Telegram Web Link
20240124_141834.amr
680 KB
የወንድማችን ወልደ ሚካኤል አጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ባህርዳር
19/9/2016

👉 ቅድመ
ጥንቃቄ ይኑራችሁ አደጋው በአካባቢያችሁ ሲከሰት እናንተም በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ላይ ሞት ሲወርድ
ሙሴ በሩን ዘግቶ ሞትን ከነወገኖቹ በምስጋና እንዳሳለፈ ሁሉ በራችሁን ዝጉ በበራችሁም ላይ የድንግልን
ማኅተም የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና ፈጣሪያችሁን በማመስገን አሳልፉ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ስምንት የተወሰደ
ምስክርነት (1)
<unknown>
የወንድማችን ተስፋ ሚካኤል እጅግ እጹብ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
19/9/2016

👉 ጌታ በእናንተ የሕይወት ምስክርነት በፊቱ በብርሃንነት ልትመላለሱ ወዶአችኋል። አገራችን ኢትዮጵያን
የዙፋኑ ማረፊያ፣ የስሙ መመስገኛ፣ የበረከቱ መፍሰሻ ምንጭ ትሆን ዘንድ ወዷል። ከዓለም ሁሉ አብልጦ
ወደዳችሁ፤ የሚወዳትን እናቱን ለእናንተ እናት ትሁናችሁ አለ። ሚካኤልን፣ ገብርኤልን፣ ሩፋኤልን፣
ፋኑኤልን፣ የሁላችሁም ጋሻና የበረከት መፍስሻ አደረገ

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አራት የተወሰደ
ስርጉተ ገብርኤል
ከስዊዘርላንድ
19/9/2016
🟢 🟡 🔴

ግንቦት 21 | አምላክን የወለደች #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ ታላቅ በዓል ነው።

እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጎናጸፈች ናት። በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር፤ ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ። በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል።

አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ።

ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ፥ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል ።

ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል። ደግሞ ጻድቃንም እንዲሁ።

ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል። በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ።

እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ "ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ" ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል።

የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች። ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል።

እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል። እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ።

#_እንኳን_አደረሳችሁ
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
☘️☘️
🌹🌹🌹
አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ፣
ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ፣
ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ፣ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሁ መዓልተ፣
ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ፤
🍀

የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል!

በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው፡፡"

~ ማኅሌተ ጽጌ ~
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 23 | #_አቡነ_ታዴዎስ ዘደብረ ጽላልሽ ልደታቸው ነው።

አቡነ ታዴዎስ ሲወለዱ ያዋለደቻቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። አባታቸው ቅዱስ ሮማንዮስ (የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት)፣ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርታ ይባላሉ።

ሲወለዱ ሀገሩ ጨለማ ስለነበረ በብርሃን ተሞላ፤ ባዶ ጎተራዎች ከአፍ ሞልተው መሬት ይፈሱ ነበር፡፡ ሐምሌ 2 ቀን ክርስትና ሲነሡ ቤተ ክርስቲያን ቆመው እያሉ እመቤታችን ወርዳ ስማቸውን ታዴዎስ ብላቸዋለች፡፡

በዚህ ዕለት የተዘራው ዘር 40 ቀን ሳይሞላው ከቤተክርስቲያን ሲመለሱ ዘር እሸት ሆነ አጎመራ፤ ፍሬ ሆኖ ተበላ። ካህናት ሲወርቡ ከእናታቸው ጀርባ ላይ ሆነው እያዜሙ አብረው ያመሰግኑ ነበር።

ካደጉም በኋላ በጾም በጸሎት ከመጋደላቸው እና ከትሩፋታቸው ብዛት ተአምራታቸው ብዙ ነው።

● እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመርፌ ቀዳዳ 30 ግመሎችን አሾልከዋል።

● ሳጥናኤልን በአገረ ጽጋጋ ለ 7 ዓመት አስረውታል።

     ▸ የተሰጣቸው ቃልኪዳን

#_በሰማዕትነት_ደማቸው_በፈሰሰበት_ፀበል_ቦታ_የተጠመቀ_በኀልዮ_በነቢብ_በገቢር_የሠራውን_ኃጢአት_ሁሉ_ደምስሼ_በማየገቦ_እንደተጠመቀ_አደርገዋለሁ

#ወንድ_እንደ_40 ቀን #ሴትም_እንደ_80 ቀን ህፃን ይሆናሉ፡፡

๏ በጸበሉ ልዩ ልዩ ደዌ ሕሙማን ቢጠመቁ እፈውሳቸዋለሁ።

#_ዝክርህን_የዘከረ_ሲኦልን_አላሳየውም፤ እምረዋለሁ።

#_አንድ_አቡነ_ዘበሰማያት ቢደግም ስዕለቱን እሰማዋለሁ፤ እፈፅምለታለሁ"

ብሎ አምላካችን በማይታበል ቃል ኪዳን ቃል ገብቶላቸዋል።

የአቡነ ታዴዎስ በረከታቸው ይደርብን፣ እንኳን አደረሳችሁ።
                ◦🌿☘️🌿
          ▸ www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Audio
🇨🇬 ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት?
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት
                 ክፍል - 3
ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ !!
ግንቦት- 23-2016 ዓ.ም
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 24 | የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም#ከቅዱሳን_ዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር ወረደ።

ያን ጊዜም እርሱ ጌታ የሁለት ዓመት ሕፃን ነበር። የጌታችንም ወደ ግብጽ መምጣት ስለ በርካታ ምክንያቶች ነው። ጥቂቶቹ፦

̏፩. ኄሮድስ ቢያገኘው ሊገድለው እንዳይችል። ስለዚህ ሌሎች ትስብእቱ (ሰው መሆኑ) ምትሐት ነው ብለው እንዳያስቡ፣

፪. የግብጽ ሰዎች በመካከላቸው በመመላለሱ ጸጋውን እንዲያገኙ፣ ጣዖታትንም ቀጥቅጦ ለማጥፋት።

፫. "እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይወርዳል ጣዖታትም በፊቱ ይወድቃሉ" ያለው የነቢይ ኢሳይያስ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ።

የክብር ባለቤት ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ ሸሸ። በመጀመሪያም የደረሱበት አገር ስሙ በስጣ ይባላል። አልተቀበሏቸውም። በዚያም የውኃ ጉድጓድ ቆፈሩ። ያቺም ውኃ ለሩቆች ፈዋሽ ስትሆን ለዚያች አገር ሰዎች ግን መራራ ሆነች።

ከዚያም በገምኑዲ መንገድ ተጉዘው ወንዝ ተሻግረው ወደ ምዕራብ ደረሱ። የክብር ባለቤት ጌታችንም ተረከዙን በአለት ላይ አደረገ። በተረከዙም አምሳል በአለቱ ላይ ተቀረጸች እስከ ዛሬ ያም ቦታ የጌታችን የተረከዝ ቅርጽ ተባለ።

ጌታችንም እመቤታችን ድንግል ማርያምን "እናቴ ሆይ በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ይሠራ ዘንድ እንዳለው ዕወቂ። በውስጡም ድንቅ ተአምራትን አደርጋለሁ፤ ስሙም ደብረ ምጥማቅ ይባላል" አላት።

ግንቦት 24 እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ በክብር ተገልጣ እየታየች 4ኛ ቀኗ ነው።
🌿🌿

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 26 | የከበሩ አባቶቻችን

🍀 ዲዲሞስ የሚባለው የከበረ ሐዋርያ
#ቅዱስ_ቶማስ በምስክርነት ዐረፈ። እርሱም ራሱን ባርያ አድርጎ በግንበኝነት ለንጉሥ ተቀጠረ። ለቤተ መንግሥቱ ግንባታ የሚሰጠውን ገንዘብ በምድር እየመጸወተ በሰማይ ከቃላት በላይ የሆነ ቤተ መንግሥት ሠራለት። ይህን ያላወቀው ንጉሥ ግን ቆዳውን አስገፈፈው።

🍀 #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ልደታቸው ነው። አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ዮስቴና የሚባሉ በሕገ እግዚአብሔር፣ በሃይማኖት፣ በትሩፋትና በምግባር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው። ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፣ ልደታቸው ግንቦት 26፣ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡

🍀
#አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ ልደታቸው ነው። ሀገራቸው ጎንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ሲና ዳኅና በሚባል ቦታ ነሐሴ 26 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 26 ቀን 1210 ዓ.ም ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ ተወለዱ፡፡ የተወለዱትም በቅዱስ ነአኲቶ ለአብ ዘመነ መንግሥት ነው። አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ታላቁን ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስን ገዳም የቆረቆሩ ደገኛ አባት ናቸው።

#አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ የአባቶቻችን፦
የተክለ ሃይማኖት (ደብረ ሊባኖስ) 
የኂሩተ አምላክ (ዳጋ እስጢፋኖስ)
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ቦረና)
የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ዳውንት) 
የአቡነ አሮን (መቄት)
የአቡነ ዮሴፍ (ላስታ).. የቆብ አባት ናቸው።

🍀 መልአከ ሞትን የማያሳይ ታላቅ ቃልኪዳን ያላቸው ጻድቁ
#አቡነ_አሞጽ በዓለ ዕረፍታቸው ግንቦት 26 ነው። እኚህም ታላቁን ቀብጽያ ገዳምን የመሠረቱት ናቸው። አቡነ አሞጽ ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የመነኮሱት ደብረ ሊባኖስ በአቡነ ዮሐንስ ከማ እጅ ነው።

🍀 #አቡነ_ሳሙኤል_ዘወገግ ፍልሰተ ዐፅማቸው ተከናወነ።

አምላከ ቅዱሳን ይለመነን
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
በሙቀት ሳቢያ ባለፉት 3 ወራት ከ24 ሺህ በላይ ሰዎች በስትሮክ ተጠቅተዋል
በህንድ ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ በከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በሀገሪቱ ያጋጠመውን ከፍተኛ ሙቀት ተከትሎ 33 ገደማ ሰዎች በሰሜናዊዋ ኡታህ ፓርዴሽ ክልል ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በኦዲሻ ደግሞ 20 ገደማ ሰዎች በሙቀት ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንደ ጅረት የሚወርደው ናዳ

በታይዋን ኬሉንግ በተባለ አካባቢ ከባድ የመሬት መንሸራረተት አደጋ አጋጥሟል።

ድንገተኛው አደጋ በርካታ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት አድርሶ መንገድ መዝጋቱም ታውቋል።

11 ተሽከርካሪዎችን ያዳፈነው ናዳ ሁለት ሰዎችን ለከባድ ጉዳት መዳረጉ ነው የተገለጸው።

ሀገር ሰላም ብለው ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች ያልጠበቁት አደጋ ሲከሰት በተሽካሪያቸው ላይ የገጠሟቸው ካሜራዎች ቀርጸውታል።
👆
«ትራንስፖርት ፍጹም ይበላሻል በየትኛውም አለም መኪና ፣ ባቡር፣ አውሮፕላን፣ መርከብ ሁሉም ለመገልገል ያስቸግራል አደጋቸውም የበዛ ይሆናል፡፡ ለምህረት ያልታደሉትን ለማጥፋት ሞት ሁሉንም መገልገያዎች ወደ መግደያነት ይለውጣቸዋል፡፡ »

► ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 3 ተፃፈ 19/07/2001 ዓ፡ም
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 29 | ከተሰዓቱ ቅዱሳን የሆኑ #አቡነ_አፍጼ እና #አቡነ_ጉባ በዓላቸው ነው፡፡

ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ በምድር ላይ ሞትን ሳያዩ የተሰወሩ ናቸው፡፡ እነዚህም አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ሊቃኖስና አቡነ አፍጼ ናቸው።

☘️ አቡነ አፍጼ ☘️

አቡነ አፍጼ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ፡፡

ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር ‹‹አፍፄ-አፈ ዐፄ›› ብሏቸዋል፡፡ ይኽም የዐፄ/የንጉሥ አንደበት ያለው›› ወይም ‹‹ንግግር አዋቂ›› ማለት ነው፡፡

አቡነ አፍጼ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው ግንቦት 29 ቀን በ684 ዓ.ም በሞት ፈንታ ተሰውረዋል፡፡

☘️ አቡነ ጉባ ☘️

እርሳቸውም የተወለዱት ታኅሣሥ 29 ቀን 336 ዓ.ም በመንፈቀ ሌሊት ነው፡፡ አባታቸው ጌርሎስ እናታቸው ቴዎዶክስያ የተባሉ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡

አቡነ ጉባ በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር፡፡ ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው አመስግነዋል። በዚህም ቀን ዐረፉ።
🍀

#አቡነ_መዝራዕተ_ክርስቶስ
አባታቸው ለባሴ ክርስቶስ የዐፄ ፋሲል የቅርብ ወዳጅ የነበረ የጦር አዛዥ ደጃዝማች ሲሆን እናታቸው ሚላንያ ትባላለች፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 29 ቀን በጎንደር ተወለዱ፡፡

ዓፄ ፋሲል ሴት ልጃቸውን ሊድሩላቸው ሲሉ ሸሽተው መነኮሱ። ከዛም በአርማጭሆ ደብረ ሙጅና፣ በዋልድባ፣ በጉንዳጉንዲ ማርያም፣ በመጠራ በምንኩስና ሲጋደሉ ኖሩ።

በዋልድባ ገዳም ሥዕለ ማርያምን በጎኑ ታቅፎ ሲያዝን ለብዙ መናንያን የተሰወረችው ደብረሲና የተባለች ቅድስት ቦታ ተገልጣላኋለች።

በኋላም በመሠረቷት በማይ ዱር ገዳም በ93 ዓመታቸው ግንቦት 29 ዐረፉ።

T.me/Ewnet1Nat
2024/11/15 12:26:29
Back to Top
HTML Embed Code: