Telegram Web Link
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

🥢 ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ የትዕቢተኛዎችንም ኵራት አዋርዳለሁ።
ትንቢተ ኢሳያስ 13፡11

በ 21/3/2017 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት ይለቀቃል 👇👇👇
20241112_020535.aac
2.3 MB
የወንድማችን ገብረ ሥላሴ እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ናዝሬት
21/3/2017
ክፍል ፩

👉 ጊዜ  የለም  አብቅቷል  መሽቶባችኋል።  አሁን  ከፊታችሁ  ሁሉም  ነገር  ተጭኖ  መጥቷል።  መግቢያ  የለም። መደበቂያ በፍጹም የለም አበቃ!!

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 47የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም
20241112_020858.aac
9.4 MB
የወንድማችን ገብረ ሥላሴ እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ናዝሬት
21/3/2017
ክፍል ፪

👉 በዚህም  መሰረት  ለወዳጆቻቸው በየግንባራቸው  ላይ  ምልክት  ተደርጓል  ፡፡  ይህንን  የሚያዩት  ለቁጣው  ጠረጋ  እሳት  ለብሰው  እሳት  ጎርሰው  ምድርን እያንቀጠቀጡ  የሚመጡት  ቀሳፊ  መላእክት  መቅሰፍትን  ያዘሉ  ፍርድና  ትእዛዝ  ፈፃሚዎች  ተግባር  ላይ  ሆነው  ያለ  ምሕረት ምልክት  አልባ  የሆኑትን  እንደተፈረደባቸው  እንደተወሰነባቸው  እንደታዘዘባቸው  የአፈፃፀም  እርምጃ  ሲያከናውኑ  ሲያዩ  ብቻ ነው  ፡፡  በጊዜውና  በሰአቱ  የታዘዙበትን  ሲፈፅሙ  ብትጮህ  ብትለምን  እንባህን  እንደጎርፍ  ብታፈስ  ደምም  ብታነባ  እሚሰማህ የለም  ቀሳፊዎቹ  የመጡት  የአምላካቸውን  ትእዛዝ  ለመፈፀም  ተግባራዊ  ለማድረግ  እንጂ  ሊማለዱ  ሊያማልዱ  አይደለም  ፡፡

👉 ከኢትዮጵያ  የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት በአብርሃሙ ሥላሴ ፈቃድ የወጣ                                                መልእክት አስር ገጽ 30 የተወሰደ
ተጻፈ 7/5/2015 ዓ.ም
20241102_214907.aac
12.1 MB
የወንድማችን ሰይፈ ሚካኤል እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስ አበባ
21/3/2017

👉 ወገኖቼ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! አዎን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች! እንዲሁም ይህን መልእክትም ሆነ የቀደሙትን ሰባት መልእክታት ለመስማት ዕድሉ የገጠማችሁ፥ ይህን ታላቅ ምሥጢር የእግዚአብሔርን እውነት ለመገንዘብ የሚያስችል ልቡና ይስጣችሁ! መቼም እግዚአብሔር ልቡናችሁን ካላበራው የቀደመው እባብ ሐሰተኛው ነቢይ ዘንዶው ያላደነቆረው፣ ወደራሱም ያላካተተው የአዳም ዘር የለምና! ጥቂቶቹ በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ የተመረጣችሁ የከበራችሁ ታላቁን መከራ የታገሳችሁ ልትፅናኑ ይገባችኋል። ዛሬ ቀናችሁ ሊሆን ነውና! ብርሃናችሁ ሊበራ ድካማችሁ ሊታይ ሸክማችሁ ሊራገፍ መድኃኔዓለም ሊክሳችሁ ነውና! አመስግኑ!

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 9 የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም
የእህታችን ምፅላለ መድህን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስ አበባ
21/3/2017

👉 ሰባቱም መላእክት የቁጣውን ፅዋ ሁሉ ሊያፈሱት በፍጥነት ወደ ምድራችን ገሰገሱ። እንግዲህ ወዴት መሸሸግ ይቻልሃል? የመከርነው የዘከርነው የጮህነው ከዚህ እቶን ላይ ወድቀህ ከነዘር ማንዘርህ እንዳትጠፋ ነበር፤ አልሆነም! እኔም ምናምንቴው በፊቱ የታመንሁ የሥላሴ ባሪያ ለ15 ዓመታት ጮኬ ለፍልፌ አቅሜን ሁሉ ጨረስኩ ዛሬ የምነግርህ የሥላሴ ብርቱ ትእዛዝ ሆኖብኝ እንጂ ዳግም ወደእናንተ መድረስ አልሞክረውም ነበር። ስለ አባቴ ፍቅር ስለአባታዊ ትእዛዙ ስል ስለእናቴ ድንግል ስል መርዶህን እነግርሃለሁ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 6 የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም
የእህታችን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
21/3/2017

👉 ከዚህ  ደብዳቤ  ጋር  በልዑል  ፊት  ከከበሩት  ዋና  ዋና  ሊቃነ  መላእክቶች  ---  ሊቀ  መላእክት  ቅዱስ  ሚካኤል፣ ሊቃነ  መላእክት  ቅዱስ  ገብርኤል፣  ሊቃነ  መላእክት  ቅዱስ  ሩፋኤል  ትእዛዙንና  ውሳኔውን  ለመፈጸም  በኃያል ሙላት ተነቃንቀዋል።

👉 የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ተጻፈ በ7/5/2012 ዓ.ም
የወንድማችን ገብረ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት።
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
21/03/2017 ዓ.ም

👉 እንግዲህ ከጠረጋው ቁጣ ማን ይተርፋል? ማንስ ወደትንሣኤው ዘመን ይሻገራል? ግልጽ ነው ደግሜ እላለሁ ለአውሬው ያልሰገደ ምልክቱንም ያልወሰደ ያላመለከ ተሻጋሪ ነው። ኃብትንም እውቀትንም ጉልበትንም ማምለክ ሌላው የአውሬው አምልኮትም እንደሆነ እንወቅ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ገጽ 6 የተወሰደ
ተጻፈ ታህሳስ 21 2013 ዓ.ም
ተው ዓለም ተመለስ 16k
ዝማሬ ዳዊት
#ተው_ዓለም_ተመለስ

ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
በቁጣ መዓቱ ይቀጣሃል ጌታ ይቀጣሃል ጌታ

ትውልዱ ተመታ በታላቅ በሽታ /፪/
ኧረ በልክ ይሁን ጭፈራና ደስታ /፪/
በማዕበል በጎርፍ እያየህ ሲቀጣ/፪/
አሁንም ተመለስ የከፋ ሳይመጣ /፪/
#አዝ
ነነዌን ሊያጠፋ የወረደው እሣት /፪/
አንተን እዳይመታህ ተነሳ ለጸሎት/፪/
ዓለም ብትሰጥኽ አንተ እድትተጋ /፪/
ሀልወተ እግዚአብሔር እንደምን ይዘንጋ
#አዝ
ችግር ለበዛበት እጅግ ለታወከው/፪/
አምላክ መሐሪ ነው ለተንበረከከው/፪/
የዓለም መድሐኒት የዓለሙን ቤዛ /፪/
ጠይቀው ምሕረትን ሠው ሆይ ልብ ግዛ
#አዝ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
በቁጣ መዓቱ ይቀጥሃል ጌታ ይቀጣሃል ጌታ።

         ሊቀ መዘምራን
     ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።

👇👇👇👇👇👇
📌 በዚህ የኢትዮጵያ ክፍል የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን በማን ትዕዛዝ እየታረዳችሁ፣ እየተፈናቀላችሁና እየተሳደዳችሁ እንዳለ ከዚህ ዜና ልትረዱት ይገባል ። ከዚህ በተጨማሪ መጪውን ጊዜም ልታስተውሉ ይገባል !

📌 ትላንትም ዛሬም ለኢትዮጵያ ጥፋት አንድ ነበሩ ነገም አንድ ናቸው። የምንሰማው ሁሉ የማስመሰል ስምምነት ነው።

(ከራስ ጋር መፈራረም ብላችሁ ቁጠሩት!)
አዲስ አበባን ዛራም ጎሮ አካባቢን አቃጥለውታል
ዳንኤል ክብረት (ጋኔል ክብሪት) ፤ አስቀድሞ ስለራሱ እንዲኽ ተንብዮ ነበር!
🟢🟡🔴
ኅዳር 25 | #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ሰማዕትነት ተቀበለ።

#ቅዱስ_መርቆሬዎስ ስሙ ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ይባላል። ትርጉሙም "የአብ ወዳጅ" ማለት ነው። በኋላ ሊቃውንት መርቆሬዎስ  አሉት። መርቆሬዎስ ማለት ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ (የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ) ነው።

የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ደግሞ ለሰማዕቱ ያላቸውን ፍቅራቸውን ጨምረው አቡ ሰይፊን (Abu Seifin- ባለ ሰይፉ አባት) ይሉታል።

ቅዱስ ገብርኤል በርበሮችን እንዲያጠፋ ከንጉሥ ዳኬዎስ ጋር ሲዘምት ሰይፍ ያቀዳጀው፣ ገጸ ከልብ (ፊቱ የውሻ፣ መኻሉ የሰው፣ እግሩ የአንበሳ፣ ታቹ የጋለ ነሐስ የሆነ ፍጡር) ጓደኛው የሆነ፣ እርሱ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ጥቁሩ ፈረሱ ወንጌልን የሰበከ ቅዱስ ነው።

ከበርበሮች ጋር ጦርነቱ በእግዚአብሔር ኃይል ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ። በዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጥቶ ለአማልክት ዕጣን አሳርግ እና ስገድ አለው።

በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው፦ "እኔ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም! ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም።"

ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፉት ዘንድ አዘዘ።

በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት
ፈርቶ ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠሪያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ።

ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ።

◦◦🌿◦◦
T.me/Ewnet1Nat
2024/12/28 04:03:39
Back to Top
HTML Embed Code: