Telegram Web Link
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🇨🇬 ስለ ደገኛው ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ መነሳትና መንግሥቱ ምን አይነት እንደሚሆን በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳት መጽሐፍት ትውልዱ ይማርና ይጠብቀው ዘንድ ቅዱሳን አባቶቻችን በስውርም በግልጽም አትመው ለእኛ ትውልድ አድርሰውልናል። ይሁንምና "ኢይከብር ነቢይ በሃገሩ" ሆኖ ማንም እነሱ ያሉትን ሲያምንና ሲቀበል አይታይም። ይልቁንስ በዘመን መካተቻ ወቅት የተነሳው የእኛ ትውልድ አንዳንዱ በዲያብሎስ መንፈስ ተታሎ ያልሆነውን "እኔ ነኝ የምስራቁ ቴዎድሮስ ይመጣል የተባልኩት ንጉሥ" ሲል ብዙኃኑ ደግሞ "የምን ቴዎድሮስ የምን ንጉሥ በ21ኛ ክፍለ ዘመን" ሲል ይውላል ያድራል።

ቢሆንም እውነተኛው በቅዱሳት መጻሕፍት እልፍ ጊዜ ስሙ የተጻፈው ለዘመናት ሲጠበቅ የኖረው የኢትዮጵያ ትንሣኤ አብሳሪ በልዑል እግዚአብሔርና በእናቱ የተቀባው ንጉሠ ነገሥት ብርሃን ዘኢትዮጵያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት መልዕክታት የተገለጠ በመሆኑ ልብ ያለው ልብ ይሏል፤ ሌላ የለም፡ አይኖርምም። መቼስ ሃሰተኛ መሲህ ክርስቶሶችና የሃሰተኛው መሲህ ቤተሰቦች ምድርን ስለከደኑ እውነተኛው የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስና እውነተኛ ክርስቲያኖች የሉም አይባልም። ይኼም ያው ነው። "እኔ ቴዎድሮስ ነኝ፤ እኔ የኢትዮጵያ መጻኢ ንጉሥ ነኝ፤ ከእኔ ውጭ ኢትዮጵያ ተስፋ የላትም" ብሎ የተናገረው ቀርቶ በልቡ ያሰበውም ቅጣቱን አይችለውም። ምክንያቱም ቴዎድሮስነት በጥረት የሚሆኑት ሳይሆን ከእግዚአብሔር የሚቀበሉት ስጦታ ነው። ይኽም ለአንድ ባርያው ከተሰጠ ከረመ።

👑 “አመድ ፡ ከዘነመ ፡ ከአራት ፡ ዓመት ፡ በኋላ ፡ የጌታችን ፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሰማዕት ፡ የሆነ ፡ በፊቅጦር ፡ በገድሉ ፡ መጽሐፍ ፡ እንደተነገረው፡ የስሙ ፡ ምልክት ፡ <ቴ> ተብሎ ፡ የተመለከተው ፡ ይነግሳል ፡፡”

👉🏿ድርሳነ ዑራኤል ዘጥቅምት 2፥44
በሶማሌ ክልል የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ በበርካታ ወረዳዎች ላይ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ 2 ሺሕ 827 አባውራዎች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉ የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል። በቀላፌ፣ ሙስተሂል እና ፌር-ፌር ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች በጎርፉ እንደተጥለቀለቁና ጎርፉ በ6 ሺሕ186 ሄክታር የሰብል መሬትና በስድስት ትምህርት ቤቶችና የሕክምና ተቋማት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ቢሮው ገልጧል። በክልሉ የጎርፍ መጥለቅለቅ የተከሰተው፣ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ነው ተብሏል። [ዋዜማ]
ነሐሴ 2፣2016

#ሱዳን

በሱዳን የጣለ ዶፍ ዝናብ በጥቂቱ ለ17 ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑ ተሰማ፡፡

ዶፍ ዝናቡ እጅግ በርካታ ቤቶችን መደረማመሱን አልባዋባ ፅፏል፡፡

ከባድ መጥለቅለቅም ማስከተሉ ተሰምቷል፡፡

አደጋው የደረሰው በናይል ግዛት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ 170 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት ገጥሟቸዋል ተብሏል፡፡

ባለፈው 1 ወር በሱዳን በደረሰ ጎርፍ የሟቾቹ ብዛት 30 መድረሱ ታውቋል፡፡

#ጃፓን

ጃፓን በ2 ከባባድ ርዕደ መሬቶች መመታቷ ተሰማ፡፡

ኪየሹ የተባለችዋ ደቡባዊ ደሴት በርዕደ መሬት መለኪያ ሬክተር ስኬል 6. 9 እና 7.1 ሆነው በተመዘገቡ ነውጦች መመታቷን ገልፍ ኒውስ ፅፏል፡፡

በነውጦቹ ስለደረሰው ጉዳት ለጊዜው በዝርዝር የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

WA እንደፃፈው ደግሞ በከባዶቹ ርዕደ መሬቶች ምክንያት የባህር ማዕበል /ሱናሚ/ ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰምቷል፡፡
Audio
መልክአ 144 ሺህ የቤቴልሔም ሕፃናት ።
Audio
መልክአ አቡነ ፍሬካህን።
Audio
መልክአ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ.
2024/09/24 04:26:29
Back to Top
HTML Embed Code: