Telegram Web Link
📌 «ፍርዱ መጥቶ አጥራቸውን ነቅንቋል፡፡ ጥበቃውን አንሥቷል፡፡ አሁን ቤተክርስቲያን ጠባቂ የለም፡፡ እግዚአብሔር አንሥቷል፡፡ ባዶ ነው አጥር የላቸውም፡፡ እግዚአብሔር ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይታጋ የለም፡፡ አዎ ዝምብለው ነው አሁን ታዯቸዋላችሁ አሁን ትንሽ ቆይቶ ደግሞ የሚሆነውን ዝም ብላችሁ በትዕግሥት ከቆያችሁ ሁሉንም ታዩታላችሁ ፡፡ አንዲቷም ቃል ሳትቀር ትፈጸማለች ።
አንዲቷም ቃል !

እግዚአብሔር እውነት ላይ አላግጦ ቤቱን አጥፍቶ የእግዚአብሔርን ዓይን የመውጋት ያህል ልጆቹን በአውሬ አስበልቶ ባዶ ሜዳ ላይ ጥሎ እኖራለሁ ብለው ይደክማሉ፡፡ በቁጣ ላይ ቁጣውን እየጨመሩ የእግዚአብሔርን ቁጣ የበለጠ እያጋሉት እየሄዱ ነው ያሉት ፡፡»

⚡️ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
መግለጫ እና የሉቃስ ወንጌል ትምህርት
ክፍል 11 (ሀ) ላይ የተወሰደ፡፡
#ጥንቃቄ_ይኑረን

“... ወዮልህ አስጥላለሁ ብለህ እጅህን ምትሰድ፡፡ ተጠንቅቀህ ኑር፡፡ ተጠንቅቀህ ተጓዝ፡፡ እግዚአብሔር የፈረደበትን አንተ አዳኝ ኾነህ ምትቆምና እከላከላለሁ ምትል አብረህ ነው ምትቀጣው፡፡ በእግዚአብሔር ፍርድ ውስጥ እጅ መስደድ አይቻልም፡፡ እንዲያውም አንተ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ ኾነህ ነው መቆም ያለብህ ለትዕዛዙ፤ ለቃሉ፤ ለፍርዱ፡፡ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ በእግዚአብሔር ቃል ላይ በትዕዛዙም በሥርዓቱም በሁሉም ላይ ሲያላግጥ ሲያፌዝ የኖረ ሕዝብ፣ በእሳት ሲያዝ ሲቀጣ ለፍርድ ሲጣል፣ አዛኝ አንጓች ኾነህ እንዳትቆም ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጣሪ በላይ አንተ እሱ የፈጠረው አምላክ ከሚራራለት በላይ አንተ ርህሩህ ኾነህ ልትቀርብ አይገባህም፡፡ ምናደርገውን አስተውለን ማድረግ ይገባናል ወገኖቼ፡፡  ...”

ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሐዋርያት ሥራ ትምህርት ክፍል 8 (ሀ) ላይ የተወሰደ።

🟩
#ስለሁሉም_የልዑል_እግዚአብሔር_ቅን_ፍርድ_ደስተኞች_ልንሆን_ይገባናል !
🟨
#ስለሁሉም_የልዑል_እግዚአብሔር_ቅን_ፍርድ_አመስጋኞች_ልንሆን_ይገባናል !
🟥
#ስለሁሉም_የልዑል_እግዚአብሔር_ቅን_ፍርድ_ልባችንን_ልናጸናና_ልናጽናና_ግድ_ይለናል !

☀️ በአቅም ላይ የተመሠረተና ሁሉን አቀፍ የሆነ፦
⚡️ መንፈሳዊ
⚡️ ስነ ልቦናዊና
⚡️ ሥጋዊ
ዝግጅት ሊኖረን ያስፈልጋል ።


www.tg-me.com/Ewnet1Nat
▮ወርኀ ጳጉሜን▮

እግዚአብሔር አዝማናትን የፈጠራቸው ለሰው ልጆች ጥቅም መሆኑ ይታወቃል። እርሱ ባወቀ፣ በረቂቅ ሥልጣኑ ዓለምን ፈጥሮ፣ ጊዜያትን እንዲከፍሉ ብርሃናትን (ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብትን) ፈጥሮልናል።

ጊዜያትንም በደቂቃ፣ በሰዓት፣ በቀን፣ በሳምንት፣ በወር፣ በዓመታት፣ በኢዮቤልዩ፣ በክፍላተ ዘመናት እንድንቆጥር ያስተማረንም እርሱ ነው። የሰከንድ 540,000 ክፋይ ከሆነችው 'ሳድሲት' እስከ ትልቁ ቀመር (532 ዓመት) ድረስ እርሱ ለወደዳቸው እንዲያስተውሉት ገልጧል።

በየዘመኑም በቅዱስ ድሜጥሮስ፣ በቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ፣ በቅዱስ አቡሻኽር እና በሌሎቹም አድሮ መልካሙን አቆጣጠር አስተምሯል። ሃገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ የአሥራ ሦስት ወራት የፀሐይ ጸጋ ያላት፣ አራቱ ወቅቶች የተስማሙላት ናት።

ሌላው ዓለም ወሮችን 31,30,29 (28) እያደረገ ሲጠቀም እኛ ግን እንደ ኖኅ [ዘፍ 8፥1-15] አቆጣጠር ወሮችን በሠላሳ ቀናት ወስነን፣ ጳጉሜንን ለብቻዋ እናስቀምጣለን።

◆ ጳጉሜን 'ኤጳጉሚኖስ' ከሚል የግሪክ (ጽርዕ) ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም 'ትርፍ፣ ጭማሪ' እንደ ማለት ነው።

የወርኀ ጳጉሜን አምስቱ/ስድስቱ ቀናትም ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገሪያ እንደ መሆናቸው ብዙ ምሳሌያት (ምሥጢራት) አሏቸው። ዋናው ግን በዚህ ጊዜ ዳግም ምጽዓት (የክብር ትንሣኤና የውርደት ትንሣኤ ቀን) ይታሠባል።

▸ ጊዜውንም በጾምና በጸሎት ሊያሳልፉት ይገባል። ግን በፈቃድ ነው እንጂ የግዴታ አይደለም።
በኢንግሊሽ ቻናል ላይ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን የሆኑ ስደተኞች ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

የፈረንሳይ ባለስልጣናት ስደተኞችን ጭና የነበረችው ጀልባ ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይን በሚያዋስነው የውሃ አካል ላይ ከተገለበጠች በኋላ ቢያንስ 12 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ብለዋል።

ሮይተርስ የዜና ወኪል የፈረንሳይ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው በጀልባ መገልበጥ አደጋው ሕይወታቸውን ያጡት አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን ናቸው ብሏል።

የፈረንሳይ የአገር ውስጥ ሚንስትር ጀራልድ ዳርማኒን ሕይወታቸው ካለፉ 12 ሰዎች በተጨማሪ ሁለት ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።


BBC Amharic
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
«...በምንም ነገር በሚከናወነው ሁሉ አትረበሹ፡፡ ሊሄድ የሚገባው ይሄዳል፡፡ ሊፈርስ የሚገባው ይፈርሳል፡፡ ሊወድቅ የሚገባው ይወድቃል፡፡ የሚቆመው ደግሞ ይቆማል እሱ የተከለው እንደተተከለ ነው ማንም አይነካውም፡፡ ምንም አይሆንም ። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ የሚከናወን ነገር የለም በአሁኑ ጊዜ ፡፡ ሁሉም እግዚአብሔር የመደበለትን ሩጫ ሮጦ ሲያበቃ  ያበቃል በቃ፡፡ ለጥፋት የተሰማራውም መንግስት ይሄው  እንደምታዩት ለጥፋት ተሰማርቶ የለም !! ከነምኑ ከነምኑም በቃ የዛች  የተሰጠችውን ሩጫ ሄዶ ሲጨርስ ይቆማል፡ እጣው ነው እጣውን ይቀበላል፡፡»

⚡️ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ክፍል -9-  ላይ የተወሰደ፡፡
🟢🟡🔴
ጳጒሜን 1 | #ቅዱስ_ዮሐንስ መጥምቅ ወደ እሥር ቤት ገብቷል።

ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ ንጉሡ ኄሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ኄሮድያዳን በማግባቱና በመሰል ክፋቶቹ ቅዱስ ዮሐንስ ይገሠጸው ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ "መምህር ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ — ፊት አይቶ የማያዳላ" ነውና ገሠጸው።

ኄሮድስ ቅዱሱን ይፈራው ያከብረውም ነበር። በኋላ ግን ፈቃደ ሥጋው ስላየለበት ወንድሙን ገድሎ ባገባት ዘማዊት ሚስቱ ምክር ከሰባት ቀናት በኋላ ልደቱን ሲያከብር እንዳይረብሸው በመስጋት በዚህች ቀን በወታደሮቹ አስይዞ እሥር ቤት ውስጥ
ጥሎታል።

ለሰባት ቀናት በጨለማ ውስጥ አሥሮ መስከረም 2 ቀን ራሱን አስቆርጦታል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
#እንዴት_እንሻገር ?
#መመዘኛ_መስፈርቶቹ?

📌 "እንግዲህ በዚህ ዘመን ያለው ዋናው መስፈሪያ በፍጹም የማይታለፈው መስፈሪያ መለኪያ ደጋግመን ስንገልጸው ስናስተምረው ስንመክረው እንደኖርነው  ያለመታከት ደጋግመን ለቤተሰቦቻችን ሊሰሙን ለወደዱት ሁሉ እንደነገርነው ከዚህ በታች እንደምንገልጸው ያንን ያላሟላ ከዚህ መስፈሪያ መለኪያ የጎደለ ሁሉ መላው የአዳም ዘር ኢትዮጵያዊ ብቻ አይደለም ።

ሁሉም የሰው ዘር በመላው ዓለም ላይ ያለው ሁሉ ያለ ምንም ምሕረትና ርህራሄ በታላላቆቹ መቅሰፍቶች የቁጣ እሳትና ፍሰቶች ተበልቶ ተጠርጎ ከዚች ምድር ይሰናበታል።

ከጎደለ ከዚች መስፈሪያ!!

የተሰጠውን የንስሓ ጊዜ በራሱ ትዕቢት በንቀቱ በጉልበቱ በእውቀቱ  በጨበጠው ሀብት ዲያብሎስ ባስጨበጠው የሸንበቆ መደገፊያ  ታምኖ የቆመ ሁሉ የትም ይሁን የት አይደለም በቤቱ ባፈረሳት ቤተ ክርስቲያን በተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ቢጠለል እንኳን ታቦተ ሕጉን ቤተ እግዚአብሔርን ንቆ አፍርሶ ለካቶሊኮች ለተሀድሶች  ለሌባ ለዘራፊ ለሀሰተኛ ነጋዴ እረኛዎች ለመንግሥት ካድሬዎች ሰላዮች የቆብና የቀሚስ ነጋዴዎች የሸጠና ያወደመ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን አትከልለውም አታድነውም አትታደገውም ፈራጁ በታቦተ ሕጉ ላይ ያለው

እግዚአብሔር አብ
እግዚአብሔር ወልድ
እግዚአብሔር መንፈስ ቀዱስ  ነውና!!

ዛሬ ደጋግመን ስላለው ሁኔታ ብናነሳው ሰሚና አሰተዋይ ከሌለ ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው እንደሚባለው አልሰማ ያለ ትውልድ ነጋሪት ቢጎሰምም አይሰማም ።

አንዴ እንደ ሰዶምና ገሞራ እንደ ኖህ ዘመን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ለጥፋት ተጽፏልና እርሳችን ታላቅ እርስ ነውና ወደዚያ እንዝለቅና በማስተዋልም እንረዳ። አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል እናድምጠው ከዚያ በፊት ግን ቀድመን መስፈሪያውን ብናነሳ መልካም ነው መስፈርቱ ግልጽ ነው።
ግልጽ ነው።

📌 ኢትዮጵያዊነት

📌 ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነትን መጨበጥ

📌 ሰንደቋን የቃል ኪዳን ምልክቷን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ታምኖበት መቀበል።

ከልብ ነው፥ ከልብ መቀበል።

🇨🇬 እግዚአብሔር የሰጠንን የቃል ኪዳን ቃሎች፦

ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር፤
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም፤
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን፤
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ።
እነዚህን አምኖ መቀበል ከዚህ የጎደለ እግዚአብሔር ያጸደቀውን የዘመኑን የቃል ኪዳኑን ተስፋ የናቀ ያቃለለ እንኳን ለትንሣኤ ተስፋ ሊያደርግ ኑሮ !!

አሁን ከሚመጣው መቅሰፍት እየተከናወነ ካለው መቅሰፍት ከሚከብደውም ቁጣ  ከዛ ሁሉ አያመልጥም።

ይህ ግልጽ የማያሻማ መስፈሪያ መሆኑን እንድታውቅ መላው የአዳም ዘር ኢትዮጵያዊ ሆንክ የውጭ ዜጋ ሆንክ ማን ሆንክ የአዳም ዘር በሙሉ ይሄ መለኪያ  ተቀምጧል። ከፍታ ዝቅታ የለውም።"

⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ? ትምህርት ክፍል 1 _መ ከደቂቃ 40__44 ደቂቃ ድረስ ካለው ተምህርት ላይ የተወሰደ።
🌪  የቻይና ሁለት ግዛቶች በታይፎን ያጊ አርብ አመሻሽ ላይ ይመታሉ ተብሎ የተተነበየ ሲሆን በሃይናን እና ጓንግዶንግ ሪዞርቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።

በሃይናን ደሴት ወደ 420,000 የሚጠጉ ሰዎች አካባቢው እንዲለቁ የተደረገ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፤ በተጨማሪም የአየር በረራ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
Audio
መልክአ ቅዱስ ራጉኤል
Audio
መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ
. ጳጕሜን 3
   🌈 ርኅወተ ሰማይ
🌈
💚💛❤️

ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት፣ አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት፣ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ – ሰማይ የሚከፈትባት ቀን" ትባላለች።

[አሁን] በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት፣

[አንድም] ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ።

እመቤታችን ድንግል ማርያም ለዓፄ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው፥ በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል።

#በቅዱስ_ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል።

ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት፥ ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ። በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል።

«☘️ ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን ☘️»

💚 www.tg-me.com/christian930
💛
www.tg-me.com/AlphaOmega930
❤️
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2024/09/23 04:25:12
Back to Top
HTML Embed Code: