Telegram Web Link
በ 12 ቀን 12 ቢሊዮን ዶላር‼️እስራኤልላይ የኢራን ጥቃት 3 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ጉዳት ማድረሱን የእስራኤልን ገንዘብ ሚኒስቴር ጠቅሶ ብሉምበርግ ዘግቧል።
በአንፃሩ እስራኤል ለጦርነቱ የተጠቀመችውን መሳሪያ ጨምሮ አጠቃላይ 9 ቢሊዮን ዶላር ያወጣች ሲሆን በኢራን ጥቃት የደረሰውን ጉዳት እና ለተጎዱ ዜጎቿ የምትከፍለውን ካሳ ጨምሮ አጠቃላይ 12 ቢሊዮን ዶላር መክሰሯ ተጠቁሟል።
እንደ ሂብሪው ሚዲያ እና እስራኤል ኢንሳይደር ዘገባ በኢራን ሚሳይል ጥቃት አጠቃላይ 240 ህንፃዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን 2,305 የዜጎች አፓርትመንት መኖሪያዎች ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን ጠቅሰው አጠቃላይ 13,197 ዜጎች ቤት አልባ መሆናቸውን ዘግበዋል።
አጠቃላይ 41,550 የእስራኤል ዜጎች የንብረት ጉዳት ካሳ ጠይቀዋል። 29 እስራኤላውያን በጦርነቱ ሞተዋል።
ኢራን በበኩሏ ከ935 በላይ ዜጎች በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል ብላለች።
በኢራን በኩል የደረሰው ጉዳት ከእስራኤል ጋር ተቀራራቢ ቢሆንም ኢራን 16 የኑክሌያር ሳይንቲስቶቿን ማጣቷ እና በኑክሌር ጣቢያዎቿ ላይ የደረሰው ጉዳት በጦርነቱ ያስተናገደችው ከፍተኛ ኪሳራ ተደርጎ ተወስዷል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዐይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።
ወደ ሮሜ 3፡18
📌 ብጹዕ ወቅዱስ አዘናጊ ፓትርያርክ አባ ማትያስ ወአደናጋሪ ሳዊሮስ ዘችግኝ መትከል ወእጨጌ ዘመንበረ ብልጽግና
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"እነ ብፁዕ ወቅዱስ" ጉዳችሁ በሙሉ አደባባይ ወጥቶ መሰጣት አለበት ። ግድ ነው!!

እግዚአብሔር ይመስገን !

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
በፓኪስታን በደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ 46 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ‼️

በሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን እና በሌሎች አቅራቢያ ስፍራዎች ለአንድ ሳምንት የሚጠጋ ጊዜ እየዘነበ ባለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሟቾች ቁጥር 46 መድረሱ ተገልጿል።

የሀገሪቱ መንግስት የሟቾቹን ቁጥር ይፋ ሲያደርግ ለበርካታ ቀናት እየዘነበ ያለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ አደጋውን አባብሶታል ሲል አስታውቋል።

የፓኪስታን የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ፤ እየተመዘገበ ያለው የዝናብ መጠን ከሚጠበቀው በላይ መሆኑን ገልፆ፤ ኑሮዋቸውን በወንዝ አካባቢ ያደረጉ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲው የሃገሪቱ ዜጎች ወንዞችን እና ጅረቶችን ከማቋረጥ እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ማቅረቡን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በፓኪስታን በተደጋጋሚ ጊዜ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚያጋጥም ሲሆን በቅርቡ በ2022 የተከሰተው እና በርካታ የሀገሪቱን ክፍል በሸፈነው የጎርፍ አደጋ የ1 ሺህ 737 ዜጎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።
ETHIOPIA_THE_LIGHT_OF_THE_WORLD_INSTRUCTIVE_STATEMENT_AND_THE_FINAL.pdf
323.7 KB
Ethiopia the Light of the World: Instructive Statement and the Final Ending Word of Decision and Judgment.

Translated in English
📄(PDF)

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ትምህርት አዘል መግለጫ እና የመጨረሻው መጨረሻ የውሳኔ እና የፍርድ ቃል።

በእንግሊዝኛ ቋንቋ
📄(በፒዲኤፍ)
THE FINAL ENDING WORD OF DECISION AND JUDGMENT
ETHIOPIA_THE_LIGHT_OF_THE_WORLD_INSTRUCTIVE_STATEMENT_AND_THE_F…
Ethiopia the Light of the World: Instructive Statement and the Final Ending Word of Decision and Judgment.

Translated in English
🔊(Audio)

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ትምህርት አዘል መግለጫ እና የመጨረሻው መጨረሻ የውሳኔ እና የፍርድ ቃል።

በእንግሊዝኛ ቋንቋ
🔊(በድምፅ)
" የግፍ አገዳደል ነው የተፈጸመው ፤ የሟቹን ወንድም ቤትም ታጣቂዎቹ አቃጥለውታል ፤ የአካባቢው ነዋሪም ወደ አጎራባች ቦታዎች ተፈናቅሏል " - የሟች የቅርብ ሰው

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይና የሰባት ልጆች አባት ካህን በአሰቃቂ ሁኔታ በ "ሸኔ" በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ግድያው አሰቃቂ መሆኑን፣ ሟች ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ከቤታቸው በታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ ባለቤታቸውም በተመሳሳይ ከተገደሉ አመት ከስድስት ወራት እንዳስቆጠሩ፣ የ11 ዓመት ልጃቸውም በጥይት ተመትቶ ካህኑ በጥልቅ ሀዘን አንደነበሩ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

አንድ የካህኑ የቅርብ ሰው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ፣ " ካህኑን እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ ነው የገደሏቸው " ሲሉ በተሰበረ ልብ ገልጸዋል።

" አካላቸውን አፍሰን ነው ይዘን የመጣነው፤ ሰዎች በቄየው ሄደው ለቃቅመው ግማሽ አስከሬናቸው ግማሽ አካላቸው በሮቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሁድ አርፏል፤ ግማሹን ደግሞ ትላንት ለቃቅመው ነው የቀበሩት። ለመናገርም ይዘገንናል " ሲሉም አክለዋል።

" ካህኑን ' እባካችሁ ቦታውን ለቃችሁ ወደ ከተማው ኑ ብንላቸውም ' ቤተክርስቲያኑን ለቅቄ አልሄድም የሆነው ይሁን ' ብለው ሳይመጡ ቀሩ " ብለው፣ " ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም ቤተ ክርስቲያን ውለው ማታ ሲገቡ ጠላት ቀድሞ ቤታቸውን ምሽግ አድርጎ ጠብቆ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ ገደላቸው " ሲሉም ተናግረዋል።

" የሟች ወንድም ደውሎ መከላከያ እንዲደርስ አደረገ፣ ካህኑ ግን ተገድለው ተገኙ፣ የግፍ አገዳደል ነው " ያሉት እኝሁ አካል፣ የሟቹን ወንድም ቤትም ታጣቂዎቹ እንዳቃጠሉት፣ የአካባቢው ነዋሪም ወደ አጎራባች ቦታዎች መፈናቀሉን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።
በህንድ የመድኃኒት ፋብሪካ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 36 ሰዎች ሞቱ።

የፍንዳታ አደጋው የተከሰተው የኬሚካል ማብላያ ላይ እሳት በመፈጠሩ ነው ተብሏል።

በህንፃው ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚታመን ተገልጿል። 
🟢 የሚጠብቀን አይተኛም !! አያንቀላፋም።
🟡 አሻጋሪያችን ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መልአኩ
🔴 ሁሌም የሚመራን የሚባርከን የሚጠብቀን!!!
🟢🟡🔴
ሰኔ 26 | የሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ገብርኤል በዓሉ ነው፨

በዚህች ቀን ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው።

በውስጧም ከቤተ ክርስቲያኗ የጣራ ዕንጨት ብዙ ተአምር ይገለጽ ነበር። ጽጋብ በሚሆንባት በዚያች ዓመት ውኃ ይንጠፈጠፋል። ረሀብ ከሆነ ግን ላብ እንኳ አይታይም ነበር።

የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ተአምራቶቹ ብዙዎች ናቸው።

እንዲሁም በዚሁ ወር ሰኔ 13 ቅዱስ ዳንኤል ነቢይን ያዳነበት በዓሉ ነው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
in_hebrew_ethiopia_the_light_of_the_world_final_statement_and_judgment.pdf
268.6 KB
In Hebrew: Ethiopia, the Light of the World — Instructive Statement and Final Word of Judgment

באתיופיה: "אתיופיה, אור העולם" — הצהרה מחנכת והמילה הסופית של החלטה ומשפט
በእብራይስጥ ቋንቋ
קובץ (ፒዲኤፍ) (PDF) 📄
בעברית Final Statement and Judgment (in Hebrew)
Ethiopia the Light of the World
In Hebrew: Ethiopia, the Light of the World — Instructive Statement and Final Word of Judgment

באתיופיה: "אתיופיה, אור העולם" — הצהרה מחנכת והמילה הסופית של החלטה ומשפט
በእብራይስጥ ቋንቋ
אודיו  (በድምፅ) (Audio) 🔊
2025/07/03 12:19:07
Back to Top
HTML Embed Code: