Telegram Web Link
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
☀️ ውድ እና ዕንቁ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን !              ሰኔ ፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
🍀🍀
ከዘጠኙ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው፡፡ በዓለ ዕርገት ከትንሣኤ በዓል በኋላ በ40ኛው ቀን ስለሚውል ሐሙስን አይለቅም፡፡

ዕርገት ማለት ዐርገ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ወደ ላይ መውጣት ከምድር ከፍ ከፍ ማለት... እስከ ሰማየ ሰማያት መምጠቅ ማለት ነው፡፡ የጌታ ዕርገት እንደ ኤልያስ እንደ ሔኖክ እንደሌሎቹም ቅዱሳን ያይደለ በገዛ ሥልጣኑ የሆነ ነው ሌሎቹ አጋዥ አስነሽ ይሻሉና ነው፡፡

ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ቅዱስ ዳዊት «አምላክ በዕልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ» (መዝ 46፥5) በማለት በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ በመንፈስ ዘምሯል። ይህም ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቢታንያ ይዟቸው ሄዷል። (ሉቃ 24፥50)

ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በተለያየ ቦታ ተገልጾ ታይቷቸዋል። ትምህርትም አስተምሯቸዋል። «ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ዐርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግስት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ህያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው» (ሐዋ 1፥3)

በነዚህ ቀናት ውስጥ ጌታችን ሥርዓትን አስተምሯቸዋል። ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ትምህርት ኪዳን ብላ ትጠራዋለች። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለሐዋርያት የነገራቸው መጽሐፈ ኪዳን ይባላል፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀናት በምድር ቆይታ ባደረገበት ወቅት በግልጽ ተገልጦ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና መጽሐፈ ኪዳንን አስተምሯቸዋል፡፡ ጉባኤ ዘርግቶ ያስተማራቸው ለሦስት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ዮሐ.21፤14

እነሱም፦
1. ሞትን ድል አድርጎ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በተነሳበት በትንሣኤ ዕለት
2. ምሳ ባበላቸው /በአግብኦተ ግብር/ ዕለት
3. በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ናቸው፡፡

በዚህ በዕርገቱ ዕለት ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቁን ሹመት የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻን ቁልፍ ተሰጥቶታል ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ሞትን ሳይቀምስ እስከ እለተ ምፅአት እንደሚቆይ ተገልጿል ዮሐ. 21፤15-23

#እንዴት_ዐረገ?
ሐዋርያትን ከባረካቸው በኋላ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ሥጋ በማነስ፣ በመርቀቅ፣ በመጥፋት ሳይሆን በመራቅ ሐዋርያት በዓይናቸው እየተመለከቱት በጥቂት በጥቂት ምድርን ለቆ ከፍ ከፍ እያለ በፍጹም ምሥጋና ፈጽሞ ወደ አልተለየው ወደ ባሕሪ አባቱ ዐርጓል፡፡

በሥጋና በነፍስ፣ በአጥንትና በደም፣ በጅማት፣ በጸጉርና በፂም እንዳለ በጥንተ አኗኗሩ በአብ ቀኝ ተቀመጠ በሰማይ በምድር ያሉትን ረቂቁም ግዙፉም ሁሉ ተገዙለት፡፡ 1ኛጴጥ. 3፤22 ክርስቶስ የሰውን አካል የሰውን ባህሪ ገንዘቡ አድርጎ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ሲገለጥ ሰውም የአምላክን ገንዘብ ገንዘብ አድርጎ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በዘባነ ኪሩቤል የመላእክትንም ምሥጋና ለመቀበል በቃ፡፡

#ለምን_ዐረገ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሩ ማረጉ፥ በሙሴ የሕግ መጽሐፍት በነቢያትም የትንቢት መጽሐፍ እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት የተነገረው ትንቢት አለና ይህ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ መዝሙረኛው ልብ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለጌታችን ዕርገት እንዲህ በማለት ጽፏል፡፡

መዝ. 47፥5 ‹‹…. አምላክ በእልልታ በእግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ››
መዝ. 67፥18 ‹‹ወደ ላይ ዐረግህ ፣ምርኮን ማረክ ፣ ስጦታን ለሰዎች ሰጠህ››
መዝ. 16፥10 ‹‹ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በነፋስም ክንፍ በረረ….›› በማለት በትንቢት መነጽር ተመልክቶ የዘመን ግድግዳ ሳያግደው የተናገረው ኃይለ ቃል ነው፡፡

#ዕርገቱን_ለምን_በተነሣ_በ40ኛው_ቀን_አደረገ?

◦ አዳም በ40 ቀን አግኝቶ ያጣትን ልጅነት እንደተመለሰለት ለማጠየቅ፣

◦ አንድም ጌታ በረቀቀ ጥበቡ ተሸብሮ የነበረውን የሐዋርያትን ልቡና እያረጋጋና እያጽናና መቆየቱን መርጦ ነው፡፡

◦ አንድም ለአይሁድ ምክንየት ለማሳጣት ነው ዕርገቱን ከትንሣኤው አስከትሎ ወዲያው ቢያደርገው ዕርገቱ ምትሐት ናት እንዳይሉ በእርግጥ በሞቱ ሞት ድል አድረጎ የተነሣው ወልደ እግዚአብሔር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መሆኑን እንዲረዱ እንዲገነዘቡበ የጥርጣሬ መንፈስ በአዕምሯቸው እንዳይሰርጽ ነው፡፡

◦ አንድም ላላመኑት ለእስራኤላውያን (ለአይሁድ) የንስሐ ጊዜ ሲሰጣቸው ነው ብዙዎች በክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት አምነው የተመለሱ አሉና፡፡

#ዕርገት_በዓል_መቼ_ነው?
ጥንተ ዕርገቱ በወርሐ ግንቦት ስምንት ኀሙስ ቀን በ34 ዓ.ም በዘመነ ማርቆስ ነው፡፡

የዕርገት በዓል አከባበር እስከ አራተኛው መቶ ዓመት ድረስ እንደ ዛሬው ሐሙስን ሳይጠብቅ በጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ቀን ብቻ ይከበር ነበር፡፡ በአራተኛው ምዕተ ዓመት ወዲህ ግን ትንሣኤ በዋለ በአርባኛው ቀን ብቻ እንዲከበር ቅዱስ ዲሜጥሮስ በባሕረ ሐሳብ ቀመሩ ስሌት መሠረት ይከናወን ዘንድ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኖ በሥራ ላይ ውሎ ይገኛል፡፡
🍀🍀
🟢🟡🔴
ሰኔ 7 | #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ የዕረፍቱ በዓል ነው።

ይህም ቅዱስ አባት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ነው።

ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው። ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር።

አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በ3 ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው። ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ። ሊቀ ጳጳሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው።

የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ። ጳጳሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት።

እርሱም፦
፩- ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ፣
፪- ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ
፫- እንዲሁም ከፈጣሪዬ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው።

ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ጳጳሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሐ በቅተዋል።

ቅዱስ ያዕቆብ በዘመኑም የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል፣ ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል፣ በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል።

ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል።

☘️☘️☘️
T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 8 | #_የእመቤታችን_ማርያም ቅዳሴ ቤት ተከናወነ፨

በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም በስደቷ ወቅት ልጇ ያፈለቀው የውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው።

ይኽም ከእመቤታችን 33ቱ ዋነኛ በዓላት አንዱ ነው።

ይህም እንዲህ ነው፦ ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ።

ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ። በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ። የእመቤታችን ስደት የጀመረው ግንቦት 24 ቀን ነው። ለ3 ዓመት ከ6 ወርም ተወዳጅ መድኃኒት ልጇን ይዛ በስደት ቆይታለች።

ሄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት። ወደ እስራኤልም አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ አዘዘው።

በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ። ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት። እርሷም እስከ ዛሬ አለች።

ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ። ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ። በዛሬዪቱ ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ።

እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

                🌹
T.me/Ewnet1Nat
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🟢🟡🔴
ሰኔ 9 | #አቡነ_በኵረ_ድንግል በዓላቸው ነው፨

እኚህም የአቡነ ብፁዓ አምላክ ረዳት ሲሆኑ አቡነ ብፁዓ አምላክ ካረፉ በኋላ በደብረ ምዕዋን ምንኩስና ተሹመው ብዙ አገልግለዋል።

የአቡነ በኵረ ድንግል አባታቸው ማርቆስ እናታቸው እግዚእክብራ ይባላሉ ሁለቱም ጻድቅ ነበሩ።

አቡነ በኵረ ድንግል በእናታቸው ማኅፀን እያሉ ብዙ ተአምራትን አድርገዋል። በተወለዱ ጊዜ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ከተወደደ ልጇ ከቸሩ መድኃኔዓለም ጋር በልባቸው ተሥሎ ተወለዱ።

ሲወለዱም እንደሌሎች ቅዱሳን ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ›› እያሉ አመሰገኑት ።

ወላጆቻቸው በ40ኛ ቀናቸው ሊያጠምቋቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዷቸው የሚያጠምቃቸው ኤጲስ ቆጶስ የእመቤታችንን ሥዕል እና የመድኃኔዓለም ሥዕል በልባቸው ተሥሎ አይቶ ሜሮን ሊቀባቸው ሲል ደነገጠ። ቅዱስ ሚካኤል ግን ተገልጦ ኤጲስቆጶሱን ያለ ፍርሃት እንዲያጠምቃቸው አዘዘው።

በተጠመቁ ጊዜ የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወዳጅ ልጇ ጋር ተገኝታ በመስቀሉ ምልክት ባርካቸው የመስቀል ምልክትም በሥጋቸው ላይ ዳግመኛ ተሥሏል።

ለመማር በደረሱ ጊዜ ግዕዝ ፣ ዐረብኛ ፣ ዕብራይስጥ፣ ግሪክ፣ ሮማንስ፣ ብሉይና ሐዲሳት፣ ሌሎችም ብዙ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረዋል።

☘️◦ ከተሰጣቸው ቃል ኪዳን ◦☘️

. . በስምህ የሚዘክር፣ ስምህን የሚጠራ፣ በዓለ ዕረፍትህን የታመመውንና የታሰረውን የሚጠይቅ፣ የተራበውን የሚያበላ፣ የተጠሙትን ያጠጣ፣ በስምህ ልጁን የሚጠራ፣ እኔ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ፤ ክፉም አያገኘውም።

በስምህ በታነጸው ቤተክርስቲያን ቅዱስ ቁርባንን የተቀበለውን እምርልሀለሁ፤ እኔ ኃጢያቱን ይቅር እለዋለሁ።

       ◦☘️☘️☘️
T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 11

ስንክሳሩ ንጽሕናውንና ቅድስናውን ለማጠየቅ ሲል "የመልአክት አርአያ ያለው" ብሎ የገለጸው ሰማዕቱ #ቅዱስ_ገላውዴዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡

#አቡነ_መዝሙረ_ድንግል
ሀገራቸው ጎጃም ሲሆን ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ባለ ውለታ ናቸው።

ጻድቁ በአምስት ሊቃውንት እየተመሩ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራቱን ወንጌላት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም በግእዝ፣ በአረማይክ፣ በዕብራይስጥና በዐረብኛ ጽፈው በአራት ዓምት ያዘጋጁ ታላቅ አባት ናቸው። ዛሬም በሞጊና ገዳም ይገኛል።

ከዚህም ሌላ ነገረ ማርያምንም በግእዝና በዕብራይስጥ አዘጋጅተው ጽፈውታል። ሌሎችንም በርካታ መጻሕፍት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች እየተረጎሙ ጽፈው ያስቀመጡ ነበር።

ጸሎተኛ፣ ደራሲ፣ ባሕታዊ፣ ጻድቅና መናኝ የሆኑት አቡነ መዝሙረ ድንግል ሰኔ 11 ዐርፈው የተቀበሩት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነው።

#_አቡነ_ገብረ_ኢየሱስ
ለግብፃውያን አባቶች ትንቢት ይነግሯቸው የነበሩት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ገብረ ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ በሀገራችን ብዙ ተአምራትን በማድረግ ወንጌልን ሲሰብኩ ከኖሩ በኋላ የግብፅ ገዳማትን ለመሳለም ወደ ግብፅ ወርደው አባ መቃርስ ገዳም ገቡ፡፡

ከዚያም ወጥተው በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ገብተው በዚያ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ፡፡ አቡነ ገብረ ኢየሱስ ታላቅ የሆነ ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባት ስለሆኑ በዚህም ግብፃውያኑ ይቀኑባቸው ነበር፡፡

በወቅቱ የነበረው የግብጻውያኑ ንጉሥ በጣም ብዙ ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም አቡነ ገብረ ኢየሱስ ሄደው በድፍረት አስተምረውትና ገሥጸውት በአንድ ሚስት ብቻ እንዲጸና አድርገውታል።

የአባታችን ገድላቸው በጣና ይገኛል። ዐርፈው የተቀበሩት ግን በዛው በግብጽ በቊስቋም ገዳም ነው። ግብጻውያን ታቦት ቀርጸው በዓል ያደርጉላቸዋል።
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 12 | በዚህች ቀን፦

የከበረ #የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣

ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል #_ቅድስት_አፎምያን ያዳነበት፣

ዳግመኛም መልአከ ብርሃን ቅዱስ ሚካኤል #_የቅዱስ_ባህራን_ቀሲስ የሞት ደብዳቤ ቀዶ እርሱን ለታላቅ ክብር ያበቃባት ቀን ናት፡፡

🍀 ዳግመኛም ካህን እና ንጉሥ፣ ጻድቅ እና ንጹሕ #ቅዱስ_ላሊበላ የዕረፍቱ በዓል ነው።

#_እንኳን_በቸርነቱ_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
☘️ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ኢትዮጵያ☘️

▸ ቅዱስ፣ ንጹሕ፣ ካህን ወንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ (ላል-ይበላ) ታኅሣሥ 29 ተወለደ፤ ሰኔ 12 ተጋድሎውን ጨርሶ ዐረፈ።

ሙሉውን ታሪክና ቃልኪዳን ለማንበብ 👇
Audio
ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል ዘወርኃ ሰኔ.
Audio
ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ዘወርኃ ሰኔ
የሟቾች ቁጥር ወደ 550 ማደጉ ተሰማ

አመታዊውን የሀጂ ስነስርአት ለመካፈል ወደ ሳኡዲ ካቀኑ ሰዎች መካከል ከ550 በላይ ሰዎች በሙቀት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

ከከፍተኛ የሙቀት መዕበል ጋር በተያየዘ በሚፈጠሩ በሽታዎች ነው ሃጃጆቹ ህይወታቸው ያለፈው፡፡ ከሟቾቹ መካከል 323 የግብጽ ፣ 144 የኢንዶኔዢያ፣ 35 የቱኒዝያ ፣ 11 የኢራን ፣ 6 የሴኔጋል ዜግነት ያላቸው ሃጃጆች ናቸው ተብሏል፡፡

የሟች ቤተሰቦች በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሳኡዲ ሆስፒታሎች ዘመዶቻቸውን በማፈላለግ ላይ ሲሆኑ ዮርዳኖስ በበኩሏ በሃጂ የሞቱ ዜጎቿን ለመቀበር 41 የመቃብር ስፍራዎችን ማዘጋጀቷን በትላንትናው እለት አስታውቃለች፡፡
በጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የሦስት ኢትዮጵያውያን አሽከርካሪዎች ሕይወት አለፈ‼️
በጎረቤት አገር ጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሦስት የከባድ መኪና አሽርካሪዎች እና የመኪና ጥገና ባለሙያ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሕይወት እንዳለፈ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር አስታወቀ።
2024/09/24 22:23:49
Back to Top
HTML Embed Code: