Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️At least 40 people were killed and 60 injured in an Israeli air strike on a neighborhood in Khan Yunis in the Gaza Strip, Al Jazeera reports
🟢🟡🔴
መስከረም 1 | ርእሰ ዐውደ ዓመት

#ርእሰ_ዐውደ_ዓመት

በግእዝ ዐውደ ዓመት ይባላል - ርእሰ ዐውደ ዓመት - የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ በዓመቱ ውስጥ የሚውሉት በዓላትና አጽዋማት የሚወጡት መስከረም አንድን መነሻ አድርጎ ስለሆነ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ተባለ።

[🌼] በዚህች ቀን ከ9ኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ የከበረ መልአክ ራጉኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል መስከረም 1 ቀን ከሊቃነ መላእክት በብርሃናት ላይ የተሾመበት ዕለት ነው።

ግንቦት 1 ቀን ለታላቁ አባት ለሄኖክ ምሥጢራትን የገለጸበት በዓሉ ነው፡፡

በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ነቢዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡

እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው።

የመልአኩ ልዩ ቃልኪዳን
"የራጉኤል አምላክ ይቅር በለኝ በማለት አንዲት ቃልስ እንኳን ቢናገር እንደ ወዳጄ እንደ አብርሃም፣ እንደ ባለሟሌም እንደ ይስሐቅ፣ እንደ አከበርኩትም እንደ ያዕቆብ ክብርን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ። በራሱ ላይም አክሊል አቀዳጀዋለሁ። ረጅም ዘመናት ሰፊ፣ ወራትም እሰጠዋለሁ" ሲል ቃሉን ሰጥቶታል፡፡

[🌼] ዳግመኛም በዚህች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ሐዋርያ #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ በአሸዋ ከረጢት ውስጥ ተከቶ ወደ ባሕር በመጣል ምስክር ሆኖ ዐረፈ።

[🌼] በዚችም ዕለት #ጻድቁ_ኢዮብ በፈሳሽ ውኃ ታጥቦ ከደዌው ሁሉ ተፈወሰ።

[🌼] ይህች ቀን የታላቁ የቊልዝም ሰው የሆነ ፍጹም ጻድቅ፣ ሰይጣንን አስሮ ዐሥራ አራት ሰው ሊይዙት የማችሉትን ደንጊያ ያሸከመው #የአባ_ሚልኪ የዕረፍት በዓሉ ነው።

#እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
☑️ ፳፻፲፯ ዓ.ም [ ዘመነ ማቴዎስ ሐዋርያ]

"እውነትን አፍቅራት፤ አንግሣትም!"
"ምስክርነታችን ለተዋሕዶና ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ነው!"
"2017ም እንደ ባለፉት አመታት እውነትን ብቻ በይፋ እንመሰክራለን!"
"እንኳን አደረሳችሁ የገጻችን ተከታታይ የሆናችሁ እንቁ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እንዲሁም ቅን የዋሕ ትሑት ኢትዮጵያዊያን የተዋሕዶ ልጆች"
"አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ"

«ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ። እንሆ፥ በቶሎ እመጣለኹ፥ ለያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋራ አለ።  አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ዃለኛው፥ መዠመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።

የዮሐንስ ራዕይ 22፥11-14

🟢
www.tg-me.com/AlphaOmega930
🟡
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🔴
www.tg-me.com/aleqayalew
Audio
ድርሳነ ቅዱስ ራጉኤል ዘወርኃ መስከረም
Audio
መልክአ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
Audio
የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት እና ማሳሰቢያ
ከራዕይ ዮሐንስ 20
መስከረም/1/2017 ዓ.ም
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
እነሆ መድኃኒት ፤
የኃጢአት ስርየት ፤
መስከረም ኹለት፤
በዮሐንስ ምህረት።

የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ከፈጣሪው የተቀበለው ቃልኪዳን፦

{🌼} የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ገድል ሲነበብ ውኃ አምጥቶ በበላዩ ላይ አንብቦ፣ አስነብቦ፣ የገድሉ መጽሐፍ የተነበበበትን ውኃ የተጠመቀውን፥

በሚጠመቁ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ ወደርሱ መጥቶ ፊቱን በትምእርተ መስቀል አርአያ በእርሱ ስም ዮሐንስ ብሎ ያትመዋል።

እስከ ሰማኒያ ዓመት የሠራው ኃጢአቱ ቀርቶለት ይሠረይለታል።
{🌼} በወር በወሩ መጠመቅ ባይቻለው መስከረም ሁለት ቀን ይጠመቅ የሠራው ኃጢአቱ ሁሉ ፈጽሞ ይሠረይለታል፡፡

#በእምነት_ተጠቀሙበት !!

www.tg-me.com/Ewnet1Nat

https://www.tg-me.com/christian930/5498
🟢🟡🔴
መስከረም 2 | የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ #አጥማቂው_ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው፦

ቅዱስ ዮሐንስ ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር። ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች። መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች። ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።

ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት። እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው።

ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ፤ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ። ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጧት። እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች።

በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።

ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም አለች። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

#እንኳን_አደረሳችሁ
                  ◦🌿🌼🌿
2024/09/24 12:24:07
Back to Top
HTML Embed Code: