Telegram Web Link
Audio
ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ዘወርኃ ሰኔ
የሟቾች ቁጥር ወደ 550 ማደጉ ተሰማ

አመታዊውን የሀጂ ስነስርአት ለመካፈል ወደ ሳኡዲ ካቀኑ ሰዎች መካከል ከ550 በላይ ሰዎች በሙቀት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

ከከፍተኛ የሙቀት መዕበል ጋር በተያየዘ በሚፈጠሩ በሽታዎች ነው ሃጃጆቹ ህይወታቸው ያለፈው፡፡ ከሟቾቹ መካከል 323 የግብጽ ፣ 144 የኢንዶኔዢያ፣ 35 የቱኒዝያ ፣ 11 የኢራን ፣ 6 የሴኔጋል ዜግነት ያላቸው ሃጃጆች ናቸው ተብሏል፡፡

የሟች ቤተሰቦች በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሳኡዲ ሆስፒታሎች ዘመዶቻቸውን በማፈላለግ ላይ ሲሆኑ ዮርዳኖስ በበኩሏ በሃጂ የሞቱ ዜጎቿን ለመቀበር 41 የመቃብር ስፍራዎችን ማዘጋጀቷን በትላንትናው እለት አስታውቃለች፡፡
በጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የሦስት ኢትዮጵያውያን አሽከርካሪዎች ሕይወት አለፈ‼️
በጎረቤት አገር ጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሦስት የከባድ መኪና አሽርካሪዎች እና የመኪና ጥገና ባለሙያ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሕይወት እንዳለፈ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር አስታወቀ።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ሚል 4፥1

እነሆ ይመጣል የተባለው መምጣቱን ልብ ያልው ልብ ይበል።
በከባድ ሙቀት ህይወታቸው ያለፈ ሀጃጆች ቁጥር ከ1 ሺህ ተሻገረ

1081 የ10 ሀገራት ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ የተነገረ ሲሆን፥ ከ650 በላዩ ግብጻውያን ናቸው ተብሏል። በዘንድሮው ሃጂ የተመዘገበው ጉዳት ከ2015 ወዲህ ከፍተኛው መሆኑ እየተነገረ ነው።
🔥     🔥    🔥
በዓለ ጰራቅሊጦስ
(መንፈሰ ጽድቅ)
   

የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ። ዛሬም አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን በቀመሩ ስናከብር ግንቦት 18 ደሞ በጥንተ በዓሉ እናከብራለን።

ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል
🍀 ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ፣ በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ፣
🍀 በኅቱም ድንግልና ተወልዶ፣ ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጎ፣
🍀 በ30 ዘመኑ ተጠምቆ፣ ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ፣
🍀 በፈቃዱ ሞቶ፣ በባሕርይ ሥልጣኑ ተነሥቶ፣
🍀 በአርባኛው ቀን አርጓል።

ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሣ በ50ኛው ቀን፣ በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች። 120ው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው።

ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች፣ አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ። በአዕምሮ ጎለመሱ፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን ተናገሩ፣ ምሥጢርም ተረጎሙ። በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ።

ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል። አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል። ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል።

"ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ፥
ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ፥
ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ" እንዳለ ደራሲ።

በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ፦

1. "የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት"

እርሱ ከአብ የሠረጸ፣ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በባሕርይ ሥልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ፣ የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም ጌታችን አምላካችን ነውና።

2. "ቅድስት ቤተ ክርስቲያን"

አብ ያሰባት፣ ወልድ በደሙ የቀደሳት፣ መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት (የፈጸማት) የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት፣ አንድም ቤት ናትና ዛሬ በጉባዔ ተመሥርታለች።
🍀🍀

የመንፈስ ቅዱስ ቸርነቱ፣ ምሕረቱ፣ ጸጋው ይደርብን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል፥
ወለወላዲቱ ድንግል፥
ወለመስቀሉ ዕፀ ሣህል። አሜን፨
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ
#በዓለ_መንፈስቅዱስ

እንኳን አደረሰን ፤ እንኳን አደረሳችሁ !
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🟢🟡🔴
ሰኔ 17 | #ቅዱስ_አቡነ_ገሪማ (ይስሐቅ) ተሰወሩ፨

አቡነ ገሪማ ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ። ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑና ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው። ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት።

በልጅነቱ በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ። ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል።

ከግብፅ በርሃ አባ ጰንጠሌዎን መልዕክት ልከው "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" አሉት።

ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ። ቅዱስ ገብርኤልም ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ጰንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው። በኋላ 9 ሆነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ።

በአንዱ ቀን ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ተብለው ቢታሙ፥ ጉዳዩን ለማስረዳት "ሰዎች ብቻ አይደሉም ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ተጠራርጎ ሸሸ።

ይህንን የተመለከቱት አባ ጰንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "#አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ፡፡

ጻድቁ ወንጌልን ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፦

🍀 ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ደርሶ፣ ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ደርሶ ቁርባን ይሰዉ ነበር

አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ።

🍀 ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች። ወንጌልን እየጻፉ ሊመሽ ቢሆን ፀሐይን አቁመዋታል።


🍀 በስምህ የዘከረ 12 ትውልድ ይማራል፣ የተራቈተውንም ለሚያለብስ የብልህ እጅ ያልሠራው የብርሃን ግምጃን አለብሰዋለሁ የሚል ቃልኪዳን ተቀብለዋል።

ሞትን አትቀምስም ተብለው ተሰወሩ። መላእክትም በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ ሕያዋን አደረሷቸው።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመካከለኛው ምሥራቅ አሜሪካ የተከሰተው ጎርፍ!!
🟢🟡🔴
ሰኔ 20 | የመጀመርያዋ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን #በእመቤታችን ስም ታነፀች።

ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው።
ይህችም በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር፥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት፣ ያለ ጭቃና ውኃ በሦስት ደንጊያዎች በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው።

አናጺውም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ሐዋርያት በስብከትና በጥምቀት ወደ ክርስትና ያመጧቸው ምእመናን ስለበዙ ለጸሎትና ለቍርባን የሚሆናቸውን ቦታ ሻቱ። ሕንጻንም ሊሠሩ ሱባኤ ገቡ።

ጌታችንም በታላቅ ግርማ መለኮት ተገልጦ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው። በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ። ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው።

ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ። ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው። እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል።

ይህም የሆነው እመቤታችን ካረገች ከ4ኛ ዓመቱ በ52 ዓ.ም ነው።
(ታሪኩ ወደ ሰኔ 21 ይቀጥላል)
🌹

ዳግመኛም ታላቁ ነቢይ #ቅዱስ_ኤልሳዕ ዐረፈ።
ኤልሳዕ ማለት ‹‹እግዚአብሔር ጠባቂ ነው›› ማለት ነው። ታላቁ ነቢይ ኤልያስ በመንገድ ሲሄድ የሳፋጥ ልጅ አልሳዕን በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው።

ኤልያስም ሄዶ መጎናጸፊያውን በላዩ ጣለበት፡፡ ኤልሳዕም እርሻውን ትቶ ተከተለው፡፡ ተመልሶም በመምጣት በሬዎቹን አርዶ፣ ሕዝቡን መግቦ፣ በፍጹም ልቡ ኤልያስን ተከተለ። እግዚአብሔርንም በትንቢቱ 50 ዓመት አገልግሎ በሰላም ዐረፈ።

          #_እንኳን_አደረሳችሁ
        ▸ T.me/Ewnet1Nat
2024/11/15 05:18:03
Back to Top
HTML Embed Code: