Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇨👨‍🚒 ኪቶ በከባድ የእሳት አደጋ ተውጣለች

የኢኳዶር ዋና ከተማ የሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ሲሆን እሳቱን ለመከላከል የእሳት አደጋ ሠራተኞች እና የጦር አውሮፕላኖች ተሰማርተዋል።
በትራፊክ አደጋ የ55 ሰዎች ሕይወት አለፈ። (updated)

ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ55 ሰዎች ሕይወት አለፏል፡፡በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ እንደገለጹት

አደጋው ዛሬ ቀን 7 ሠዓት ላይ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፈታታ ቀበሌ መከሰቱንም አረጋግጠዋል፡፡የተከሰተው አደጋ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
📌ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ !!! የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ !!

📎ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 9 ገፅ 57 - መጨረሻው፣ በድምፅ ካለው ክፍል 5 የተወሰደ።
@AlphaOmega930
@christian930

አዋጅ ! አዋጅ ! አዋጅ ! 
 ሁሉም የሰው ዘር በእግዚአብሔር ቅን ፍርድ የሚጎበኝበትና ፍርድን የሚቀበልበት ሰአት እነሆ ደረሰ ! 

የተዘጋጁ ! ንስሐ የገቡ ! በተዋህዶ እምነታቸው የፀኑ ከዚህ ዓለም ጉድፍ የተጠበቁ ታሰቡ የአባቶቻቸውን ዋጋ በዚህ ምድር ተክሰው ተወደው ሊፅናኑ ለእራት ተጠርተዋልና ስማ ! ኢትዮጵያ ታሰበች ! በታላቅ ተጋድሎዋ ድልን ነሳች ! ስማ ! የአዳም ዘር ሁሉ ስማ ! አድምጥ ! 
https://telegra.ph/ከኢትዮጵያ-የዓለም-ብርሃናዊ-መንግሥት-የወጣ-የአስቸኳይ-ጊዜ-አዋጅ-02-09

"⚡️INSTANT VIEW" በሚለው ገብተው ሁሉንም በትግስት ያንብቡ! ለሁሉም ሰው SHARE ያድርጉ!👇
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
" የሚሰማ ይስማ ! የማይሰማ አይስማ !"
Audio
የሐሙስ ውዳሴ ኪዳነ ምሕረት
Audio
መልከአ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
◦✞◦ እመቤቴ ሆይ፥ በቃል ኪዳንሽ ኃጢአቴን አስተሥርዪልኝ። #ያለ_ቃል_ኪዳንሽና #አዳኝ_ከሚሆን_ከክርስቶስ_መስቀል በስተቀር ከሲዖል የሚድን ሰው ከቶ አይኖርምና። ◦✞◦
[መልክዐ ኪዳነ ምሕረት ቁ. 16]
🌼🌼🌼
#እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ ቤተሰቦቼ፡፡
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
👆👆🏾👆🏽
የመስቀለ ኢየሱስ ቃልኪዳን በጥቂቱ
~ [ ድርሳነ መስቀል ]
       
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
መስከረም 17 | #በዓለ_መስቀል
🌼◦✞◦🌼

መስከረም ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ለከበረ መስቀል በዓሉ ነው። ይህም የጻድቁ ንጉሥ የቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ከተሠወረበት የገለጠችው ነው።

የጎልጎታን ኮረብታ በአስጠረገች ጊዜ የከበረ መስቀልን አገኘችው። ታላቅ ኮረብታም የሆነበት ምክንያት እንዲህ ነው፦

ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቃብሩና ከመስቀሉ የሚገለጡ ሁነው ሙታን ይነሡ ነበርና የጎበጡና በሽተኞች ሁሉ ይፈወሱ ነበር።

ስለዚህም አይሁድ ተቆጡ እንዲህም ሥርዓትን ሠርተው አዘዙ። "በይሁዳ አገር ሁሉና በኢየሩሳሌም ቤቱን የሚጠርግ ሁሉ ወይም አፈር ወይም ጉድፍ የሚጠርግ በናዝሬቱ ኢየሱስ መቃብር ላይ ይጥል ዘንድ" እንዲህም እያደረጉ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣች ድረስ ከሦስት መቶ ዓመት በላይ ኖሩ።

እርሷም በመጣች ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብርን እስከ አሳዩዋት ድረስ አይሁድን ይዛ አሠቃየቻቸው። ያንን ኮረብታም እስከ ጠረጉ ድረስ አስገደደቻቸው የከበረ መስቀሉም ከተቀበረበት ተገልጦ ወጣ።

ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራች። በዚች ቀንም አከበሯት። ለመስቀሉም በዓልን መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን አከበሩለት።

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በምሕረቱ አደረሳችሁ
🌼◦✞◦🌼
T.me/Ewnet1Nat
2024/09/27 17:25:02
Back to Top
HTML Embed Code: