Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️A Palestinian woman is seen cleaning her heavily damaged house in Gaza after Israeli airstrikes, as displacement camps are overcrowded and Israel targets Rafah.
❗️Tanzania devastated by deadly El Nino floods

Prime Minister Kassim Majaliwa confirmed 155 people have died from the catastrophic flooding across the country, with 236 more injured and over 200,000 people affected.

Neighboring Kenya has also suffered heavily from the weather system, with 45 people left dead since March and 100,000 people displaced by the flooding there.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️Aftermath of Israeli raid on Lebanese border town of Houla
✧ ━━━━━━━━ 🌿 ━━━━━━━━ ✧

#ሆሣዕና #በዓለ_ተፂዕኖ #የፀበርት_እሑድ

ይህ በዓል ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ከሆሳዕና ጀምሮ እስከ ጰራቅሊጦስ ድረስ ያሉ ዐበይት በዓላትን ሁለት ጊዜ ታከብራለች። በዚህም መሠረት፦

1ኛው "ጥንተ በዓል" ሲሆን {"ጥንተ በዓል" ማለት በዓሉ : ተአምሩ (የማዳን ሥራው) የተፈፀመበት የመጀመሪያው ቀን ማለት ነው} ይህም መጋቢት 22 ቀን ነው።

2ኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል።
መሠረቱ የቅዱሳን ሐዋርያት ቀኖና እና የአባታችን የድሜጥሮስ መንፈሳዊ ቀመር ነው።

የሰሞነ ሕማማት የመጀመሪያው ቀን፤ የዐቢይ ጾም ስምንተኛውና የመጨረሻው ሳምንት ሆሣዕና ይባላል።

በዕብራይስጡ ‹‹ሆሼዕናህ›› የሚል ሲሆን ትርጕሙም ‹‹እባክህ አሁን አድን፤ አንድም መድኀኒት›› ማለት ነው፡፡ በትንቢተ ዘካርያስ ላይ በአህያ ላይ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ (በግእዙ ተፂዕኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ኢየሩሳሌም በክብር) ስለሚል በአብዛኛው የሃገራችን ክፍል ከጥንት ጀምሮ በዋነኛነት ‹‹የተፂዕኖ በዓል›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንዲሁም ዘንባባ በግእዙ ፀበርት እየተባረከ ስለሚሰጥ ‹‹የፀበርት እሑድ›› ይባላል።

በዚህ ዕለት ጌታችን የማዳን ሥራውን ወደሚፈጽምባት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ... ቤተ ፋጌ ሲደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ‹‹ያስፈልጉኛልና የታሠሩትን አህያና ውርንጫ ይዛችሁልኝ ኑ፡፡›› ብሎ ላካቸው፡፡

በምስጢሩም የአዳምን ልጆች ከዲያብሎስ ቁራኝነት ሊፈታ እንደ መጣ ለማጠየቅ ነው፡፡ እነርሱም እንደታዘዙት አመጡ፤ እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲሆን 14ቱን በእግሩ፣ 2ቱን ምዕራፍ (ከደብረ ዘይት ተራራ አካባቢ አንስቶ እስከ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ) በአህያ ሄዶ፣ ቤተ መቅደሱን 3 ጊዜ በውርንጫላዋ ከዞረ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡

#ለምን_ጌታችን_በአህያ_ውርንጫ_ተቀምጦ_ወደ_ቤተ_መቅደስ_ገባ?

🌿 ቀድሞ በነቢያት ዘመን ጸብዕ (ጥል) በሆነ ጊዜ በፈረስ ተቀምጠው፥ የጦር ዕቃ ይዘው፥ ዘገር ነቅንቀው፥ ጦር ሰብቀው፥ (ነጋሪት እያጎሰሙ፥ መለከት እያስነፉ) ይታዩ ነበር፤ ዘመነ ሰላም፥ ዘመነ ምሕረት በሆነ ጊዜ ደግሞ በአህያ ተቀምጠው፥ መነሳንስ ይዘው ይታያሉ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በነቢያት ሥርዐት ‹‹ዘመነ ሰላም ይዤላችሁ›› መጣሁ ሲል፤

🌿 በ7ቱ መስተጻርራን /ተጣልጠው የነበሩ/ (በሰውና በእግዚአብሔር ፣ በሰውና በመላእክት፣ በሥጋና በነፍስ፣ በተገዘሩት በሕዝበ እሥራኤልና ቆላፍ በሆኑት በአሕዛብ መካከል) የነበረው ጠብ ማብቃቱን ለመግለጥ እንዲሁም በነቢያት የተተነበየውን ሊፈጽም፤

🌿 ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ 117፥25-26 ‹‹በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፡፡›› ብሏል፤ ነቢዩ ዘካርያስም በትንቢቱ በአህያ እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር ‹‹የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡›› /ዘካ. 9፥9/፡፡

◦ ጌታችንም ኢየሩሳሌምን ሰላምሽ ዛሬ ነው ሰላሟን አውጆላታል፤ በሌላ አንቀጽም ከተማይቷን እየተመለከተ አልቅሶላታል፡፡ /ሉቃ. 19፥24/

◦ የተዋረደች እንስሳ (አህያም) በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊ ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ መቀመጫ አደረጋት፤ ሸክም ያቆሰላት፥ ዱላ የሰለቻት፥ ዕረፍት የናፈቃት ‹‹ቀንበሬ ልዝብ፥ ሸክሜ ቀላል ነው›› ያለ ንጉሥ ተቀመጠባት፡፡

#ለምን_የዘንባባ_ዝንጣፊ (ፀበርት)፤ (የቴምር ዛፍ ዝንጣፊና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ) ይዘው ዘመሩ?

🌿 በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባም ደቀ መዛሙርቱና በግራና በቀኝ የነበሩ ሕዝቦችም ‹‹እንኳን አንተ የተቀመጥክባትም አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም›› እያሉ ግማሹ ልብሱን፥ ግማሹ የዘንባባ ዝንጣፊ አነጠፉለት፤ ክብሩንና መድኀኒትነቱን ገለጡ፡፡

🌿 አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ፣ እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ፣ ዮዲት ሃገሯን ሊወር የመጣውን ሆሎፎርኒስ የተባለ የአይሁድ ንጉሥ በገደለች ጊዜ ዘንባባ ይዘው አመስግነው ነበር፤

በዚያ ልማድ ጌታችንንም ዘንባባ ይዘው ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፥ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፥ ሆሣዕና በአርያም›› /መዝ. 8፥2፣ ሉቃ. 19፥38/ እያሉ አመሰገኑት፤ ዘመን የተቈጠረለት፥ ምሳሌ የተመሰለለት፥ ትንቢት የተተነበየለት፥ ምሥጢር የተመሠጠረለት የዳዊት ልጅ፤ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን መሰከሩ፡፡

◦ አይሁድም ሕፃናት ሲያመሰግኑ ሰምተው በቅንአት በታወረ ልቦናቸው ‹‹ዝም አስብላቸው እንጂ›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ አፍ ምስጋና ለራስህ አዘጋጀህ›› /መዝ. 8፥2/ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል ጠቅሶ አሳፍሯቸዋል፡፡ በሌላም አንቀጽ ዝም በሉ እያሉ ሊያስቆሙ ሲሞክሩ የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው አመስግነውታል፤ ይህንንም ተመልክተው አፍረዋል፡፡

🌿 አንድም ዘንባባ እሾኻም ነው የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤

🌿 አንድም ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ፤

🌿 አንድም ዘንባባ ረጅም (ልዑል) ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ አንጥፈው ተቀብለውታል፡፡

🌿 አንድም ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል፤ አንተም የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ፤

🌿 ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ፤

🌿 ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በዚያ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ በመቆጣት የለዋጮችን ገበታ እየገለበጠ አስወጣቸው፡፡

ታሪኩ በነቢያት መጻሕፍትና በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ይገኛል፡፡ (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)፨

🌿🌿🌿
እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው አውዳሚ ጦርነት ያልፈነዱ መሳሪያዎችን ጨምሮ ፍርስራሾችን ለማጽዳት 14 አመታት ገደማ ሊፈጅ እንደሚችል የተመድ ባለስልጣን በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🌿🌿 ምሥጢረ ሆሣዕና 🌿🌿

ፋሲካቸው በስምንት ቀን ሊሆን፣
ከፋሲካ በሚቀድመው ሰሞን፣
ዘካርያስ የሚባል ነቢይ ካህን፣
ደስ ይበልሽ ኢየሩሳሌም ጽዮን፣
ንጉሥሽ ይመጣልና አሁን፣
በአህያ ላይ እንደ አንድ ድሃ ምስኪን፣
እንዲህ ብሎ የተናገረው ቃሉን፣
ለመፈጸም በአህያ ሆኖ መድኅን፣
ሲመጣ አይታ እርሱ መሆኑን ለይታ፣
ሀገሪቱ ተቀበለችው በእልልታ፣
በመንገዱም ቅጠሉን ቆርጠው በርጥቡ፣
ልብሳቸውን ያነጠፉ አሉ ከሕዝቡ።

°°°
ሁለተኛም ዳዊት የአምላክ ልቡና፣
ሲዘምር እያስማማ በገና፣
አስቀድሞ ይቺን ዕለት አየና፣
ሲሰብክልን የዚችን ዕለት ዜና፣
አዘጋጀህ ከሕፃናት አፍ ምስጋና፣
ላለው ትንቢት መፈጸሚያ ቀን ናትና፣
እንዲህ ሆኖ ከቤተ መቅደስ ሲገባ፣
ሕፃናቱ እየወረዱ ከጀርባ፣
በጣታቸው እየጨበጡ ዘንባባ፣
በእግዚአብሔር ስም የምትመጣው አምላክ፣
ቡሩክ ነህ ለዘለዓለም ቡሩክ፣
የዳዊት ልጅ መድኃኒት ብትሆን ለሁሉ፣
ሆሣዕና መባል ተገባህ እያሉ፣
ተቀናጡ በፊት በፊቱ ዘለሉ።

°°°
ይህን ሰምተው ፈሪሳውያን ጸሐፍት፣
ቢናደዱ ቢሞላባቸው ቅንዓት፣
ሕፃናቱን ተዉ በላቸው አሉት፣
እንዲህ አለ ሲመልስላቸው ጌታ፣
ከጠላችሁ የሕፃናቱን እልልታ፣
ድንጋዮቹ የሚገባቸው ዝምታ፣
ያመስግኑ በእናንት በሰዎች ፋንታ፣
በዚህ ጊዜ አምላክነቱን ሊገልጡ፣
ድንጋዮቹ በፊት በፊቱ እየሮጡ፣
እንደ ሰዎች የምስጋና ድምጽ ሰጡ፣
ስብሐት ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ፣
ለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ።

× | መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ዘድማኅ
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️Natural disasters continue in Guangdong, China's most populous province .
2024/09/26 23:16:53
Back to Top
HTML Embed Code: