Telegram Web Link
በዶዶላ የጣለው ከባድ ዝናብ ያደረሰው የከፋ ጉዳት

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ሰኞ አመሻሽ ላይ ነፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በማሳዎች እና የቤት እንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡ ታይቶ የማታወቅ በተባለው ከባድ ዝናብ እስካሁን የጠፋ የሰው ህይወት ግን አልተሰማም፡፡

ከባድ ዝናቡ ባስከተለው አደገኛ ጎርፍ ከ270 በላይ ሄክታር በምርት የተሸፈነ መሬት ከጥቅም ውጪ ስለመሆኑም ነው የተነገረው፡፡
"ጎርፎች ታይተው በማይታወቅ መጠን ይመጣሉ፡፡ ይጠርጋሉ ።"

⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ገጽ 29 ተጻፈ መስከረም 21/01/2004 ዓ .ም
#መረጃ፦ትላንት ማለትም በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ሀምባ ሆሌ ቀበሌ ላይ በረዶና ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ በርካታ የቤት እንስሶችን ፈጅቷል ተብሏል።

🟥🟥🟥

"ጎርፎች ታይተው በማይታወቅ  መጠን ይመጣሉ፡፡ ይጠርጋሉ ።"

⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ገጽ 29 ተጻፈ መስከረም 21/2004 ዓ .ም

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌 እምንመክርህ እንድትድን ነው።

ኢትዮጵያዊነትን እመንበት

ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነትህን ጨብጥ !

ሰንደቋን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ ውደድ !

እሰረው በልብህም፣ በክንድህም፣ በአንገትህም አርገው ።

ከዚህ ውጪ ወደእኛ ና አላልልንም።

ባለህበት ግን የእግዚአብሔር ወገን ሁን።

ለእውነተኛይቱ  ቤተክርስቲያን እውነተኛ ልጇ ሁናት ።

ከሚመስሉህ ጋር  የጽዋ ማህበር አቋቁም ።
እጣ አውጥተህ ዘክር ።

ፈጣሪህን፣ እናትህን ድንግልን  አመስግን።
ይበልጥም ለቤተክርስቲያን በጸሎትም በጾምም ዘብ ሁን። ለቤተ ክርስቲያን ዘብ ሁን።

በኢትዮጵያ ትንሣኤ የጸና ተስፋ ይኑርህ።

በቃ!! የምንመክርህ ይኸንን ነው። እኛ ያልነው ይኸንን ነው። ሌላ 'ምንለው ነገር የለንም።

በውኑ እኛ መልእክታቱ የተናገሩት የሰማችሁት ሰምታችኋል ያልሰማችሁት ባትሰሙትም  ይሄው እንደ ቃሉ እየመጣ አይደለም ወይ ?

ብዙ አባቶች ተናግረዋል። የሚሰማ ግን የለም።
...

🟢🟡🔴 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን 
መግለጫ እና የሉቃስ ወንጌለ ትምህርት ክፍል 13(ሀ) ላይ የተወሰደ። አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
ሸዋ ደብረሲና!

በሸዋ ደርበሲና የመሬት መሸራተት ተከሰተ የመሬት መንሸራተቱ የተከሰተዉም ልዩ ስሙ እንዶዴ አካባቢ ሲሆን አደጋው በመኖሪያ ቤቶች እና በእርሻ መሬት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።አሁንም ቢሆ ን የአካባቢዉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትኩረት ያሻዋል!
🇳🇬 በናይጄሪያ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ባለፉት ሳምንታት 170 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ዘገባዎች አመለከቱ

በሰሜናዊ ናይጄሪያ በሚገኙ አስር ግዛቶች በተከታታይ ቀናት በጣለ ዝናብ ሳቢያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በእርሻ መሬቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና የሀገሪቱን የምግብ እጥረት እንዳያባብስ ስጋት መፈጠሩን የምዕራቡ ዓለም ጋዜጣ ሰኞ እለት ዘግቧል።

በተፈጥሮ አደጋው ከ200,000 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንደተፈናቀሉ የገለጸው ዘገባው ሰሜን ናይጄሪያ በጎርፉ በክፉኛው እንደተጎዳች አክሏል።

ጋዜጣው የናይጄሪያ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ባለስልጣን ቃል አቀባይ ማንዞ ኢዝኪዬል "በሚቀጥሉት ቀናት ማእከላዊ ክፍሎች እንዲሁም ወደታች ወረድ ብሎ ደቡባዊ ክፍሎችም ተመሳሳይ ጎርፍ ይገጥማቸዋል" ማለታቸውን ጠቅሶ አስነብቧል።

በናይጄሪያ በቅርቡ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 2,000 ሰዎች እንደተጎዱ እና ከ100,000 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት መውደሙን ዘገባው አክሎ ገልጿል።
2024/09/29 22:18:38
Back to Top
HTML Embed Code: