Telegram Web Link
🛑 ''ዛሬ የኛው ፈርኦኖች መንግስታቸው ተቆረጠ። ተፈጠመ። አራተኛ የኢሕአዲግ ጭንብል አጥልቆ ብቅ ማለት የለም። ውህድ ነኝ፤ ድምር ነኝ፤ ምርጥ ዲሞክራሲ ነኝ፤ የአሜሪካው የእንግሊዙ ዘመናዊ ዲሞክራሲ ነኝ። የለም አይሰራም። ከሁሉም ምንነታችሁ ጋር ተሰናብታችኋል። አብቅታችኋል። እግዚአብሔር ብርሃናዊ መንግስት እንደ ንጋት ፀሐይ ብቅ ይላል። ሲጨንቃችሁ የሽግግር መንግሥት ትሉ ይሆናል። ዲያብሎስና ምድርን የሸፈኑ ቅራቅንቦዎች መንግሥታት ተብዬዎች ደግፎ ከያዛቸው ስርአት ጋር ተደምድመዋል። ከእንግዲህ የኛ የምትሉት ዘመን የለም። እቅድ የለ ፤ በጀት መበጀት የለ ፤ የመጪው ዓመትን ማየት የለ። ሩቅ አሳቢዎች አዳራችሁ ቅርብ ነው በቃ!!''

📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ ገጽ-4 ተጻፈ ጥር 7/2012 ዓ.ም
#ርሃብ.... (የጦርነት የበኩር ልጅ!!)
🟢🟡🔴
ሐምሌ 25 | #ቅዱስ_መርቆሬዎስ የልደቱና የተአምሩ በዓል ነው፨

ይህም ሰማዕት ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ።

ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ።

ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት።

መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ። በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ።

እነርሱም አብሯቸው የሚጓዝ መስላቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ። እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ።

በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ። ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው።

ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው። ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ።

ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል። ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል።

በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኮሳትን አፍርቷል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Audio
ገድለ መርቆሬዎስ ዘወርኃ ሐምሌ
Audio
ገድለ ቅዱስ አቡነ አቢብ
🟢🟡🔴
ሐምሌ 26 | ጌታችን ያከበራቸው፦

🍀 መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው #ጻድቁ_ዮሴፍ ዐረፈ።

🍀 «ስለ ትምህርትህና ስለ ስብከትህ ኢትዮጵያን ከጨለማ አውጥተህ በሃይማኖት ስለ አበራሃት…» ብሎ ቃልኪዳን የሰጣቸው #አቡነ_ሰላማ #ከሣቴ_ብርሃን ዕረፍታቸው ነው፡፡

ሜሮጵዮስ ሰው ወደ ሕንድ አገር ሊአልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር መጣ። ከእርሱም ጋራ ዘመዶቹ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ። የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ የሁለተኛውም ኤዴስዮስ ይባላል። ሲድራኮስ የሚሉትም አሉ።

በኢትዮጵያ በኩል ወዳለው ወደ አፍሪቃ ባሕር ወደብ ደረሱ ልቡ የተመኘችውን የኢትዮጵያን አገር መልካምነቷን ሁሉ ተመለከተ። 

ከዚህም በኋላ በድንገት ወንበዴዎች ተነሥተው በመርከብ ከአሉት ሁሉ ጋር ገደሉት። እኒህ ሁለት ልጆች ግን ተረፉ። የአገሩ ሰዎችም አገኟቸው፤ ወደ ንጉሥ አይዛና ወስደው አንድ እጅ መነሻ አድርገው እነርሱን ሰጡት። ንጉሡም ተቀበላቸው። 

የንጉሡም ልጆች አብርሃ ወአጽብሓ አድገው በነገሡ ጊዜ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመለሰ። ፍሬምናጦስ ግን ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስም ሔደ።

ስለ ኢትዮጵያውያንም ሃይማኖት ጳጳስ ሳይኖራቸው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳመኑ ነገረው። 

አባ አትናቴዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ። ፍሬምናጦስንም የነጻ ሕዝብ አገር ለሆነችው ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስ ይሆን ዘንድ በግድ ሾመው

በኢትዮጵያም አገሮች ሁሉ የቀናች ሃይማኖትን ሰበከ። አስተማረም ክብር ይግባውና ክርስቶስን የጌትነቱን ብርሀን በሁሉ አገሮች ገለጠ። ስለዚህም ከሣቴ ብርሃን (#ብርሃንን_ገላጭ_ሰላማ) ተባለ። ሁሉንም አስተካክሎ በሰላም ዐረፈ።

T.me/Ewnet1Nat
Audio
መልክአ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ኢትዮጵያዊ የተክለሃይማኖት ወዳጅ🇨🇬🇨🇬🇨🇬)
🟢🟡🔴
ሐምሌ 27 |
#የቅዱስ_ላሊበላ ሚስት #ቅድስት_መስቀል_ክብራ ዐረፈች፨

ይኽች ቅድስት የትውልድ ሀገሯ ወሎ ላስታ ቡግና ነው። በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነገደ አገው ከሆኑት ከአባቷ ስምዖን እና ከእናቷ ሶፍያ ተወለደች።

የታላቁ ጻድቅ ንጉሥ የቅዱስም ላሊበላ ሚስት ናት። ከእርሱም ደገኛውን ይትባረክን ወልዳለች።

ቅዱስ ላሊበላን እና ቅድስት መስቀል ክብራን ሁለቱ እንዲጋቡ ያዘዛቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ንድፎችንና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር መለሰው።

በድጋሚ ተገልጦለት "እንዳንተ የተመረጠች ናት። እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም። እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል።

ቅዱስ ላሊበላ 11 እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ፣ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል።

ቅድስት መስቀል ክብራ ቅ/ገብርኤል በመንገድ እየመራ፣ ቅ/ሚካኤል ዘወትር እየጠበቃት በትግራይ ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች። በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል።

ይኽችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች። ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዱጠመቁ አድርጋለች።

T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሐምሌ 28 | ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ፣ ሐዋርያና ሰማዕት #አቡነ_ፊልጶስ ዐረፉ፨

የጻድቁ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሲሆኑ የተወለዱት በምድረ ሽዋ በ1266 ዓ/ም ነው። ከልጅነታቸው ጀምረው ምሥጢር ተመራማሪና መጻሕፍትን መርማሪ የነበሩት ጻድቁ የመነኑት ገና በ15 ዓመታቸው ነበር።

#በደብረ_ሊባኖስ በአሞክሮ ለ3 ዓመታት ቆይተው መንኩሰዋል። ለ22 ዓመታትም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው አገልግለዋል።

አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1306 ዓ/ም ነሐሴ 24 ቀን ሲያርፉ የተተኩት አባ ኤልሳዕ ቢሆኑም ለ3 ወራት ቆይተው ዐርፈዋል።

ከ1307 ዓ.ም ጀምሮ ለ28 ዓመታት አቡነ ፊልጶስ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት (እጨጌ) ሁነዋል።

ከዚያም በዘመነ ዓፄ ዓምደ ጽዮንና በአፄ ሰይፈ አርዕድ እውነትን በመናገራቸውና ነገሥታቱን በመገሠጻቸው ብዙ ስደት፣ መከራ፣ እሥራትና ግርፋት ደረሰባቸው። በስደትም ለ6 ዓመታት ከ9 ወራት ቆዩ።

ሃገሪቱን በስብከተ ወንጌል ካበሩ #12ቱ_ንቡራነ_እድ አንዱ የሆኑት #እጨጌ_አባ_ፊልጶስ በተወለዱ በ74 ዓመት ከ9 ወራቸው በ1341 ዓ/ም ዐርፈዋል።


ባልና ሚስት የሆኑት ቅዱሳን እንድራኒቆስና አትናስያ ዐረፉ፨

#እንድራኒቆስና_አትናስያ በዘመናቸው ከልጅነት ጀምረው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙ፣ ለወላጆቻቸው የሚታዘዙ ነበሩ።

በእግዚአብሔር ፈቃድ በተክሊል ተጋቡ፤ 40 ቀን ጾሙ። እንደጨረሱ አብረው ሳይተኙ ለዓመታት እንግዳና ነዳያንን በመቀበል በፍቅር ኖሩ።

በኋላም ሁለት ልጆችን ወለዱ፤ በ12 ዓመታቸው ሞቱባቸው። ቅ/እንድራኒቆስ እያለቀሰ አመሰገነ፤ ቅ/አትናስያ ግን መቃብራቸው ላይ ስታነባ ልጆቿ ገነት እንደገቡ በራእይ አየች።

ስለዚህ ተስማምተው መነኮሱ። 12 ዓመት ተለያዩ። ኋላም በምንኩስና ጓደኛማቾች ሆነው ሐምሌ 28 ዐረፉ።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from ቅድስት በርባራ ዘኒቆመዲያ Saint BarBara Αγία Βαρβάρα (ገድላት እና ስንክሳር)
ስለ አሁኑ ዘመን የአቡነ ፊሊጶስ ትንቢት፦

በወቅቱ የነበሩት ጳጳስ አባ ያዕቆብ በብዙ ልመናና ምክር አቡነ ፊሊጶስን ጳጳሱ ራሱ የሚለብሰውን የክብር ልብስ አልብሶ በሸዋ አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾመው።

ከተሾሙም በኋላ አቡነ ፊሊጶስን ‹ሌሎችን ሹምልን› የሚሉ በርካቶች ሲያስቸግሯቸው እሳቸው የሰጡት ምላሽ ‹‹በሥልጣን ፍለጋ ምክንያት ይህችን የትህርምትና የጽሙናን ቦታ (ደብረ ሊባኖስን) የጨዋታ የተድላ ቦታ እናደርጋታለን›› በማለት በወቅቱ ማንንም አልሾምም ብለው ነበር።

አያይዘውም በዚሁ በሹመት ሽኩቻ ምክንያት ወደፊት የሚፈጠረውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት አይተውት የሚከተለውን ትንቢት ተናግረዋል፦

‹‹እውነት እላችኋለሁ በመጨረሻው ዘመን ደጋጎች ሰዎችን ክፉዎችና ተሳዳቢዎች የሚያደርጉ፣ ሐሰተኞችና ዋዛ ፈዛዛ የሚወዱትን ደጋጎች የሚያደርጉ ሰዎች ይመጣሉ፡፡

«በመጨረሻው ዘመን ኃጥአን በጻድቃን ይመሰላሉ፣ ጻድቃንን ኃጢአተኞች ያደርጓቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን እውነተኛዎቹ መምህራን አይሾሙም፣ ኃጢአተኞች መማለጃ ሰጥተው ወሬ እያቀበሉ ይሾማሉ፣ እንደ እባብ ክፉ ነገርን ለማድረግ ፍላፃቸውን ያሾሉ ደጋግ ሰዎችን በነገር ያጠፏቸው ዘንድ በእውነት ንጹሕ የሆኑትን ሰዎች አመፅን በተመላ አንደበታቸው ሹመትን ከመውደድ የተነሣ በቅናት ያጠፏቸዋል፡፡

«በዚያን ዘመን መጻሕፍትን የሚያውቁ አይሾሙም፣ ነገርን የሚያመላልሱና የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቁ ከመኳንንትና ከነገሥታት ዘንድ ሔደው ነገርን የሚሠሩ ሰውን የሚያጣሉ በአመፅ ሹመትን የሚያገኙ ብቻቸውን ይሾማሉ እንጂ ደጋጎች አይሾሙም፡፡

«በሚመረጡበትም ጊዜ ከአባታቸው ከሰይጣን ጋር ሆነው ‹እገሌ መጻሕፍትን ያውቃል፣ የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቅ ይሾም› ይላሉ፡፡

ያንጊዜም አመፅ ይበዛል፣ ፍቅርም ትጎድላለች፡፡ ከእኔ በኋላ የሚሆነውን እነሆ ነገርኳችሁ ይህንንም አውቃችሁ በልቡናችሁ ያዙ፡፡››

የአቡነ ፊሊጶስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡

🍀🍀🍀
2024/09/24 20:37:06
Back to Top
HTML Embed Code: