Telegram Web Link
🟢🟡🔴
ሰኔ 20 | የመጀመርያዋ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን #በእመቤታችን ስም ታነፀች።

ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው።
ይህችም በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር፥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት፣ ያለ ጭቃና ውኃ በሦስት ደንጊያዎች በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው።

አናጺውም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ሐዋርያት በስብከትና በጥምቀት ወደ ክርስትና ያመጧቸው ምእመናን ስለበዙ ለጸሎትና ለቍርባን የሚሆናቸውን ቦታ ሻቱ። ሕንጻንም ሊሠሩ ሱባኤ ገቡ።

ጌታችንም በታላቅ ግርማ መለኮት ተገልጦ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው። በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ። ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው።

ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ። ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው። እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል።

ይህም የሆነው እመቤታችን ካረገች ከ4ኛ ዓመቱ በ52 ዓ.ም ነው።
(ታሪኩ ወደ ሰኔ 21 ይቀጥላል)
🌹

ዳግመኛም ታላቁ ነቢይ #ቅዱስ_ኤልሳዕ ዐረፈ።
ኤልሳዕ ማለት ‹‹እግዚአብሔር ጠባቂ ነው›› ማለት ነው። ታላቁ ነቢይ ኤልያስ በመንገድ ሲሄድ የሳፋጥ ልጅ አልሳዕን በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው።

ኤልያስም ሄዶ መጎናጸፊያውን በላዩ ጣለበት፡፡ ኤልሳዕም እርሻውን ትቶ ተከተለው፡፡ ተመልሶም በመምጣት በሬዎቹን አርዶ፣ ሕዝቡን መግቦ፣ በፍጹም ልቡ ኤልያስን ተከተለ። እግዚአብሔርንም በትንቢቱ 50 ዓመት አገልግሎ በሰላም ዐረፈ።

          #_እንኳን_አደረሳችሁ
        ▸ T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 21 | የመጀመሪያዋ ቤ/ክ
ቅዳሴ ሆነ። እንዲሁም #እመቤታችን በልጇ መቃብር ላይ እያነባች ጸልያ ልዩ ቃልኪዳን ተቀብላለች።
(ሰኔ ጎልጎታን መጸለይ እንዳትረሱ)

ሰኔ 20 ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ። ፊልጵስዩስ በምትባል ሃገር በጴጥሮስ እጅ የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር።

በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ መላዕክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ። ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፦

1. አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አሳየ፣

2. ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው። ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ጳጳሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው።

በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት "አክዮስ" እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ። አክዮስ ማለት "ይገባዋል ያሥምርለት" እንደ ማለት ነው። ጌታችን ከዚህ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ።

☘️ አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ

☘️ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ

☘️ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ

☘️ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ።


በዚያች ቀን በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ። ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው፦

"ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን እነጹ። ይህችን ዕለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ።" ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር ዐረገ።

T.me/Ewnet1Nat
 #እንኳን_አደረሳችሁ
【ሰኔ ጎልጎታ】
🌹🍀🌹🍀🌹

"ምሕረትን የምትለምኚ ድንግል እናቱ፤
አንድያው ልጅሽ አያጥፋን በከንቱ!"

"በእንቲአነ በሊዮ ሰአሊተ ምሕረት እሙ፤
ኢታማስን ግብረ እዴከ እንተ ለሐኮ ቀዲሙ!" (አርኬ)

🌹🍀🌹🍀🌹
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🌹🌹🌹

በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ማርያም ሰኔ 21 ቀን ያደረገችው ተአምር ይኽ ነው፨
▰ ▰ ▰

በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውስጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።

ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ ባለጸጋውም ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም።

ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ። ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ። ልጆቹም ፈሩ። ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና እንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት።

ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዓሊ ሰጠው። እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት። ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ ላይ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛ ሰው እጅ ወስዶታልና።

እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ። ያንንም ሠሌዳ አገኘው። ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።

ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳችው። እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ። ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ። እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው። በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ። እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ በውስጧም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ።

እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ። ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ወር በሃያ አንድ ቀን ነው።

በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ። አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች። ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ። ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት። እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ አላት። በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት። እርሷ የረከሰች ስትሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል። ስለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሆኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው።

                     🌹🌹🌹
                  T.me/Ewnet1Nat
Audio
ድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ዘወርኃ ሰኔ.
◦ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ◦
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🟢🟡🔴
ሰኔ ፳፭ | በሰማዕትነት ያረፉ ክቡራን፦

#ቅዱስ_ይሁዳ_ሐዋርያ
በዘመነ ሐዋርያት ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ ማርያም ትባል ነበር።

እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ ቢሆንም ገና በልጅነቱ ድንግል ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች። አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር።

ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል። ቅዱስ ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል። (ዮሐ. 14፥22)

ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ፣ መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ አሕጉራትን ዙሯል። አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል።

አንዲት አጭር (ባለ አንድ ምዕራፍ) መልእክትም ጽፏል። አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው። ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ ደርቧል።
🌿

#ቅዱስ_ጲላጦስ_መስፍን
ብዙዎቻችን መስፍኑን ጲላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን።

የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ፣ እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል። የጲላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል። ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል።

በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል።
🌿

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 26 | የሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ገብርኤል በዓሉ ነው፨

በዚህች ቀን ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው።

በውስጧም ከቤተ ክርስቲያኗ የጣራ ዕንጨት ብዙ ተአምር ይገለጽ ነበር። ጽጋብ በሚሆንባት በዚያች ዓመት ውኃ ይንጠፈጠፋል። ረሀብ ከሆነ ግን ላብ እንኳ አይታይም ነበር።

የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ተአምራቶቹ ብዙዎች ናቸው።

እንዲሁም በዚሁ ወር ሰኔ 13 ቅዱስ ዳንኤል ነቢይን ያዳነበት በዓሉ ነው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🟢🟡🔴
ሰኔ 28 | ተጋዳይ አባቶቻችን፦

፩- #አባ_ቴዎዶስዮስ

ጻድቁ 33ኛ የግብፅ ሊቀ ጳጳሳት ሲሆን ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው። ከልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ በመንኖ ጥሪት የሚኖር ደግ ሰው ነበር።

ያ ዘመን መለካውያንና ልዮናውያን (ክርስቶስን 2 ባሕርይ የሚሉ) የሰለጠኑበት ዘመን ነበር። በአንጻሩ ደግሞ ተዋሕዶን የሚያምኑ ሊቃውንትና ምዕመናን ቁጥራቸው የተመናመነ ነበር።

እረኝነት እንደተሾመም ተዋሕዶን ትቶ መለካዊነትን (ኩትልክናን) እንዲቀበል ግድ ቢሉት እምቢ በማለቱ በዚህ ምክንያት በቀጥታ ግዞት (ስደት) ተፈረደበት።

ስደት ሳያግደው ሕዝቡ በተዋሕዶ እንዲጸና መልእክት በየጊዜው ይጽፍላቸው ነበር። እጅግ ብዙ ከሆኑት መልእክቶቹ የተወሰኑት ዛሬም ድረስ #ሃይማኖተ_አበው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ።

አባ ቴዎዶስዮስ በብዙ ስቃይ ውስጥም ሆኖ ሕዝቡን ግን በመልካም እረኝነት ከምን*ፍቅና ታደገ። ፓትርያርክ የሆነው ለ32 ዓመታት ሲሆን 28ቱን በስደትና በመከራ ተጋድሎ ሰኔ 28 ዐረፈ።

፪- የምሥራቁን ኮከብ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ መታሰቢያው ነው፡፡

ከላይ የዘከርነው አባ ቴዎዶስዮስ በግዞትና በስደት ሳለ ንግሥቲቱ ታኦድራ ትራዳው፣ ምዕመናንንም ትንከባከብ ነበር።

ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ ከሊቀ ጳጳሱ ዘንድ ክህነትን ተቀብሎ ከሶርያ እስከ ምድረ ግብጽ ስለ #ተዋሕዶ ሕልውና ተጋድሏል። ምናልባትም ከሐዋርያው #ቅዱስ_ጳውሎስ በኋላ በፈሊጥ ክርስትናን በማስፋፋት ቀዳሚ አባት ነው።

ለአገልግሎት ፈጣን እና ከቦታ ቦታ ገስጋሽ ስለሆነ "እል በረዲ" ተብሏል። ትርጉሙ ሠጋር በቅሎ፣ ፈጣን ሠረገላ እንደ ማለት ነው እንጂ የሀገሩ ስም አይደለም።

ብዙ ሕዝብ እያጠመቀ መለያ እንዲሆን በአንገት ላይ ጥቁር ማኅተብ ማሰርን ያስጀመረን ይህ አባት ነው።

፫- #ኣቡነ_ክፍለ_ሥላሴ ዘዛውል ወዘባንብቆ ዕረፍታቸው ነው።

አቡነ ክፍለ ሥላሴ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ የተመረጡ ስለነበሩ እግዚአብሔርን በመፍራት ይታወቁ ነበር። ስመ ሥላሴን በከንቱ አያነሡም ነበር።

ስመ እግዚአብሔርም ከተጠራባቸው በፍርሃት ይታዘዛሉ። እረኞችም ከብቶቻቸውን እንዲመልሱላቸው የእግዚአብሔርን ስም ከጠሩባቸው ይታዘዟቸው ነበር። በዚኸም ነገር አቡነ ክፍለ ሥላሴ ታላቁን ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእን መሰሉ።

አቡነ ዐቢየ እግዚእ "ስለ እግዚአብሔር ብለህ" ብለው ጦር ላይ እንዲወድቁ፣ የአህያ ቁስል እንዲልሱ ቢጠየቁ ስለ ስሙ ክብር ብለው እሺ ያሉ አባት ናቸው።

አቡነ ክፍለ ሥላሴ ራሳቸው "በአባታችን በአብርሃም የመታሰቢያ ቀን ከናንተ እለያለሁ" እንዳሉ ሰኔ 28 ዐርፈዋል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 29 | ከቅዱሳን ንጉሦች መካከል፦

👑 ኢትዮጵያዊው የንጉሥ ዳዊት ልጅ #ንጉሥ_ቴዎድሮስ_ቀዳማዊ ዐረፈ።

ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ በዕውቀትና በተግሣጽ አደገ። የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የተማረ ደግሞም ቀስት ማፈናጠርንና ፈረስ ግልቢያን ተማረ። ኃይል ያለውም ብርቱ ሰው ሆነ።

ከታናሽነቱም ጀምሮ በእግዚአብሔር ፍቅር ታሠረ። ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች ይመጸውት ነበር። አብያተ ክርስቲያንንም እጅ መንሻ ከመያዝ ጋራ ይጎበኝ ነበረ። በጸሎትና በጾምም ይጋደል ነበረ።

ካንዲት ሴት በቀር አላገባም። በማንም ላይ ዐመፅና ግፍ ከቶ አልሠራም።

ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ በአሰበ ጊዜ አባ ማርቆስን አማከረው። እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ያውቅ ነበረና ክፍልህ አይደለም አለው።

ከዚህም በኋላ ባረፈ ጊዜ በክረምት ወራት በድኑን ሲወስዱ ሞልቶ የነበረው ወንዝ ወዲያና ወዲህ ተከፍሎ ተሻገሩ። በቀበሩበትም ቦታ ሕይወትነት ያለው ውኃ መነጨ እስከ ዛሬም አለ።

👑 ንጹሕ ጻድቅ የሆነ የሮሜ #ንጉሥ_ማርቆስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ።

ይህም ቅዱስ በድንግልናው አምስት ዓመት ነገሠ። ሕዝቡንም እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅን ፍርድ ጠበቀ።

እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ሚስትን እንዲአገባ መኳንንቱ አስገደዱት። እርሱ ግን በሌሊት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ቁሞ ጸለየ።

እመቤቴ ሆይ ላንቺና ለማይሻር ንጉሥ ልጅሽ እገዛ ዘንድ ወደ ምሔድበት ምሪኝ አላት። እርሷም ወደ ቶርማቅ ተራራ ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋራ ይኑር አለችው።

ከዚህም በኋላ በሌሊት ወጥቶ ሔደ። ወደ ባሕር ወደብም በደረሰ ጊዜ ያለ መርከብ ተሻግሮ ወደ ቶርማቅ ተራራ ደረሰ።

ከአጋንንት ጋራም እየተጋደለ በውስጡ ስልሳ ዓመት ኖረ። በዐረፈ ጊዜም መላእክት በልዩ ክብር ቀበሩት።

T.me/Ewnet1Nat
2024/09/27 07:28:56
Back to Top
HTML Embed Code: