከፈጣሪዋ ህልም የመተርጎም  ጥበብ የተቸራት ነች።

በሮሙ ንጉሥ እስክንድሮስ ዘመን መቶ ጠቢባነ ሮም ተመሳሳይ ህልምን 9 አይነት ፀሐዮችን አይተው የሚተረጉምላቸው አጥተው፡፡ ዝናዋን የሚያውቁ ከኤፌሶን አስጠርተዋታል፡፡ እርሷም ፈጣሪዋን በጸሎት ጠይቃ ህልማቸውን በዝርዝር ተርጉማላቸዋለች፡፡

ከ9ኙ ፀሐይ በ6ተኛው በደንብ ሐተታ እንደሰጠችበት ይነገራል ይሄውም ሰለነገረ ልደቱ እና ሞቱን ነግራቸዋለች፡፡

የኢትዮጵያን ትንሣኤንና ደጉን ንጉሥ ቴዎድሮስም በዚሁ ተጠቅሷል።


በጸሎቷ ይማረን፤ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ያቅርብልን፨

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
በ11 ቀበሌዎች የ770 አርሶ አደሮች ሰብል ወድሟል።

<<ከተቃጠለው ሰብል ውጭ ሌላ ምንም አዝመራ የለንም>>ተጎጅ አርሶ አደሮች
በአንድ ሰዓት ውስጥ ሶስት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ‼️
ዛሬ አዳሩን ከተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል ከፍተኛ 5.2 የተመዘገበ ሲሆን የተከሰተው ከለሊት 9:19 ከአዋሽ በሰሜን በ30ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው፣በዚህም አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ የተባለ ንዝረት ተሰምቷል።
ዛሬ ለሊት የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ:-👇
1. ለሊት 8:42 በአፋር ገርባ ከአዋሽ ሰሜናዊ ምዕራብ በ12ኪ.ሜ ርቀት በሬክተር ስኬል 4.60 የሆነ

2. ለሊት 8:58 አማራ ክልል ብጨንቀኝ በሬክተር ስኬል 4.50 የሆነ

3. ለሊት 9:19 ከአዋሽ ባስተሰሜን በ30ኪ.ሜ ርቀት የምሽቱ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.20 የሆነ

4. ለሊት 10:50 ከመተኻራ በደቡባዊ ምስራቅ በ25ኪ.ሜ ርቀት በሬክተር ስኬል 4.30 የሆነ

5. አሁን ጧዋት 12:22 ከመተኻራ በደቡብ አቅጣጫ በ28ኪ.ሜ ርቀት በሬክተር ስኬል 4.40 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግቧል።
አዩዘሀበሻ
2025/01/12 12:45:37
Back to Top
HTML Embed Code: