Telegram Web Link
#Update

ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል።

4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈፀመውን ድርጊት " #የሽብር_ጥቃት_ነው " ሲል ጠርቶ አውግዟል።

ለጥቃቱ #IS ኃላፊነቱን መውሰዱን በበይነ መረብ የወጣ አንድ ያልተረጋገጠ መግለጫ አመልክቷል።
የአልሸባብ ክንፍ በኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የአልሸባብ ክንፍ በመሆን የሚጠረጠር የታጠቀ ቡድን መደራጀቱን እና እንቅስቃሴ መጀመሩን የክልሉ ባለስልጣናት በፀጥታ ስጋትነት ማስቀመጣቸውን ኢሰመኮ ዓርብ መጋቢት 13 ቀን ባወጣው ሪፖርት አሳውቋል። በኡንጋዳ፣በኬንያ እና በሶማሊያ ሀይሎች ጭምር ይደገፋል የሚባለው ይህ ሸማቂ ሀይል በፖሊሶች እና በመንግሥት አመራሮች ላይ ጥቃት መክፈቱ ችግሩ እንዳወሳሰበው ኢሰመኮ በሪፖሪቱ ገልጿል።
"እንበለ ኪዳንኪሰ ወመስቀለ ክርስቶስ ወራሲ፥
አልቦ እምሲዖል ዘይድኅን ብእሲ
"

🍀 🍀 🍀
#እመቤቴ ሆይ ... ባንቺ ኪዳን ያላመነ፣ በመስቀለ ክርስቶስም ያልታመነ እንዴት ከሲዖል መዳን ይቻለዋል!?


#ያለ_ድንግል_ማርያም_አማላጅነት_ዓለም_አይድንም

በረከተ ኪዳኗ ይብዛልን፡፡

www.tg-me.com/Ewnet1Nat  🇨🇬
www.tg-me.com/AlphaOmega930  🇨🇬
🟢🟡🔴
መጋቢት 17 | #አቡነ_ዮናስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

አቡነ ዮናስ አባታቸው ንዋየ እግዚእ እናታቸው ኂሩተ ማርያም ይባላሉ። በኅዳር 17 ቀን 1357 ዓ.ም በሀገረ ቡር (ሀገረ መስቀል) የሚባል ቦታ ተወለዱ።

አቡነ ዮናስ በሕፃንነታቸው በጎች እየጠበቁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም መዝሙረ ዳዊት ኣስተማራቸው። እርሳቸውም ይህን ዓለም ንቀው ከመነኮሱ በኋላ 150 መዝሙር እየጸለዩ 3 ሺህ ስግደት ይሰግዱ ነበር።

ቀንና ሌሊት ሲጸልዩም "ጠላቂት" በሚባል ሐይቅ ውስጥ እየገቡ እስከ አንገታቸው ድረው በሐይቁ ውስጥ ገብተው ይጸልዩ ነበር።

ከተሰጧቸውም ጸጋዎች ውስጥ አንዱ 10 ጣቶቻቸው ወደ ሐይቁ ሲገቡ ይበሩ ነበር። አቡነ ዮናስ በየቀኑ ከ5 ፍሬ "ዳዕሮ" ወይም "ዓየ" በቀር ሌላ ምግብ አይመገቡም ነበር።

ከዚኽም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ኀብስተ አኰቴትን ጽዋ በረከት ከሰማይ አውርዶላቸዋል።

ጻድቁ እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት ወደተለያዩ ቦታዎች እየዞሩ የተለያዩ ተኣምራት በማድረግ ሕሙማንን በመፈወስ ሙታን በማስነሣት ብዙዎችን ከክህደት ወደ እምነት ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ከጣኦት ኣምልኮ ወደ እግዚአብሔር ኣምልኮ መልሰዋል።

አቡነ ዮናስ ይይዙት በነበረው መቋሚያ በውኃ እየታጠበ ውኃው በጣም ለታመሙ ሰዎች እየተሰጠ በቶሎ ከበሽታቸው ይድኑበታል፣ የማይድኑም ከሆነ ቶሎ በሞት ያርፋሉ። የሚታጠቡበት ሁሉ ለድኅነት ከሆናቸው በአጭር ጊዜ ይድናሉ ወይም ለዕረፍት ከሆናቸው ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ያሰናብታቸዋል።

አቡነ ዮናስ ያረፉት መጋቢት 17 ቀን ሲሆን ይህ ወቅት ታላቁ ዐቢይ ጾም የሚውልበት ስለሆነ በዓለ ዕረፍታቸውን ጥር 21 ቀን እንዲያከብሩ ለልጆቻቸው አስቀድመው ነግረዋቸዋል።
🍀

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
በትናንትናው ጭፍጨፋ በአጠቃላይ 11 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የደብሩ መርጌታ ከነሚስቱና ከነሁለት ለጆቹ፣ አንድ ዲያቆን ከነሚስቱና ከሚስቱ እህት ጋራ ተገድለዋል። በተጨማሪም ከሌላ ቦታ የመጠ 4 ሰዎች ተገድለዋል። ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል።
🟩 🟨 🟥

❮ መድኃኒቱ #ሰንደቁ ላይ ነው ❯

...ምሕረት ትፈልጉ እንደኾነ፥ ይቅርታ ትፈልጉ እንደሆነ፥ የጸጋ ምጽዋት ትፈልጉ እንደኾነ፥ ቀኑ እየቀረበ፥ እየመሸ፥ እየጠበበ፥ እየመጣ ነውና የምጥ ቀን ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ #አኹኑኑ_ንስሐ_መግባት_ይመረጣል ፡፡

#ኢትዮጵያውያን_ፊታችንን_ወደ_እግዚአብሔር_እንመልስ! በተለይም ክርስቲያኖች! አኹን ያመጹ ክርስቲያኖች ናቸው። በልዩ ልዩ ቋንቋ፥ ልዩ ልዩ ወገን ፈጥረው የሚያስቸግሩት፥ እግዚአብሔርን የሚያስቸግሩት ክርስቲያኖች ናቸውና ክርስቲያኖች እንዲታረሙ ያስፈልጋል።

#ኢትዮጵያውያን
#ኢትዮጵያውያን
#ኢትዮጵያውያን ስሙ!
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!
#ወደኔ_ተመለሱ_እመለስላችኋለሁ❞ ይላል እግዚአብሔር።

ከዚኽ በቀር፥ ይሄ እንደው ዝም ብሎ
#በየሜዳው_እንደ_ክረምት_እንቁራሪት_መጯጯኹና_መፎከሩ_የሚያወጣ_አይኾንም፡፡

🟢 አርማ፥ አንድ አርማየኢትዮጵያ አርማ፦ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ኢየሱስ ክርስቶስ፣

🟡 ሰንደቅ አላማ፥ አንድ ሰንደቅ አላማ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ፦ ሦስት መልክ አብ ፥ ወልድ ፥ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ተብሎ ሲመሰገንበት ሲመለክበት የኖረው አንድ ሰንደቅ አላማ፣

🔴 አንድ ሕዝብ፣ አንድ ወገን፣ አንድ ኢትዮጵያዊ እንጅ አማራ፣ ትግሬ፣ ጎንደሬ ማለት የለም፡፡

❗️እምቢ ያለ እምቢ ያለ፥ ከእግዚአብሔር በረከት የተለየ ነው!
እሺ ያለ፥ ከእግዚአብሔር በረከት ተሳታፊ ነው፡፡
#የእግዚአብሔር_ሰይፍ_ተመዟል_እንዲያው_አይመለስም! እንዲያው አይመለስም!
▰ ▰

አለቃ አያሌው ታምሩ —
የካቲት ፲፮ ፥ ፲፱፻፹፬ ዓ.ም በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ከሰጡት ትምህርት ተቀንጭቦ የተወሰደ ፨

www.tg-me.com/Ewnet1Nat  🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930  🇨🇬
ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_መግለጫ_ጥር_15_2016_በድምጽ_የተለቀቀ.pdf
508.2 KB
🟩🟨🟥 122) ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ
ለመላው የአዳም ዘር በሙሉ በጽሑፍ (PDF)
15/ጥር/2016 ዓ.ም
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🟩 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
🟨 ተዋሕዶ እምነት
🟥 የኖኅ መርከብ
በድሬዳዋ ከተማ ትናንት ወደ ማታ አካባቢ ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በከተማዋ ድንገተኛ ጎርፍ ተከስቶ የንብረት ጉዳት ደርሷል። ለጉልት ገበያ ሲያገለግሉ የነበሩ በሸራ የተሰሩ ቤቶች በጎርፉ ተወስደዋል።
እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።
2024/09/27 13:24:23
Back to Top
HTML Embed Code: