Telegram Web Link
የእህታችን ምፅላለ መድህን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስ አበባ
21/3/2017

👉 ሰባቱም መላእክት የቁጣውን ፅዋ ሁሉ ሊያፈሱት በፍጥነት ወደ ምድራችን ገሰገሱ። እንግዲህ ወዴት መሸሸግ ይቻልሃል? የመከርነው የዘከርነው የጮህነው ከዚህ እቶን ላይ ወድቀህ ከነዘር ማንዘርህ እንዳትጠፋ ነበር፤ አልሆነም! እኔም ምናምንቴው በፊቱ የታመንሁ የሥላሴ ባሪያ ለ15 ዓመታት ጮኬ ለፍልፌ አቅሜን ሁሉ ጨረስኩ ዛሬ የምነግርህ የሥላሴ ብርቱ ትእዛዝ ሆኖብኝ እንጂ ዳግም ወደእናንተ መድረስ አልሞክረውም ነበር። ስለ አባቴ ፍቅር ስለአባታዊ ትእዛዙ ስል ስለእናቴ ድንግል ስል መርዶህን እነግርሃለሁ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 6 የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም
የእህታችን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
21/3/2017

👉 ከዚህ  ደብዳቤ  ጋር  በልዑል  ፊት  ከከበሩት  ዋና  ዋና  ሊቃነ  መላእክቶች  ---  ሊቀ  መላእክት  ቅዱስ  ሚካኤል፣ ሊቃነ  መላእክት  ቅዱስ  ገብርኤል፣  ሊቃነ  መላእክት  ቅዱስ  ሩፋኤል  ትእዛዙንና  ውሳኔውን  ለመፈጸም  በኃያል ሙላት ተነቃንቀዋል።

👉 የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ተጻፈ በ7/5/2012 ዓ.ም
የወንድማችን ገብረ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት።
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
21/03/2017 ዓ.ም

👉 እንግዲህ ከጠረጋው ቁጣ ማን ይተርፋል? ማንስ ወደትንሣኤው ዘመን ይሻገራል? ግልጽ ነው ደግሜ እላለሁ ለአውሬው ያልሰገደ ምልክቱንም ያልወሰደ ያላመለከ ተሻጋሪ ነው። ኃብትንም እውቀትንም ጉልበትንም ማምለክ ሌላው የአውሬው አምልኮትም እንደሆነ እንወቅ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 6 የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም
ተው ዓለም ተመለስ 16k
ዝማሬ ዳዊት
#ተው_ዓለም_ተመለስ

ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
በቁጣ መዓቱ ይቀጣሃል ጌታ ይቀጣሃል ጌታ

ትውልዱ ተመታ በታላቅ በሽታ /፪/
ኧረ በልክ ይሁን ጭፈራና ደስታ /፪/
በማዕበል በጎርፍ እያየህ ሲቀጣ/፪/
አሁንም ተመለስ የከፋ ሳይመጣ /፪/
#አዝ
ነነዌን ሊያጠፋ የወረደው እሣት /፪/
አንተን እዳይመታህ ተነሳ ለጸሎት/፪/
ዓለም ብትሰጥኽ አንተ እድትተጋ /፪/
ሀልወተ እግዚአብሔር እንደምን ይዘንጋ
#አዝ
ችግር ለበዛበት እጅግ ለታወከው/፪/
አምላክ መሐሪ ነው ለተንበረከከው/፪/
የዓለም መድሐኒት የዓለሙን ቤዛ /፪/
ጠይቀው ምሕረትን ሠው ሆይ ልብ ግዛ
#አዝ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
በቁጣ መዓቱ ይቀጥሃል ጌታ ይቀጣሃል ጌታ።

         ሊቀ መዘምራን
     ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።

👇👇👇👇👇👇
📌 በዚህ የኢትዮጵያ ክፍል የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን በማን ትዕዛዝ እየታረዳችሁ፣ እየተፈናቀላችሁና እየተሳደዳችሁ እንዳለ ከዚህ ዜና ልትረዱት ይገባል ። ከዚህ በተጨማሪ መጪውን ጊዜም ልታስተውሉ ይገባል !

📌 ትላንትም ዛሬም ለኢትዮጵያ ጥፋት አንድ ነበሩ ነገም አንድ ናቸው። የምንሰማው ሁሉ የማስመሰል ስምምነት ነው።

(ከራስ ጋር መፈራረም ብላችሁ ቁጠሩት!)
አዲስ አበባን ዛራም ጎሮ አካባቢን አቃጥለውታል
ዳንኤል ክብረት (ጋኔል ክብሪት) ፤ አስቀድሞ ስለራሱ እንዲኽ ተንብዮ ነበር!
🟢🟡🔴
ኅዳር 25 | #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ሰማዕትነት ተቀበለ።

#ቅዱስ_መርቆሬዎስ ስሙ ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ይባላል። ትርጉሙም "የአብ ወዳጅ" ማለት ነው። በኋላ ሊቃውንት መርቆሬዎስ  አሉት። መርቆሬዎስ ማለት ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ (የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ) ነው።

የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ደግሞ ለሰማዕቱ ያላቸውን ፍቅራቸውን ጨምረው አቡ ሰይፊን (Abu Seifin- ባለ ሰይፉ አባት) ይሉታል።

ቅዱስ ገብርኤል በርበሮችን እንዲያጠፋ ከንጉሥ ዳኬዎስ ጋር ሲዘምት ሰይፍ ያቀዳጀው፣ ገጸ ከልብ (ፊቱ የውሻ፣ መኻሉ የሰው፣ እግሩ የአንበሳ፣ ታቹ የጋለ ነሐስ የሆነ ፍጡር) ጓደኛው የሆነ፣ እርሱ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ጥቁሩ ፈረሱ ወንጌልን የሰበከ ቅዱስ ነው።

ከበርበሮች ጋር ጦርነቱ በእግዚአብሔር ኃይል ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ። በዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጥቶ ለአማልክት ዕጣን አሳርግ እና ስገድ አለው።

በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው፦ "እኔ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም! ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም።"

ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፉት ዘንድ አዘዘ።

በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት
ፈርቶ ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠሪያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ።

ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ።

◦◦🌿◦◦
T.me/Ewnet1Nat
🇨🇬 ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ 🇨🇬
            ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
           
             ▰  #የፍቅር_ዕዳ_አይኑርባችሁ !  ▰
  🇨🇬 የኢ.ዓ.ብ የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት ፫ 🇨🇬
           | 🕛 | ከ፶፯ ደቂቃ ከ፲ ሰከንድ ጀምሮ

× × ×
[ሮሜ 13፥8] የፍቅር ዕዳ ሲባል ምን ማለት ነው?

አዎ!
ወንድምን መጥላት፣ መቀየም፣ ወንድማችን ላይ ቅሬታን  ማሳደር፣ ማዘን፥ መከፋት በሰውዬው ላይ ፣ ቂምን ቋጥሮ መቆየት፣ ጥላቻን ማሳደር፣ እንቅፋትን ማኖር፣ ክፉ ክፉውን መናገር፣ በጎን አለማሰብ፣ ስለጭንቀቱ፥ ስለማዘኑ፥ ስለ መከፋቱ አለማዘን፣ አለመርዳት፣ በቅንነትና በፍቅር አለመመልከት እነዚኽ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር አያቀራርቡም።

ስለዚኽ እነዚኽን ሁሉ የምንሸከም ከኾነ #ዕዳ አለብን ማለት ነው።

ስለዚኽ የፍቅር ዕዳ እንዳይኖርብን ባልጀራችንን መውደድ አለብን። ቢጠሉንም እንኳ፥ ጠላቶቻችን እንኳ ቢኾኑ ሰው ናቸውና ልንወዳቸው ይገባል።

ወደው አይደለም እኮ ክፉ ሥራ የሚሠሩት ወገኖቼ! በላያቸው ላይ የሚያርፈው፥ በሥጋቸው ላይ የሚሠለጥነው ክፉ መንፈስ ነው ወደ ክፋት እየገፋ ፣ ወደ ጥፋት እየገፋ ለጥፋት የሚዳርጋቸው።

#እነሱ_እኮ_ደምና_አጥንት_ናቸው#ዲያቢሎስ_ግን_መንፈስ_ነው። በእነርሱ ላይ አድሮ እኛን የሚዋጋ፣ እኛ ወደ ክፉ ሥራ ለመግፋት የሚያንደረድረን፣ ቂም በቀል ክፋት በልባችን እንድናሳድር በእነሱ ላይ አድሮ እኛን የሚዋጋ ዲያቢሎስ መኾኑን ልናምን ልናውቅ ልንረዳ ይገባል።

#መሠረታዊ_ጠላታችን_ማን_ነው
▸ ዲያቢሎስ ነው! የጨለማው ገዢ ነው! ክፉው መንፈስ ነው!

ስለዚኽ ወንድምኽን አትቀየመው! እኅትኽንም አትቀየማት! አንዳንድ ጊዜ በደካማነታቸው በእምነታቸው አለመጠንከር ወይ ሙሉ በሙሉ በዲያቢሎስ ተሸንፈው ባንተ ላይ ክፉ ሊሠሩ ይችላሉ።

ግን እዘንላቸው!
አንተስ አስተዋይ ኾነኻል፤ ነጻ ወጥተኻል። እውነትን መረዳት ችለኻል። በብርሃን ውስጥ ትመላለሳለኽ። ስለዚኽ በጨለማ ለታሰረው ወንድምኽ ልታዝንለት ይገባል!
~
www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
"በኢትዮጵያ ትንሣኤ የጸና ተስፋ ይኑርህ።

በቃ!! የምንመክርህ ይኸንን ነው። እኛ ያልነው ይኸንን ነው። ሌላ 'ምንለው ነገር የለንም።
"

🟢🟡🔴 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን 
መግለጫ እና የሉቃስ ወንጌለ ትምህርት ክፍል 13(ሀ) ላይ የተወሰደ።
🟢🟡🔴
ኅዳር 25 | ኢትዮጵያዊው ሰማዕት አቡነ ሚካኤል ዐረፉ።

እኚህ ቅዱስ አባት ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ቤተ ክርስቲያን ከአቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት ጋር የተጋደሉ ናቸው። ከመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት አንዱ ናቸው።

ኮሎኔል ማልታ እሥረኛውን ጳጳስ ከእሥር ቤት አስመጥቶ ሕዝቡ በተሰበሰበበት አደባባይ አቀረባቸው። «ለኃያሉ የኢጣሊያ መንግሥት ለመገዛት ቃል ይግቡና ሕዝቡም እንዲገዛልን ይስበኩልን። ይህንን ካደረጉ እንለቅዎታለን።» በማለት በልዩ ልዩ መደለያ ጭምር አባበሏቸው።

‹እኔ የማምነው በአንድ እግዚአብሔር ነው። የምቀበለው የነፃነታችን ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ብቻ ነው። ኢጣሊያ የሚባል ገዥ አላውቅም።

ለፋሽስት ኢጣሊያ የተገዛ እንደ አርዮስ የተረገመ ይሁን። እንኳንስ ሕዝቡ ምድሪቱም እንዳትገዛላቸው አውግዣለሁ።›
በማለት በዚያ ለተሰበሰበው ሰው ሁሉ ውግዘታቸውን አሰሙ።

የጠላት ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማልታ የብፁዕነታቸው የዓላማ ፅናትና ቆራጥነት ተገነዘበ። እሳቸውን መሸንገል እንደማይቻል ሲያረጋግጥ በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ወሰነ።

ከጎሬ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በታች አሮጌው ቄራ አጠገብ ጉድጓድ ተቆፈረ።

በዚህን ጊዜ አቡነ ሚካኤል ለጥቂት ደቂቃዎች ፀሎት እንዲያደርጉ ጠይቀው ተፈቀደላቸው። ጸሎታቸውን
አድርሰው ሲያበቁ መስቀላቸውን በግንባራቸው አድርገው ‹በል እንግዲህ የፈለከውን አድርግ› አሉ።

የወታደሮቹ አዛዥ የተኩሱን ትዕዛዝ ሰጠ። ከእነ አቡነ ሚካኤል ፊት ለፊት በተርታ ተደርድረው በአባታችን እና በአርበኞች ላይ ጠመንጃቸውን ያነጣጠሩት የጠላት ወታደሮች በእሩምታ ተኮሱ። ሰማዕትነታቸውንም ፈጸሙ።

የቀብራቸውም ሥነ ሥርዓት በአግባቡ አልተፈፀመም። አቶ ወልደአብ የተባሉ የአገር ፍቅር የነበረባቸው የአካባቢው ነዋሪ ናቸው በሌሊት የቀበሯቸው።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2025/01/10 01:06:46
Back to Top
HTML Embed Code: