Telegram Web Link
🇱🇧 🇮🇱 እስራኤል በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች ባደረሰችው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 37 መድረሱን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

💬 "በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች በተፈጸመው የአየር ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 37 ደርሷል" ሲል ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ቀደም ሲል እንዳስታወቀው በጥቃቱ ሶስት ህጻናትን ጨምሮ 31 ሰዎች ሞተዋል። ሌሎች 68 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

መስከረም 7 እና 8 ፔጀሮች እና ዎኪ ቶኪዎች በሊባኖስ የተለያዩ ክፍሎች ፈንድተዋል። እንደ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ገለጻ 37 ሰዎች ሲሞቱ ከ3,000 በላይ የሚሆኑት ቆስለዋል። ሄዝቦላ እና የሊባኖስ ባለስልጣናት ለጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል። እስራኤል በጥቃቱ እንደተሳተፈች ከማረጋገጥ ወይም ከመካድ ተቆጥባለች።
🇵🇱 ወደ 57,000 የሚጠጉ ፖላንዳውያን በአስከፊ ጎርፍ ሳቢያ በቀጥታ ጉዳት ደርሶባቸዋል

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት በ 749 የፖላንድ ከተሞች በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ በድምሩ 2.39 ሚሊዮን ሰዎች ተጎጂ ሆነዋል። ከእነዚህ ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት በጎርፍ ውሃ በቀጥታ ተጎድተዋል።

💬 "በአሁኑ ጊዜ ይህ ቁጥር 57,000 ደርሷል" ሲሉ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር  ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ጃን ግራቢክ ባደረጉት የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ ላይ ገልጸው፤ ቁጥሩ ቅድመ ግምት እንደሆነም ተናግረዋል።

በደቡባዊ ፖላንድ ያልተለመደ ኃይለኛ ዝናብ ወንዞች ከልክ በላይ እንዲሞሉ በማድረጉ ሳቢያ በትንሹ 20 ሰዎች ሲሞቱ 6,544 ያህሉ ደግሞ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። እስካሁን ድረስ 11,502 ባለ አንድመኝታ ቤቶች እና አፓርትመንቶች፣ 6,033 የቤተሰብ መገልገያዎች እና 724  እንደ ትምህርት ቤቶች፣ መንገዶች እና ድልድዮች ያሉ የህዝብ መገልገያዎች ተጎድተዋል ወይም ወድመዋል ሲሉ ጃን ግራቢክ ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጃፓን በ50 ዓመታት ውስጥ ባላየችው ጎርፍ ተመታች።

በከባድ ዝናብ ምክንያት በጃፓን ከ130,000 በላይ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው መሄድ ነበረባቸው

በጃፓን ኢሺካዋ ግዛት ውስጥ የሚገኙ 12 ወንዞች ከወዲሁ ሞልተው በመፍሰሳቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል። 

የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት በርካታ ቤቶች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል እንዲሁም በመሬት መንሸራተት ሳቢያ በርካታ ሕንፃዎችን ወድሟል። 

ሀገሪቱ እንዲህ ያለ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ ለ50 ዓመታት ገደማ አላየችም።
📹🇹🇩 በቻድ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ500 በላይ ሰዎች ሲሞት 1.7 ሚሊዮን ያህሉን ደግሞ ለጉዳት ዳርጓል

ከሀምሌ ወር ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በትንሹ 503 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ( ኦቻ) አስታውቋል።

📹🇹🇩 Flooding in Chad claims over 500 lives and affects 1.7 million

Since July, flooding has resulted in the deaths of at least 503 people in Chad, according to the United Nations Office for the Coordination of Humanitarian Affairs (OCHA).

The latest OCHA report also indicated that thousands of homes destroyed.

Urgent humanitarian aid is required, and authorities have cautioned that ongoing heavy rains and rising river levels could lead to further flooding.
Historic flooding engulfs Japan’s Ishikawa Prefecture

The region is experiencing its worst flooding since 1976, with 12 rivers overflowing and one person missing.

A state of emergency has been declared, and residents are being evacuated.

The flooding has left approximately 6,000 homes without power, and there are reports of potential landslides.
2024/09/23 04:22:11
Back to Top
HTML Embed Code: